No summary available.
ታህሳስ 17 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካቾች፡- 1.አቶ ተዋበ እስጢፋኖስ 2. ወ/ሮ አበራሽ አስራት ተጠሪ፡- የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ ዐ/ህግ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ ለሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሁን የሰበር ተጠሪ ከሳሽነት የተጀመረው በምዕራብ አርሲ ዞን ቆሬ ወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁን አመልካቾች እንደቅደምተከተላቸው 1ኛ እኛ 2ኛ ተከሳሾች ነበሩ። ክሱም፡ተከሳሾች በኢ/ፍ/ዲ/ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(3) እና 481(1) (ሀ) የተመለከተውን በመተላለፍ በክሱ የተዘረዘሩትን ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችንና ጥይቶችን በቤታቸው አከማችተው በፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ ቤታቸው በፖላስ ሲፈተሸ የጦር መሳያዎቹና ጥይቶቹ ስለተገኙ ተከሰዋል የሚል ነው።
1ኛ ተከሳሽም በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል በክሱ ከተጠቀሱት ጦር መሳሪያዎች መካከል በተወሰኑት ላይ ፍቃድ ያለኝ ሲሆን ከቤቴ የተገኘ ቦንብ ባለመኖሩ የፈጸምኩት ወንጀል የለም፣ጥፋተኛም አይደለሁም ሲሉ ክደው የተከራከሩ ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ የእምነት ክህደት ቃል ስለመስጠታቸው የወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ የሚያመላክት አይደለም።
የወረዳው ፍርድ ቤትም 1ኛ ተከሳሽ ፈቃድ አለኝ ያሉአቸውን የጦር መሳሪያዎች በተመለከተ ፍቃድ የተሰጠበትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ በማዘዙ የሁለት ቺኮዝ ፣የክላሽንኮፕ ፣የኡዝ እና ካርቤን መሳሪያዎች ፍቃድ የተሰጠባቸውን ማስረጃዎች ማቅረባቸውን በፍርድ በማስፈር ኤፍ1-1 የሆነ ቦንብና በክሱ ተዘርዝረው ፍቃድ የልላቸውን የጦር መሳሪያዎች በተመለከተም የከሳሽ ምስክሮችን ቃል ከሰማ በኋላ በሰጠው ውሳኔ የተሰጠው የብርብራ ትዕዛዝ የ1ኛ ተከሳሽ እና ሼህ አህመድ ሐጂ አህመድ የተባሉት ግለሰብ ቤቶች እንዲበረበሩ ሲሆን የሚበረበሩ የጦር መሳሪያዎች ዓይነት በዝርዝር በፍርድ ቤት ብርበራ ትዕዛዝ ካለመገለጹም ልላ ብርበራው የተካሄደው 1ኛ ተከሳሽ በልሉበት ቤታቸው ተሰብሮ በመሆኑ ብርበራው የተካሕደው ህጋዊ አካሄዱን ጠብቆ አለመሆኑን የሚያሳይ ነው። ይሁን እንጂ ተከሳሾች ይህን ያህል የጦር መሳሪያ በቤት ውስጥ ማስቀመጣቸው ተገቢ ባለመሆኑ ላማሩበትና የአካባቢውም ልሎች ሰዎች ትምህርት ይሆናቸው ዘንድ እንዲሁም ብርበራው የህጉን ሥርዓት ተከትሎ ያልተደረገ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ክስ የቀረበባቸውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ) በመቀየር በወንጀል ህግ አንቀጽ 809 ጥፋተኞች ናቸው ሲል እንዳንዳቸው በብር 50 (አምሳ) እንዲቀጡ ወስኗል።
ከሳሽም በወረዳው ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሸኘት ይግባኙን ለምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማቅረባቸው ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ወገን ካከራከራቸው በኋላ በሰጠው ውሳኔ፡- በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ፖላስ የመልስ ሰጪዎችን ቤት ሲፈተሸ የጦር መሳሪያዎቹ መገኘታቸው የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፣የስር ፍርድ ቤትም ይግባኝ ባይ ምስክሮችን ከሰማ በኋላ የመልስ ሰጪዎችን ማስረጃዎች መስማት ሲገባው መልስ ሰጪዎቹ ያቀረቡትን መቃወሚያ መነሻ በማድረግ የጦር መሳሪያዎቹን ፍቃድ እንዲያቀርቡ በማድረግ በቀረበው ማስረጃ ላይ ይግባኝ ባይ አስተያየት ሳይሰጥበት ከመዘገቡ ጋር ማያያዙ ተገቢነት የለውም፣እንዲሁም መልስ ሰጪዎቹ እንዲከላከሉ ብይን ሳይሰጥ ያለአግባብ ክስ የቀረበባቸውን የወንጀል ህግ ድንጋጌ በመቀየር ቀላል ቅጣት የወሰነው መልስ ሰጪዎችንና መሰሎቻቸውን የማያስተምር እንዲሁም የህዝቡን መረጋጋት የማያረጋግጥ ጉድለት ያለበት ውሳኔ ነው። በመሆኑ የይግባኝ ባይ ምስክሮች የመልስ ሰጪዎች ቤት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሲፈተሸ ቦንብ እና ኡዝ መትርየስ የተባሉት በግል የማይያዙና ፈቃድ የማይሰጥባቸው የጦር መሳሪያዎች የተገኙ ስለመሆናቸው በማረጋገጣቸው ክስ በቀረበባቸው የወንጀል ህግ ድንጋጌ ስር ጥፋተኞች ላሆኑ ይገባል ሲል በዚሁ ድንጋጌ እያንዳንዳቸው በሁለት ዓመት እስራትና በብር 3000 እንዲቀጡ ወስኗል።
ተከሰሾችም በከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ የይግባኝ ቅሬታቸውን በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/195(1) መሰረት የሰረዘባቸው ሲሆን የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎትም የግራ ቀኙን ወገኖች ካከራከራቸው በኋላ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔና በክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ትዕዛዝ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ሲል የሰበር አቤቱታቸውን ውድቅ በማድረጉ ለዚህ ችሎት አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
አመልካቾች በአቤቱታቸውም የጠቀሱት ቅሬታ ነጥብ ሲጠቃለል፡- የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትና ሰበር ሰሚ ችሎት ያስተላለፉብን የጥፋተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ላሻር የሚገባ ነው የሚል ሲሆን ተጠሪው በበኩሉ በሰጠው መልስ፡- አመልካቾች የጦር መሳሪያዎቹን በቤታቸው አከማችተው የተገኙት ለንግድ አላማ ስለሆነ ክስ በቀረበባቸው ወንጀል ህግ አንቀጽ ጥፋተኞች ናቸው በሚል የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው የሚነቀፍበት ምክንያት ባለመኖሩ የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት እና ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ሲል የሰበር አቤቱታቸው ውድቅ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
አመልካቾችም ተጠሪው ላቀረበው መልስ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክሯል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም፡- አመልካቾች የፈጸሙት ወንጀል በወንጀል ህግ 481(1)(ሀ) የሚሸፈን ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
የአመልካቾች ቤት በፍርድ ቤት በተሰጠ የብርበራ ትዕዛዝ በፖላስ ሲፈተሽ ቦንብ እና ኡዝ መትርየስ የተባሉት በግለሰብ ደረጃ የማይያዙና ፈቃድ የማይሰጥባቸው የጦር መሳሪያዎች የተገኙ ስለመሆናቸው የተጠሪ ምስክሮች ለሥር ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ካስረዱት የተረጋገጠ ፍሬ ነገር በመሆኑ ይህን የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ይህ ችሎትም የሚቀበለው ነው። ይህንኑ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ይዘን ክስ ወደቀረበበት የወንጀል ህግ አንጽ 481(1)(ሀ) ስንመለስ፡- ማንም ሰው መንግስት አደጋ ላይ ስለመጣል በተወሰኑት ድንጋጌዎች ከተመለከተው ውጪ ፈቃድ ሳይኖረው ወይም ህግን ተቃራኒ በሆነ መንገድ ማናቸውንም አይነት የጦር መሳሪያዎች፣ፈንጂዎች፣ወይም ጥይቶች በመነገድ ዓለማ የሰራ፣ከውጭ አገር ያስመጣ ፣ወደ ወጭ አገር የላከ፣ያጓጓዘ፣የገዛ፣የተቀበለ፣ያስቀመጠ፣ያከማቸ፣የደበቀ ፣ለሽያጭ ያቀረበ ወይም እንዲዘዋወሩ ያደረገ ወይም ያከፋፈለ እንደሆነ በዚሁ ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ሆኖ እንደሚቀጣ ተመልክቷል። አመልካቾችም በብርበራ ከቤታቸው የተያዙትን የጦር መሳሪያዎች ውስጥ ፈቃድ የላቸውም የተባሉትን የጦር መሳሪያዎች በቤታቸው ውስጥ ያከማቹት ለንግድ በሚል እንደሆነ የተጠሪ ማስረጃዎች ስለማስረዳታቸው የሥር ወረዳ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሚያመላክት ሆኖ አልተገኘም። በአዋጁ አንቀጽ 481(1)(ሀ) በተነገረው መሰረት አንድን ሰው በዚህ ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ነው ለማሰኘት ግለሰቡ መሳሪያዎቹን ያከማቸው ወይም በድንጋጌው ከተዘረዘሩት ድርጊቶች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑትን ድርጊቶች የፈጸመው በመሳሪያዎቹ ለመነገድ በሚል እንደሆነ ከሳሽ ላያስረዳ ይገባል።
ምክንያቱም የወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ) በጠቅላላው ለአንቀጽ 481 ከተሰጠው ርዕስ ወይም ስያሜ ጋር በማያያዝ ላተረጎም የሚገባ በመሆኑ ነው። በመሆኑም አመልካቾቹ የፈጸሙት ወንጀል በወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ) ስር የሚሸፈን ሆኖ አላገኘንም። ይልቁንም ይህ ችሎት እንደሚገነዘበው አመልካቾች ፈቃድ የልላቸውን የጦር መሳሪያዎችንና ጥይቶችን በቤታቸው አከማችተው የመገኘታቸው ሁኔታ የኢ/ፍ/ዲ/ሪ/ የወንጀል ህግ አንቀጽ 808(ሀ) የጦር መሳሪያዎችን ና ጥይቶችን ስለመቆጣጠር የተደነገገውን የሚጥስ ሆኖ ስለሚገኝ በዚሁ በተጠቀሰው ድንጋጌ ስር የጥፋኝነትና ቅጣት ውሳኔ ላተላለፍባቸው የሚገባ ነው። ይህ ሆኖ ሳለ የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት አመልካቾችን በወንጀል ህግ አንቀጽ 481(1)(ሀ) ጥፋኞች ናቸው ሲሉ በዚሁ ድንጋጌ የቅጣት ውሳኔ ያስተላለፉባቸው በዚሁ ድንጋጌ ስር ጥፋተኞች ላሆኑ የሚያስችሉት ህጋዊ ፍሬ ነገሮች ስለመኖራቸው ተጠሪው ባላስረዳበት ሁኔታ ስለሆነ ውሳኔው በከፊል መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ በማግኘታችን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/12859 በቀን 04/12/2004 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ፣ የኦሮሚያ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/119417 በቀን 10/05/2005ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ትዕዛዝ እና የኦሮሚያ ጠ/ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ/146183 በቀን 13/12/2005 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠውን ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 195(2) (ለ)(2) መሰረት አሻሽለናል።
አመልካቾች እንዳንዳቸው በ2 ዓመት እስራትና በ3000 ብር እንዲቀጡ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት የሰጡትን የውሳኔ ክፍል ሽረናል።
አመልካቾች ጥፋተኞች ናቸው ላባል የሚገባው በወንጀል ህግ አንቀጽ 32(3) እና አንቀጽ 481(1)(ሀ) ስር ሳይሆን በወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና 808(ሀ) ስር ነው በማለት በመወሰን በዚሁ ድንጋጌ እጃቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ3 (ሦስት )ወር እስራት ላቀጡ ይገባል ብለናል።ሆኖም አመልካቾቹ በዚሁ ወንጀል የታሰሩበት ጊዜ ከ3 ወር በላይ መሆኑን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ከሰጠበት ቀን አንጻር ስለተረዳን በልላ ወንጀል የማይፈለጉ ከሆነ ዛሬውኑ ከሚገኙበት ማረሚያ ቤት እንዲለቀቁ አዘናል ። ለሚገኙበት ማረሚያ ቤት ይጻፍ ብለናል።
ፈቃድ የልላቸውን የጦር መሳሪያዎችና ጥይቶች መንግስት እንዲወርሳቸው የሥር ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው የውሳኔ ክፍልና ይህንኑ የውሳኔ ክፍል የክልሉ ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትና ሰበር ሰሚ ችሎት በማጽናት የሰጡት የውሣኔ ክፍል አልተካም ብለናል።
No topics extracted.