No summary available.
ግንቦት 8 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሴቴ ከበደ - ተወካይ ወርቁ ከበደ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1.ወ/ሮ አስናቁ ፋንታዬ - ተወካይ መኩሪያ መኮንን ቀረቡ 2. አቶ ጣፋጭ ተሾመ- መብታቸው ታልፏል 3.የጉባ ላፍቶ ወረዳ መሬት አስተዳደር ጽ/ቤት - የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ አመልካች አቤቱታ ያቀረቡት የአሁኖቹ ተጠሪዎች ጋር በጉባ ላፍቶ ወረዳ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 00951 ያላቸው ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 31 መሰረት ወደ ሀከፋ ወረዳ ፍ/ቤት ተዛውሮ እንዲታይ ያቀረቡትን የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ የተመለከተው የሰሜን ወሎ ዞን ከ/ፍ/ቤት አመልካች አቤቱታውን ያቀረቡት የሆነው መዝገብ በውሣኔ ከተቋጨ በኋላ እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 መሰረት ዳግም ዳኝነት እንዲታይ የቀረበ ጥያቄም በልለበት ሁኔታ በመሆኑ እንዲሁም የክስ ይዛወርልኝ ጥይቄው በበቂ ምክንያት ላይ ያልተመሰረተ በመሆኑ አመልካች ያቀረቡት የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም በማለት የሰጠው እና በክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በትዕዛዝ የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ የጉባ ላፍቶ ወረዳ ፍ/ቤት ዳግም ዳኝነት እንዲታይ መዝገቡ ተከፍቶ በ22/05/2004 ዓ.ም. ትዕዛዝ መስጠቱ በተመለከተበት ሁኔታ ተጠሪዎች ለክስ ይዛወርልኝ አቤቱታው በሰጡት መልስ በወረዳው ፍ/ቤት የተከፈተ መዝገብ የለም በማለት የሰጡትን መልስ ተከትሎ የአመልካች አቤቱታ ሳይስተናገድ የተከፈተ መዝገብ የለም ተብሎ የመወሰኑን አግባብነት ተጠሪዎች ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ መብታቸው ከታለፈው 2ኛ ተጠሪ በስተቀር ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዳዩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት በአንድ ወረዳ ፍ/ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ ወደ ልላ ወረዳ ፍ/ቤት ተዛውሮ እንዲታይ አንደኛው ወገን ሲያመለክት ተገቢ ምክንያቶች መኖራቸው ተረጋግጦ በክስ ይዛወርልኝ አቤቱታው እንደየሁኔታው አግባብነት ያለው ውሳኔ ላሰጥ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 31 ተመልክቷል።በዚህ ድንጋጌ መሰረት የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ለማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል።በተያዘው ጉዳይ የዞኑ ከ/ፍ/ቤት የቀረበለትን የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ላለመቀበል የሰጠው ዋነኛ ምክንያት ግራ ቀኙ በጉባ ላፍቶ ወረዳ ፍ/ቤት ክርክር ሲያደርጉበት የነበረው የሆነው መዝገብ በውሳኔ የተቋጨ መሆኑ እና መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 6 ድንጋጌ መሰረትም ሆነ በልላ ምክንያት ያልተንቀሳቀሰ መሆኑን ከግራ ቀኙ ክርክር መገንዘብ ተችሐል የሚል ሲሆን አመልካች ለክስ ይዛወርልኝ አቤቱታቸው በቂ ምክንያት አላቀረቡም የሚለው ነጥብበተጨማሪ ምክንያትነት በውሳኔው ይዘት ውስጥ የተገለጸ ከመሆኑ ውጪ ተፈጻሚነት ባለው የውሳኔ ክፍል ውስጥ ያልተጠቀሰ መሆኑን ተገንዝበናል።የጉባ ላፍቶ ወረዳ ፍ/ቤትየቀረበለትን የዳግም ዳኝነት አቤቱታ ለማየት መዝገቡ እንዲንቀሳቀስበ22/05/2004 ዓ.ም. ትዕዛዝ ሰጥቷል መባሉን በተመለከተ መዝገቡ እንዲንቀሳቀስ ተሰጠ የተባለውን ትዕዛዝ አመልካች በዞኑ ከ/ፍ/ቤት ስለማቅረባቸው የመዝገቡ ግልባጭ አያመለክትም።ቀደም ሲል እንደተገለጸው የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታውን የተመለከተው የሰሜን ወሎ ዞን ከ/ፍ/ቤት ተፈጻሚነት ባለው የውሳኔው ክፍል ላይ እንደገለጸው ጥያቄውን ሳይቀበል የቀረው የአመልካች የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ የቀረበው በስር ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ ፋይል ባልተከፈተበት ወይም የቀድሞው መዝገብ ባልተንቀሳቀሰበት ሁኔታ ስለሆነ አቤቱታው የክስ ምክንያት የለውም በማለት በመሆኑ በመሰረቱ ይህ የከ/ፍ/ቤት ውሳኔ አመልካች መዝገቡ እንዲንቀሳቀስ የተደረገ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በማቅረብ የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታቸውን በልላ መዝገብ እንደ አዲስ ከማቅረብ የሚከለክላቸው አይደለም።
ሲጠቃለል የአመልካች የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ የቀረበው በስር ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ ፋይል ባልተከፈተበት ወይም የቀድሞው መዝገብ ባልተንቀሳቀሰበት ሁኔታ ስለሆነ አቤቱታው የክስ ምክንያት የለውም በማለት በዞኑ ከ/ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።
No topics extracted.
348(1) መሰረት ፀንቷል።
የአመልካች የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ የክስ ምክንያት የለውም ተብሎ ውድቅ የተደረገው የወረዳው ፍ/ቤት መዝገብ መንቀሳቀሱን የሚያረጋግጥ ትዕዛዝ አያይዘው ባለማቅረባቸው በመሆኑቀደም ሲል ያቀረቡት አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም ተብሎ ተቀባይነት ማጣቱ የመዝገቡን መንቀሳቀስ የሚያረጋጥ ማስረጃ በማያያዝ የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄያቸውን በልላ መዝገብ በድጋሚ ከማቅረብ የሚያግዳቸው አይደለም በማለት ወስነናል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያሰከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
የማይነበቡ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።