No summary available.
ቀን 18/09/2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ አስፋው ንዳ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የጣልቃ ልግባ ጥያቄ የሚስተናገድበትን የህግ አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በዚህ ፍርድ ቤት የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ባሁኑ 2ኛ ተጠሪ ላይ የቤት ባለቤትነት መፋለም ክስ ያቀረቡባቸው ሲሆን 2ኛ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ተወካይነት ጠበቃ ተወክሎላቸው ተገቢ ነው ያሉትን ክርክር አቅርበዋል። ከዚህ በኋላ የአሁኑ አመልካችና ወ/ሮ ፀሐይ ቸበራ የተባሉ ግለሰብ ወደ ክርክሩ ለመግባት እንዲፈቀድላቸው በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41 መሰረት ጥያቄ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም የአሁኑ ተጠሪዎች በጣልቃ እንግባ ጥያቄ ላይ አስተያየት እንዲሰጡበት ያደረግ ሲሆን የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ የአሁኑ አመልካች የተከሳሽ ወኪል ሁነው ጠበቃ ወክለው ስለ ተከሳሹ ጥቅም ሁነው ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ ወደ ክርክሩ ልግባ በማለት ጥያቄ ማቅረባቸው የስነ ስርዓት ህጉን አላማ ያልተከተለ መሆኑን ገልጸው የተቃወሟቸው ሲሆን ወ/ሮ ፀሐይ ቸበራ የተባሉትን ግለሰብ ደግሞ ለጣልቃ ልግባ ጥያቄአቸው ተገቢው ማስረጃ የልላቸው መሆኑን ገልፀው ወደ ክርክሩ ላገቡ አይገባም ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የስር ተከሳሽ የሆኑት የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ በበኩላቸው የጣልቃ ልግባ ጥያቄ ላይ ተቃውሞ የልላቸው መሆኑን ጠቅሰው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ የአሁኑ አመልካች በተከሳሽ በተሰጣቸው የውክልና ስልጣን መሰረት አቶ ጌታሁን ተስፋዬ የተባሉትን ጠበቃ ወክለው ጠበቃው ቁጥሩ 3936 የሆነ ቤት የተከሳሽ የግል ቤት ሁኖ ቤቱን ተከሳሹ ለአሁኑ አመልካች የሸጡላቸውና ሰነዶቹም ቦታውን ለሚያስተዳድረው መሬት አስተዳደር ተመላሽ ሆኖ ቤቱን የአሁኑ አመልካች በእጃቸው አድርገውና ተገቢውን የይዞታ ማረጋገጫ አውጥተው የሚገለገሉበት መሆኑን በመጥቀስ የከሳሽ ክስ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት መከራከራቸውን፣የጣልቃገብነት ጥያቄው የአመልካቹ መብትና ጥቅም የሚነካበትን የህግ አግባብ የማያሳይ መሆኑን እንዲሁም አመልካች በተከሳሽነትም ሆነ በጣልቃ ገብነት በአንድ ጊዜ የሚከራከሩበት አግባብ የልለ መሆኑን በምክንያትነት ይዞ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ሲሆን የወ/ሮ ፀሐይ ቸበራ ጥያቄ ደግሞ በማስረጃ ያልተደገፈ ነው በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል። በዚህ ትዕዛዝ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ አልተቀበላቸውም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ትዕዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም፡- አመልካች የተከሳሽ ወኪል መሆናቸው ስለወኪላቸው ጥቅምና ስለራሳቸው መብትና ጥቅም የሚያቀርቡትን ክርክር የማያግዳቸው ሁኖ እያለ ጉዳዩ በማስረጃ ሳይጣራ ወደ ክርክሩ ጣልቃ ላገቡ አይችሉም የተባለው ከህግ አግባብ ውጪ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ በመደረጉ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው 1ኛ ተጠሪ በሰጡት መልስ አመልካች ከወኪላቸውና ለራሳቸው መብትና ጥቅም በአንድ ጊዜ ላከራከሩ የሚችሉበት የህግ አግባብ የልለ መሆኑን፣ አመልካች አለኝ የሚሉት የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተርም በሚመለከተው የአስተዳደር አካል ሰኔ 03 ቀን 2005 ዓ/ም የመከነ መሆኑን ዘርዝረውና ጥያቄያቸው ከስነ ስርዓት ህጉ መሰረታዊ አላማ ውጪ መሆኑን ጠቅሰው የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው የሚነቀፍበት የህግ አግባብ የለም ሲሉ ተከራክረዋል። 2ኛ ተጠሪ ደግሞ አመልካችን ደግፈው መልስ የሰጡ ሲሆን አመልካችም ለሁለቱም ተጠሪዎች መልስ የመልስ መልሳቸውን ሰጥቷል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም በጉዳዩ ላይ በተሰጠው ብይን መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት ይቻላል? ወይስ አይቻልም የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቷል።
በመሰረቱ ጣልቃ ገብነት አንድ በፍትሃ ብሕር ክርክር ተካፋይ ያልነበረ ሰው የክርክሩ ተካፋይ የሚሆንበትና መብቱንና ጥቅሙን ለማስከበር ተገቢውን ክርክር እንዲያቀርብ በህጉ የተዘረጋ ስርዓት ነው። እንደዚህ አይነት ሰው ወደ ክርከሩ የሚገባው በተከሳሽ ጠያቂነት ወይም በራሱ አነሳሽነት ላሆን እንደሚችል የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41 ድንጋጌ ይዘት ያሳያል። በዚህ ድንጋጌ እንደተመለከተው ልሎች ወገኖች በሚከራከሩበት ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሶስተኛ ወገን ከፍርድ ውሳኔ በፊት ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር እንዲፈቀድለት ላከራከር ይችላል። ሆኖም የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነ ሶስተኛ ወገን ጣልቃ ገብ ለመሆን ልሎች ስዎች በሚከራከሩበት ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ በቀጥታ መብቱንና ጥቅሙን የሚነካ መሆኑን የማስረዳት ግድታውን መወጣት አለበት። በልላ አገላለፅ ጣልቃ ልግባ ጥያቄ ተቀባይነት እንዲኖረው ውሳኔው የክርክሩ ተካፋይ ያልሆነውን ሰው መብትና ጥቅም በሚጎዳ መልኩ በቀጥታ የሚፈጸም መሆኑንና ልላ አዲስ ክስ በማቅረብ ለማስቀረት የማይቻል መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላል። ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ጣልቃ ገብ ልሁን በሚል ጥያቄ የሚያቀርብ ሰው ውሳኔው በቀጥታ መብቱንና ጥቅሙን የማይጎዳ ከሆነ እና አዲስ ክስ በማቅረብ ማስቀረት የሚቻልበት ሁኔታ ያለው ከሆነ ጥያቄው በህግ ፊት ተቀባይነት የሚያግኝበት ሁኔታ የልለ መሆኑን ነው።
No topics extracted.
ጣልቃ ልግባ የሚለው ወገን በተከራካሪ ወገኖች መካከል ባለው ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ መብቱን በምን አግባብና መልኩ ላነካ እንደሚችል ማሳየት እንደአለበት የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.41(2) ድንጋጌ ያሳያል። በመሆኑም አመልካቹ ዝርዝር ምክንያቱን በማስፈር ይህንኑ የማስረዳት ግድታ አለበት፡ የጣልቃ ገብነቱ አቤቱታ ላቀርብ የሚገባውም ጊዜ ለማራዘም፣ ክርክሩን ለማጓተት ላሆን እንደማይገባውም ከተጠቃሹ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ እንዲሁም ከፍትሃ ብሕር ስነ ስርዓት ህጉ መሰረታዊ አላማ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።
ወደ ተያዘው ጉዳይ ስንመለስ አመልካች የስር ተከሳሽ ወኪል ሁነው ስለተከሳሹ ጥቅምና መብት ጠበቃ ወክለው ቤቱ የተከሳሹ የግል ቤትና ለአሁኑ አመልካች የተላለፈ መሆኑን ጠቅሰው ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ ለራሳቸው ጥቅምና መብት ደግሞ የጣልቃ ልግባ ጥያቄ ያቀረቡ መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል። አመልካች ስለተከሳሹ የወከሐቸው ጠበቃ ቤቱ የስር ተከሳሽ የግል ቤት መሆኑን ጠቅሰው ክርክር ከማቅረባቸው ውጪ ቤቱ የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ነው ቢባል እንኳን በአመልካች እጅ የገባበት ሁኔታ ከስር ተከሳሽ ጋር ያደረጉትን ሽያጭ ህጋዊ ላያደርግ የሚችልበት ምክንያት በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.41(2) በተመለከተው አግባብ ዘርዝረው አላቀረቡም።
እንዲህ ከሆነ ደግሞ በስር ከሳሽ እና ተከሳሽ መካከል በሚደረገው ክርክር የሚሰጠው ውሳኔ ተከሳሽን የሚጠቅም ከሆነ የአሁኑን አመልካች ላጎዳ ይችላል ተብሎ ሚታሰብበት አግባብ የለም።
አመልካች ከስር ከሳሽ መብትና ጥቅም በተለየ ሁኔታ መብትና ጥቅማቸው ላከበር የሚችልበት ህጋዊ ምክንያት መኖሩን ዘርዝረው የጣልቃ ልግባ አቤቱታቸውን ስለማቅረባቸው የክርክሩ ሂደት አያሳይምና። አመልካች የመብታቸው ምንጭ የስር ተከሳሽ መሆናቸውን፤ የወኪላቸውን መብትና ጥቅም ከራሳቸው መብትና ጥቅም ጋር አዛምደው ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ የጣልቃ ልግባ ጥያቄ ማቅረባቸው ክርክሩን ለማጓተት ነው ተብሎ ከሚታሰብ ውጪ ልላ ትርጉም የሚሰጠው አይደለም። እንዲህ አይነት የጣልቃ ልግባ ጥያቄ ደግሞ የጣልቃ ልግባ አቤቱታዎች የሚስተናገዱበትን ስርዓት ከዘረጋው ስነ ስርዓታዊ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ እንዲሁም ከፍትሐብሕር ስርዓት ህጉ መሰረታዊ አላማ ውጪ በመሆኑ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባው አይደለም።
ሲጠቃለልም አመልካች ተከሳሽ ለነበሩት ግልሰብ ወኪል ሁነው ጠበቃ ወክለው ጠበቃውም አከራካሪው ቤት የስር ተከሳሽና ለአመልካች የተላለፈ መሆኑን ጠቅሰው ሲከራከሩ ቆይተው ለአመልካች መብትና ጥቅም ማስከበር ሲባል ነው በማለት የጣልቃ ልግባ ጥያቄ ማቅረባቸው የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 41 ድንጋጌ መሰረታዊ አላማ መሰረት ያላደረገ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ እንጂ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚቻለ ሆኖ ስላላገኘነው ተከታዩን ወስነናል።