No summary available.
መጋቢት 8 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወል ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ዮናስ በቀለ-ከጠበቃ አያልው ካሳ ጋር ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ብርሃኑ ኩምሳ- ቀርበዋል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ ከስራ ውል መቋረጥ ጋር የተያያዘ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ተጠሪ እና አመልካች እንደቅደም ተከተላቸው ከሳሽ እና ተከሳሽ በመሆን ያደረጉትን ክርክር የመረመረው የፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የተከሳሽን ክርክር ውድቅ በማድረግ ተከሳሽ የስራ ውሉን ያቋረጡት አላግባብ በመሆኑ ሕገወጥ የስራ ስንብት የሚያስከትላቸውን ክፍያዎች በድምሩ ብር 23,139 ከብር 200 ኪሳራ ጋር ለከሳሽእንዲከፍሉ የሰጠው እና በፍ/ከ/ፍ/ቤት የፀናው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ነው።ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር የተለዋወጡ ሲሆን እኛም በሰበር ክርክሩ ምላሽ ማግኘት የሚገባው ነጥብ የስር ፍ/ቤቶች የስራ ስንብቱ ሕገወጥ ነው ከሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ ውሳኔ የሰጡት ለክርክሩ አወሳሰን ጠቃሚ የሆኑ ፍሬ ነገሮች በግራ ቀኙ ማስረጃ እና በተገቢው ስነ-ስርዓታዊ አግባብ እንዲጣሩ ካደረጉ በኋላ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ጭብጥ መሆኑን በመገንዘብ ጉዳዩን ከዚሁ ጭብጥ አንፃር መርምረናል።
በዚህም መሰረት ተጠሪ በ28/06/2003 ዓ.ም አዘጋጅተው ያቀረቡት ክስ ይዘት ባጭሩ፡-ከሳሽ ከ01/04/1994 ዓ.ም ጀምሮ ከተከሳሽ ጋር የቅጥር ውል ፈጽመው በካሸርነት እና በአስተናጋጅነት ስራ ሲያገለግሉ እንደቆዩ እና ተከሳሽ በ26/06/2003 ዓ.ም የስራ ውላቸውን በሕገወጥ መንገድ እንዳቋረጡባቸው የሚገልጽ ሆኖ ሕገወጥ የስራ ስንብት የሚያስከትላቸውን ክፍያዎች እንዲከፍሐቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት የጠየቁበት ሲሆን ተከሳሽ በበኩላቸው በ29/07/2003 ዓ.ም በሰጡት መልስ ከከሳሹ ጋር የአሰሪና ሰራተኛ አገናኝ የደላላነት ስራ በጋራ ሲሰሩ የነበረ ከመሆኑ ውጪ በቅጥር ውል ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ያልነበራቸው መሆኑን በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱ አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ የሰጠውበግራ ቀኙ መካከል የቅጥር ውል አለ ወይስ የለም?
የሚል ጭብጥ ይዞ ሲሆን ከሳሽ ምስክሮቻቸውን አቅርበው እንዲያሰሙ ካደረገ በኋላ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያመለክታል።አመልካች በስር ፍ/ቤት ምስክሮችን ቆጥረው የነበረ መሆኑን በሰበር አቤቱታቸው ላይ የገለጹ እና ይህም በተጠሪው ያልተስተባበለ ሲሆን አመልካች ምስክሮችን ቆጥረው የነበረ ስለመሆኑም ሆነ ምስክሮቹን ሳይሰማ ስለቀረበት ምክንያት ፍ/ቤቱ በውሳኔው ላይ የገለጸው ነገር የለም።የአመልካች ምስክሮች ሳይሰሙ የቀሩት አመልካች በተያዘላቸው ቀጠሮ ሳያቀርቧቸው ስለቀሩ ስለመሆኑ ተጠሪ በመልሳቸው የገለጹ ቢሆንም ይህ ስለመሆኑ የመዝገቡ ግልባጭ አያረጋግጥም።በመሰረቱ ከግራ ቀኙ የክርክር አቋም አንጻር ፍ/ቤቱ ለክርክሩ አወሳሰን የያዘው ጭብጥ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 246-248 ድንጋጌዎች አንጻር ትክክለኛ ቢሆንም በልላኛው ወገን የተቆጠረው ማስረጃ ለጉዳዩ አግባብነት የለውም በሚል ወይም ሕጋዊ ተቀባይነት ባለው ልላ ምክንያት መሰማት አይገባውም የሚል ግልጽ ትዕዛዝ ሳይሰጥበት የክርክሩ ጭብጥ በአንደኛው ወገን ማስረጃ ላይ ብቻ ተመስርቶ ውሳኔ እንዲያገኝ መደረጉ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.255፣257፣258፣259 እና ልሎችም ድንጋጌዎች አንጻር ተገቢውን የክርክር አመራር ስርዓት የተከተለ ነው ላባል የሚችል አይደለም።
ሲጠቃለል ለክርክሩ አወሳሰን ጠቃሚ የሆኑ ፍሬ ነገሮች በግራ ቀኙ ማስረጃ እና በተገቢው ስነስርዓታዊ አግባብ እንዲጣሩ ሳያደርጉ ስንበቱ ሕገ ወጥ ነው ከሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ በፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የተሰጠው እና በይ/ሰሚው ፍ/ቤት የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የስራ ስንብቱ ሕገ ወጥ መሆኑን በመግለጽ አመልካች ሕገወጥ ስንብት የሚያስከትላቸውን ክፍያዎች በድምሩ ብር 23,139 ከብር 200 ኪሳራ ጋር አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍሉ በፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤትበመ.ቁ.40456 በ05/09/2005 ዓ.ምተሰጥቶ በፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 134431 በ14/02/2006 ዓ.ም በውሳኔ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በአመልካች የተቆጠሩትን ምስክሮች በመስማት እናየቀረበ ወይም የተቆጠረ ካለም የጽሁፍ ማስረጃ ጭምር በመመርመር በአዋጅ ቁጥር 377/1996 በአንቀጽ 3(1) በተመለከተው መሰረት በግራ ቀኙ መካከል በቅጥር ላይ የተመሰረተ የስራ ግንኙነት መኖር አለመኖሩን አጣርቶ እና መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) መሰረት ጉዳዩ ለፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት እንዲመለስ ወስነናል።
በዚሁ መሰረት መፈጸም ያስችለው ዘንድ የውሳኔው ግልባጭ ይላክለት።
የሰበር ክርክሩን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ በመሆኑ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.