No summary available.
ጥቅምት 20ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ አመልካች፡- ዘኒት አባቡ የቀረበ የለም ተጠሪ:- የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብ/ክ/መ/ዐ/ህግ በልለበት ታየ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጧል፤
ጉዳዩ ወንጀል ሲሆን የተጀመረውም በቤ/ጉ/ክ/መንግስት አሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በስር ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽ ተጠሪ ከሳሽ ነበር። የቀረበው ክስም አመልካቿ የወ/ህ/ቁ27/1/ 540 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በባሞበሲ ወረዳ ባሞበስ ከተማ 02 ቀበል ጥቅምት 14 ቀን 2004 ዓ.ም ከምሽቱ በግምት 1፡00 ሰዓት አካባቢ የግል ተበዳይ ጠይባ መሐመድ መኖሪያ ቤት አካባቢ የግል ተበዳይ በሆድዋ ላይ በመምታት ሆድዋ ውስጥ የነበረው ፅንስ ቦታውን እንዲለቅና የመውለጃ ቀን ያልደረሰ ፅንስ በሆድዋ ውስጥ እንዲሞት በማድረግ የምጥ አመጣጥና ከ4 እስከ 5 ከወላድ በኃላም የደም መርጋትና የደም መፍሰስ እንዲፈጠር በማድረግ በፈፀመችው የመግደል ሙከራ ወንጀል ተከሳለች የሚል ሲሆን አመልችም ፍርድ ቤት ቀርባ የዕምነት ክደት ቃሐን ስትጠየቅ የወንጀሉን ያልፈፀመች መሆኑን ክዳ ቃልዋን ሰጥታለች ቀጥሎም ፍ/ቤቱ በግራ ቀኙ በኩል የተቆጠሩትን ምስክሮች አስቀርቦ ከሰማ እና ጉዳዩንም ከመረመረ በኃላ ድርጊቱ ተፈፅሟል በተባለበት ጊዜ ማለትም ከጥቅምት 9 አስከ 16 ቀን 2004 ዓ.ም ድረስ አመልካች ዕቃዋን ለመውሰድ ሱዳን ሀገር ልዩ ቦታው ኩርሙክ ተብሎ የሚጠራ ቦታ ሄዳ እዚያ የነበረች እና በቦታው አለመኖሯ በመከላከያ ማስረጃ ከመረጋገጡም በላይ በልላ በኩልም አመልካች እንደተባለው በእርግጥም በወቅቱ በቦታው ብትኖርና ጉዳቱን የፈፀመች ቢሆን ኖሮ ጉዳዩ ወዲያውኑ ለፖላስ ሪፖርት በተደረገ እና አመልካችም ሳትቆይ ወዲያውኑ ቁጥጥር ስር በዋለች ነበር በማለት አመልካቿ ድርጊቱን አለመፈፀሟን በበቂና አሳማኝ ሁኔታ ተከላክላለች በማለት በወ/መ/ህ/ስ/ስ/ቁ 149(2) መሰረት ከክሱ በነጻ እንድትሰናት በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ ሰጧል።
የአሁን ተጠሪም (የስር ከሳሽ) በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለክልል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በማቅረቡና ፍ/ቤቱም በበኩሉ ግራ ቀኙን አስቀርቦ በጉዳዩ ላይ እንዲከራከሩ ካደረገ በኃላ ጉዳዩን በመመርመር አመልካች በክሱ በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ የ8ወር እርጉዝ የነበሩትን የግል ተበዳይ በክንዷ ሆዷን እንደመታቻት የግል ተበዳይም ወዲያውኑ በዚሁ ምክንያት ህመም እንደተሰማና ፅንሱም መላወሱን እንዳቆመ በኃላም የግል ተበዳይዋ ወደ ሀኪም ቤት ተወስደው ሲታዩ ሽሉ ሞቶ በመገኘቱ በህክምና መሳሪያ እንዲወጣ መደረጉንና ሆኖም ግን የግል ተበዳይ በዚሁ ጉዳት ምክንያት የታመቀና የረጋ ደም መፍሰስ ያጋጠማት ስለመሆኑ የግል ተበዳይ ጨምሮ በዐ/ህግ በኩል ቀርበው በበታች ፍ/ቤት በተሰሙት ምስክሮች ቃል እና ህክምና ማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን ገልጾ በአንፃር ግን በአመልካች በኩል የተሰሙት መከላከያ ምስክሮች ቃል በተለይም አመልካቿ በተጠቀሰው ጊዜ ኩርሙክ ቦታ ሄዳ እዚያ የነበረች ስለመሆኑ በምን አግባብ ላያውቁ እንደተቻሉ በሚመለከት የአንዱ ምስክር ቃል ከልላው የሚጣረስ በመሆኑና በዚህም ምክንያት ክብደት እንደማይሰጠውና ተዓማኒነት የልለው መሆኑ እየታወቀ የበታች ፍ/ቤት ተከሳሸዋ ወንጀሉን ተከላክላለች በማለት በነፃ እንዲሰናበቱ በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ መስጠቱ ተገቢነት የልለውና ስህተት ያለበት ነው በማለት ተከሳሷ ክሱ በቀረበበት የህጉ ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ ላባል ይገባል በማለት የጥፋተኝነትም የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበልና ከህጉ ጋርም አገናዝቦ መመልከቱን ከገለፁ በኃላ በ3 ዓመት ከ 7 ወር ፅኑ እስራት ላቀጡ ይገባል በማለት ወስኗል የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የክልሉ ሰበር ችሎትም ጉዳዩ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለውም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ሳይቀበል አልፏል።
አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም በጥቅሉ ጥፋተኛ የተባልኩበትን ድርጊት አለመፈፀሜና በመከላከያ ማስረጃ በሚገባ በማረጋገጥ የተከላከልኩ ስለመሆኔ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተመርምሮ የተሰጠው ውሳኔ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ ተሽሮ ጥፋተኛ ተብዬ መቀጣቴና እንዲሁም ይኼውም ክልሉ ሰበር ችሎትም መፅናቱ ስህተት ያለበት በመሆኑ ውሳው ላሻርልኝ ይህ የሚታፍ ከሆነም አባት የልላቸው ልጆች የማሳድግ መሆኔንና የመሳሰሉት ግንዛቤ ውሰጥ ገብቶ ቅጣቱ ሳይፈፀም በገደብ ታግዶ እንዲቆይ አላያም እንዲቀነስልኝ የሚል ነው አቤቱታውም በሰበር አጣሪ ችሎቱ ተመርምሮ ለሰበር ክርከር ችሎት ቀርቦ ላታይ ይገባል በመባሉ ምክንያት ተጠሪም ቀርቦ የበኩሉን መልስ በጽሑፍ እንዲሰጥ መጥሪያ እንዲደርሰው የተደረገ ቢሆንም ባለመቅረቡ ጉዳዩ በልለበት እንዲታይ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
No topics extracted.
የጉዳዩ አመጣጥና ይዘት ባጭር ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የሰበር አቤቱታ በቀረበት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል ላለት ይቻላል ? ወይ ወይስ አይቻለም የሚለውን ነጥብ በጭብጥነት ይዘን ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርነውም የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ የግራ ቀኙን ምስክሮች ስምቶና ጉዳዩንም መርምሮ የሥር ተከሳሻ ወንጀሉን ተከላክላለች በሚል ምክንያት በነፃ እንዲሰናበት በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ የሰጠ ቢሆንም በአሁን ተጠሪ አመልካችነት ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በበኩሉ ግራ ቀኙ እንዲከራከሩ ካደረገ በኃላ ጉዳዩን በመመርመር አመልካች በመካከላቸው የነበረውን ጥል መነሻ በማድግ የ8 ወር እርጉዝ የሆነችውን የግል ተበዳይ ጠይባ መሐመድን በሆድዋ ላይ በክንዷ መትታ ጉዳት ያደረሰችባት መሆኑ የግል ተበዳይዋም በዚሁ ምክንያት ከተመታችበት ቦታ ሳትንቀሳቀስ ብርቱ ህመም እንደተሰማትና ፅንሱም መላወሱን ማቆሙን ከዚያም ሀኪም ቤት ተወስዳ በባለሙያ ምርም ሲደረግላት ፅንሱን ሞቶ በመገኘቱ ምክንያት በህክምና መሳሪያ እንዲወጣ መደረጉንና ከግል ተበዳይዋም ብዙ የረጋና የታመቀ ደም በመፍሰሱ ምክንያት ጉዳት የደረሰባት ስለመሆኑ በምስክሮች ቃልና ህክምና ማስረጃ መረጋገጡን የገለፀ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ በስር ተከሳሽ በኩል የተሰሙት የመከላከያ ምስክሮች ቃል አንዱ ከልላው ጋር የሚጋጭ በመሆኑ ተአማኒነት የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም በማለት የሥር ፍ/ቤቱን ውሳኔ በመለወጥ በአመልካች የጥፋተኝነት ውሳኔ ካስተላለፈ በኃላ በ3 ዓመት ከ7 ወር ፅኑ እስራት ላቀጡ ይገባል በማለት ቅጣት ጥሐል። የሰበር አቤቱታ የቀረበለት ክል ሰበር ችሎትም ውሳኔው ስህተት የለውም በማለት ወስኗል።
እንግዲህ እኛም ጉዳዩን እንደተመለከትነው የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አመልካች ወንጀሉን ላያስተባሉ አልቻም ሚል ድምዳሜ የጥፋተኝነት ውሳኔውን ላሰጥ የቻለው በህግ የተሰጠውን የማስረጃ ምዘና ተግባሩን መነሻ በማድረግ መሆኑን ከውሳኔው ይዘት የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱም ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ተጠቅሞ ያረጋጠውን ፍሬ ነገር ይህ ችሎትም እንዳለ የሚቀበለው ጉዳይ ይሆናል እንጂ በዚህ ረገድ የሚቀርበውን ክርክር ችሎቱ ለማት በህግ ስልጣን አልተሰጠውም።
በልላ በኩል እነዚህን በይገባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ የተረጋገጡትን ፍሬ-ነገሮች መነሻ በማድግ በህግ አተገባበር ረገድ በበታች ፍ/ቤቱ ውሳኔ ላይ የተፈጠረ ስህተት መኖር አለመኖሩን በተመለከተ ስንመለከተው ደግሞ አመልካች የ8ወር እርጉዝ በቀጥታ በሆዷ ላይ የመታችሁ ከመሆኑ አኳያ ድርጊቱ በወ/ህ/ቁ581/ለ)፤ 27(1) 540 ስር የተመለከተውን የግድያ ሙከራ የሚያቋቁም በመሆኑ በዚህ ረገድ በጥፋተኝቱ ውሳኔ ላይ የተፈጠረ ስህተት አላገኘንም።
ቅጣትን በሚመለከት የቀረበው የሰበር አቤቱታም ቢሆን ቅጣቱ በወ/ህ/ቁ192 መሰረት ሳይፈፀም ታግዶ እንዲቆይ ለማድረግ የሚያስች ምክንያቶች ተሟልተው ባልተገኙበት ሁኔታ ቅጣቱን ማገድ የማይችል ሲሆን መጠኑን በተመለከተም ከደረሰው ጉዳትና ወንጀሉ ክብደት አኳያ በስር ፍ/ቤት የተጣለው ቅጣት ተገቢ ነው ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም።በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥናል።
የቤ/ጉሙዝ ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ03748 በ24/7/2005 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ እና እንዲሁም የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ. በ17/8/2005 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በወ/መ/ህ/ስ/ስ/ቁ195(2)(ለ)(2) መሰረት ፀንቷል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ የፀና መሆኑን አመልካች በሚገኙበት ማረሚያ ቤት በኩል ይገለፅላቸው ። ይፃፍ