No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሡልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመስል አመልች፡- ወ/ሮ አሰለፈች ይመር - ጠበቃ ችርነት ወርዶፋ ቀረቡ።
ተጠሪዎች፡-
ወ/ሮ አስመረት ተወልደ
አቶ ብርሃኔ ተወልደ ጠበቃ ማርቆስ ወ/ሰንበት ቀረቡ።
አቶ ናትናኤል ተወልደ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቶአል።
ጉዳዩ ጋብቻ ወይም የትዳር ሁኔታ መኖር አለመኖርን የሚመለከት ክርክር ሲሆን አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡት የአሁኖቹ ተጠሪዎች በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 መሰረት ያቀረቡትን የመቃወሚያ ክርክር በመቀበል የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች የአቶ ተወልደ ገብሩ ሕጋዊ ሚስት ናቸው፤ብርክቲ ተወልደ፣ሲሳያስ ተወልደ፣ዳንኤል ተወልደ እና ሄለን ተወልደ ደግሞ ከዚሁ ጋብቻ የተወለዱ የአቶ ተወልደ ገብሩ ልጆችና የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች ናቸው በማለት ቀደም ሲል በ22/03/1993 ዓ.ም. ሰጥቶት የነበረውን ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 360(2) ድንጋጌ መሰረት አሻሽሎ የአመልካችን ሚስትነት የሚመለከተውን የውሳኔ ክፍል በመሰረዝ እና የተወላጆቹን ልጅነት እና ወራሽነት የሚመለከተውን የውሳኔ ክፍል ግን በማጽናት የሰጠው እና በይግባኝ ሰሚው ፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።
የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ አቶ ተወልደ ገብሩ ባራኪ በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 17 በቀበል 20 በቤት ቁጥር 1972 ሲኖሩ ቆይተው በ12/03/1991 ዓ.ም በሞትመለየታቸውን በመግለጽ አመልካች ሚስትነታቸው እና የአራቱ ልጆች ወራሽነት እንዲሁም አመልካች ለሁለቱ ልጆች ሞግዚት መሆናቸው ተረጋግጦ ማስረጃ እንዲሰጣቸው በ29/03/1991 ዓ.ም አቤቱታ ማቅረባቸውን፣ለዚህ አቤቱታቸውም አራት ምስክሮችን መቁጠራቸውን እና ሚስትነታቸውን የሚያረጋግጥ ከወረዳ 2 ቀበል 11 ጽ/ቤት በቤተሰብ መመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተመዘገቡበትና ልሎችም ማስረጃዎች በትዕዛዝ እንዲቀርቡላቸው መጠየቃቸውን፣በልላ በኩል አቶ መስፍን ተወልደ፣ወ/ሮ ይህደጎ ተወልደ እና ወ/ሮ ፍሬ ወይኒ ተወልደ የተባሉ ሰዎች የሟች አቶ ተወልደ ገብሩ ልጆች መሆናቸውን ገልጸው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 41 መሰረት በጣልቃ ገብነት ለመከራከር ጠይቀው በተፈቀደላቸው መሰረት በ23/11/1991 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ ሟች በአድራሻቸው ይኖሩ የነበሩት ከሕጋዊ ባለቤታቸው ከወ/ሮ አክበረት አስገዶም ጋር መሆኑን፣ሟች ከአመልካች ጋር አመልካች በጠቀሱት አድራሻ ኖረው የማያውቁ መሆኑን፣አመልካች ሚስት ስለመሆናቸው የቀረበ የጽሁፍ ማስረጃ አለመኖሩን፣ልሎች አመልካቾችም በጋብቻ ውስጥ ስላልተወለዱ ልጅነታቸውን አረጋግጠው መቅረብ የሚጠበቅባቸው መሆኑን በመግለጽ መከራከራቸውን፣ለዚህ የጣልቃ ገቦች ክርክር አመልካቿ በ11/04/1992 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ ሟች ከወ/ሮ አክበረት አስገዶም ጋር የነበራቸው ጋብቻ በስምምነት የፈረሰ መሆኑን፣የጋብቻ ሁኔታ መኖሩን በምስክሮች ማስረዳት የሚቻል መሆኑን፣ተወላጆቹም የተወለዱት በጋብቻ ውስጥ በመሆኑ ወራሽነታቸው ላረጋገጥ የሚገባው መሆኑን በመግለጽ መልስ መስጠታቸውን፣ፍ/ቤቱም በሁለቱም ወገኖች አራት አራት ምስክሮችን ከሰማ በኃላ የባልና ሚስትነት ሁኔታ መኖሩን በምስክሮች ማስረዳት የሚቻል ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር.
700 1 የተመለከተ መሆኑን እና በአንጻሩ የባልና ሚስትነት ሁኔታ አለመኖሩንም በምስክሮች ማስተባበል የሚቻል ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 700(2) ተደንግጎ እንደሚገኝ፣ሟች እና አመልካች በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 17 በቀበል 20 በቤት ቁጥር 1972 ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ በባልና ሚስትነት የኖሩ፣አራት ልጆችን የወለዱ እና እሰከ ሟች ሞት ድረስ ያልተለያዩ መሆኑ በአመልካች ምስክሮች እንደተረጋገጠ፣ በማስረጃነት በትዕዛዝ የቀረበው በዞን 5 የወረዳ 2 ቀበል 11 መስተዳድር ጽ/ቤት የስራ አስፈጻሚ አባላት ያስተላለፉት ውሳኔም ሟች የአመልካች ባለቤት መሆናቸውን የሚገልጽ እንደሆነ፣ጣልቃ ገቦች ያሰሟቸው ምስክሮች በአመልካች ማስረጃ የተመሰከረውን ፍሬ ነገር የሚያስተባብል እንዳልሆነ በዝርዝር ገልጾ የጣልቃ ገቦችን ክርክር ውድቅ በማድረግ እና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 699 መሰረት የአመልካችን ሚስትነት እና የልሎችን አመልካቾች ልጅነት እና ወራሽነት በማረጋገጥ በ22/03/1993 ዓ.ም ውሳኔ መስጠቱን የውሳኔው ግልባጭ ያመለክታል።
No topics extracted.
የአሁኖቹ ተጠሪዎች በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 358 መሰረት የመቃወም አቤቱታ ያቀረቡት በዚሁ ውሳኔ ላይ ሲሆን በ28/08/2000 ዓ.ም አዘጋጅተው ያቀረቡት የመቃወም አቤቱታ ይዘትም ባጭሩ፡-ባለቤታቸው ወ/ሮ አክበረት አስገዶም ከሞቱበት ከ1973 ዓ.ም. ጀምሮ ሟች አቶ ተወልደ ገብሩ እስከ ሞቱበት ጊዜ ድረስ ልላ ጋብቻ ያልመሰረቱ መሆኑን፣አመልካች ውሳኔ ያሰጡትም ጋብቻው በክብር መዝገብ ፊት ወይም በሀይማኖት ወይም በባህል መሰረት የተፈጸመ ስለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጃ ሳይኖር መሆኑን እና ልሎች አመልካቾችም በጋብቻ ውስጥ የተወለዱ አለመሆኑን የሚገልጽ ሆኖ የሚስትነት እና የልጅነት ውሳኔው እንዲሰረዝ የተጠየቀበት ሲሆን ፍርድ ቤቱም በመቃወም አቤቱታው ላይ አመልካቿ መልስ እንዲሰጡበት ካደረገ እና የመቃወም አመልካቾችን ምስክሮች ከሰማ በኃላ
አመልካች ወ/ሮ አሰለፈች ይመር የሟች አቶ ተወልደ ገብሩ ባራኪ ሚስት ናቸው ወይስ አይደሉም?
ከወ/ሮ አሰለፈች ይመር የተወለዱት አመልካቾች የሟች አቶ ተወልደ ገብሩ ባራኪ ልጆች ናቸው ወይስ አይደሉም?
የሚሉ ጭብጦችን መስርቶ አጠቃላይ ክርክሩን በመመርመር የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካቿ ሚስትነታቸው ተረጋግጦ ማስረጃ እንዲሰጣቸው ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ጋብቻቸው የተፈጸመው በየትኛው ስርዓት መሰረት እንደሆነ እንዳልገለጹ፣አመልካች ቀደም ሲል ያሰሟቸው ምስክሮችም አመልካች ከአቶ ተወልደ ገብሩ ጋር ሲኖሩ ነበር ከማለት ውጪ ጋብቻ የነበራቸው ስለመሆኑም ሆነ ጋብቻው በየትኛው ስርዓት መሰረት እንደተፈጸመ የገለጹት ነገር እንደልለ፣የመቃወም አመልካቾቹ ምስክሮች በሁለቱ ተጋቢዎች ወይም በአንደኛቸው ባህል መሰረት የተፈጸመ ጋብቻ አለመኖሩን ወይም ጋብቻ አለመመስረቱን በተመሳሳይ ሁኔታ እንደገለጹ እና የጋብቻ ሁኔታ አለ የሚል ድምዳሜ በመያዝ ውሳኔ የተሰጠውም ባልተነሳ ጉዳይ ወይም ባልተጠየቀ ዳኝነት በመሆኑ ተቀባይነት ላያገኝ እንደማይገባ ገልጾ የሚስትነት ውሳኔውን በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 360(2) መሰረት በመሰረዝ እና ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ ግን አራቱ አመልካቾች በአንድ ወይም በልላ መልኩ ከሟች አቶ ተወልደ ገብሩ ባራኪ ጋር ግንኙነት ያላቸው መሆኑን ከክርክሩ መገንዘብ እንደቻለ እና ሟች አቶ ተወልደ ገብሩ ባራኪ በነበሩበት መረዳጃ ዕድር መሙያ ቅጽ ላይም ልጆች በሚለው ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው እንደተገኙ ገልጾ ብርክቲ ተወልደ፣ሲሳያስ ተወልደ፣ዳንኤል ተወልደ እና ሄለን ተወልደ ከሟች አቶ ተወልደ ገብሩ ባራኪ የተወለዱ ልጆች ናቸው በሚል ተሰጥቶ የነበረውን ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 360(2) መሰረት በማጽናት ውሳኔ ሰጥቶአል።
አመልካች አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት ያቀረቡት የሚስትነት ውሳኔው መሰረዙን በመቃወም ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተው ፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔን በማጽናቱ ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በአጣሪው ችሎት በተያዘው ጭብጥ እና ቀጥሎም በአጣሪው ችሎት ከተያዘው ጭብጥ አገላለጽ ጋር ተያይዞ ተጠሪዎቹ ተጨማሪ ክርክር ለማቅረብ እንዲፈቀድላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ በመቀበል ይህ አምስት ዳኞች የሚሰየሙበት ችሎት በ22/01/2006 ዓ.ም በሰጠው ትዕዘዝ መሰረት ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል። የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ለክርክሩ ወደ ተያዘው የፍሬ ነገር ጭብጥ ከመገባቱ በፊት አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ የተሰጠው በሕጉ የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት ተከትሎ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በቅድሚያ እልባት ማግኘት የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ ጉዳዩን ከዚሁ ነጥብ አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት በፍርድ ቤት የሚደረግ የፍትሐብሕር ክርክር የሚመራው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ስለመሆኑ በዚሁ ሕግ በቁጥር 1 የተመለከተ ሲሆን ተከራካሪ ወገኖች ወደ ክርክር የሚገቡትም በከሳሽነት፣ በተከሳሽነት፣ በጣልቃ ገብነት፣ በተቃዋሚነት፣ በተተኪነት በመቃወሚያ አቅራቢነት፣ በመቃወም ተጠሪነት እና በመሳሰሉ በሕጉ በተመለከቱ ሁኔታዎች ላሆን እንደሚችል አግባብነት ካላቸው የስነ- ስርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።በእነዚህ የሕግ አግባቦች ከሚደረጉት የክርክር ዓይነቶች መካከል አንዱ ተካፋይ ባልሆኑበት ክርክር የተሰጠው ውሳኔ መብቴን ይነካል በማለት አስቀድሞ ለአንድ ወገን የተሰጠውን ውሳኔ ለማሰረዝ የመቃወም አመልካች በሆነው ወገን እና አስቀድሞ በተሰጠው ውሳኔ ተጠቃሚ በሆነው የመቃወም ተጠሪ በሚባለው ወገን መካከል የሚደረግ ክርክር ነው።የዚህ ዓይነቱ ክርክር የሚቀርብበት እና የሚመራበት ስርዓት እንዲሁም የዚህ ዓይነቱን ክርክር የሚሰማው ፍርድ ቤት ስላለው ስልጣን በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ከቁጥር 358 እስከ 360 የተመለከተ ሲሆን በተለይም የመቃወም አቤቱታው መቅረብ የሚገባው በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 222 እና 223 ድንጋጌዎች መሰረት ክስ እና የማስረጃ መግለጫ የሚቀርብበትን ስርዓት መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ በግልጽ ተደንግጎአል።የመቃወም አቤቱታው እና የማስረጃው ቅጂ የመቃወም ተጠሪ ለሆነው ወገን እንዲደርስ መደረግ የሚገባው መሆኑን ከመግለጽ በስተቀር የመቃወም ተጠሪው የጽሁፍ መልስ እና የመከላከያ ማስረጃ ማቅረብ እንደሚገባው በእነዚህ ድንጋጌዎች ላይ በግልጽ የተጻፈ ባይሆንም የመቃወም ተጠሪ የሆነው ወገን በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 234 ድንጋጌ መሰረት ለቀረበበት የመቃወም አቤቱታ ያለውን የመከላከያ መልስ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚገባው ስለመሆኑ ከቁጥር 360(1) እና (2) ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ መገንዘብ ይቻላል።በተለይም የመቃወሚያው ክርክር የሚሰማው የመጀመሪያው ክርክር በተሰማበት ስነ ስርዓት መሰረት ስለመሆኑ በቁጥር 360(2) የተመለከተው አስገዳጅ ድንጋጌ በቀጥታ የቀረበ ክስ እና ክርክር የሚስተናገድበትን ስርዓት በተመለከተ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከቱት መሰረታዊ ድንጋጌዎች የመቃወሚያ ክርክርን በማስተናገድ ረገድም በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጻሚ ላደረጉ የሚገባቸው መሆኑን በግልጽ የሚያስገነዝብ ነው።በዚህ ድንጋጌ የተመለከተው የክርክር አመራር ስርዓት ዓይነተኛ ዓላማ ሁለቱም ተከራካሪ ወገኖች እኩል ዕድል እንዲኖራቸው እና በተለይም የመቃወም አመልካች የሆነው ወገን የክርክሩ ተካፋይ ባልነበረበት ጊዜ የቀረበውን የመቃወም ተጠሪ ወገን የሰው እና የሰነድ ማስረጃ በመስቀልኛ ጥያቄ እና በማስተባበያ ክርክር ጭምር የመፈተን ዕድል እንዲያገኝ ለማስቻል እንደሆነ ይታመናል።በመጀመሪያ ደረጃ የሚደረግ የፍትሐብሕር ክርክር ከሚመራባቸው መሰረታዊ የስነ ስርዓት ሕጉ ድንጋጌዎች መካከል ደግሞ የመጀመሪያ ክስ ሲከፈት ስለሚፈጸም ስነ ስርዓት እንዲሁም ክርክሩን ስለመስማት እና ምስክሮችን ስለመመርመር በአራተኛ መጽሀፍ በምዕራፍ ሁለት እንደቅደም ተከተላቸው ከቁጥር 241 እስከ 256 እና ከቁጥር 257 እስከ 271 የተመለከቱት ድንጋጌዎች ዋነኞቹ ናቸው። በመሆኑም የቀረበ አንድ የመቃወም ክርክር በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት እንዲመራ ለማድረግ ተከራካሪ ወገኖች በተለይ ደግሞ ክርክሩ የቀረበላቸው ፍርድ ቤቶች ኃላፊነት ይኖርባቸዋል።
በተያዘው ጉዳይ የመቃወም አመልካቾች በመቃወሚያችን መሰረት ያስረዱልናል ያሐቸውን ምስክሮች አቅርበው ያሰሙ ሲሆን የመቃወም ተጠሪዋ ግን በቀድሞው ክርክር ጊዜ ካሰሙት በስተቀር የመቃወም አቤቱታው ከቀረበ በኋላ ያሰሙት ምስክር አለመኖሩን ወይም በልላ አነጋገር በቀድሞው ክርክር ጊዜ አሰምተዋቸው የነበሩትን ምስክሮች በድጋሚ አቅርበው የመቃወም አመልካቾች ባሉበት ያላሰሙ መሆኑን ከግራ ቀኙ ክርክር ተገንዝበናል።ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም አመልካች ቀደም ሲል ያሰጡት የሚስትነት ውሳኔ ላነሳ ይገባል ወይስ አይገባም?
በሚለው ነጥብ ላይ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት የመቃወም አመልካቾች ብቻ ሳይሆን የመቃወም ተጠሪዋ ምስክሮች ጭምር ቀርበው እንዲሰሙ ማድረግ ሲገባው የመቃወም ተጠሪዋ ባሉበት የተሰሙትን የመቃወም አመልካቾች ምስክሮች ቃል ቀደም ሲል የመቃወም አመልካቾች በልሉበት ከተሰማው የመቃወም ተጠሪዋ ምስክሮች ቃል ጋር በማነጻጸር የአመልካቿ ሚስትነት በተጠሪዎቹ ማስረጃ ተስተባብሐል በማለት የደረሰበት ድምዳሜ እና ይህንኑ ድምዳሜ መሰረት አድርጎ የሚስትነት ውሳኔውን በመሰረዝ የሰጠው ውሳኔ ቀደም ሲል የተጠቀሱትን የክርክር አመራር ስነ ስርዓታዊ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ሆኖ አልተገኘም።ይግባኙን የተመለከተው የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በስር ፍርድ ቤት የተፈጸመውን ይህንን ስነ ስርዓታዊ ግድፈት ማረም ሲገባው ውሳኔውን ያጸናው በአግባቡ ሆኖ አልተገኘም።በመሆኑም የአመልካች የሚስትነት ውሳኔ ላሰረዝ ይገባል ወይስ አይገባም? በሚለው ጭብጥ ላይ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት የመቃወም ተጠሪዋ ምስክሮች ቀርበው የመቃወም አመልካቾች ባሉበት እንዲሰሙ ላደረግ የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል።
ሲጠቃለል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በስነ ስርዓት ሕጉ የተመለከተውን የክርክር አመራር ስርዓት ተከትሎ ያልተሰጠ እና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ01/02/2003 ዓ.ም ተሰጥቶ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በ14/12/2004 ዓ.ም በውሳኔ የጸናው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ-ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሐል።
በተራ ቁጥር 1 ከተጠቀሰው ውሳኔ ውስጥ ከአመልካቿ የተወለዱት አራት ልጆች ከሟች አቶ ተወልደ ገብሩ ባራኪ የተወለዱ ልጆች ናቸው በማለት የተሰጠው የውሳኔ ክፍል በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በተራ ቁጥር 1 ከተጠቀሰው ውሳኔ ውስጥ የአመልካችን የሚስትነት ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 360(2) መሰረት በመሰረዝ የተሰጠው የውሳኔ ክፍል በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የመቃወም ተጠሪዋ ቀደም ሲል ያሰሟቸውን ምስክሮች፣እነዚህ ምስክሮች ላቀርቡ የማይችሉበት በቂና አሳማኝ ምክንያት ካለም የመቃወም ተጠሪዋ የሚቆጥሯቸውን ተለዋጭ ምስክሮች አስቀርቦ የመቃወም አመልካቾች ባሉበት ከሰማ እና የጽሁፍ ማስረጃም ካለ የመቃወም አመልካቾች አስተያየት እንዲሰጡበት ካደረገ በኋላ አጠቃላይ ክርክሩን መርምሮ አመልካች ቀደም ሲል ያሰጡት የሚስትነት ውሳኔ ላሰረዝ ይገባል ወይስ አይገባም? በሚለው ነጥብ ላይ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዳዩ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት ለፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲመለስ ወስነናል።
በዚሁ መሰረት መፈጸም ያስችለው ዘንድ የውሳኔው ግልባጭ መሰረት ለፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣እንዲያውቀው ደግሞ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።