No summary available.
ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ሱልጣን አባተማም ሙስጠፋ አህመድ ተኽላት ይመስል አመልካች፡- ወ/ሮ ሳኒያ ከድር ጠበቃ ዘካርያስ መሐመድ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኮሪያ ዘማቾች ቤተሰቦች ሽመናና ስጋጃ ስራ ጠበቃቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዳዩ የተጀመረው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁን አመልካች ከሣሽ ሲሆኑ ተጠሪ ተከሣሽ ነበሩ።ይዘቱም በግራ ቀኙ መካከል በነበረው የሁከት ይወገድልኝ ክርክር ክስ ለመስማት በተቀጠረበት ቀን እንደማንኛውም ሰው ፍርድ ቤት ቀርቤተራዬን እየጠበቅኩ ስሜ የተጠራ መስሎኝ በልላ ሰው መዝገብ ችሎት ገብቼ የእኔ ያልሆነው መዝገብ ሲዘጋ የእኔ መስሎኝ በመሄድ የእኔ መዝገብ ሲጠራ ባለመቅረቤ መዝገቡ ተዘግቷል።ይህ የሆነው ባለመስማትና ባለማሰብ በጥፋቴ ስለሆነ የተዘጋው መዝገብ ይንቀሳቀስልኝ በማለት ሲሆን ተጠሪዎችም የአመልካች ጥያቄ ደርሶአቸው በሰጡት መልስ(ሀሳብ)አመልካች በራሳቸው ጥፋት መዝገቡ መዘጋቱን ስለገለፀው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉ እንደዚህ አይነቱን ጥፋት ይቅርታ የሚያደርግበት አግባብ ስለማይኖር መዝገቡን ለማስከፈት በቂ ምክንያት አይሆንም በቸልተኝነታቸው በመሆኑ ላንቀሳቀስ አይገባም ብለዋል።
ፍ/ቤቱም በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን ክርክር ከፍ/ብ/ሥ/ሥህቁ.74(2)አንጻር ለመመርመር ከላይ አመልካች ባለመቅረባቸው ምክንያት ነው ብለው የሰጡትን ሀሳብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጋችን በቂ የሆነ እክል ምክንያት ትርጉም ባይሰጠውም አመልካችን ከችሎት መቅረብ ያገደው ምክንያት በቂ እክል ላሆን የሚችል አይደለም በማለት መዝገቡ ላቀሳቀስ አይገባም በማለት ጥያቄው ሳይቀበለው ቀርቷል።
የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በይግባኝ የቀረበለትን መዝገብ በ22-4-2006 በዋለው ችሎት ይግባኙን ሰርዞታል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው በዚሁ ውሣኔ ላይ ነው።በአቤቱታቸውም ላይ የሥር ውሣኔዎች የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህጉን ቁጥር 74(2)አላማ ያላገናዘበ ትርጉም የተሰጠው ስለሆነና መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ ላታረምልን ይገባል ሲሉ ጠይቋል።
በዚህም የሰበር ችሎት እንዲታይ የተደረገው አመልካች የልላ ሰው ሥም ሲጠራ በስህተት ወደ ችሎት ገብተው መዝገባቸው የተዘጋ መስሐቸው መሄዳቸው በቂ እክል ምክንያት ነው?አይደለም የሚለውን ለመመርመር ነው።
በዚህም መሰረት ይህን ነጥብ ግራ ቀኙ ወገኖች ካቀረቡት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንግዲህ አመልካች በዚህ ጉዳይ የሚሉት በፍ/ቤቱ ቅጥር ጊቢ መጥቼ ተራዬን በመጠባበቅ ላይ እያለሁ በስህተት የልላሰው መዝገብ በተጠራበት ወደ ችሎት ገብቼ መዝገቡ የተዘጋ መስሎኝ መሄድ በጉዳዩ መሣሣቴና ያለማሰቤን ይገልፃልና መዝገቡ ላንቀሳቀስልኝ ይገባል የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው እንደዚህ ያለው ስህተት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ ህጋችን እንደበቂ ምክንያት ላቆጠር የሚገባው ነው አላለም ስለዚህ ላንቀሳቀስላቸው አይገባም የሚል ነው።የሥር ፍ/ቤቶችም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰሙ በኃላ አመልካች በንቃት መከታተል ነበረባቸው ጥፋት መሆኑን እራሳቸውም አምኗልና መዝገቡ ላንቀሳቀስ አይገባም በማለት በብይን ዘግቶታል።
ይህ የሰበር ችሎትም የጉዳዩን አመጣጥ ሲመረምረው አመልካች ቀጠሮአቸውን አውቀው ወደ ፍ/ቤት ጊቢ መጥተው መሄዳቸው ተጠሪ በፅሑፍ ከሰጡት መልስም ሆነ የሥር ፍ/ቤቶች የተቀበሉት እውነታ ነው ይህ ከሆነ ደግሞ የአመልካች በስም ስህተትና ባለማስተዋል ችሎት ገብቶ መዝገባቸው የተዘጋ መስሐዋቸው መሄድ በቸልተኝነት ወይም ሆነ ብለው ጉዳያቸውን ትተው የሄዱ ናቸው ወደ ሚለው ድምዳሜ የሚያደርስ አለመሆኑን ተገንዝበናል።
ተጠሪ እንደሚሉትም አመልካች ጉዳዩን ለመጎተትና ተጠቃሚ ለመሆን ሲሉ እያዬ ሄዱ የሚለው ክርክርም ከግምትነት በዘለለ የተረጋገጠም አይደለም።በመሆኑም ችሎቱ ይህን አባባል አልተቀበለውም።
የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.74(2)ድንጋጌ መሰረታዊ ዓላማም የአመልካችን አይነት ተከራካሪ ወገን ለመገደብ ተብሎ የተቀረፀ ነው ብሎ ለመደምደም የሚቻልበት ህጋዊ ምክንያት አላገኘንም።
በመሆኑም አመልካች ለመዝገቡ መዘጋት እንደምክንያት ያቀረቡዋቸው ምክንያት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.(74(2)ሥር እንደበቂ የእክል ምክንያት ላቆጠር አይችልም ተብሎ በስር ፍ/ቤቶች ተቀባይነት ማጣቱ መሰረታዊ የሆነ የሥነ-ሥርዓታዊ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
No topics extracted.
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ብይንና የፍ/ከ/ፍ/ቤት ትዕዛዝ ተሽረዋል።
አመልካች መዝገቡ እንዲንቀሳቀስላቸው ያቀረቡት ምክንያት በፍ/ስ/ሥ/ሥ/ቁ.74(2) መሰረት በቂ ነው ብለናል።
መዝገቡ እንደገና ተንቀሳቅሶ ጉዳዩ ከቆመበት ይቀጥል ብለን ጉዳዩን ለስር ፍ/ቤት መልሰናል።ይፃፍ።
የግራ ቀኙ ውጪና ኪሣራቸውን ይቻቻሉ።