No summary available.
የሰ/መ/ ህዳር 17 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል አላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት ነ/ፈጅ አባይነህ ዘውዱ ተጠሪ፡- ደብረ አማን ተክለኃማኖት ቤተክርስቲያን መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍረድ ቤት በመዝገብ ጥቅምት 5 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ጥር 14 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወን ነው። ጉዳዩ የሁከት ይወገድልኝ ክስን የሚመለከት ነው። በስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ቦታው በካርታው ውስጥ የተጠቃለለ አይደለም። በቦታው ላይ ቀደም ሲል የኢትፍሩት ኮንቴነርና ተንቀሳቃሽ ሽንት ቤት ተቀምጦበት እንደነበር ከሳሽ ለክሳቸው ገልፀዋል። ተከሳሽ የመንግስት ቦታ የማስተዳደር ስልጣን በህግ ተሰጥቶታል። ከህብረተሰቡ በቀረበለት አቤቱታ መሰረት ከሳሽ የፓርኪንግ አገልግሎት እንዳትሰጥ መከልከሉ የሁከት ተግባር አይደለም በማለት ተከራክሯል።
የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኃላ ቦታው ከአጥር ውጭ የሚገኝ ቢሆንም ከሳሽ በእጇ አድርጋ ይዛ ስትገብርበት የኖረችው ይዞታዋ ነው። ተከሳሽ የዚህን ቦታ ከሳሽ የፓርኪንግ አገልግሎት እንዳትሰጥ የፃፈው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር ነው። ስለዚህ የፓርኪንግ አገልግሎት እንዳትሰጥ የፃፈው ማስጠንቀቂያ የሁከት ተግባር ነው ስለዚህ የፓርኪንግ አገልግሎት እነዳይሰጥ የሰጠው ትዕዛዝና ክልከላ ተወግዷል። በከሳሽ ይዞታ ላይ የፈጠረው ሁከት ይወገድ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ሚያዝያ 8 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ቦታው የተጠሪ ይዞታ አይደለም በቦታው የነበረው የኢትፍሩት ኮንቴነርና ጊዜያዊ ሽንት ቤት የተነሳው በአስተዳደሩ ፈቃድ ነው። አመልካች ተጠሪ ቦታውን የፓርኪንግ አገልግሎት እንዳትሰጥበት የፃፍኩት ደብዳቤ የሁከት ተግባር አይደለም። ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ ግንቦት 23 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ መልስ መሬቱ ለረዥም ዓመታት በእጃችን አድርገን ስንጠቀምበት የነበረ ህጋዊ ይዞታችን ነው። ስለዚህ በይዞታችን ላይ የተለያዩ ሃይማኖታዊ በዓላት እንድናከብር ለምዕመናን የፓርኪንግ አገልግሎት እንዳንሰጥ አመልካች የወሰነው ውሰኔ የሁከት ተግባር በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥታለች። አመልካች ሰኔ 13 2005 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል። በመልስ መልሱ ውሳኔው ደንብ ቁጥር 14/1996 ድንጋጌዎችን ያገናዘብ አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ተጠሪ በአጥር ካጠረውና በካርታ ቁጥር 01-11.35/77/00 ከሚታወቀው ቦታው ፊት ለፊት የሚገኘው ቦታ ላይ የምትሰጠውን የፓርኪንግ አገልግሎት እንድታቆም አመልካች የፃፈው ደብዳቤ የሁከት ተግባር ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ የህግ መሰረት ያለው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው ተጠሪ የሁከት ይወገድልኝ ክስ ያቀረበችበት ቦታ ከቤተክርስቲያኑ አጥር ክልል ውጭ የሚገኝና የቤተክርስቲያኗን ህጋዊ ይዞታ በሚያረጋግጠው የካርታ ቁጥር ል11-35/77/00 የማይጠቃለል ነው። አከራካሪው ቦታ በቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት የሚገኝ ተጠሪ ከመቶ ዓመታት በላይ ኃይማኖታዊ በዓላትን ለማክበር ምእመናን ፀሎት ለማድረግና መኪኖቻቸውን ለማቆም ሲጠቀሙበት የኖሩ መሆኑን ተጠሪ ከስር ፍርድ ቤትና ለዚህ ሰበር ችሎት ባቀረበችው ክርክር በግልፅ አስፍራለች። ከዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ የከተማ ቦታ የማስተዳደርና የትኛው ቦታ ለምን አይነት አገልግሎት መዋል እንዳለበት የመወሰን ስለጣን ያለው የከተማው አስተዳደር ነው ወይስ የቦታው ተጠቃሚና ባለይዞታ ነን የሚለው ግለሰብ ድርጅት ወይስ ኃማኖታዊ ተቋም? የሚለው ጥያቄ ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክልል ውስጥ የሚገኘውን መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ማስተዳደር ሥልጣን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሆነ በአዋጁ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 11 ንዑስ አንቀፅ 2(ሰ) በግልፅ ተደንግጓል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ከወረዳው ክልል ሥር ያለውን ከተማ መሬት ማስተዳደር የትኛው ቦታ ለፓርኪንግ አገልግሎት የሚውል ስለመሆኑ የትኛው ለፓርኪንግ አገልግሎት እንደሚሆን የከተማዋን መሪ ፕላን የማህበረሰብ ደህንነትና የፀጥታና ልሎች ቦታዎችን በማገናዘብ የመወሰን ሥልጣን ያለው አመልካች ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 11 ንዑስ አንቀፅ 2(ለ) እና አንቀፅ 38 ድንጋጌዎች ይዘት በማየት ለመረዳት ይቻላል።
አመልካች ከላይ በገለጽነው ህግ ድንጋጌ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የወረዳ አስተዳደር ስልጣንና ኃላፊነት ለመወሰን የወጣውን አዋጅ መነሻ በመድረግ ተጠሪ ከይዞታው ፊት ለፊት ባለው ቦታ ላይ የፓርኪንግ አገልግሎት መስጠቷ ለህዝብ ደህንነትና ፀጥታ አስጊ በመሆኑ አገልግሎቱን እንድታቆም የፃፈው ደብዳቤ አመልካች በህግ የተጣለበትን ኃላፊተን እየተወጣ መሆኑን የሚያሳይ እንጅ የሁከት ተግባር አይደለም በመሆኑም አመልካች ተጠሪ በአጥር ከታጠረውና ከህጋዊ ይዞታው ፊት ለፊት ባለው ቦታ ላይ የምትሰጠውን የመኪና ፓርኪንግ አገልግሎት እንድታቋርጥ በቁጥር ል/ክ/ከ/ወ/አስ/624/2004 ታህሳስ 12 ቀን 2004 ዓ.ም የፃፈው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የሁከት ተግባር ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ የአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀፅ 11 ንዑስ አንቀፅ 2(ሰ) አንቀፅ 33 እና የፍታብሕር ህግ ቁጥር 1149 ንዑስ አንቀፅ 3 ድንጋጌዎችን ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች ለተጠሪ የፃፈው ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሁከት ተግባር አይደለም በማለት ወስነናል።
አመልካች በወረዳው ክልል ውስጥ ያለውን መሬትና የተፈጥሮ ሀብት ማስተዳደርና የከተማውን ፕላን መሰረት በማድረግ የትኛው ቦታ ለምን ዓይነት አገልግሎት መዋል እንዳለበት መወሰን ስልጣን በአዋጅ ቁ
No topics extracted.