No summary available.
ሚያዝያ 7 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወል ረታ ቶለሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ብርሃኑ አማረ ጠቅላላ ሕንፃ ስራ ተቋራጭ - ነ/ፈጅ አንተነህ ድንበሩ ቀረቡ ተጠሪ፡- ፋርማ ብርብር ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ጠበቃ ወነድወሰን ተ/ማርያም ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ በፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር ስለዋናዎቹ ባለጉዳዮች በመሆን ልሎች ሰዎች በተሟጋችነት ላቀርቡ የሚችሉበትን ስርዓት የሚመለከት ነው።የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ ክርክሩ በተጀመረበት በፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከሳሽ የነበረው የአሁኑ ተጠሪ ተከሳሽ በነበሩት በአቶ ብርሃኑ አማረ(በአሁኑ አመልካች) ላይ የመሰረተው ክስ በልሉበት ተሰምቶ በተከሳሹ ላይ ውሳኔ መሰጠቱን፣ተከሳሹም ክሱ በልሉበት ተሰምቶ ውሳኔ የተሰጠባቸው መጥሪያው በተገቢው ስርዓት እንዲደርሳቸው ሳይደረግ በመሆኑ ውሳኔው ተነስቶ ክርክሩ ባሉበት እንደገና እንዲታይ ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው በፍ/ስ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78 መሰረት አቤቱታ ማቅረባቸውን፣አቤቱታውን ያቀረቡትም ብርሃኑ አማረ ጠቅላላ ሕንፃ ስራ ተቋራጭ በሚል ስም መሆኑን፣ከሳሹም የአቤቱታው ግልባጭ ደርሶት በሰጠው መልስ ክሱን ያቀረበውም ሆነ ውሳኔ ያሰጠው በአቶ ብርሃኑ አማረ ላይ እንጂ በብርሃኑ አማረ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ላይ ባለመሆኑ ከከሳሹ ጋር የውል ግንኙነት በልለው እና ውሳኔ ባልተሰጠበት ድርጅት ነገረ ፈጅ አማካይነት የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ላኖረው አይገባም በማለት መከራከሩን፣ፍ/ቤቱም ወደአቤቱታው ፍሬ ጉዳይ ሳይገባ የአቤቱታ አቀራረቡን ስነስርዓታዊነት ከመረመረ በኋላ ተከሳሹ ግለሰብ ነጋድ መሆናቸውን፣ከተከሳሹ ስም ቀጥሎ የተመለከተው ሐረግም የሚያመለክተው ተከሳሹ በሕግ መሰረት የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን ሳይሆን የግለሰብ ነጋድውን የንግድ ስም መሆኑን፣ነገረ ፈጅ መወከል የሚችለው በሕግ አግባብ የተቋቋመ ድርጅት እንጂ ግለሰብ(የተፈጥሮ ሰው) አለመሆኑን ገልጾ ተከሳሽ የሕጉን መመዘኛ ሳያሟሉ ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት መዝገቡን ዘግቶ መመለሱን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡት የፍ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኙን ዘግቶ በማሰናበቱ ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት አቤቱታ የቀረበው አመልካችን ወክሎ ለመከራከር በሚችል ሰው አይደለም መባሉ የመዝገብ መዘጋት ውጤትን የሚያስከትል መሆን አለመሆኑን ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በክርክሩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው ነጥቦች
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት የተዘጋጀ አቤቱታ ፈርመው በማቅረብ ስለአመልካቹ ሆነው በፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የቀረቡት ተወካይ በአመልካቹ ስም በፍ/ቤት በተሟጋችነት ለመቆም በስነ ስርዓት ሕጉ የሚጠየቀውን መስፈርት የሚያሟሉ ስላልሆኑ አመልካቹን ወክለው ላከራከሩ አይችሉም በማለት የተሰጠው ትዕዛዝ ተገቢነት ያለው ነው ወይስአይደለም?
ተገቢነት ያለው ነው ከተባለ መስፈርቱን አለማሟላታቸው የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት ምን ላሆን ይገባል?
የሚሉ መሆናቸውን በመገንዘብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዚሁ ጭብጦች አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ ቀደም ሲል እንደተገለጸው ተጠሪ ክሱን የመሰረተው እና ውሳኔ ያሰጠው የአመልካቹን ስም ብርሃኑ አማረ ገብረአብ ብሎ በመግለጽ ሲሆን አመልካች ደግሞ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.78 መሰረት ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ስማቸውን የገለጹት ብርሃኑ አማረ ጠቅላላ የህንፃ ስራ ተቋራጭ በማለት ነው። በመሰረቱ ከአመልካቹ ስም ቀጥሎ "ጠቅላላ የህንፃ ስራ ተቋራጭ" በሚል የተመለከተው ሐረግ የተሞላው የአመልካቹን የንግድ ስራ ዘርፍ ወይም የንግድ ስም ለማመልከት ታስቦ ከመሆኑ ውጪ አመልካቹ ሕጋዊ ሰውነት የተሰጠው ተቋም መሆኑን ለማመላከት እንዳልሆነ በግራ ቀኙ ያልተካደ ጉዳይ ስለመሆኑ ከክርክራቸው ይዘት መገንዘብ ይቻላል።አመልካቹ የተፈጥሮ ሰው መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ ቀጥሎ መታየት የሚገባው ጉዳይ በስር ፍ/ቤት የአመልካቹ ነገረ ፈጅ ሆነው የቀረቡት ሰው በፍርድ ቤት በሚደረግ ክርክር በተሟጋችነት ላቆሙ ስለሚችሉ ሰዎች በሕጉ የተመለከተውን መስፈርት የሚያሟሉ ናቸው ወይስ አይደሉም? የሚለው ጥያቄ ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ በማናቸውም ፍ/ቤት አቤቱታ ለማቅረብ ወይም ለመከራከር ባለጉዳዩ ራሱ እንዲቀርብ የሚያስገድድ ሕግ ወይም በፍ/ቤቱ የተሰጠ የተለየ ትዕዛዝ የልለ በሆነ ጊዜ ባለጉዳዩ ራሱ ለመቅረብ የማይችል ወይም የማይፈቅድ ሲሆን ነገሩን ለማስረዳት፣ ለመከራከር፣ለሚጠየቀው ሁሉ በቂ መልስ ለመስጠት የሚችል ሰው በዋናው ባለጉዳይ ተተክቶ በነገረ ፈጅነት፣በወኪልነት፣በጠበቃነት እንዲከራከር ለማድረግ እንደሚቻል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.57 ተደንግጎ የሚገኝ ሲሆን በዚሁ ሕግ በቁጥር 60፣61 እና 62 ስር የተመለከቱት ልዩ ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው አበል ሳይሰጣቸው ስለልላ ሰው ሆነው በወኪልነት ወይም በነገረ ፈጅነት አቤቱታ ለማቅረብ፣ለመከራከር፣ለመሟገት እና ነገሩን ለመከታተል የሚችሉት የዋናው ባለጉዳይ ባለቤት፣ወንድም፣እህት፣ልጅ፣አባት ወይም አያት ስለመሆናቸው በቁጥር 58(1) ስር ተመልክቷል።በተያዘው ጉዳይ ስለአመልካቹ በመሆን በስር የመ/ደ/ፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ሰው ከዋናው ባለጉዳይ ጋር በቁጥር 58(1) ከተመለከተው የዝምድና ግንኙነት መካከል አንዱን የሚያሟሉ ስለመሆኑ ወይም ዋናው ባለጉዳይ በቁጥር 60፣61 እና 62 ስር ከተመለከቱት ልዩ ሁኔታዎች መካከል በአንዱ የሚሸፈኑ ስለመሆኑ በአመልካች በኩል የቀረበ ክርክር ካለመኖሩም በላይ የውክልና ሰነዱም ይህንን የሚያረጋግጥ አይደለም።እንዲህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ክርክሩን ራሳቸው ወይም በጠበቃ ወይም መስፈርቱን በሚያሟላ ተወካይ አማካይነት መከታተልና መምራት የሚችሉ ከመሆኑ ውጪ በስር የመ/ደ/ፍ/ቤት ስለአመልካቹ ሆነው የቀረቡት ሰው በክርክሩ ለመቀጠል የሚችሉበት ስነ-ስርዓታዊ አግባብ አይኖርም።በመሆኑም ስለአመልካቹ ሆነው በፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የቀረቡት ተወካይ በአመልካቹ ስም በፍ/ቤት በተሟጋችነት ለመቆም በስነ ስርዓት ሕጉ የሚጠየቀውን መስፈርት የሚያሟሉ ስላልሆኑ አመልካቹን ወክለው ላከራከሩ አይችሉም በማለት የተሰጠው የትዕዛዝ ክፍል ላነቀፍ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት አልተገኘም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ስለአመልካቹ ሆነው የቀረቡት ተወካይ በፍ/ቤት በተሟጋችነት ለመቆም በስነ ስርዓት ሕጉ የሚጠየቀውን መስፈርት የማያሟሉ መሆኑ የተረጋገጠ ቢሆንም በልላ በኩል ግን ከዋናው ባለጉዳይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 63 ድንጋጌ መሰረት በተገቢው ባለስልጣን ዘንድ ተረጋግጦ የተሰጣቸው የውክልና ስልጣን መኖሩ ተረጋግጧል።እንዲህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ክርክሩን ራሳቸው ወይም በጠበቃ ወይም መስፈርቱን በሚያሟላ ተወካይ አማካይነት መከታተልና መምራት እንዲችሉ ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 197(1) በተመለከተው መሰረት ተለዋጭ ትዕዛዝ እና ቀጠሮ መስጠት ይገባው የነበረ ከመሆኑ ውጪ አመልካች ሙሉ በሙሉ አቤቱታ እንዳላቀረቡ ወይም ጉዳዩን እንዳልተከታተሉ በመውሰድ መዝገቡን ዘግቶ ማሰናበቱ የስነስርዓት ሕጉን አጠቃላይ ዓላማ እና መርህ ያገናዘበ ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ትዕዛዝ በከፊል መሰረታዊ ሕግ ስሕተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ስለአመልካቹ ሆነው የቀረቡት ተወካይ በአመልካቹ ስም በፍ/ቤት በተሟጋችነት ለመቆም በስነ-ስርዓት ሕጉ የሚጠየቀውን መስፈርት የሚያሟሉ ስላልሆኑ አመልካቹን ወክለው ላከራከሩ አይችሉም ሲል መዝገቡን ዘግቶ በማሰናበት የፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤትበመ.ቁ.100727 በ21/10/2005 ዓ.ምየሰጠው እና በፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ.149227 በ26/11/2005 ዓ.ም በትዕዛዝ የጸናው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሻሽሐል።
ከላይ በተ.ቁ. 1 ከተመለከተው ውሳኔ ውስጥ ስለአመልካቹ ሆነው የቀረቡት ተወካይ በአመልካቹ ስም በፍ/ቤት በተሟጋችነት ለመቆም በስነ-ስርዓት ሕጉ የሚጠየቀውን መስፈርት የሚያሟሉ ስላልሆኑ አመልካቹን ወክለው ላከራከሩ አይችሉም በማለት የተሰጠው የትዕዛዝ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ከላይ በተ.ቁ. 1 ከተጠቀሰው ውሳኔ ውስጥ መዝገቡን ዘግቶ በማሰናበት የተሰጠው የትዕዛዝ ክፍል በፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ክርክሩን ራሳቸው ወይም በጠበቃ ወይም መስፈርቱን በሚያሟላ ተወካይ አማካይነት መከታተልና መምራት እንዲችሉ ፍ/ቤቱ ተለዋጭ ትዕዛዝ እና ቀጠሮ በመስጠት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 78 መሰረት ከቀረበለት አቤቱታ ጋር ተያይዞ የግራቀኙን ክርክር መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዳዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341(1) መሰረት ለፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት እንዲመለስ ወስነናል።
በዚሁ መሰረት መፈጸም ያስችለው ዘንድ የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ለፍ/የመ/ደ/ ፍ/ቤት ይላክ።
በዚህ መዝገብ ተሰጥቶ የነበረው የአፈጻጸም ዕግድ ተነስቷል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።