No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች-፡ ተገኔ ጌታነህ አልማው ወል ረታ ቶለሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካቾች፡- 1.ወ/ሮ አለዊያ ዑመር 2. አቶ አህመድ ሁሴን 3 .ወ/ሮ ኑር ሁሴን 4. ወ/ት አስማ ሁሴን 5. አቶ ሙህሲን ሁሴን 6. ወ/ት አይዳ ሁሴን ተጠሪ፡- አቶ ሐሺም ሁሴን መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ የውርስ ዕዳ ክፍያን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ በፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ተከሳሾች በነበሩት የአሁኖቹ አመልካቾች ላይ ባቀረቡት ክስ ነው።በ17/10/2003 ዓ.ም አዘጋጅተው ያቀረቡት ክስ ይዘትም ባጭሩ፡-የ1ኛ ተከሳሽ ባለቤት የነበሩት እና የቀሪዎቹ ተከሳሾች አባት የሆኑት አቶ ሁሴን አህመድ በ28/09/1992 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ተከሳሾቹ የሚስትነት እና የወራሽነት ማስረጃ መውሰዳቸውን፣ሟች እና ሼህ አህመድ ሁሴን አል አሙዲበኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የብርጭቆ ፋብሪካ በሽርክና ሲያቋቁሙ ከሳሽ ፋብሪካውን እንዲያስተዳድሩ ተስማምተው የነበረ መሆኑን፣ከሳሽም ከሶስት ዓመታት ያለምንም ስራና ክፍያ ሲጉላሉ መቆየታቸውን፣የፕሮጀክቱን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ በሂደት ላይ እያሉ ሼህ አህመድ ሁሴን አል አሙዲ በገዛ ፈቃዳቸው ራሳቸውን ከፕሮጀክቱ ያገለሉ መሆኑን፣ከሳሽ ያለምንም ስራና ክፍያ ለቆዩባቸውሶስት ዓመታት ክፍያና ካሳ የሚውል ብር 400,000 በሼህ አህመድ ሁሴን አል አሙዲ በስህተት ለሟች እንዲከፈል መደረጉን እና ሟችም ክፍያው የተከፈላቸው በስህተት መሆኑን አምነው በ10/05/1985 ዓ.ም በተጻፈ መተማመኛ በእማኞች ፊት አረጋግጠው እያለ ይህንን ክፍያ ሳይፈጽሙ በሞት መለየታቸውን የሚገልጽ ሆኖ ተከሳሾቹ የአውራሻቸው የሆነውን ይህንኑ ዕዳ ከነወለዱ እንዲከፍሉ ይወሰን ዘንድ ዳኝነት የተጠየቀበት ነው።
ተከሳሾቹ በበኩላቸው በ14/11/2003 ዓ.ም ባቀረቡት መልስ ሟች መተማመኛ ሰጡ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ከ18 ዓመት በላይ የሚሆነው በመሆኑ ክሱ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን፣1ኛ ተከሳሽ የሟች ባለቤት፣ቀሪዎቹ ተከሳሾች ደግሞ ወራሾች ስለመሆናቸው የቀረበ ማስረጃ አለመኖሩን፣ሟች በ10/05/1985 ዓ.ም ሰጡ በተባለው መተማመኛ ላይ ያለው ፊርማ የሟች አለመሆኑን፣2ኛ ተከሳሽ ዕዳውን አምነው የተቀበሉበት ነው በተባለው በ09/12/2001 ዓ.ም በተጻፈው ሰነድ ላይ ያለው ፊርማም የ2ኛ ተከሳሽ አለመሆኑን እና ውርሱ ሳይጣራ እና የውርስ ክፍያው ሳይፈጸም ወራሾች በሟች ዕዳ ላጠየቁ የማይገባ መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል።ፍ/ቤቱም ፊርማዎቹ በተካዱት ሁለቱ ሰነዶች ላይ የተመለከቱት ፊርማዎች ተመርምረው ውጤቱ እንዲገለጽ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በሟች ተሰጠ የተባለው መተማመኛ በአረብኛ የእጅ ጽሑፍ የተጻፈ በመሆኑ መመርመር እንዳልተቻለ የተገለጸ ሲሆን በ2ኛ ተከሳሽ የተሰጠ ነው በተባለው መተማመኛ ላይ ያለው ፊርማ ግን በ2ኛ ተከሳሽ የተፈረመ መሆኑ ተረጋግጦ ቀርቧል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን አጠቃላይ ክርክር ከመረመረ በኋላ 1ኛ ተከሳሽ የሟች ባለቤት፣ ቀሪዎቹ ተከሳሾች ደግሞ ወራሾች መሆናቸውን እንዳረጋገጡ፣ሟች መተማመኛ ሰጡ ከተባለበት ከ10/05/1985 ዓ.ም.ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት 17/10/2003 ዓ.ም ድረስ ከ18 ዓመት በላይ ያለፈው ቢሆንም 2ኛ ተከሳሽ በ09/12/2001 ዓ.ም በሰጡት መተማመኛ ሟች በሰጡት ማስረጃ መሰረት ብር 400,000 ፋብሪካው ከተሸጠ በኋላ የሚከፈል መሆኑን በማረጋገጥ መተማመኛ የሰጡ በመሆኑ እና ተከሳሾቹ በሰነዱ ላይ የተመለከተው ፊርማ የ2ኛ ተከሳሽ አለመሆኑን ክደው የነበረ ቢሆንም ፊርማው የ2ኛ ተከሳሽ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ይህ በ2ኛ ተከሳሽ የተሰጠው የዕዳ ማረጋገጫ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1851(ሀ) መሰረት ይርጋውን የሚያቋርጥ እንደሆነ እና ተከሳሾቹ በወረሱት የገንዘብ መጠን የሟችን ዕዳ የመክፈል ግድታ እንዳለባቸው በመግለጽ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ከወለድ እና ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዲከፍሉ ውሳኔ ሰጥቷል።በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ተከሳሾቹ ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የፍ/ከ/ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ተከሳሾቹ በስር ፍ/ቤት ለክሱ በሰጡት መልስ 2ኛ ተከሳሽ ዕዳውን አምነው የተቀበሉበት ነው በተባለው በ09/12/2001 ዓ.ም በተጻፈው ሰነድ ላይ ያለው ፊርማም የ2ኛ ተከሳሽ አለመሆኑን ክደው ከመከራከር ውጪ 2ኛ ተከሳሽ የሰጠው መተማመኛ ልሎች ተከሳሾችን አይመለከትም በሚል ያቀረቡት ክርክር ባለመኖሩ በይግባኝ ክርክር ደረጃ 2ኛ ተከሳሽ የሰጠው መተማመኛ ልሎች ተከሳሾችን አይመለከትም በሚል ያቀረቡት ክርክር በስር ፍ/ቤት ያልተነሳ አዲስ ክርክር በመሆኑ ምክንያት ተቀባይነት የልለው መሆኑን ገልጾ የስር ፍ/ቤት ውሳኔን በማጽናት ውሳኔ ሰጥቷል።
No topics extracted.
አመልካቾቹ ለዚህ ሰበር ችሎት አቤቱታ ያቀረቡት ይዘቱ ከላይ የተመለከተው የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ አመልካቾች ለሟች ዕዳ የአንድነት ባለዕዳዎች ናቸው የሚባል ቢሆን እንኳ 2ኛ አመልካች በ09/12/2001 ዓ.ም. ብቻውን በግሉ ሰጠ የተባለው የባለዕዳነት መተማመኛ የተቀሩትን ባለዕዳዎች ሁኔታ ላያከብድ የሚችል መሆን አለመሆኑን ከፍ/ሕ/ቁ.1906 አንፃር ተጠሪው ባሉበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህም መሰረት ሕግ በልላ አኳኋን ካልወሰነ በቀር ውሉ እንዲፈጸም ወይም ካለመፈጸሙ የተነሳ ስለሚደርስ ጉዳት ወይም ውሉ እንዲፈርስ የመጠየቅ መብት በአስር ዓመት ይርጋ ቀሪ እንደሚሆን እና የይርጋ ቀን መቆጠር የሚጀምረውም ግድታውን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ወይም ውሉ የሚሰጠው መብት ከተሰራበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ በፍ/ሕ/ቁ. 1845 እና 1846 ላይ ተመልክቷል።አመልካቾቹ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት የሚከራከሩትም ሟች መተማመኛ ሰጡ ከተባለበት ከ10/05/1985 ዓ.ም.ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት 17/10/2003 ዓ.ም.ድረስ ከ18 ዓመት በላይ አልፎታል በማለት ሲሆን የፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ይህን የይርጋ መቃወሚያ ላለመቀበል የሰጠው ምክንያት በ2ኛ ተከሳሽ በ09/12/2001 ዓ.ም. የተሰጠው የዕዳ ማረጋገጫ በፍ/ሕ/ቁ. 1851(ሀ) መሰረት ይርጋውን መቆጠር ያቋርጠዋል የሚል ነው።ይሁን እንጂ በሕግ ተለይቶ የተወሰነ የይርጋ ጊዜ የመቋረጥ እና ያለመቋረጥ ጉዳይ አከራካሪ ነጥብ ሆኖ ላነሳ የሚችለው የይርጋውን መቆጠር ያቋርጠዋል የተባለው ምክንያት የተከሰተው የይርጋው ጊዜ ከመሙላቱ በፊት በሆነ ጊዜ እንጂ የይርጋው ጊዜ የሞላ ወይም ያለፈ በሆነ ጊዜ ጭምር አይደለም።በተያዘው ጉዳይ ሟች መተማመኛ ሰጡ ከተባለበት ከ10/05/1985 ዓ.ም.
ጀምሮ 2ኛ አመልካች መተማመኛ ሰጡ እስከተባለበት 09/12/2001 ዓ.ም.ድረስ 16 ዓመት ያለፈ በመሆኑ እና ይህም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 ከተመለከተው የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ የሚበልጥ በመሆኑ 2ኛ አመልካች ሰጡት የተባለው መተማመኛ የይርጋውን መቆጠር የሚያቋርጥ ነው በሚል በስር ፍ/ቤቶች የተያዘውን አቋም ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘንም።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ሟች በሰጡት ማስረጃ መሰረት ብር 400,000 ፋብሪካው ከተሸጠ በኋላ የሚከፈል መሆኑን በማረጋገጥ 2ኛ አመልካች በ09/12/2001 ዓ.ም. መተማመኛ የሰጡ መሆናቸው ተረጋግጧል።በመሰረቱ የይርጋ ተጠቃሚ የሆነ ሰው የሞላውን ይርጋ ለመተው እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1856(1) የተመለከተ በመሆኑ አመልካቾቹ ሟች በ10/05/1985 ዓ.ም.ከሰጡት መተማመኛ አንጻር ሞልቶ የነበረውን ይርጋ በመተው አዲስ የመተማመኛ ሰነድ የሰጡ መሆኑ የተረጋገጠ እስከሆነ ድረስ ይህ በ2ኛ አመልካች በ09/12/2001 ዓ.ም የተሰጠው መተማመኛ ይርጋን የሚያቋርጥ ሳይሆን አዲስ የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምርበትን ጊዜ የሚያመለክት በመሆኑ ተጠሪ ያቀረቡት ክስ በይርጋ የሚታገድ የመሆን አለመሆኑ ጉዳይ ላወሰን የሚገባው የይርጋ ጊዜውን ከ09/12/2001 ዓ.ም. በመቁጠር ነው።ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ሲቆጠር ደግሞ ይርጋው አልፏል ለማለት የሚቻል አይደለም።
አመልካቾቹ አጥብቀው የሚከራከሩበት ልላኛው ነጥብ 2ኛ አመልካች በ09/12/2001 ዓ.ም.መተማመኛ የሰጡት በራሳቸው ሰም እንጂ በልሎች አመልካቾች ስም ጭምር አይደለም የሚል ነው።በመሰረቱ አመልካቾቹ ከስር ጀምሮ የሚከራከሩት በአንድነት ሲሆን በከ/ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ እንደተገለጸው በሰነዱ ላይ የተመለከተው ፊርማ የ2ኛ ተከሳሽ አይደለም ከማለት በስተቀር ይህን የክርክር ነጥብ በስር የመ/ደ/ፍ/ቤት አንስተው አልተከራከሩበትም።በመጀመሪያ ደረጃ ያልተነሳውን ክርክርና ያልቀረበውን አዲስ ነገር በይግባኝ ደረጃ መቀበል የማይቻል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.329(1) ስር የተመለከተ በመሆኑ ይህ የክርክር ነጥብ ተቀባይነት ላያገኝ የሚችልበት አግባብ የለም።ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ 2ኛ አመልካች ከ1992 ዓ.ም. ጀምሮ ስለልሎች አመልካቾች የውክልና ስልጣን ያላቸው ስለመሆኑ እና በ09/12/2001 ዓ.ም መተማመኛውን በፈረሙ ማግስት በግልግል ዳኞች ጉባኤ ዘንድ ቀርበው ስለሁሉም አመልካቾች የዕርቅ ሰነድ የፈረሙ ስለመሆኑ ተጠሪ በመልሳቸው ላቀረቡት ክርክር አመልካቾች ያቀረቡት የማስተባበያ ክርክር አለመኖሩን ከክርክሩ ተገንዝበናል።ይህም 2ኛ አመልካች መተማመኛውን የፈረሙት በራሳቸው ስም ብቻ ሳይሆን በልሎችም አመልካቾች ስም መሆኑን መገንዘብ የሚያስችል በመሆኑ 2ኛ አመልካች መተማመኛውን የፈረሙት በራሳቸው ስም ብቻ ነው በማለት አመልካቾች ያቀረቡትን ክርክር የሕግ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
ሲጠቃለል ከላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች ሁሉ አቤቱታ የቀረበበት የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
348(1) መሰረት ፀንቷል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።