No summary available.
መጋቢት 25 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ስንታየሁ ተፈሪ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ማርታ በቀለ - ጠበቃ ሽመልስ መንግስቱ ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩየፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 43 ድንጋጌ መሰረት ወደ ክርክሩ እንዲገባ የተደረገ ተከራካሪ ወገን ጉዳዩን የፍድራል የሚያደርገው የነበረ ሁኖ እያለ ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት ስልጣን ሳይኖረው ስረ ነገሩን አስተናግዶ ዳኝነት ከሰጠ በኋላ ይኼው ተከራካሪ ወገን በይግባኝ ደረጃ በነበረው ክርክር የተሰጠውን ዳኝነት ተቀብሎ ከወጣ በኋላ በልሎች ጉዳዩን የፍድራል ላያደርጉ በማይችሉ ተከራካሪ ወገኞች መካከል የተሰጠው ውሳኔ ከመነሻውም የፍድራል ጉዳይ ነው ተብሎ ላወሰድ የሚችልበትን አግባብ የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኗ ተጠሪ ላይ በጩኮ ወረዳ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።የአመልካች የክስ ይዘትም፡-የተጠሪ መኪና በአካላቸው ላይ ጉዳት ያደረሰባቸው መሆኑን ዘርዝረው ተጠሪ በድምሩ ብር 269,266.44(ሁለት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ ስድስት ብር ከአርባ አራት ሳንቲም) የአካል ጉዳት ካሳ እንዲከፍሉ ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።ተጠሪም ለክሱ ኃላፊነት የልለባቸው መሆኑንና የጉዳት ካሳ መጠን ጥያቄው ተገቢነት የልለው መሆኑን ጠቅሰው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ከመከራከራቸውም በተጨማሪ በተጠሪ ላይ ጉዳት አደረሰ የተባለው መኪናቸው የመድን ሽፋን ከአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ያለው መሆኑን ጠቅሰው ይኼው አካል ወደ ክርክሩ እንዲገባ ይታዘዝላቸው ዘንድ ዳኝነት ጠይቀዋል።ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ወደ ክርክሩ እንዲገባ በማድረግ ክርክሩን ከመራ በኋላ ተጠሪንና ኡንሹራንስ ድርጅቱን ለክሱ ኃላፊ አድርጎ ኢንሹራንስ ድርጅቱ የውል ግድታ ስላለበትየሞራል ካሳን ጨምሮ ለአመልካች ብር 98,750.00 እንዲከፍል፣ተጠሪ ደግሞ ብር 12,460.00 እንዲከፍሉ ሲል ወስኗል።በዚህ ውሳኔ ግራ ቀኙ ቅር በመሰኘት በየፊናቸው ይግባኛቸውን ለሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ ለአመልካች የጉዳት ካሳ ይክፈል ተብሎ የተወሰነው በአግባቡ ነው በማለት ከደመደመ በኋላ የጉዳት ካሳ መጠኑን በተመለከተ ግን የሥር ፍርድ ቤት ስህተት መፈፀሙን ገልፆ ለአመልካች ላከፈል የሚገባው የጉዳት ካሳ መጠን ብር 143,016.44(አንድ መቶ አርባ ሶስት ሺህ አስራ ስድስት ብር ከአርባ አራት ሳንቲም) መሆኑን ለይቶ ከወሰነ በኋላ መድን ሰጪ ድርጅት ላጠየቅ የሚገባው ግን በመድን ውሉ መሰረት ነው በማለት ብር 30,000.00(ሰላሳ ሺህ) ብቻ ለተጠሪ እንዲከፍል በማለት ወስኗል።በዚህ ውሳኔ የአሁኗ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት አቅርበው ከአሁኑ አመልካች ጋር ብቻ ከተከራከሩ በኋላ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ዳኝነት ሙሉ በሙሉ ጸንቷል።ከዚህ በኋላ ደግሞ ተጠሪ የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበው ከአሁኑ አመልካች ጋር ብቻ ከተከራከሩ በኋላ ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ በወረዳው ፍርድ ቤት በጣልቃ ገብነት ገብቶ የተከራከረ ሲሆን ይህም ጉዳዩን የፍድራል ጉዳይ የሚያደርገውና የወረዳው ፍርድ ቤት ደግሞ ጉዳዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የልለው በመሆኑ ውሳኔው ከመነሻውም ሕጋዊ አይደለም በሚል ምክንያት ሙሉ በሙሉ ሽሮታል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ ይግባኝም ሆነ የሰበር አቤቱታ ባልቀረበበት ሁኔታ ጉዳዩ የፍድራል በመሆኑ ከመነሻውም በወረዳው ፍርድ ቤት ላታይ የሚችል አልነበረም ተብሎ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው ውሳኔ የስነ ስርዓት ሕጉን አላማ ያላገናዘበ ነው የሚል ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲታይ በመደረጉ ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችሎቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ ሁኖ የተገኘው የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩ የፍድራል ጉዳይ ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪ ለአመልካች የሰጡትን ውሳኔ መሻሩ የፍትሃ ብሕር ስነ ስርዓት ሕጉን መሰረታዊ አላማ ያገናዘበ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ በይግባኝ ደረጃ በነበረው ክርክር የተሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ ከክርክሩ ውጪ መሆኑ መረጋገጡን፣አመልካችና ተጠሪ በክልሉ ነዋሪ ሁነው የክሱ መሰረትም የጉዳት ካሳ ክፍያ ጥያቄ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ አንድ ተከሳሽ ከእሱ ጋር ኃላፊነት ላወስድ ወይም ላካፈል የሚችል ሦስተኛ ወገን ወደ ክርክሩ እንዲገባለት እንዲታዘዝ ማመልከት እንደሚችል የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 43(1) ድንጋጌ ያመለክታል። በዚህ ጥያቄ መነሻ ወደ ክርክሩ እንዲገባ የተደረገ ተከራካሪ ወገን በክርክሩ ውስጥ ላያነሳ የሚችለው የኃላፊነት እና የኃላፊነት መጠን አስመልክቶ የክርክሩ ዘንግ ከተከሳሽ፣ ከከሳሽ ወይንስ ከሁለቱም ወገን ጋር ላሆን ይገባል? የሚለውን ጥያቄ አስመልክቶ በሁለት አቅጣጫ ምላሽ ላያገኝ እንደሚችል መረዳት ያስፈልጋል። ይኸውም የጣልቃ ገብ ኃላፊነት ምንጭ ውል ወይንስ ሕግ የሚለው በመሰረታዊ ሕግ ድንጋጌዎች የሚወሰን መሆኑ እና በልላ በኩልም የክርክሩ አቀራረብ እና ይዘት በሥነ ሥርዓት ሕጉ በተደነገገው አግባብ መሆን እንዳለበት መረዳት ይቻላል።
በዚህ ጉዳይ በወረዳው ፍርድ ቤት አዋሽ ኢንሹራንስ ጣልቃገብ ሁኖ የተከራከረ ሲሆን ጣልቃ ገብነት በፍትሓብሕር ስነስርዓት ሕጉአግባብ የተፈቀደ አንዱ የክርክሩ ተሳታፊ የሚሆንበትና ራሱን የቻለ መሰረታዊ አላማ ያለው፣ በስነ-ስርዓት ሕጉ የተዘረጋ ስርዓት መሆኑ የሚታወቅ ነው።በ1958ቱ ፍትሃብሄር ስነ-ስርዓት ሕግ ወደ ክርክሩ ላገባ የሚችልበት ስርዓት የተለያየ ቢሆንም ይህ ስርዓት አገሪቱ ከምትከተለው የፍድራል ስርዓትና በዚሁ ስርዓት ከተዘረጋው የፍርድቤቶች አደራጃጀት ጋር ተጣጥሞ በመታየት ስራ ላይ ላውል የሚገባው መሆኑ ይታመናል።በመሆኑም አንድን ጉዳይ የፍድራል ወይም የክልል ብሎ ለመለየት ይቻል ዘንድ በአዋጅ ቁጥር 25/1988 የተቀመጠው መስፈርት ታይቶ የጉዳዩን የመዳኘት የስረነገር ስልጣንም ከዚሁ አንጻር መለየት ያለበት ጉዳይ ነው።
ከዚህ አንጻር ጉዳዩን ስንመለከተው በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5 ስር አንድን ጉዳይ የፍድራል ጉዳይ ለማለት የሚያስችሉ ምክንያቶች ተገልጸዋል። አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ በፍድራል መንግስት የተቋቋመና የተመዘገበ የልማት ድርጅት ሲሆን በፍድራል መንግስቱ አካላት የተመዘገቡ ወይም የተቋቋሙ የንግድ ድርጅቶችና ማህበሮችን በሚመለከት የሚነሱ ክርክሮችን የማየት የስረነገረ ስልጣን የተሰጠው ለፍድራል ፍ/ቤቶች መሆኑ እና እስከ ብር 500,000 ግምት ያለው የገንዘብ ክርክር የማየት ስልጣን ደግሞ በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስልጣን ስር የሚወድቅ መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 25/88 በአንቀጽ 5(6) እና በአንቀጽ 14 ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንረዳው ጉዳይ ነው። በኢ.ፍ.ዲ.ሪ. ሕገ መንግስት በአንቀጽ 80(4) እና በደቡብ ብሕር ብሕረሰቦችና ሕዝቦች ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ሕገ መንግስት በአንቀጽ 75(3) በተመለከተው የስልጣን ውክልና መሰረት በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ስር የሚወድቁ በክልሉ የሚነሱ ጉዳዮችን የማየት ስልጣን የተሰጠው ለክልሉ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።ስለሆነም ከመነሻው ሲታይ በእርግጥ የወረዳው ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን አልተሰጠውም።እንዲሁም የሥረ ነገረ የስልጣን ጥያቄ በማናቸውም የክርክር ደረጃ የሚነሳና ፍርድ ቤቱም በራሱ አነሳሽነት ጭምር ማየት የሚችለው ጉዳይ መሆኑ የሚታወቅ ነው።በመሆኑም የጩኮ የወረዳው ፍ/ቤት የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ወደ ክርክሩ መግባቱ ጉዳዩን ከስረ ነገር ስልጣኑ ውጪ የሚያደርገው መሆኑን ተገንዝቦ ክሱ ጣልቃ ገቡን ባካተተ ሁኔታ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት ይቀርብ ዘንድ ጉዳዩን ዘግቶ ማሰናበት ሲገባው ክርክሩን ቀጥሎ በማየት ውሳኔ መስጠቱ ተገቢ ያልነበረ ሲሆን የሲዳማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ቢሆን ጉዳዩን ከዚህ አንፃር በመመልከት በጉዳዩ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ መሻር ይገባው ነበር።ጉዳዩን የፍድራል ጉዳይ ለማድረግ በሕጉ መለኪያ የተቀመጠው ተከራካሪ ወገን በይግባኝ ደረጃ የክርክሩ ተሳታፊ የነበረ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በዚህ ረገድ በወረዳው ፍርድ ቤት የተፈጸመውን ስህተት ሳያርም መቅረቱ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 እና 231(1(ለ))የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ያላገናዘበ መሆኑ ግልጽ ነው።ይሁን እንጂ አንድን ክርክር የፍድራል ብሎ ለመውሰድ ያስችል የነበረው የአዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ተቀብሎ በስርዓቱ መሰረት ክርክሩን በበላይ ፍርድ ቤቶች ያልቀጠለ ከመሆኑም በላይ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ ቅሬታ ያደረባቸው የአሁኗ ተጠሪ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሲያቀርቡ በመልስ ሰጪነት የሰየሙት የአሁኑን አመልካች ብቻ ነው።ተጠሪ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኛቸው ተቀባይነት ሲያጣም ለክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በተጠሪነት የሰየሙት የአሁኑን አመልካች ብቻ እንጂ አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያን ጭምር አይደለም።ስለዚህ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በነበረው የክርክር ደረጃ ጉዳዩ የፍድራል መሆኑን የሚያስገነዝብ ተከራካሪ ወገን የነበረ ሲሆን ከዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ በኋላ በነበሩት የክርክሩ ሂደቶች ግን ይህ አካል ተሳታፊ አይደለም።ይህም የሚያሳየው ጉዳዩን የፍድራል ለማድረግ ይችል የነበረው የሕግ ምክንያት ቀሪ የሆነ መሆኑንና በአመልካችና በተጠሪ መካከል የሚደረገው ክርክር ደግሞ በባሕርይው የፍድራል ጉዳይ ለመሆን የሚያስችል የሕግ ምክንያት የልለው መሆኑን ነው።
የክርክሩ ሂደት የሚያስገነዝበው ከላይ የተገለጸውን ሁኔታ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ እልባት ማግኘት ያለበት ከስነ ስርዓት ሕጉ አላማ ጋር ተዛምዶና ታይቶ ላሆን ይገባል።የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ መሰረታዊ ዓላማ ክርክሮችን ፍትሃዊ በሆነ እና ሥርዓት ባለው መንገድ በመምራት በአጭር ጊዜ እና በአነስተኛ ወጭ ተገቢውን እልባት እንዲያገኙ ማድረግ መሆኑ ይታመናል።በተለይም የሥነ - ሥርዓት ድንጋጌዎችን መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ እና በክርክሩ አመራር በህጉ በግልፅ ያልተሸፈኑትን ነገር ግን ፍ/ቤቱ በእራሱ በመሰለው እንዲወሰን፣ ትዕዛዝ እንዲሰጥ በሚያስችል አኳኋን በተደነገገ ጊዜ እንደቅደም ተከተሉ ከትክክለኛው ትርጉም ለመድረስና የተሰጠውንም ሥልጣን (Discretionary power) በአግባቡ ለመጠቀም ይህ የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌ ዓላማ ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ ጉዳዩን ማየቱ ጠቀሜታው የጎላ እንደሚሆን ይታመናል።እንደሚታወቀው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ መሰረታዊ መብቶችንና ግድታዎችን ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል መሣሪያ በመሆኑ ይህንኑ ሂደት ውጤት እንዳይኖረው የሚያደርግ የስነ ስርዓት ሕግ አተገባበር ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም።ከዚህ አንፃር ጉዳዩን ስንመለከተው በተከራካሪ ወገን ማንነት የተነሳ አንድ ጉዳይ የፍድራል ነው ለማለት የሚቻልበት የሕግ ምክንያት ባለበት ሁኔታ ጉዳዩን ስልጣን የልለው ፍርድ ቤት አይቶ ዳኝነት ከሰጠና በይግባኝ የክርክር ሂደትም ይኼው ሳይታረም ቀርቶ ጉዳዩን የፍድራል ነው ብሎ ለማለት የሚያስችል ተከራካሪ ወገን በፍሬ ጉዳዩ የተሰጠውን የይግባኝ ሰሚውን ፍርድ ቤት ውሳኔ በመቀበል ከክርክሩ ውጪ ከሆነ እንዲሁም ክርክሩ ጉዳዩን የፍድራል ጉዳይ ለማድረግ በማያስችሉ ተከራካሪ ወገኖች መካከል ከቀጠለ ስልጣን በልለው ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ውጤቱ ምን ይሆናል? የሚለው የስነ ስርዓት ሕግ ጥያቄን አዋጅ ቁጥር 25/1988"ም" ሆነ ልሎች አግባብነት ያላቸው ሕጎች ግልጽ ምላሽ የማይሰጡበት በመሆኑ ምላሽ ማግኘት ያለበት ከፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕጉ መሰረታዊ አላማ አንፃር ሁኖ አግኝተናል።ስለሆነም የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደረጃ ቀሪ የሆነውን የሕግ ምክንያት በመያዝ ጉዳዩ ከመነሻውም ስልጣን በልለው ፍርድ ቤት የተሰጠ ነው በማለት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተሰጠውን ዳኝነት መሻሩ የፍትሃ ብሕር ስነ ስርዓት ሕጉን መሰረታዊ ዓላማ ያላገናዘበ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠውን ውሳኔ መሻር እና በዋናው ጉዳይ በአመልካችና በተጠሪ መካከል በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የፀናው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት መሆን ያለመሆኑን የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት አይቶ የመጨረሻ ዳኝነት እንዲሰጥበት ማድረጉ ስነ ስርዓታዊ ሁኖ አግኝተናል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ውሣኔ
No topics extracted.