No summary available.
ሚያዝያ 6 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ኢትዮጵያ ንጉሴ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አዲስ ጡብ ማምረቻ ድርጅት - ጠበቃ ምናለ ዓለሙ ቀረቡ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ በአሰሪው የተወሰደበትየስራ ስንብት እርምጃ ሕገወጥነት በፍርድ ተረጋገጦ ወደስራው እንዲመለስ ለተወሰነለት ሰራተኛ ውዝፍ ደመወዝ መከፈል የሚገባው ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 43(5) የተመለከተውን ድንጋጌ አፈጻጸም የሚመለከት ነው።
የጉዳዩን አመጣጥ በተመለከተ ተጠሪው የወሰደውን የስንብት እርምጃ በመቃወም አመልካች ባቀረቡት ክስ ሳቢያ ጉዳዩን የተመለከተው የፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ስንብቱ ሕገወጥ እንደሆነ መረጋገጡን ገልጾ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 43(5) መሰረት የስድስት ወር ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሐቸው ወደ ቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ በመ/ቁ.74375 በ02/08/2005 ዓ.ም ውሳኔ መስጠቱን፣በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪው ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ይ/ሰሚው ከ/ፍ/ቤት አፈጻጸሙን አግዶ ካቆየ በኃላ በመጨረሻ ግንበመ.ቁ.133025 በ02/11/2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት ይግባኙን በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/.ቁ. 337 መሰረት ዘግቶ ማሰናበቱን፣ከዚህ በኋላ አመልካች ጉዳዩ በይ/ሰሚው ፍ/ቤት ለቆየበት ጊዜ ውዝፍ ደመወዝ ታስቦ እንዲከፈላቸው በመጀመሪያው የስረ-ነገር መዝገብ ላይ በ26/02/2006ዓ.ምበተጻፈ ማመልከቻ ለፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ጥያቄ ማቅረባቸውን፣ፍ/ቤቱም ጥያቄው መቅረብ የሚገባው ለይ/ሰሚው ፍ/ቤት እንደሆነ ገልጾ በ29/02/2006 ዓ.ም ትዕዛዝ መስጠቱን፣ቀጥሎም ይ/ሰሚው ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን ባፀናበት ወቅት በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 43(5) መሰረት የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ሳይወስንላቸው ያለፈው በስህተት በመሆኑ ውሳኔው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.208መሰረት እንዲታረምላቸውበ18/03/2006ዓ.ምበተጻፈ ማመልከቻ ለፍ/ከ/ፍ/ቤት ጥያቄ ማቅረባቸውን፣ፍ/ቤቱም አመልካች አቤቱታ ያቀረቡበት ነጥብ ውሳኔ ያላረፈበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.208 መሰረት ላታረም የሚችል ጉዳይ አይደለም በማለት በ26/03/2006 ዓ.ም. ትዕዛዝ መስጠቱን እና አመልካች አቤቱታ ያቀረቡትም ሁለቱ የስር ፍ/ቤቶች በመጨረሻ የሰጧቸው ሁለት ትዕዛዞች መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመባቸው በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮበዚህ ጉዳይ አመልካች ጉዳዩ በይግባኝ ታይቶ ስለፀና በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 43(5) መሰረት ውዝፍ ደመወዝእንዲከፈላቸው የዳኝነት ጥያቄያቸውን በግልጽ አቅርበው እያለ በአቤቱታው ላይ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 ተጠቅሷል በሚል አቤቱታው በሙሉ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት የአመልካቿ መሰረታዊ የክርክር ነጥብ ይ/ሰሚው ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 133025 በ02/11/2005 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ዘግቶ ያሰናበተው አፈጻጸሙን አግዶ ካቆየ በኋላ በመሆኑ በመ/ደ/ፍ/ቤት ከተወሰነልኝ የስድስት ወራት ውዝፍ ደመወዝ በተጨማሪ ይ/ሰሚው ፍ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 43(5) መሰረት ልላ የስድስት ወራት ውዝፍ ደመወዝ ላወስንልኝ ይገባ ነበር የሚል መሆኑን ከክርክሩ ተገንዝበናል።እንደተባለው የፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው በ02/08/2005 ዓ.ም ሲሆን ይ/ሰሚው ከ/ፍ/ቤት ደግሞ አፈጻጸሙን አግዶ ካቆየ በኋላ ይግባኙን ዘግቶ ያሰናበተው በ02/11/2005 ዓ.ም በመሆኑ አፈጻጸሙ ለሶስት ወራት ያህል ታግዶ ቆይቷል።ይ/ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኙን ዘግቶ ያሰናበተው አፈጻጸሙን ለሶስት ወራት አግዶ ካቆየ በኋላ በመሆኑ ይግባኙን በሰረዘበት ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 43(5) በተመለከተው መሰረት ተጨማሪ ውዝፍ ደመወዝ ላወስንልኝ ሲገባው በዝምታ ያለፈብኝ አላግባብ ነው የሚሉ ከሆነ ይ/ሰሚው ፍ/ቤት ተጨማሪ ውዝፍ ደመወዝ ሳይወስን ይግባኙን ዘግቶ በማሰናበት በ02/11/2005 ዓ.ም.
በሰጠው ትዕዛዝ ላይ አመልካች ስርዓቱን ጠብቀው የሰበር አቤቱታቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸው የነበረ ሆኖ እያለ ይህንን አላደረጉም።ይልቁንም የመዝገቡ ግልባጭ የሚያመለክተው ይ/ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኙን ዘግቶ ካሰናበተ ከአራት ወር ከሶስት ሳምንት በኋላ አመልካች የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዲታረምላቸው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 ድንጋጌን በመጥቀስ ውሳኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት አቤቱታ ማቅረባቸውን ነው።በመሰረቱ አንድ ፍ/ቤት በሰጠው ፍርድ ወይም ትዕዛዝ ውስጥ ውሳኔ ላያሳርፍበት ይገባው የነበረውን መብት አላግባብ አልፎብኛል የሚል ተከራካሪ ወገን አላግባብ ታለፈብኝ የሚለውን መብት ማስከበር የሚችለው በሕጉ በተዘረጋው ስርዓት መሰረት ቀጥሎ ላለው የፍ/ቤት እርከን ይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታ በማቅረብ ከሚሆን በስተቀር የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 ድንጋጌን ጠቅሶ ውሳኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት አቤቱታ በማቅረብ አይደለም።የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 ድንጋጌ ለተያዘው ዓይነት ክርክር አግባብነት/ተፈጻሚነት/ የልለው ስለመሆኑም ከድንጋጌው አነጋገር በግልጽ መገንዘብ ይቻላል።
ሲጠቃለል አመልካች አቤቱታ ያቀረቡበት ነጥብ ውሳኔ ያላረፈበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
208 መሰረት ላታረም የሚችል ጉዳይ አይደለም በማለት የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ይ/ሰሚው ፍ/ቤት የስር ፍ/ቤት ውሳኔን ባጸናበት ወቅት በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 43(5) መሰረት የአንድ ዓመት ውዝፍ ደመወዝ ሳይወስንልኝ ያለፈው በስህተት በመሆኑ ውሳኔው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 መሰረት ይታረምልኝ በማለት አመልካች በ18/03/2006 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ ያቀረቡትን ጥያቄ የመረመረው የፍ/ከ/ፍ/ቤት አመልካች አቤቱታ ያቀረቡበት ነጥብ ውሳኔ ያላረፈበት በመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 208 መሰረት ላታረም የሚችል ጉዳይ አይደለም በማለት በመ.ቁ. 133025 በ26/03/2006 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
የውሳኔው ግልባጭ ለስር ፍ/ቤቶች ይላክ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.