No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 05 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ መስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ገላና ኦልጅራ ጠበቃ አቶ ግርማ ሚደቅሳ ቀረቡ ተጠሪዎች፡
ጉዳዩ የቀረበው የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በአንደኛ ተጠሪና በሶስተኛው ተጠሪ ላይ ያቀረብኩትን ክስ በመዝገብ በማየት ታህሳስ 13 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በይግባኝ መዝገብ አይቶ ሚያዝያ 25 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት በዚህ መዝገብ ያቀረበውን ሰበር አቤቱታና አመልካች የፊንፊኔ ዙሪያ አሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ የአመልካችን የሁለተኛውን ተጠሪና የሶስተኛውን ተጠሪ ክርክር ሰምቶ ጥር 8 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ ኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዝገብ ሚያዚያ 25 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት በሰበር መዝገብ ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ጉዳዩ የቤት ሽያጭ ውል ለገዥው የሚያስገኘውን መብትና በገዥ በሶስተኛ ወገኖች ላይ ላያቀርባቸው የሚችለውን የመብት ጥያቄ የሚመለከት ነው። ጉዳዩ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲታይ በመዝገብ አመልካች ከሳሽ አንደኛ ተጠሪና ሶስተኛ ተጠሪ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል። እንደዚሁም በመዝገብ አመልካች ከሳሽ ሁለተኛ ተጠሪና ሶስተኛ ተጠሪ ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል የክርክሩ መነሻ አመልካች ከላይ በተገለጹት መዛግብት በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ነው።
ስለሆነም ለእኔ በሸያጭ ውል ያስተላለፈውን ጅምር ቤት እንድትሸጥ እንደትለውጥና ለሶስተኛ ወገን እንድታስተላለፍ አንደኛ ተከሳሽ/አንደኛ ተጠሪ/ ለልላ ሴት የሰጠው ልዩ የውክልና ስልጣን እኔ በቤቱ ላይ ያገኘሁትን መብት የሚጥስ በመሆኑ በፍርድ ፈራሽ ሆኖ እንዲሻርልኝ። አንደኛው ተከሳሽ/አንደኛ ተጠሪ/ በሽያጭ ውል ለእኔ ያስተላለፈውን የቦታውንና የቤቱን ካርታና ፕላን እንደጠፋበት ሀሰተኛ መግለጫ ለሁለተኛው ተከሳሽ በማቅረብ ያገኘው ካርታና ፕላን በማጭበርበር የተገኘ ካርታና ፕላን ስለሆነ እንዲሰረዝልኝ አንደኛ ተከሳሽ /አንደኛ ተጠሪ/ የሽያጭ ውሉን የሚያፈርስ ተግባር የፈፀመ በመሆኑ በሽያጭ ውሉ የተቀመጠውን የመቀጫ ገንዘብ ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺ/ ብር እንዲከፍል ይወሰንልኝ። ሁለተኛው ተከሳሽ/ሁለተኛው ተጠሪ/ የቤቱን ስመ ሀብትና ካርታ በስሜ እንዲያዛውር ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
No topics extracted.
ልዩነቱ አመልካች የካርታ ቁጥሩ L/x/L/D/1223/00 የሆነውን የሁለተኛ ተጠሪ ቤት ህዳር 12 ቀን 2001 ዓ.ም በብር 85,000 /ሰማንያ አምስት ሺ ብር/ የገዛ መሆኑንና ሁለተኛ ተጠሪ ጅምር ቤቱን የቦታውንና የቤቱን ካረታና ፕላን አስረክቦኝ ብር 250,000/ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ብር/ በማውጣት ፎቅ ቤት ገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ እያለ ሁለተኛው ተጠሪ የቦታውና የቤቱ ካረታና ፕላን የጠፋበት መሆኑን ሀሰተኛ መግለጫ ለሶስተኛው ተጠሪ አቅርቦ አዲስ ካርታና ፕላን ከወሰደ በኋላ ጀምር ቤቱን እንድትሸጥ እንድትለውጥና ለሶስተኛ ወገን እንደታስተላልፍ ለወ/ሮ ትዕግስት ወርቁ ልዩ የውክልና ስልጣን የሰጠ መሆኑ ነው። አመልካች ለሁለተኛ ተጠሪ ለትዕግስት ወርቁ የሰጠው ውክልና እንዲሻር በሀሰት መግለጫ የተሰጠው ካርታና ፕላን እንዲሰረዝና ሁለተኛ ተጠሪ 15,000/አስር አምሰት ሺ ብር/መቀጫ ገንዘብ እንዲከፍልና ሶስተኛ ተጠሪ የቤቱን ሰመ ሀብት ካርታና ፕላን በስሙ እንዲያዛውር ፍርድ እንዲሰጥለት ጠይቋል።
በሁለቱም መዛግብት ተጠሪዎች በተከሰሱበት መዝገብ በተከሳሽነት ቀርበው የመጀመሪያ የክስ መቃወሚያዎችን አቅርበዋል። ጉዳዩን የማየት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን የለውም አንድ ሰው ለልላው ሰው የሰጠው ውክልና እንዲሻር ጥያቄ ለፍርድ ቤት ሳይሆን ለሚመለከተው አካል መቅረብ ያለበት ነው የካርታ ይሰረዝልኝ ጥያቄ ተቀብሎ ውሳኔ የመሰጠት የአስተዳደር አካላት እንጅ የፍርድ ቤቶች የዳኝነት ስልጣን የላቸውም የስም ይዛወርልኝ ጥያቄም ውሉን በተናጠል ለከሳሽ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ያፈረስነው ስለሆነ የሕግ መሰረት የለውም የሚል መከራከሪያ አቅርበዋል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካችና ተጠሪዎች ያቀረቡትን ክርክር ከመረመር በኋላ ከሳሽ ካርታና ፕላን እንዲሰረዝለት ያቀረበው ጥያቄ በአስተዳደር አካላት የሚወሰን እንጅ በፍርድ ቤት ታይቶ የሚወሰን አይደለም። ከሳሽ ልዩ የውክልና ስልጣን እንዲሻርለት ያቀረበውን ጥያቄ የመወሰን ስልጣን ያለው ውልን የሚመዘግበው አካል ነው። ፍርድ ቤቱ ስልጣን አለው ቢባል እንኳን በመጨረሻ የጠየቀው ብር 15,000 /አስራ አምስት ሺ ብር/ ስለሆነ ከዞኑ ከፍተኛ ፍርድቤት የስረ ነገር የዳኝነት ስልጣን ስር የሚወድቅ ሳይሆን የወረዳ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን ነው። በመሆኑም ጉዳዩን የማየት የዳኝነት ስልጣን የለኝም በማለት ሁለቱንም መዛግብት በመዝጋት አመልካችንና ተጠሪዎችን አስናብቷቸዋል።
አመልካች የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰጠውን ውሳኔ በመቃወም በይግባኝ መዝገብ የስር ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጠውን ውሳኔ በመቃወም በይግባኝ መዝገብ አቅርቧል። የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሁለቱ ይግባኝ መዛግብት አመልካች ያቀረበውን የይግባኝ ቅሬታና የተጠሪዎችን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካችና ተጠሪዎች የኦሮሚያ ክልልና የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በመሆናቸውና አመልካች የጠየቀው ዳኝነት ብር 15,000 ብቻ እንዲከፈለው ባለመሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን የማየት የዳኝነት ስረ ነገር ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው የውሣኔ ክፍል ስህተት ያለበት ነው ሆኖም በውጤቱ ደረጃ አመልካች ካርታ እንዲሰርዝለት እና ልዩ የውክልና ስልጣን እንዲሻርለት ያቀረበው ጥያቄ በሚመለከታቸው አስተዳደር ክፍሎች የሚወሰን እንጂ በዳኝነት የሚያልቅ ጉዳይ አይደለም ያለው ውሣኔ ክፍል ትክክል በመሆኑ የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ነው በማለት በሁለቱም መዛግብት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የውሣኔ ምክንያት ብቻ በማሻሻል ውሣኔውን አጽንቶታል።
አመልካች የኦሮሚያ ክልል ጠቅላል ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በይግባኝ መዝገብ የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም በሰበር መዝገብ ሀምል 26 ቀን 2004 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል እንዲሁም አመልካች ይግባኝ ሰሚው ችሎት በይግባኝ መዝገብ የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም በሰበር መዝገብ ሀምል 10 ቀን 2004 ዓ.ም የተፃፈ የሰበር አቤቱታ አቀርቧል። አመልካች በሁለቱ መዛግብት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ይዘት እኔ በውል የገዛሁትንና የተራከብኩት ጅምር ቤት ካርታና ፕላን እንደኛ ተጠሪና ሁለተኛ ተጠሪ ለመሸጥ ለመለወጥ እንዲመቻቻው በማሰብ የቤቱና የቦታው ካርታና ፕላን እንደጠፋባቸው ሀሰተኛ መግለጫና ማስረጃ ለሶስተኛ ተጠሪ በማቅረብ የተሰጣቸው አዲስ ካርታና ፕላን የእኔን መብት የሚጎዳና በሀስትና በማጭበርበር የተሰጠ መሆኑ ተረጋግጦ በፍርድ እንዲሰረዝልኝ ያቀረብኩትን የዳኝነት ጥያቄ ፍርድ ቤቶች አከራክረው የመወሰን የዳኝነት ስልጣን አላቸው ስለዚህ ጉዳዩ በፍርድ ላያልቅ የሚችል አይደለም በማለት የስር ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ በውል ለእኔ የሸጠልኝንና እኔ ከፍተኛ ገንዘብ ወጭ በማድረግ የገነባኃቸውን ቤቶች፣ በሀሰተኛ መግለጫና ሐሰተኛ ማስረጃ ተጠቅመው ያወጡትን አዲስ ካርታና ፕላን ጋር ወ/ሮ ትእግስት ወርቁ እንድትሸጥ እንድትለውጥና ለሶስተኛ ወገን ቤቶቹን እንድታስተላልፍ የሰጧት ልዩ የውክልና ስልጣን በንብረቴ የተሰጠና እኔ በቤቶቹ ላይ ያለኝን መብት የሚጎዳ ነው። የውክልና ስልጣኑ የውል ሰነድ ነው። ስለዚህ ውሉ እንዲፈርስ ያቀረብኩት ጥያቄ የግራ ቀኛችንን ማስረጃ በመስማት ውሣኔ የሚሰጡት ፍርድ ቤቶች እንጂ የውልና ማስረጃ የመዝገባ ስልጣን ያለው አካል አይደለም። ስለዚህ ጉዳዩን በዳኝነት አይቶ ለመወሰን ስልጣን እንደልላቸው በመግለጽ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ በሰበር ታይቶ እንዲታረምላቸው በማለት አመልክቷል።
አንደኛ ተጠሪ ሕዳር 7 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ መልስና ሁለተኛው ተጠሪ ሕዳር 18 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ተመሣሣይ ይዘት ያለው ክርክር አቅርበዋል። የውክልና ስልጣን አንድ ወገን ወካይነት የማቋቋምና ላሻር የሚችል በመሆኑ የውክልና ሰነዱን በመመርመር ፍርድ ቤቶች ላሰርዙትና ላሽሩት ይችላሉ በማለት አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ የሕግ መሰረት የለውም።
ተጠሪዎች ከአመልካች ጋር ያደረግነው ጅምር ቤት ሽያጭ ውል በሕጉ የተገለፀውን ፎርም እንደማያሟላ ገልፀን ውሉን ሰርዘነዋል አመልካች የወሰደውን ካርታና ፕላን እንዲመልስልን ስንጠይቀው ጠፍቶብኛል በማለት እንቢተኛ በመሆኑ ለሚመለከተው የፖላስ ክፍል አመልክተንና በበከልቻ ኦሮሚያ ጋዜጣ ጥሪ በማስድረግ የቤት ካርታና ፕላን ሶስተኛው ተጠሪ ተሰጥቶናል ይህም በሀሰት የመጣ ካርታና ፕላን ነው በማለት የሚያቀርበው ክርክር ተገቢነት የልለው ነው ስለዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የልለበት በመሆኑ እንዲያፀናልኝ በማለት ተከራክረዋል።
ሶስተኛ ተጠሪ በበኩሉ በሁለቱ የሰበር መዛግብት አመልካች ላቀረበው የሰበር አቤቱታ ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም እና ሕዳር 17 ቀን 2005 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርቧል። ሶስተኛው ተጠሪ አንደኛውን ተጠሪ ሁለተኛው ተጠሪና የቤትና የቦታ ካርታና ፕላን እንደጠፋባቸው በተናጠል በማመልከታቸው ጉዳዩ በፖላስ በኩል የተሰጠውን ማስረጃ መሰረት በማድረግ በጋዜጣ ተቃዋሚ ካለ እንዲቀርብ ጥሪ አድርጌ ተቃዋሚ የልቀረበ በመሆኑ ለአንደኛና ለሁለተኛ ተጠሪዎች አዲስ የቤት የቦታ ካርታ ፕላን ሰጥቻለሁ። ይህንን የፈፀምኩት በሕጉ የተደነገገውን ሥርዓት በመከተል የሰበር አቤቱታውን ውድቅ ሆኖ በነፃ እንድሰናበት ውሣኔ ይሰጥልኝ የሚል ይዘት ያለው ክርክር አቅርቧል አመልካች ተጠሪዎች ለሰጡት መልስ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር አመልካች ተጠሪዎች በዚህ መዝገብና ከዚህ መዝገብ ጋር በተጣመረው በሰበር መዝገብ ያቀረቡት የጽሑፍ ክርክር ይዘት ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የሥር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረባቸው የዳኝነት ጥያቄዎች በፍርድ የማያልቁ በሚመለከተው የአስተዳደር ክፍል ውሣኔ የሚሰጥባቸው ናቸው በማለት ውድቅ ማድረጋቸውን ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ከላይ የተገለፀውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ ለማቅረብ መነሻ የሆነውን መሰረታዊ ጉዳይና የክርክሩ ጭብጥ በፍተሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉ በተደነገገው መሰረት በመለየትና በመመስረት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመስማት በመመርመርና በመመዘን ውሣኔ ለመስጠት የዳኝነት ኃላፊነታቸውን የተወጡ መሆኑን መመርመር አስፈላጊ ነው። አንድ ጉዳይ አከራካሪ መሰረታዊ ጭብጥ አንደኛው ወገን የጠየቀውና ልላኛው ወገን የካደው መሆኑ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 246 የሚደነግግ ሲሆን የአንድ ክርክር ጭብጥ የሚመሰረተው ከሣሽ በክስ በማመልከቻው የገለፀው እና ክሱን ለማስረዳት ያቀረባቸውን የሰነድ ማሰረጃዎች ተከሣሸ ክሱን ለመከላከል ያቀረበውን የጽሑፍ መልስና ክሱን ለመከላከያ ያቀረበው የጽሑፍ ማስረጃና ተከራካሪዎች ለፍርድ ቤት የቃል ምርመራ የገለፁትን ፍሬ ጉዳይ መሰረት በማድረግ መሆን እንዳለበት የፍተሐ ብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 248 ይደነግጋል።
አመልካች በተጠሪዎች ላይ በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ መሰረታዊ መነሻ ከአንደኛ ተጠሪ ጋር ሕዳር 12 ቀን 2001 ዓ.ም ያደረገው የካርታ ቁጥሩ L/X/L/D/131/00 የሆነውን ጅምር ቤት በብር 85,000 /ሰማንያ አምስት ሺ ብር/ ለመግዛት የተዋዋለው ውልና ከሁለተኛ ተጠሪ ጋር ሕዳር 19 ቀን 2001 ዓ.ም የካርታ ቁጥር L/X/L/D/1223/00 የሆነ ጅምር ቤት ለመግዛት የተዋዋለው ውል ነው አመልካች በውል የገባውን ግድታ በመፈፀምና የገባቸውን የቤት ዋጋ በመክፈል የቤቶቹን ካርታዎች እና ጅምር ቤቶቹን ከአንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች ተረክቦ የጅምር ቤቶቹን ፕላን በማስቀየር ከፍተኛ ወጭ በማውጣት ፎቅ ቤቶችን በመገንባት በማጠናቀቅ ሒደት ላይ እያለ ተጠሪዎች በውል የገቡትን ግድታ በመጣስና በውል ያገኘውን መብት ዋጋ ለማሣጣት የተለያዩ ተግባራትን ፈጽመዋል የሚል ነው። አመልካች ተጠሪዎች በሽያጭ ውልና በፍተሐብሕር ሕግ ቁጥር 2879/1/ መሰረት ለእኔ ያስተላለፉትን ካርታ በሐሰት ጠፋቶብናል የሚል ማመልከቻና ማስረጃ ለሶስተኛው ተጠሪ በማቅረበ አዲስ ካርታ መውሰዳቸው በዚህ አዲስ ካርታ መሰረት እኔ የገዛሁትን እና ወጭ አውጥቼ የገነባኋውን ቤት ትእግስት ወርቁ እንድትሸጥ እንድትለወጥ ወይም ለሶስተኛ ወገን እንድታስተላልፍ ልዩ የውክልና ስልጣን የመስጠት ተግባር ፈጽመዋል እነዚህ ተግባራት በፍርድ ተመርምረው ይሰረዙልኝ የሚል ይዘት ያለው ክስና ክርክር አቅርቧል።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ከአመልካች ጋር ውል ከተዋዋሉና የቤቱን ዋጋ ከተቀበሉ በኃላ ውሉ ጐድቶናል በሚል ሃሣብ የተቀበሉትን ገንዘብ የመለሱ መሆኑንና ውሉም የፈረሰ መሆኑን ገለፀው እንደተከራከሩ አመልካች የወሰደውን ካርታና ፕላን ጠፋቶብኛል ስላላቸው አዲስ ካርታ ፕላን የወጣ መሆኑ ቤቱ ንብረታቸው መሆኑን ገልፀው እንደተከራከሩ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በውሣኔው ካሰፈራቸው መሰረተ ሃሣቦች ተረድተናል።
ከላይ የገለጽናቸው አመልካችና አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪ ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክርክር መሰረታዊ ጭብጦች /ሀ/ አንደኛ ተጠሪ የካርታ ቁጥሩ L/X/L/D/131/00 የሆነውን ቤት ለአመልካች ለመሸጥ ሕዳር 12 ቀን 2001 ዓ.ም ያደረገውን የጅምር የቤት ሽያጭ ውል ፈርሶ ተጠሪ የተቀበለውን የቤቱን ዋጋ ለአመልካች መልሷል ወይስ አልመለሰም፣ /ለ/ ሁለተኛ ተጠሪ የካርታ ቁጥር L/X/L/D/1223/00 የሆነ ጅምር ቤት ለአመልካች ለመሸጥ ሕዳር 12 ቀን 2001 ያደረገው ውል ፈርሶ ሁለተኛ ተጠሪ የተቀበለውን የቤቱን ዋጋ ለአመልካቾች መልሷል ወይስ አልመለስም?
/ሐ/ አመልካች ከአንደኛ ተጠሪና በሁለተኛ ተጠሪ ጋር በተናጠል ያደረገው የጅምር ቤት ግዥ ውል በሕጉ አግባብ አልፈረሰም ቢባል አንደኛና ሁለተኛ ተጠሪዎች የሽያጭ ውሉን ሲዋዋሉ በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 2879/1/ መሰረት ለአመልካች አሣልፈው የሱጡት የቤትና የይዞታ ካርታና ፕላን እንደጠፋባቸው ሀሰተኛ መግለጫ በማቅረብ አዲስ ካርታና ፕላን ከሶስተኛው ተጠሪ መወሰዳቸው ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም?
/መ/ ሶስተኛው ተጠሪ ለተጠሪዎች አዲስ የቤትና የቦታ ካርታና ፕላን ሲሰጥ የቀድሞው ካርታና ፕላን ተጠሪዎች ጠፍቶብናል በማለት ባቀረቡት ማመልከቻና ማስረጃ መሰረት መሰረዙ በሶስተኛ ወገን /አመልካች/ ላይ ላያስከትል የሚችለውን ጉዳት ለማስወገድ ተጠሪዎች በፍታብሕር ሕግ ቁጥር 1197 ንዑስ አንቀጽ 2 መሰረት በቂ ዋስትና እንዲሰጡ አድርጓል ወይስ አላደረገም?
/ሰ/ አመልካች ከአንደኛ ተጠሪና ከሁለተኛ ተጠሪ ጋር በተናጠል ያደረገው የቤት ሽያጭ ውል በሕጉ አግባብ አይፈረስም ከተባሉ ተጠሪዎች በውል ለአመልካች የሸጡትን ቤት ወ/ሮ ትእግስት ወርቁ እንድትሸጥ እንድትለውጥ በማናቸውም ወገን ለሶስተኛ ወገን እንድታስተላለፍ ልዩ የውክልና ሰልጣን መስጠት ይችላሉ ወይስ አይችሉም? አይችሉም የሚባል ከሆነ ውጤቱ ምንድ ነው?
/ረ/ አመልካች ከተጠሪዎች ጋር ባደረገው የቤት ሽያጭ ውል መሰረት ብር 150,000 / አንድ መቶ ሃምሣ ሺ ብር/ ከአንደኛ ተጠሪ በገዛው ጅምር ቤት 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሣ ሺ ብር/ ከሁለተኛው ተጠሪ በገዛው ጅምር ቤት ላይ ወጭ አውጥቶና የቤቱን ፕላን ወደ ፎቅ አስለውጦ የግንባታ ሥራ ሰርቷል? ወይስ አልሰራም? ሰርቷል የሚባል ቢሆን ውጤቱ ምን ይሆናል?
/ሰ/ ሶስተኛ ተጠሪ ለአንደኛ ተጠሪና ለሁለተኛ ተጠሪ የሰጠውን አዲሰ ካርታና ፕላን በመሰረዝ የቤቱቹን ስመሃብት ወደ አመልካች እንዲዛወር ማድረግ ይገባዋል ወይስ አይገባውም? የሚሉት ጭብጦች ላይ በግራ ቀኙ የቀረቡ ማስረጃዎችን በመስማት በመመርመርና በመመዘን ተገቢውን ማጣራት በማድረግ በፍርድ መወሰን የሚጠይቅ ነው። እነዚህን ከላይ የገለጽናቸውን ተያያዥነት ያላቸው ጭብጦች በፍርድ የሚያልቁ እንጂ የአስተዳደር ክፍሎች ግራ ቀኙን በማከራከርና ማስረጃ በመስማት በአስተዳደራዊ ውሣኔ የሚጨርሷቸው ጉዳዮች አይደሉም። በመሆኑም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በተጣመሩት የሰበር መዝገቦች የቀረበውን ጉዳይ በዳኝነት እንደማያልቁ በመግለጽ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ እና በመዝገብ የሰጣቸው ውሣኔዎች ተሽሯል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ መዝገብ እና በይግባኝ መዝገብ የሰጣቸው ውሣኔዎች ተሽረዋል።
የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት መዝገበ እና የመዝገብ በማንቀሣቀስ ከላይ በተራ ቁጥር 12 የተገለፁትን ጭብጦች በመመስረትና ማስረጃ በመስጠት ልሎች ተያያዥነት ያላቸወን ጉዳዩች በማጣራት በጉዳዩ ውሣኔ እንዲሰጥበት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ግ/ቁ 341/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሣቸው ይቻሉ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ