No summary available.
የካቲት 24 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወል ረታ ቶለሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አስመረት ኃ/ሚካኤል ጠበቃ ጌትነት የሻነህ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዳዩ አላግባብ የተያዘ ነው የተባለን ቤት በፍርድ ኃይል ከማስለቀቅ ጋር ተያይዞ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የአሁኖቹ አመልካች እና ተጠሪዎች ጉዳዩ በተጀመረበት የፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት እንደቅደም ተከተላቸው ከሳሽ እና ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል።
ከሳሽ በ16/03/2003 ዓ.ም.አዘጋጅተው ያቀረቡት ክስ ይዘትም ባጭሩ፡- ከሳሽ ከአቶ ዘርዓይ ሐጎስ ጋር በ16/05/2002 ዓ.ምባህላዊ ጋብቻ ፈጽመው በ04/02/2003 ዓ.ምጋብቻውን በማስመዝገብ ማስረጃ የተሰጣቸው መሆኑን፣ በ18/05/1998 ዓ.ም በተጻፈ የኮንዶሚኒየም ቤት ሽያጭ ውል በቦል ክ/ከተማ በቀበል 01 ውስጥ በብሎክ 2 የሚገኝ ቁጥሩ ቢ.አር.አር.ቢ2-1/ዐ5 የሆነ ቤት ከቦል ክ/ከተማ ለአቶ ዘርዓይ ሐጎስ የተላለፈ መሆኑን፣ ከሳሽ እና ባለቤታቸው ይህንኑ ቤት በ16/05/2002 ዓ.ም በተጻፈ የጋብቻ ውል የጋራ ያደረጉት መሆኑን፣ ይህንን ቤት በተመለከተ ባለቤታቸው ለ1ኛ ተከሳሽ በ25/12/2002 ዓ.ምየተጻፈ የውክልና ስልጣን ሰጥተው የነበረ ቢሆንም የውክልና ስልጣኑን ከ24/01/2003 ዓ.ም ጀምሮ የሻሩ መሆኑን እና ተከሳሾቹ ምንም መብት ሳይኖራቸው ተከራዮችን በማስወጣት ቤቱን በሕገወጥ መንገድ ይዘው የሚገኙ መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ ቤቱን ለቀው እንዲያስረክቡ እና ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ኪራዩን እንዲከፍሉ ይወሰን ዘንድ ዳኝነት የተጠየቀበት ነው።
1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በበኩላቸው በ12/04/2003 ዓ.ም.በተዘጋጀ ማመልከቻ ከሳሽ የአቶ ዘርዓይ ሐጎስ ባለቤት ስላልሆኑ ቤቱን በተመለከተ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት የላቸውም የሚል መቃወሚያ ካስቀደሙ በኋላ በፍሬ ጉዳዩ ረገድ በሰጡት መልስ ክስ ያስነሳውን ቤት አቶ ዘርዓይ ሐጎስ በ25/12/2002 ዓ.ም. በተጻፈ ውል በብር 345000 ለ1ኛ ተከሳሽ በሽያጭ ያስተላለፉ መሆኑን፣ ለዋስትና ይሆን ዘንድም አቶ ዘርዓይ ሐጎስ የብር 345ዐዐዐ ብድር ውል በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ለ1ኛ ተከሳሽ የፈረሙ መሆኑን፣ የብድር ውሉን የፈረሙትም ትዳር እንደልላቸው ከሚመለከተው ክፍል ማረጋገጫ በማቅረብ መሆኑን፣ ይህ በተደረገበት ጊዜም ከሳሽ የአቶ ዘርዓይ ሐጎስ የአክስት ልጅ እንደሆኑ በመግለጽ አብረዋቸው የነበሩ መሆኑን፣1ኛ ተከሳሽ ከአቶ ዘርዓይ ሐጎስ በተሰጣቸው የውክልና ስልጣን መሰረት የቤቱን ጠቅላላ እዳ ከፍለው ከክፍለ ከተማው ጋር የሽያጭ ውል ያደረጉ መሆኑን እና ቤቱን የተላለፈባቸው በሽያጭ ውል በመሆኑ የውክልና ስልጣኑ የተሻረ የመሆን አለመሆን ጉዳይየሚያስከትለው ውጤት አለመኖሩን በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ የተከራከሩ ሲሆን 3ኛ ተከሳሽ በበኩላቸው ቤቱን ያልያዙና ተከራዮችንም ያላስወጡ መሆኑን በመግለጽ መልስ ሰጥተዋል።
ፍ/ቤቱም መቃወሚያውን በ16/06/2003 ዓ.ም. በብይን አልፎ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ቤቱን ይዘው የሚገኙት ከሳሽ እንደሚሉት ምንም ዓይነት መብት ሳይኖራቸው በሕገወጥ መንገድ ሳይሆን በአቶ ዘርዓይ ሐጎስ እና በ1ኛ ተከሳሽ መካከል በተደረገ የሽያጭ ውል መሰረት እንደሆነ መረጋገጡን፣ የሽያጭ ውል መኖሩ በከሳሽም ያልተካደ መሆኑን፣ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ከሳሽ ቤቱን በተመለከተ ክስ ለማቅረብ መብት የሚኖራቸው የሽያጭ ውሉን ከማስፈረስ አንጻር ከሚሆን በስተቀር ተከሳሾቹ ምንም ዓይነት መብት ሳይኖራቸው ቤቱን በሕገወጥ መንገድ ይዘዋል በማለት እንዳልሆነ እና ከሳሽ የውል ይፍረስልኝ ክስ ባላቀረቡበት ሁኔታ ውሉ ላፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም የሚል ጭብጥ መስርቶ በመዝገቡ ማከራከርና ውሳኔ መስጠት ስነ ስርዓታዊ አግባብነት እንደልለው በመግለጽ ክሱን ውድቅ አድርጓል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡት ይ/ሰሚው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በማጽናቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ አመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ተጠሪዎች በሕገ ወጥ መንገድ መያዛቸውን በገለጹበት እና የኮንዶሚኒየም ቤቶችን ከአምስት ዓመት በፊት ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የማይቻል ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 19/1997 በተደነገገበት ሁኔታ የስር ፍ/ቤቶች 1ኛ ተጠሪ ቤቱን የያዙት በሽያጭ ውል በመሆኑ የሽያጭ ውሉን የማስፈረስ ክስ ካልቀረበ በስተቀር በዚህ ክስ የውሉ ሕጋዊነት ላመረመር አይችልም በሚል አመልካች በሚስትነታቸው ያቀረቡትን የቤት ይልቀቁልኝ ጥያቄ ውድቅ የማድረጋቸውን አግባብነት ተጠሪዎች ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለጉዳዩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
No topics extracted.
በዚህም መሰረት ቀደም ሲል እንደተገለጸው ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በአመልካቾች በሕገ ወጥ መንገድ ተይዞአል በሚል አመልካች ያቀረቡትን ክስ ውድቅ ያደረገው ቤቱ በተከሳሾቹ የተያዘው ከሳሽ እንደሚሉት በሕገ ወጥ መንገድ ሳይሆን በሽያጭ ውል መነሻ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ከሳሽ ቤቱ የተያዘው በውል መሆኑን እያወቁ በሕገወጥ መንገድ እንደተያዘ አድርገው ክስ ማቅረባቸው ተገቢውን የክስ አቀራረብ ስርዓት የተከተለ አይደለም በማለት ነው። በመሰረቱ ማናቸውም ለፍርድ ቤት የሚቀርብ ክስ ሁሉ ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዳዩን በሚገባ መርምሮ ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት በሚያስችለው በዚያው ነገር ልላ አከራካሪ ጉዳይ በማያስከትል ሁኔታ ግልጽ በሆነ አጻጻፍ መቅረብ እንዳለበት፣ በክስ ማመልከቻ ላይ መገለጽ ከሚገባቸው ነገሮች መካከልም አንዱ የክሱ ምክንያት እና ለክሱ ምክንያት የሆኑት ነገሮችና እነዚሁ የተፈጠሩበት ጊዜና ስፍራ እንደሆነ የክስ አቀራረብን ከሚመለከቱ የፍ.ስ.ስ.ሕ.ቁ 8ዐ(2)፣213(1)፣216(1)፣222(1)(ረ) እና ልሎችም ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። የእነዚህ ድንጋጌዎች ዓላማም የፍትሐብሄር ጉዳዮችን በተመለከተ በሰዎች መካከል የሚፈጠሩት የግንኙነት ዓይነቶች፣ እንዲሁም እነዚህ ግንኙነቶች የሚገዙባቸው የህግ ድንጋጌዎች፣ ግንኙነቶቹን አስመልክቶ የሚነሱ ክርክሮች የሚመሩበት ስርዓትም ሆነ የተለያዩ ግንኙነቶችን አስመልክቶ ከተከራካሪ ወገኖች የሚቀርቡት የክርክር ነጥቦች የተለያዩ በመሆናቸው ምክንያት እንደየግንኙነቱ እና ክርክሩ ዓይነትና ሁኔታ ለፍ/ቤት የሚቀርቡትን ክርክሮች በተቀላጠፈ ሁኔታ እና በተገቢው ስነ ስርዓታዊ አግባብ መርቶ እልባት ለመስጠት ማስቻል እንደሆነ የሚታመን ነው።
በተያዘው ጉዳይ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት አቶ ዘርዓይ ሐጎስ በ25/12/2002 ዓ.ም.
በተጻፈ ውል በብር 345000 ለ1ኛ ተጠሪ በሽያጭ ያስተላለፉ መሆኑ በአመልካች እንዳልተካደ እና ቤቱ በተጠሪዎች እጅ የገባው እና ይዘው የሚገኙት በዚሁ ውል ምክንያት እንደሆነ የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል። እንዲህ ከሆነ ደግሞ አመልካች በዚህ ሁኔታ በውል በተላለፈው ቤት ላይ መብት አለኝ የሚሉ ከሆነ ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች መሰረት በቤቱ ላይ አለኝ የሚሉትን መብት ማስከበር የሚችሉት ውሉን ከማስፈረስ አንፃር ከሚሆን በቀር በተጠሪዎች በውል የተያዘውን ቤት በሕገወጥ መንገድ እንደተያዘ አድርገው ክስ ለማቅረብ የሚችሉበት ስነ ስርዓታዊ አግባብ አይኖርም። ቤቱ በሕገ ወጥ መንገድ የተያዘ ነው ማለት እና ቤቱ የተያዘበት ውል የሕጉን መስፈርቶች አሟልቶ የተደረገ አይደለም ማለት ደግሞ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው።
አመልካች ይህንኑ ተገንዝበው በፍ/ከ/ፍ/ቤት የውል ይፍረስልኝ ክስ አቅርበው በክርክር ላይ የሚገኙ ስለመሆኑ ተጠሪዎች የመዝገብ ቁጥሩን ጭምር ጠቅሰው ላቀረቡት ክርክርም አመልካች ያቀረቡት ማስተባበያ አለመኖሩን ተገንዝበናል።
ሲጠቃለል አመልካች ያቀረቡት ክስ ተገቢውን የክስ አቀራረብ ስርዓት የተከተለ ስላልሆነ ተቀባይነት የለውም በማለት በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የሰጠው እና በፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ በ23/ዐ4/2ዐዐ5 ዓ.ም. በፍርድ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
አመልካች የውል ይፍረስልኝ ክስ ለማቅረብ ያላቸው መብት በዚህ ውሳኔ አልተነካም።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።