No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 07 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- በቂርቆስ ክ/ከተማ የወረዳ 7 አስተዳደር ጽ/ቤት - አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሁን የሰበር ተጠሪዎች ከሳሽነት የተጀመረው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ደግሞ ተከሳሽ ነበር። ከሳሾች ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ/ም አሻሽለው ባቀረቡት ክስ፡- ታህሳስ 01 ቀን 1996 ዓ/ም ከተከሳሽ ጋር ባደረግነው የአጭር ጊዜ የላዝ ውል 128 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ 4 ክፍል የንግድ ቤቶችን በግል ገንዘባችን ሰርተን ስንጠቀምበት የቆየን ቢሆንም ቦታው ለሸራተን ሆቴል ማስፋፊያ ምክንያት እንዲፈርስ ተወስኖ ቤቶቹን ተከሳሽ ያስፈረሰ ቢሆንም ፍራሹን ለከሳሾች መስጠት ሲገባው ከልሎች ከፈረሱት የመንግስት ቤቶች ጋር ተሸጧል በሚል ስለከለከለን ለቤቶቹ መሥሪያ የዋሉትን ቁሳቁሶች ዋጋ እና ቤቶቹን ለሰሩት ባለሙያዎች የተከፈለውን የእጅ ዋጋ በድምሩ ብር 130,000.00 ተከሳሽ እንዲከፍል ይወሰንልን ሲሉ የንብረቶቹን ዝርዝር እና ግምታቸውን በማስፈር ጠይቀዋል።
ተከሳሽም ጥር 30 ቀን 2005 ዓ/ም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ከማቅረቡም ልላ በአማራጭ በፍሬ ጉዳዩ ላይ መልስ ሰጥቷል። የመቃወሚያ ነጥቦቹም፡- በከሳሾች እና ተከሳሽ መካከል በተደረገው የላዝ ውል አንቀጽ 12 በውሉ ትርጉምና አፈጻጸም ዙሪያ አለመግባባቶች ሲከሰቱ በስምምነት ላፈቱ እንደሚገባ፤ካልተቻለም በሽምግልና ጉባዔ የመጨረሻ ውሳኔ ተሰጥቶ እንደሚጠናቀቅ ስለተስማማን ከሳሾች በቀጥታ ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡትን ክስ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ለማከራከር ሥልጣን የለውም፣የላዝ ውሉ ጊዜው የተጠናቀቀ በመሆኑ ቀሪ የሆነውን ውል መሰረት አድርገው ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም የሚሉ ናቸው። እንዲሁም በፍሬ ጉዳዩ ላይ በሰጠው መልስ፡-በላዝ ውሉ አንቀጽ 6(4) መሰረት ከሳሾች ቦታው ለልማት ተፈልጎ እንዲነሱ በሚጠይቁበት ጊዜ ለግል ሥራቸው ለገነቧቸው ግንባታዎች ወጪም ሆነ ካሳ ላጠይቁ እንደማይችሉ የተደነገገ በመሆኑና ቦታውም ለልማት መፈለጉን ባልካዱበት ሁኔታ ያቀረቡት የንብረት ግምት ክስ አግባብነት የለውም ሲል ከመከራከሩም በተጨማሪ ከሳሾች ምትክ ቦታ እንዲሰጣቸው ጠይቀው በኮንቴይነር ኢንተርፕራዝ እንዲደራጁ ከተደረገ በኋላ የተሰጣቸውን የንግድ ማከናወኛ ቦታ ለ3ኛ ወገን አስተላልፈው በመገኘታቸው በመመሪያው መሰረት እንዲነጠቁ ተደርጓል፤ ብር 130,000.00 ለንብረታቸው ግምት እንዲከፈላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ንግድ ቤቱ ሲሰራ የተሰራበት ዕቃ የወጪ ዝርዝር በማስረጃ አስደግፈው ካለማቅረባቸውም ልላ ተከሳሽም ንብረቱን በምን ያህል ዋጋ እንደሸጠ የሚያስረዳ ማስረጃ አላቀረቡም። በመሆኑም ከሳሾች ክሳቸውን በዝርዝር ማስረጃ አስደግፈው ስላላቀረቡ ውድቅ ላደረግባቸው ይገባል ሲል ተከራክሯል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ያቀረባቸውን የመቃወሚያ ነጥቦች ውድቅ በማድረግ በፍሬ ጉዳዩ ላይ በሰጠው ፍርድ፡- በከሳሾች እና ተከሳሽ መካከል ታህሳስ 01 ቀን 1996 ዓ/ም በተደረገው የአጭር ጊዜ የላዝ ውል አንቀጽ 6.4 ውል ሰጪ ቦታውን ለልላ ልማት ፈልጎት ውል ተቀባዩ እንዲለቅ ሲጠየቅ ውል ተቀባዩ ለግል ሥራው ይጠቅመኛል ብሎ ለገነባቸው ቤቶች ወጪም ሆነ ኪሳራ ላጠይቅ እንደማይችል የተገለጸ ቢሆንም በአንቀጹ የሰፈረው ሁኔታ ከሳሾች ቦታውን ሲለቁ ለግንባታ የተጠቀሙባቸውን ንብረቶች የመጠየቅ እና ከተከለከሉም ግምታቸውን ከመጠየቅ የሚያግዳቸው አይደለም፣ተከሳሽም የከሳሾችን ቤቶች ስለማፍረሱ እና የቤቶቹን ፍራሽ አካላት መሸጡን በማመኑ ተከሳሾች በክሳቸው ለጠቀሷቸው ንብረቶች ግምታቸውን የማይከፍልበት ምክንያት አይኖርም ሲል ከሳሾች እንዲከፈላቸው ክስ ካቀረቡት የብር 130,000.00 የንብረት ግምት ውስጥ ብር 31,620.00 በመቀነስ ቀሪውን ብር 73,780.00 ፍርዱ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር እንዲከፍል ወስኗል።
ተከሳሹም በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍርድ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ወገኖች ካከራከራቸው በኋላ በሰጠው ፍርድ፡-የሥር ፍርድ ቤት የተሻሻለ ክስ እንዲቀርብ የሰጠው ትዕዛዝ መልስ ሰጪዎች ግምቱን በተመለከተ ዘርዝረው እንዲያቀርቡ ከሚገልጽ በስተቀር ልላ የተለየ ይዘት የለውም፣ይግባኝ ባይም ቀደም ሲል የቀረበው ክስ ግልጽ ባለመሆኑ ለመከላከል የሚያስችል አይደለም በማለት በዝርዝር እንዲቀርብ አለመጠየቁ በወቅቱ በቂና ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን አምኖ መቀበሉን ስለሚያሳይ በተሻሻለው ክስ መልስ አልሰጠሁም ሲል ያቀረበው ቅሬታ መሰረታዊ ነው ተብሎ ላወሰድ የሚገባ አይደለም፣እንዲሁም ይግባኝ ባዩ በሥር ፍርድ ቤትም ሆነ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ደረጃ ተገቢ ነው የሚላቸውን ክርክሮች በማቅረቡ ክርክሩን ለሥር ፍርድ ቤት መመለስ መልስ ሰጪዎችን ለመጉላላት ከሚዳርግ በስተቀር ጠቀሜታ የለውም ብሐል። በልላ በኩል ይግባኝ ባዩ እንዲከፍል ክስ የቀረበበትን ገንዘብ በተመለከተም ከብር 130.000.00 ውስጥ ብር 73,780 ይግባኝ ባዩ እንዲከፍል መወሰኑ ፍትህን የሚያጓድል አይደለም ሲል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ አጽንቷል።
አመልካችም በሥር ፍርድ ቤቶች ፍርድ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታውን ለዚህ ችሎት ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የጠቀሳቸው የቅሬታ ነጥቦችም፡- ለአመልካች የደረሰው ክስ በ03/02/2005 ዓ/ም የተጻፈ ሲሆን የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በራሱ አነሳሽነት አመልካችን ሳይጠራ ክሱ እንዲሻሻል በማዘዝ በ15/04/2005 ዓ/ም ተሻሽሎ በቀረበው ክስ ላይ መልስ እንድሰጥበት ሳያደርግ እና የመከላከያ መልሴን ሳላቀርብ ተሻሽሎ የቀረበውን ክስ መሰረት አድርጎ ፍርድ መስጠቱም ሆነ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ማጽናቱ ፍርድ ቤቶቹ መሰረታዊ የሆነ የሥነ ሥርዓት ህግ ጥሰት መፈጸማቸውን የሚያሳይ ነው፤ለአመልካች የተሻሻለው ክስ ቢደርስ ኖሮ በቀረበው የንብረት ግምት ዝርዝር እና ማስረጃ ዝርዝር አንጻር አመልካችም ንግድ ቤቶቹ ከመፍረሳቸው በፊት በባለሙያ የተሰራውን ግምት እና ቤቶቹ ሲፈርሱ የነበሩትን እማኞች በማቅረብ ማስተባበል የምችል ሆኖ ሳለ ክርክሩ ወደ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንዲመለስ ማድረጉ ጠቀሜታ የለውም ሲል ከፍተኛው ፍርድ ቤት በፍርዱ ያሰፈረው ያለአግባብ ነው የሚሉ ናቸው።
ተጠሪዎች በበኩላቸው በሰጡት መልስ፡- በመጀመሪያው ክስ በጥቅል ቀርቦ የነበረው የንብረት ግምት ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ/ም ተሻሽሎ በቀረበው ክስ በዝርዝር ከመቅረቡ ውጪ የተሻሻለው ክስ በመጀመሪያ ከቀረበው ክስ የፍሬ ነገር ልዩነት የለውም። የተሻሻለውና በዝርዝር የቀረበው ክስ ለአመልካች ቢደርስ ኖሮ አመልካቹ ምናልባት እንደገና ግምቱን ከመቃወም በስተቀር አስቀድሞ የንግድ ቤቶቹን ማፍረሱን በማመኑ ክዶ መልስ የሚሰጥበት ሁኔታ አይኖርም። በመሆኑም ለአመልካች የተሻሻለው ክስ ቢደርሰውም እንኳን ውሳኔውን የሚያስለውጥ ክርክር ማቅረብ በማይችልበት ሁኔታ የመከላከል መብቴ አልተከበረም ሲል ያቀረበው ክርክር ውድቅ ላደረግበት የሚገባ ነው ሲሉ ተከራክረዋል።
አመልካችም ተጠሪዎች ላቀረቡት መልስ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም፡-የሥር ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ ፍርድ የሰጡት አግባብነት ያላቸውን የፍትሃብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ድንጋጌዎች ጠብቀው ነው?
ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍርዱ መግቢያ ላይ የአሁን ተጠሪዎች ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ/ም የተጻፈ የተሻሻለ ክስ ማቅረባቸውን የገለጸ ሲሆን አመልካችም ጥር 30 ቀን 2005 ዓ/ም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና በአማራጭ በፍሬ ጉዳዩ ላይ መልስ ማቅረቡን መዝግቧል። ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ፍርድ የሰጠውም ይህንኑ የተሻሻለውን ክስ እና አመልካች ጥር 30 ቀን 2005 ዓ/ም ያቀረበውን መልስ መሰረት በማድረግ ነው። ሆኖም በተሻሻለው የተጠሪዎች ክስ ላይ አመልካች መልስ ስለመስጠቱ የፍርድ ቤቱ ፍርድ አያመላክትም። ጥር 30 ቀን 2005 ዓ/ም አመልካች የሰጠው መልስ ለመጀመሪያው ክስ እንጂ ለተሻሻለው ክስ አለመሆኑን በከፍተኛ ፍርድ ቤት ደረጃ ከተደረገው ክርክር እና ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከሰጠው ፍርድ መረዳት ከመቻሉም ልላ በዚህ በሰበር ደረጃም በተደረገው ክርክር ተጠሪዎች አመልካች ለተሻሻለው ክስ መልስ አለመስጠቱን በማመን ተከራክረዋል።
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተሻሻለው ክስ ላይ አመልካች የበኩሉን መልስ እንዲሰጥበት ያላደረገው ምክንያት ግልጽ ባይሆንም የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግን ለተሻሻለው ክስ አመልካች መልስ አለመስጠቱን ካረጋገጠ በኋላ አመልካች በተሻሻለው ክስ መልስ እንዲሰጥበት ማድረጉ የሚያመጣ ለውጥ አይኖረውም ወደሚለው ድምዳሜ የደረሰው ተጠሪዎች አሻሽለው ያቀረቡት ክስ ግምቱን በተመለከተ በዝርዝር ማቅረባቸውን ከሚያሳይ በስተቀር ከመጀመሪያው ክስ የተለየ ይዘት ያለው ካለመሆኑም ልላ አመልካችም ግምቱ ተገቢ እንዳልሆነ በመጀመሪያው ክስ ተከራክሯል በሚል ነው። ይሁን እንጂ መጀመሪያ በቀረበው ክስ ንብረቶቹ የሚያወጡት ዋጋ ግምት እና ተያያዥነት ያላቸው ወጪዎች በዝርዝር አለመቅረባቸው ተረጋግጦ ክሱ ተሻሽሎ የንብረቶቹ ዝርዝር ከነግምታቸው እና የተለያዩ ተያያዥነት ያላቸው ወጪዎች ተለይተው በዝርዝር እንዲቀርቡ እስከተደረገ አመልካችም የተሻሻለው ክስ ደርሶት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.
234(1)(ሰ) በተነገረው መሰረት የማያምናቸውን የንብረቶቹን ግምት እና ተያያዥነት ያላቸው ወጪዎችም ካሉ በግልጽ እና በዝርዝር በመካድ እንዲከራከር፣ እንዲሁም በዚሁ የህግ ቁጥር በፊደል (መ) መሰረት የበኩሉን ማስረጃዎች በማቅረብ እንዲያስተባብል ዕድል መስጠት በድንጋጌው የተመለከተው መብቱ እንዲከበርለት የሚያደርግ ከመሆኑም ልላ ትዕዛዙን የሰጠው ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 91(1) መሰረት ክሱ እንዲሻሻል በራሱ አነሳሽነት ሲያዝ ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት ይረዳል በሚል የያዘውን ዓላማ ከግብ እንዲያደርስ ለማድረግ የሚያስችል ነው።
በመሆኑም በተሻሻለው የተጠሪዎች ክስ ላይ አመልካች መልስ ሳይሰጥበት እና የበኩሉን የማስተባበያ ማስረጃዎችን ሳያቀርብ የሥር ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ ፍርድ የሰጡት ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ደንጋጌዎች ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ፍርዱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህግ የተደነገገውን የክርክር አመራር ሥርዓት መሰረት በማድረግ የተሰጠ አለመሆኑን ስለሚያሳይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ስንል ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 02230 በቀን 19/07/2003 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ፍርድ እና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/135414 በቀን 23/03/2006 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/348(1) መሰረት ሽረናል።
ተጠሪዎች ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ/ም አሻሽለው ያቀረቡት ክስ ለአመልካች ደርሶት አመልካችም የበኩሉን መልስ እንዲሰጥበት ከተደረገ በኋላ የግራ ቀኙን ማስረጃዎች በመስማት በጉዳዩ ላይ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የበኩሉን ፍርድ እንዲሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል። ለቂርቆስ ምድብ ችሎት ትዕዛዝ ይጻፍ።
የዚህን ፍርድ ቤት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻሉ።
No topics extracted.