No summary available.
ሚያዝያ 24 ቀንዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ስላስ ረዳ - ጠበቃ ጠጅነሽ ሰይፉ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዳዩ ከንግድ መደብር ኪራይ ጋር ተያይዞ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሆኖ ክርክሩም የተጀመረው የሰበር አመልካች ከሳሽ ሆነው በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻነት ነው። አመልካች በ14/06/2005 ዓ/ም በተፃፈ ለስር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ አቤቱታ፡- አመልካች ለንግድ ቤትነት ለመገልገል ከ 2ኛ ተጠሪ ተከራይተው በነበረው ቤት ላይ የፀጉር ስራ ንግድ ፈቃድ በማውጣትና ለስራው የሚያስፈልጉ ልሎች ነገሮችንም ካሟላ በኋላ የንግድ ድርጅቱን ከነፈቃዱና ሙሉ እቃው ለ1ኛ ተጠሪ በወር ብር 4,000 ኪራይ ያካራዩ መሆኑን ጠቅሰው ሆኖም ግን 1ኛ ተጠሪ ከህግ አግባብ ውጭ በንግድ ድርጅቴ ላይ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የኪራይ ውል አቋቁሜያለሁ በማለት ድርጅቴን ለማስረከብ ፈቃደኛ ስላልሆነ ተጠሪዎች ከህግ ውጭ በድርጅቴ ላይ ያደረጉት ኪራይ ውል ፈርሶ 1ኛ ተጠሪ ድርጅቱን ከነ ሙሉ እቃው ለአመልካች እንዲያስረክብ እንዲወሰንላቸው እና እንዲሁም 1ኛ ተጠሪ ከመሰከረም 2004 ዓ/ም ጀምሮ ያልተከፈለ የድርጅቱን ውዝፍ ኪራይ ገንዘብ ብር 24,000 መከፈል ከነበረበት ቀን አንስቶ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ለአመልካች እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ጠይቋል።
ጉዳይን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም በበኩሉ በጉዳዩ ላይ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ ጉዳዩን በመመርመር አመልካች ከ2ኛ ተጠሪ ተከራይተው የነበረውን ንግድ ቤት በኪራይ ውሉ በገቡት ግድታ መሰረት አስቀድመው አከራይን (2ኛ ተጠሪን) ሳያሳውቁ ለ1ኛ ተጠሪ አሳልፈው ማከራየታቸው የኪራይ ውሉን ስምምነት የጣሱ ስለሆነ እና 2ኛ ተጠሪም ይሄንኑ ተከትሎ ከአመልካች ጋር የነበረውን የቤቱን ኪራይ ውል አቋርጦ ቤቱን ለ1ኛ ተጠሪ ማከራየቱ መብቱና ተገቢ ስለሆነ ይህ በተጠሪዎች መካከል በቤቱ ላይ የተደረገው ኪራይ ውል ይፍረስልኝ በማለት አመልካች ያቀረቡትን ጥያቄ አልተቀበልኩም በማለት ጥያቄውን ወድቅ በማድረግ አልፏል። የንግድ መደብሩን ኪራይ ክፍያ ጥያቄ በተመለከተ ደግሞ 1ኛ ተጠሪ ላከፍሉ የሚገደዱት ኪራይ በአመልካችና 1ኛ ተጠሪ መካከል ተደርጎ የነበረው ኪራይ ውል እስከተቋረጠበት (28/02/2004 ዓ/ም) ድረስ ያለው ኪራይ ብቻ ስለሆነ በዚህ መሰረት የመሰከረምና ጥቅምት ወር 2004 ዓ/ም የ2 ወራት ኪራይ ክፍያ ብር 8,000 ውሳኔ ከተሰጠበት ከ 15/06/04 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር 1ኛ ተጠሪ ለአመልካች ይክፈሉ በማለት ወስኗል።
አመልካችም በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ አቤቱታዋን ለፍድራል ከ/ፍ/ቤት አቅርበው እና ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን አስቀርቦ ካከራከረ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ አመልካች አሳልፈው ለ1ኛ ተጠሪ ያከራዩት ንግድ ቤቱን ሳይሆን ንግድ መደብር መሆኑን ከገለፀ በኋላ የንግድ መደብሩን ደግሞ በንግድ ህጉ ቁ.145(1) እና ፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት መ/ቁ.31264 አስገዳጅ ውሳኔ መሰረት የአከራዩን ፈቃድ መጠየቅ ሳያስፈልግ ማከራየት ስለሚችልና በዚህም መሰረት አመልካች ንግድ ድርጅቱን 2ኛ ተጠሪ ሳያሳውቁ ለ1ኛ ተጠሪ ማከራየታቸው ህጉን መሰረት ተደረጎ እንጂ ህጉን ያልተከተለ አድራጎት ባለመሆኑ በአመልካችና 2ኛ ተጠሪ መካከል ተደርጎ የነበረው የቤቱ ኪራይ ውል መቋረጡ በአግባቡ ስላልሆነ ውሉ ፀንቶ ላቀጥል ይገባል በማለት ከወሰነ በኋላ በልላ በኩል ግን በተጠሪዎች መካከል በቤቱ ላይ የተደረገው የኪራይ ውል ህጋዊ ባለመሆኑ ላፈርስ ይገባል በማለትና እንዲሁም 1ኛ ተጠሪ ንግድ ድርጅቱን ቀድሞ በተረከበበት ሁኔታ መልሰው ለአመልካች ላያስረክቡ ይገባል በማለት ወስኗል።
አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታም ይሄንኑ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ የተሰጠውን ውሳኔ በከፊል በመቃወም ሲሆን ቅሬታ ነጥቡም ባጭሩ፡- 1ኛ ተጠሪ ንግድ መደብሩን በወር ብር 4000 ተከራይተው የነበሩ መሆኑን ሳይክዱና ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱም በበኩሉ የስር ፍ/ቤቱን ውሳኔ በመሻር 1ኛ ተጠሪ ንግድ ድርጅቱን ከነ እቃው ለአመልካች እንዲያስረክቡ በማለት ከወሰነ በኋላ ኪራዩን በተመለከተ ግን ውሳኔ ሳይሰጥበት በዝምታ ማለፉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስላለበት ውሳኔው ታርሞ ይወሰንልኝ የሚል ነው። አቤቱታውም ተመርምሮ አመልካች 1ኛ ተጠሪ የተከራዩትን የንግድ ድርጅት ኪራይ ይክፈሉኝ በማለት ያቀረቡት የዳኝነት ጥያቄ በዝምታ የመታለፉን አግባብነት ለመመርመር ሲባል አቤቱታው ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ ተደርጎ ግራ ቀኙም ተከራካሪ ወገኖች ቀርበው በጉዳዩ ላይ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
No topics extracted.
የጉዳዩ አመጣጥና ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በበኩላችን አቤቱታው ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ ሲደረግ ተይዞ ከነበረው ጭብጥ አንፃር ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት ለመገንዘብ እንደተቻለው አመልካች የንግድ ድርጅቱን ኪራይ ክፍያ በተመለከተ ስር ፍ/ቤት እንዲከፍላቸው ዳኝነት የጠየቁት ብር 24,000 ብቻ መሆኑን ፤ ከዚህ ውስጥም የመስከረምና ጥቅምት 2004 ዓ/ም የ2 ወራት የድርጅቱ ኪራይ ብር 8,000 በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለአመልካች መወሰኑን፤ የድርጅቱ ኪራይ መጠንም በወር ብር 4,000 መሆኑን፤ 1ኛ ተጠሪም የኪራይ መጠኑ ብር 4,000 አለመሆኑን ክዶ አለመከራከሩን፤
አመልካችም የስር ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ ላይ ሳይከፈላቸው ከቀረው የድርጅቱ ኪራይ ክፍያን ጨምሮ አለኝ ያሉትን ቅሬታቸውን በሙሉ ለይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ግን የንግድ መደብሩን ልረከብ ጥያቄን አስመልክቶ በስር ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ክፍል ለውጦ አመልካች ድርጅቱን እንዲረከቡ በማለት ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም ሆኖም ግን ለአመልካች ላከፈላቸው አይገባም በማለት ወድቅ ተደርጎ የታለፈውን ኪራይ በተመለከተ ምንም አይነት ዳኝነት በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ ሳይሰጥበት በዝምታ መታለፉን ነው።
በመሰረቱ በአመልካችና 1ኛ ተጠሪ መካከል ተደርጎ የነበረው የድርጅቱ ኪራይ ውል ህጋዊና ተገቢ ነው በማለት በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ ተወስኗል። ይህ ብቻ ሳይሆን በተጠሪዎች መካከል በቤቱ ላይ የተደረገው ኪራይ ውልም ህገ-ወጥ ነው ተብሎ እንዲፈርስ ከመደረጉም በላይ 1ኛ ተጠሪም ድርጅቱን ለአመልካች እንዲያስረክቡ በማለት ጭምር ተወስኗል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ 1ኛ ተጠሪ በድርጅቱ ኪራይ ውል መሰረት እንዲከፍሉ የተጠየቁትን ቀሪ የድርጅቱን ኪራይ ክፍያ በተመለከተ ላከፍሉ የማይገባበትን ህጋዊ የሆነ ክርክር ባላቀረብበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ ቀሪው ኪራይ ለአመልካች እንዲከፈል ሳይወስን በዝምታ ማለፉ ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.182(1) እና 348(1) ድንጋጌዎች ይዘት አኳያ የውሳኔው በከፊል መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስላገኘን ላታረም የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍድራል ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ.128192 በ30/10/05 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348(1) መሰረት ተሻሽሐል።
አመልካች ስር ፍ/ቤት እንዲከፈላቸው ዳኝነት ከጠየቁት ብር 24,000 የድርጅቱ ኪራይ ውስጥ የመሰከረምና ጥቅምት 2004 ዓ/ም ብር 8,000 በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተወሰነላቸው ሲሆን ቀሪው ብር 16,000ም ላከፈላቸው የማይገባበት በቂና ህጋዊ ምክንያት ስላላገኘን ይሄው ገንዘብ ይህ ውሳኔ ከተሰጠበት ከ 24/08/06 ዓ/ም ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ 1ኛ ተጠሪ ለአመልካች ላከፍሉ ይገባል በማለት ተወስኗል።
የሰበር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
ከፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና እንዲሁም ፍድራል ከ/ፍ/ቤት በትዕዛዝ የቀረቡት መዝገቦች ይመለሱ ብለናል። ይፃፍ።
በተሻሻለው ውሳኔ መሰረት ይፈፀም ዘንድ የውሳኔ ግልባጩ ለስር ፍ/ቤቶች ይድረስ።