No summary available.
ታህሳስ 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ የቀረበ የለም ተጠሪ፡ -አቶ ሞላ እርቄ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ ለፍርድ አፈጻጸም የተያዘ ንብረት በሁለተኛ ጊዜ በሀራጅ ላሸጥ የሚችልበትን ዋጋ መጠን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በኢላባቦር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባስከፈተው የአፈፃጸም መዝገብ ነው።አመልካች ለተጠሪ ብድር ሰጥቶ በብድር ውሉ መሰረት ባለመከፈሉ ክስ መስርቶባቸው ተጠሪ የተበደሩትን ገንዘብና እና ወለድ ከወጪ እና ኪሳራ ጋር ለአመልካች እንዲከፍሉ ተብሎ ተወስኖ አፈፃጸሙ በዚህ ውሳኔ መሰረት ቀጥሎ የተጠሪ የተለያዩ ንብረቶች ተሸጠው ለእዳው ገቢ የሆኑ ቢሆንም ብር 209,000.00(ሁለት መቶ ዘጠኝ ሺህ ብር) በመቅረቱ ይህንኑ የገንዘብ መጠን ለማስፈጸም ንብረትነቱ የተጠሪ መሆኑ በተረጋገጠና በኢላባቦር ዞን ጮራ ወረዳ ክልል ውስጥ የሚገኝ ባህርዛፍ አመልካች ለፍርዱ ማስፈፀሚያነት እንዲሸጥለት አመልክቶ ባህርዛፍ በብር 125,500.00(አንድ መቶ ሃያ አምስት ሺህ ብር) ተገምቶ ቀርቧል።ከዚህም በኋላለ 1ኛ ጨረታ በቀረበው ግምት መሰረት በሐራጅ እንዲሸጥ አፈፃጸሙን የያዘው ፍርድ ቤት በማዘዝ በ1ኛ ጫረታ ሳይሸጥ ቀርቷል። ከዚህ በመቀጠል ንብረቱ በሁለተኛ ጫረታ እንዲሸጥ ትዕዛዝ ሰጥቶ ጫረታው ሳይከናወን ቀርቶ ይህንኑ መነሻ በማድረግ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሲሰጥ ባህርዛፉ በ2ኛ ጨረታ ባለሙያ ባቀረበው ግምት በላይ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች እንዲሸጥ በማለት ጠቅሷል።በዚህ ትዕዛዝ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ጸንቷል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የተጠሪ ንብረት በሁለተኛ ጫረታ ሲሸጥ ከባለሙያ ግምት በላይ በተገኘ ከፍተኛ ዋጋ እንዲሸጥ ተብሎ መታዛዙ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 428 ድንጋጌን ያላገናዘበ እና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ጫረታ የሚካሄድበትን አግባብ በተመለከተ ከፍተኛ ዋጋ ለአቀረበ የሚል ሁኖ እያለ ይኼው ትዕዛዝ በበላይ ፍርድ ቤት ባልተሻሻለበት በራሱ ችሎቱ መለወጡ ያላግባብ ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም በዚህ ችሎት እንዲታይ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበውም ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምረናል።እንደመረመረው እንዲሸጥ የታዘዘው የተጠሪ ንብረት በሁለተኛ ጫረታ የሚሸጥ ከሆነ ከግምት በላይ ከፍተኛ ዋጋ ነው መሸጥ ያለበት ተብሎ መወሰኑ ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ለላባቸው እዳ ንብረታቸው የሆነው ባህርዛፍ እንዲሸጥ ትእዛዝ ተሰጥቶ በ1ኛው ጫረታ ገዥ ባለመገኘቱ በሁለተኛ ጫረታ እንዲሸጥ የታዘዘ መሆኑን፣በዚህ ጊዜ ንብረቱ ሲሸጥ ግን በ2ኛ ጫረታ ባለሙያ ባቀረበው ግምት በላይ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ንብረቱ እንዲሸጥ ተብሎ በበታች ፍርድ ቤቶች መወሰኑን ነው።
በመሰረቱ የመጀመሪያ የጨረታ ማስታወቂያ ወጥቶ ገዥ አለመቅረቡ ከተረጋገጠ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 428(1) እንደተመለከተው ድጋሚ ጨረታ እንዲወጣ ማድረግ የግድ አስፈላጊ ነው።በመጀመሪያው ጫረታ ማስታወቂያ በተገለፀው የዋጋ ግምት መነሻ ተጫራች ካልቀረበ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 428(1) መሰረት ድጋሚ ማስታወቂያ በማውጣት በሁለተኛ ጨረታ እንደሚደረግ፣ንብረቱም የሚሸጠው በሁለተኛ ጨረታ ማስታወቂያ ጥሪ መሰረት ውድድር በማድረግ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች እንደሆነ ተጠቃሹ ድንጋጌ ያሳያል።በድንጋጌው "-------- ከፍተኛ ዋጋ ለሚያቀርብ ተጫራች-----------" የሚለው ሐረግም የሚያስገነዝበው በመጀመሪያ ጫረታ ጊዜ በግምቱ መነሻ ተጫራች ያልቀረበ በመሆኑ የፍርድ ባለመብቱም በፍርድ ያገኘው ውሳኔ እንዲፈፀምለት፣ባለእዳውም ያለበትን ግድታ እንዲወጣ ማድረግ ይቻል ዘንድ በሁለተኛ ጨረታ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ባለሙያ በገመተው ዋጋ መነሻ ሳይገደብና ከዚያም ባነሰ የዋጋ መነሻ ጫረታ ላደረግ እንደሚችልና ንብረቱም ላሸጥ የሚችለው ከተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራቾች መሆኑን ነው። እንዲህም ሲሆን ይህ በውድድሩ ጊዜ የተገኘው ከፍተኛ የተባለው ዋጋም በመጀመሪያ ጫረታ ጊዜ ከተመለከተው የዋጋ መነሻ ዝቅ ላል እንደሚችል መታወቅ አለበት እንጂ ፍርድ ቤት በሁለተኛ ጫረታ ጊዜም ዋጋው ከባለሙያው ግምት ላያንስ አይገባም በማለት የሚገድበው አይደለም።በሁለተኛ ጨረታ ባለሙያ ባቀረበው ግምት በላይ በተገኘ ከፍተና ዋጋ ላቀረበ ተጫራች እንዲሸጥ የግድ ማድረግ የንብረቱ ዋጋ የባለሙያውን ግምት ካልደረሰ ንብረቱ የሚሸጥበት ሁኔታ እንዳይኖር በማድረግ ባለገንዘቡ ገንዘቡን እንዳያገኝ፣ባለእዳውም ግድታውን እንዳይወጣ የማድረግ ውጤትን የሚያስከተል በመሆኑ የፍርድ አፈፃጸም ስርዓት የሚቀበለው አካሄድ ነው ተብሎ አይታሰብም።ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች የተጠሪ ንብረት በሁለተኛ ጨረታ ሲሸጥ ባለሙያ ባቀረበው ግምት በላይ በተገኘ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች እንዲሸጥ በማለት የሰጡት የአፈጻጸም ትዕዛዝ ለጉዳዩ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያለው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 428(1) ድንጋጌ ያላስቀመጠው መስፈርት መሰረት ያደረገ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስሰአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
በኢላባቡር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 25 ቀን 2004 ዓ/ም ተሰጥቶ በኦሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ ጥር 14 ቀን 2005 ዓ/ም የፀናው የአፈጻጸም ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በሁለተኛ ጨረታ ጊዜ ለፍርድ አፈጻጸም የተያዘ ንብረት ላሸጥ የሚገባው ባለሙያ ባቀረበው ግምት በላይ በተገኘ ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች ሳይሆን ግምቱን ሳይጠብቅ ከተወዳዳሪዎች መካከል ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች ነው ብለናል።በዚህ መሰረት አፈጻጸሙን እንዲቀጥል ጉዳዩን ለኢላባቦር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።ይጻፍ።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።