No summary available.
መጋቢት 09 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳን ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ ጠበቃ አትናፍን]ጋሣ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አስቴር ንጉሴ ወኪል የአሮ ኤፍሬም ንጉሴ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የመድን ዋስትና ሽፋን ውል የሚሻሻልበትን ሥርዓት የሚመለከት ነው። የሰበር አቤቱታው ላቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 17 ቀን 2004 ዓ.ም በፃፈው አቤቱታ የአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 10522 የካቲት 09 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት ለተጠሪ አመልካች በድምሩ ብር 73,523.00 ከዳኝነት፣ ከሕጋዊ ወለድ እና ከ10 የጠበቃ አበል እንዲሁም በቁጥር ከብር 500.00 ወጪ ጋር እንዲከፍል የሰጠውና በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 07 ቀን 2004 ዓ.ም የጸናው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ግድፈት የተፈጸመበት ነው በማለት እንዲሻርለት ስለጠየቀ ነው።
ጉዳዩ የተጀመረው በአዳማ ልዩ ዞን ከፍተኛ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካች በስር ተከሳሽነት፣ የአሁኑ ተጠሪ ደግሞ በከሳሽነት ነው።
የተጠሪ ክስ ይዘቱም አመልካች የሰልዳ ቁጥር 2-78918 አ.አ በሚል ለምትታወቀውና ንብረትነቷ የአሁኑ ተጠሪ ለሆነችው የኪራይ መኪና የኢንሹራንስ ሽፋን ሰጥቶ የነበረ መሆኑን፣ ይህ መኪና በተጠሪ ተወካይ አቶ ስንታየሁ ተካልኝ ለተባለ የመንጃ ፈቃድ ላለው ሰው ተከራይቶ የተከራየው ሰው በማሽከርከር ላይ እያለ የፊት ጎማው ፈንድቶ በመገልበጥ በመኪናው ላይ የአካልና የመካኒካል ጉዳት የደረሰበት መሆኑን፣ ከአመልካች ላይ ባላቸው የመድን ውል በዚህ መኪና ላይ አደጋ እንደደረሰ የሚጠግኑ ጋራጆችን አወዳድረው የዋጋ ማቅረቢያ ከሰሰበሰቡ በኋላ አመልካች ኢንሹራንስ ከገባው ሰው ወይም እሱ ከቀጠረው ሹፍር ወጪ በልላ ሶስተኛ ወገን ሲሽከረከር አደጋ የደረሰበት ሰለሆነ የደረሰውን ጉዳት ለመተካት ኃላፊነት የለብኝም በማለት ጥገናውን ወይንም ለጥገናው የሚያስፈልገውን ወጪ አልቀበልም ማለቱን፣ ከዚህ በኋላ ተጠሪ ይህን መኪና አካል ጨረታውን ባሸነፈው ጋራጅ አሰርቶ ለውስጥ እቃ ጉዳት የሚያስፈልገውን የመለዋወጫ እቃም አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋራጅ ላይ ማግኘቱን ገልፆ አመልካች ከጉዳቱ ኃላፊነት አለበት ተብሎ መኪናውን ለማስነሳት፣ ለትራንስፖርት የወጣውን የማስጠገኛ ዋጋ በድምሩ ብር 76,523.00 ለተጠሪ እንዲከፍል ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም ለደረሰው አደጋ በሕጉ አግባብ ከተጠሪ ጋር የገባው የመድን ዋስትና ውል እንደልለ፣ ከተጠሪ ጋር ባደረጉት ተጨማሪ ውል ላይ ቀደም ብለው ያደረጉትን የኢንሹራንስ ሽፋን መኪናው ላይ አደጋ የደረሰው ኢንሹራንስ ገቢው ወይም እሱ ከቀጠረው ሹፍር ውጪ በሶስተኛ ወገን ሲሽከረከር ከደረሰ ኢንሹራንስ ሰጪን የማይመለከተው መሆኑን በመግለጽ ስምምነት መደረጉን ገልፆ ኃላፊነት የለብኝም በማለት በኃላፊነት ረገድ የተከራከረ ሲሆን በኃላፊነት መጠኑ ላይም የአደጋ መነሻ ብር 3000.00 ሳይቀነስ መቅረቡ ተገቢ ያለመሆኑን፣ መኪናውን ለመጫን ብር 5000.00 ከፍያለሁ የሚሉትም ሐሰት መሆኑን፣ በመኪው ላይ የደረሰ የመካኒካል አደጋ ለመኖሩ በባለሞያ የቀረበ ማስረጃ የልለ መሆኑን፣ በተደረገው ጨረታ አነስተኛ ዋጋ ያቀረበ ስራውን መውሰድ ሲገባው ከፍተኛውን ያቀረበ መውሰዱ ያላግባብ መሆኑን፣ ለመካኒካል ጉዳት ያስፈልጋል ተብሎ ከተጫራቾች ቀረበ የተባለው ፕሪፎርማ እርስ በራሱ የሚጋጭ መሆኑን ገልጾ ገንዘቡንም ልከፈል አይገባም በማለት የተከራከረ ሲሆን ገንዘቡን ክፍል የሚባል ከሆነም ተጠሪ የመለዋወጫ እቃዎችን ላመልስ ይገባል ሲል ተከራክሯል። ተጠሪ በበኩሉ ተጨማሪ ውሉን የማያውቁት መሆኑን ጠቅሰው ተከራክረዋል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ጉዳዩን መርምሮ አመልካች ተጠሪ በሕጉ አግባብ ያደረጉት የተጨማሪ የመድን ሽፋን ውል መኖሩ መረጋገጡን፣ በዚህ ውል ደግሞ የመድን ሽፋን የተሰጠው መድን ገቢው ወይም እሱ በቀጠረው ሹፍር እየተሽከረከረ ባለበት ጊዜ እንጂ በልላ ሶስተኛ ወገን ሲሽከረከር አደጋ ከደረሰ አመልካች ኃላፊነት የልለበት መሆኑን መገለጹን በምክንያትነት ይዞ የተጠሪን ክስ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎልታል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ አመልካቹ ውሉ ስለመሻሻሉና ይህን ውል ስለማሻሻሉ ለተጠሪ ያሳወቀ መሆኑን አላስረዳም በሚል ምክንያት ተጨማሪ የመድን ውል የለም ሲል በቀድመው የመድን ውል መሰረት አደጋው እንደሚሸፍን ጠቀሶ ለጉዳዩ አመልካችን ኃላፊ ያደረገ ሲሆን የካሳውን መጠን በተመለከተ ደግሞ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን አከራክሮ እንዲወስን ጉዳዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት መልሶለት የስር ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ አመልካች ለተጠሪ ብር 73,523.00 ከዳኝነት፣ከሕጋዊ ወለድ እና ከ10 የጠበቃ አበል እንዲሁም በቁጥር ከብር 500.00 ወጪ ጋር እንዲከፍል በማለት ወስኗል። በዚህ የካሳ መጠን ላይ ይግባኝ የቀረበለት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ውሳኔውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 377 መሰረት አፅንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ውሳኔ ላይ ነው። አሁን በተያዘው መዝገብ ላይ አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በአመልካችና በተጠሪ መካከል ተጨማሪ የመድን ሽፋን ውል ስለመኖሩ የተጠሪ ወኪል መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም የጻፋት ማመልከቻ ቀርቦ እያለ ይኼው ሳይታይ ታልፎ ተጨማሪ ውል የለም ተብሎ ለአደጋው ሽፋን እንዳለው ተደርጎ ካሳውን ለተጠሪ እንዲከፈል መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችሎቱ ላታይ ይገባዋል ተብሎ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ጠበቃቸው በሰጡት መልስ አመልካች ኃላፊነቱን አሰመልክቶ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ማቅረቢያ የጊዜ ገደብ ያልጠበቀ መሆኑን፣ አመልካች ለጉዳቱ ኃላፊ የተባለውም ተጨማሪ ውሉን ተጠሪ ያልፈረሙበትና የሚያውቁት ሰለመሆኑ ባለማስረዳቱ መሆኑን፣ መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም የተጠሪ ወኪል ጻፋ የተባለበት ማመልከቻም በክልሉ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ታይቶ የሚታመን አይደለም፣ ተጨማሪ ውል ሰለመኖሩ የሚያሳይ አይደለም ተብሎ ውድቅ የተደረገ እና በዚህ ችሎት ላመዝን የሚችልበት አግባብ የልለ መሆኑን ዘርዝረው በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ላጸና ይገባል በማለት ተከራክረዋል። የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው ከሰ/መ/ አንፃር ሲታይ የሰበር ማቅረቢያ ጊዜው ያላለፈ መሆኑን በመጥቀስና ልሎች የሰበር አቤቱታ ነጥቦችን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብቅ አንጻር በሚመለከተው መልኩ መርምሮታል። በዚህም መሰረት ተጨማሪ የመድን ሽፋን ስምምነት አልተደረገም ተብሎ አመልካች ለጉዳቱ ኃላፊ መባሉ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ለተጠሪ ጥያቄ ኃላፊነት የለብኝም በማለት የሚከራከረው አደጋው መድን የገባው ወይም እርሱ ከቀጠረው ሾፍር ውጪ በለ ሶስተኛ ወገን ሲሽከረከር ከደረሰ ሽፋን የልለው መሆኑ ሰኔ 24 ቀን 2002 ዓ.ም የተጨማሪ ውል ስምምነት አድርገናል፣ ይኼው ውል ስለመኖሩ ደግሞ የተጠሪ ወኪል መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም የፃፋት ማመልከቻ ያሳያል በማልት ነው። ተጠሪ በበኩላቸው ተጨማሪ ውል የለም፣ አላውቀውም፣ በቀደመው መሰረት አደጋ ሽፋን አለው በሚል ነው። በቅድሚያ ተጠሪ ኃላፊነቱን አስመልክቶ የቀረበውን የሰበር አቤቱታ ጊዜውን ጠብቆ የቀረበ አይደለም በማለት ያቀረቡትን ተቃውሞ ተመለክተናል።
አመልካች የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ኃላፊነቱን አስመልክቶ በሰጠው ውሳኔ የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታውን ለፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርቦ በመ/ ተከፍሎ ለባለሶስቱ የሰበር አጣሪ ችሎት ቀርቦ እስከ ሚያዝያ 03 ቀን 2004 ዓ.ም ተገቢው ትዕዛዝ ሳየሰጥበት ከቆየ በኋላ የኃላፊነቱን መጠን ተመልክቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት የታዘዘው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጉዳዩ ላይ የካቲት 09 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት ውሳኔ ሰጥቶ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ይህንኑ ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት መጋቢት 07 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት በማፅናቱ አመልካች በዚሁ ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታውን መጋቢት 17 ቀን 2004 ዓ.ም ለፍደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርቦ ጉዳዩ አሁን በተያዘው መዝገብ ተከፍቶ የሰበር ሰሚ አጣሪ ችሎቱ ጉዳዩን መርምሮ መጋቢት 24 ቀን 2004 ዓ.ም ላመረመር የሚገባ የሕግ ነጥብ መኖሩን አምኖ ጉዳዩን ለዚህ ችሎት እንዲቀርብ ያደረገ ሲሆን ሚያዝያ 02 ቀን 2004 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ አመልካች በሰ/መ/ ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ ባሁኑ መዝገብ አጠቃልሎ ማቅረቡንና ጉዳዩም ያስቀርባል የተባለ መሆኑን በመዘርዘር በሰ/መ/ የቀረበው መዝገብ እንዲዘጋለት አመልክቶ የሰበር አጣሪ ችሎትም ይህንኑ የአመልካችን አቤቱታ መነሻ በማድረግ ዋናውን ጉዳይ ሳይመለከት የዳኝነት ገንዘቡ በደንቡ መሰረት ተቀንሶ እንዲመለስለት በማዘዝ መዝገቡን ዘግቶአል። በመሆኑም አመልካች በኃላፊነት ውሳኔው ላይ በወቅቱ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡ ሲሆን የካሳ መጠን ክርክሩ ደግሞ በሰበር አጣሪው ችሎት የቀረበው የኃላፊነት ቅሬታ መቋጫ ሳያገኝ አስቀድሞ እልባት አግኝቶ የካሳው መጠን ውሳኔ ቅሬታ ለአጣሪ ችሎቱ ቀርቦ በኃላፊነት ጉዳይ ላይም ቅሬታ ተጠቃልሎ ቀርቦ ታይቶ ተገቢው ትዕዘዝ የተሰጠ መሆኑን ስለተገነዘብንና በአንድ ጉዳይም ሁለት መዝገቦች መከፈት የልለባቸው በመሆኑ ተጠሪ በዚህ ረገድ ያቀረቡት መቃወሚያ ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 22(4) እና ከክርክር አመራር ስርዓት አንጻር ተገቢነት ያለው ሁኖ ስላለገኘን አልተቀበልነውም። ዋናውን ጉዳይ በተመለከተ ከላይ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለው ተመልክተናል።
በመሰረቱ የንግድ ሕግ አንቀጽ 657 ስለኢንሹራንስ ውሉ ፎርማላቲ የሚደነግገውም ሀሳብ የያዘ ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት የኢንሹራንስ ውል የኢንሹራንስ ውል ፖላሲ በሚባል ጽሁፍ እንደሚገለጽና የመድህን ገቢውን ጥያቄ መሰረት በማድረግ በፖላሲው ላይ መድህን ሰጭው ከፈረመ ህጋዊ የሆነ የኢንሹራንስ ውል ግንኙነት በመድህን ሰጭው እና በመድህን ገቢው መካከል እንደሚመሰረት ተቀምጧል። ይህ ሁኔታ ደግሞ የንግድ ሕጉ ልዩ የሆነ የኢንሹራንስ ውል እንደመሆኑ መጠን ከጠቅላላው ሕግ የበላይ ተፈፃሚነት እንዲኖረው የሚደረግ መሆኑን ተቀባይነት ያላቸው የሕግ አተረጓጎም ደንቦች የሚያሳዩን ጉዳይ ነው። በመሆኑም የኢንሹራንስ ውል አደራረግ አፈጻጸሙ በጠቅላላ የውል ሕግ የሚመራ ግንኙነት አይደለም፣ ይህ ሰበር ችሎትም የኢንሹራንስ ውል አደራረግ አፈጻጸሙ በጠቅላላ የውል ሕግ የሚመራ ግንኙነት አይደለም፣ ይህ ሰበር ችሎትም የኢንሹራንስ ውል አለ ለማለት መድን ሰጪው በሚያዘጋጀው ፖላሲ ላይ መፈረም እንዳለበት በን/ሕ/ቁጥር 657 ላይ ከመመልከቱ በስተቀር መድን ገቢው መፈረም እንደሚገባው ያልተመለከተ በመሆኑና በውል ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ መድን ገቢው ከፈረመና በፖላሲው ላይ ደግሞ መድን ሰጪው ከፈረመ በሁለቱ መካከል የመድን ውሉ ስለመደረጉ በቂ መሆኑን በ
ሚያዝያ 09 ቀን 2000 ዓ.ም በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤትን የሚያስገድድ ውሳኔ ሰጥቶበታል። እንዲሁም የኢንሹራንስ ፖላሲ ተጨማሪ በሆነ ጽሑፍ ካልሆነ በቀር ላለወጥ እንደማይቻል የን/ህ/ቁጥር 657(2) አስገዳጅነት ባለው መልኩ ደንግጓል። የዚሁ አንቀጽ ንዑስ ቁጥር ሲታይም ፖላሲው ወይም የፖላሲው ተጨማሪ ጽሁፍ ከመፈረሙ በፊት ለጊዜው ኢንሹራንስ ሰጪው ኢንሹራንስ ለሚገባው ሰው ፖላሲው ወይም ለፖላሲው ተጨማሪ ጽሑፍ እስከ ተፈረመ ድረስ ማረጋገጫ መድን የሚሆነው ጽሑፍ የሰጠው እንደሆነ ኢንሹራንስ ሰጪውና ኢንሹራንስ ገቢው አንዱ ለአንዱ ግድታ እንደገቡ ይቆጠራል በሚል ይደነግጋል። የዚህ ድንጋጌ አይነተኛ ዓላማም ውሉ ስለመኖሩ የሚረጋገጠው በጽሑፍ በሆነ ሰነድ መሆኑን ማሳየት ነው ተብሎ ይታመናል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም አመልካች ከመድን ገቢው ወይም እራሱ ከቀጠረው ሾፍር ውጪ መኪናው ሲሽከረከር አደጋ ከደረሰ የመድን ሽፋን የልለ መሆኑን የሚያሳይ ተጨማሪ ውል አለ በማለት የተከራከረው ሰነዱን በማቅረብና ይህንኑ ሰነድ ተጠሪ ባይፈርሙበትም ሰነዱ ያለ ነው፣ ሰነዱ የለ መሆኑንም በተጠሪ ወኪል መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም ያቀረቡት ማመልከቻ ያሳያል በማልት ነው። ይሁን እንጂ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያለው የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጨማሪ ውሉ ተጠሪ የሚየውቁት ስለመሆኑ አመልካች አላስረዳም፣ መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም ተጻፈ የተባለ ማመልከቻም የሚታመን አይደለም በማለት የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረገው መሆኑን ውሳኔው ያሳያል። ይህም የሚያሳየው ተጠሪ በተጨማሪ ውል ላይ መፈረም አለመፈረማቸው የሚያስከትለው የሕግ ውጤት ምንድነው የሚለውን ከመታየቱ በፊት ሰነዱ በተጠሪ የማይታወቅ፣ ማመልከቻውም የማይታመን ነው ወደሚለው ድምዳሜ ፍሬ ነገርን የማጣራት፣ ማስረጃን የመመዘን ሥልጣን ያላቸው የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዳይ በዚህ ችሎት የሚታይበት አግባብ የልለ መሆኑን ከኢ.ፍ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3) ሀ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ጉዳይ በመሆኑ ተጠሪ ደረሰ የተባለውን አደጋ የሚሸፈነው የቀደመው ውል በተጨማሪ ውል ስለመለወጡ ፈቃዳቸውን የሰጡ ወይም ተጨማሪ ውሉን ያወቁት የነበረ መሆኑን ፍሬ ነገሩን በመመርመርና ማስረጃን በመመዘን የሚይዘው ድምዳሜ የለም። በመሆኑም በተጠሪ ወኪል መስከረም 29 ቀን 2003 ዓ.ም ተፃፈ የተባለው ማመልከቻ በማስረጃነት ቀርቦ ሰነዱ የማይታመን መሆኑና ተጠሪ ተጨማሪ ውሉን እንደሚያውቁት ላያስረዳ እንደማይችል በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች የቀደመውን ውል ከአስር ወር ቆይታ በኋላ አሻሽዬዋለሁ በማለት የሚያቀርበው ክርክር የሕግ ጥያቄ በመሆን ከላይ ከተጠቀሱት የንግድ ህጉ ድንጋጌዎችና ከን/ሕ/ቁጥር 659 ድንጋጌ አኳያ ላታይ የሚገባው ሁኖ አላገኘንም። በካሳ መጠኑ ላይ የቀረቡት ክርክሮችም የፍሬ ነገርና የማስረጃ ክርክሮች በመሆናቸው በዚህ ችሎት የሚታዩበትን አግባብ አላገኘንም። ሲጠቃለልም የአመልካች የሰበር አቤቱታ የመሰረታዊ ሕግ መመዘኛን የሚያሟላ ባለመሆኑ ተቀባይነት የልለው ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
በአዳማ ልዩን ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 10522 የካቲት 09 ቀን 2004 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ፣ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት በኮ/መ/ ነሐሴ 26 ቀን 2003 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ፣ እንዲሁም በዚሁ ችሎት በመ/ መጋቢት 07 ቀን 2004 ዓ.ም የተሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348(1) መሰረት ጸንቷል።
ለተጠሪ አመልካች በድምሩ ብር 73,523.00 /ሰባ ሶስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ሶስት ብር/ ከዳኝነት፣ ከሕጋዊ ወለድ እና ከ10 የጠበቃ አበል እንዲሁም በቁጥር ከብር 500.00 ወጪ ጋር እንዲከፍል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ ብለናል።
No topics extracted.