No summary available.
መስከረም 22 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አመልካች፡- የፍድራል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዐ/ህግ ዋልታንጉስ ፍቅሬ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሰለሞን ዩሐንስ ከጠበቃ ተስፋዬ አባተ ጋር ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው የወንጀል ጉዳይን የሚመለከት ነው።ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነውም የፍድራል ሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ ተጠሪን ጨምሮ በአምስት ሰዎች ላይ በ1996 ዓ/ም በወጣወ የኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32(1(ሀ) እና 407(1)(ሀ)(ለ)) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በስልጣን ያላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በማለት በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ተጠሪው ጥፋተኛ ተብለው በሶስት አመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እና በብር 2000.00 (ሁለት ሺህ) እንዲቀጡ በተሰጠው ውሳኔ የአሁኑ ተጠሪ ቅር በመሰኝት ይግባኛቸውን ለፈድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ችሎቱ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ተጠሪን በወንጀል ተጠያቂ መደረጉን ተቀብሎ አድራጎታቸው የሚወድቀው ግን የስራ ግድታን መጣስ በሚያስጠይቀው የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 420(1) ድንጋጌ ነው በማለት ቅጣቱን በተመለከተ ደግሞ ከቅጣት አወሰሳን መመሪያው በመውጣት በአራት ወር ቀላል እስራት እና በብር 600.00 እንዲቀጡ አሻሻሎ በመወሰኑ ነው።
አመልካች በተጠሪው ላይ ያቀረበው ክስ ዝርዝር ይዘት ተጠሪው የወ/ህ/ቁ 32(1(ሀ) እና 407(1(ሀ)(ለ)) በመተላለፍ በትራንስፖርት ኮንስትራክሽን ዲዛይን አክሲዩን ማህበር ምህንድሰና መምሪያ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የተሰጣቸውን የስልጣን ችሎታ ከመጠን በላይ አሳልፈው በመገልገል ሕገ ወጥ ጥቅምን ለሳባ ኢንጂነሪንግ ለማስገኘትና በመንግስትና ሕዝብ ጥቅም ላይም ጉዳት ለማድረስ በማሰብ የትራንስፖርት እና ኮንስትራስክሽን ዲዛይን አክሲዩን ማህበር ለጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/97 በ29/10/2004 እ.ኤ.አ በአወጣው የጨረታ ማስታወቂያ መሰረት አዲስ ሪግ ግዥ ተፈጽሞ እቃው በውለታውና በ"እስፔስፊኬሽኑ" መሰረት በትክክል ሳይቀርብ በኢንስፔክሽን ኮሚቴው በቀረበው ሪፖርት ላይ የሪጉ አካል ስለሆነው የውሃ ፓምፕ የተገለጸው በ"ስፔሲፊኬሽን"ና "ሰርቴፊኬት ኦፍ ኦርጂን" መሰረት እንዳልሆነ እና አሮጌ መሆኑ ተገልጾላቸው እያለ አዲስ መሆኑ ተረጋግጧል በማለት ርክክቡ እንዲፈፀም ሰኔ 02 ቀን 1998 ዓ/ም ለጂ.ኦ ቴክኒካል ምህንድስና ዋና ክፍል በጽሑፍ ትዕዛዝ በመስጠት እንዲሁም ከሣባ ኢንጂነሪግ ጋር ሚያዚያ 06 ቀን 1998 ዓ/ም በተደረገው ውይይት ተገዛ የተባለው ሪግ የውሃ ፓምፕ አሮጌ እና የማያገለግል መሆኑን በውይይት ጊዜ ተገልጾ እያለ የመስሪያ ቤቱን ጥቅም በሚጎዳ አኳኋን ስለውሃው ፓምፕ የተገለፀውን ጉዳይ ወደ ጎን በመተው በልሎች አነስተኛ ጉዳዮች ላይ ብቻ ስምምነት በመፈሙና "አክሴፕታንስ ሰርተፊኬት" እንዲፃፍ በማድረጋቸውና ከልሎች ተከሳሾች ጋር ሁነው በሙሉ ፍላጎታቸውና እውቃታቸው በብር ከፍተኛ ወጪ የተገዛው ንብረት ለመንግስት ያላግባብ ገቢ እንዲሆን በማድረግ ጉዳት አድርሰዋል የሚል ነው።
ተጠሪ የቀረበባቸውን የወንጀል ክስ ክደው ተከራክረዋል። በመሆኑም ዓቃቤ ሕግ ክሱን ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰውና የተለያዩ የሰነድ ማስረጃዎች አቅርቧል። ፍ/ቤቱም ዓቃቤ ሕግ እንደክስ አቀራረቡ አስረድቷል በማለት ተጠሪ እንዲከላከሉ ብይን በመሰጠቱ ተጠሪ የመከላከያ ማስረጃቸውን አቅርበዋል።ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ የተጠሪን መከላከያ ማስረጃዎችን የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን የሚያስተባብሉ አይደሉም በሚል ምክንያት ውድቅ አድርጎ ተጠሪን በቀረበባቸው የወንጀል ክስ ጥፋተኛ ናቸው በማለት በሶስት አመት ከስድስት ወር ፅኑ እስራት እና በብር 2000.00 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ላይ ተጠሪ ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ በተጠሪ ላይ የተሰጠውን የጥፋተኛነት ውሳኔ ድንጋጌውን በመቀየር ያፀናው ሲሆን ቅጣትን በተመለከተ ግን ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ መውጣት ተገቢ መሆኑን ያሳያሉ ያላቸውን ምክንያቶችን ጠቅሶ ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ በመውጣት በአራት ወር ቀላል እስራትና በብር 600.00 ተጠሪው እንዲቀጡ ሲል ወስኗል።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። ይህ ችሎት በአመልካች የቀረበውን የሰበር አቤቱታ መነሻ በማድረግ ግራ ቀኙን በጽሑፍ እንዲከራከሩ አድርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎት ክሱን መጀመሪያ በቀረበበት ፍ/ቤትና ጉዳዩን በይግባኝ በተመለከተው ፍ/ቤት የተሰጡ ውሣኔዎች አግባብነት ካላቸው ሕጐች ጋር በማገናዘብ በሚከለተው መልኩ መርምሮታል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ዋና ቅሬታ የተጠሪ አድራጎት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1(ሀ))እና በአንቀጽ 4107(1(ሀ)(ለ) ስር የሚሸፈን ነው፣ይህ ቢታለፍ እንኳን አድራጎቱ በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 411 ስር የሚወድቅ እንጂ እንደይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ድምዳሜ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 420 ስር የሚሸፈን አይደለም፣ከተጠሪ ጋር የተከሰሱት ግለሰቦችም በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ጥፋተኛ የተባሉትና የተቀጡት በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 411 ስር ነው፣ተጠሪ በውሉ አግባብ ያልቀረበ መሆኑን በኢንሲፔክሽን ኮሚቴ ተረጋግጦና ይህንኑ እያወቁ በጻፉት የአክሴፕታንስ ሰርቲፊኬት በመንስግስት ላይ ጉዳት መደረሱ ተረጋግጦ እያለ አድራጎታቸው የሙያ ግድታ በመጣስ የሚሸፈን ነው ተብሎ መወሰኑ ያላግባብ ነው፣እንዲሁም ተጠሪው ለግዥው ስፔሲፊኬሽን ሲሰራ ያልነበሩ መሆኑ ተጠያቂ የሆኑት ከግዥው በኋላ ለነበረው ሂደት በመሆኑና ከልሎች የማኔጅመንት አባለት ጋር ሁነው የግዥ ሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ ማድረጋቸውም የተጠሪ ጥረት ምን እንደሆነ በማስረጃ ባልተረጋገጠበት እና ወንጀሉ ውጤቱን ከአገኘ በኋላ በልላ ሰው በተፈፀመ የፍትሃ ብሄር ክስና ክርክር መነሻ ሁኖ በመሆኑ አንቀፁን ለመለወጥ የማያስችሉ ምክንያቶች ናቸው፣ተጠሪው የአደገኛነት ባህርይ ያላቸው ናቸው የሚል ነው።ተጠሪ በበኩላቸው የአመልካች የሰበር ቅሬታ ነጥቦች ተቀባይነት የልላቸው መሆኑንና ጥፋተኛ የተባሉትም የወንጀል መስራት ሀሳብ ስለመኖሩ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ መሆኑን ዘርዝረው መልሳቸውን ሰጥተዋል።
ጉዳዩን የተመለከትነውም ከዚሁ ከቀረበው አቤቱታ አንፃር ነው። ይህ ችሎት በዋናነት መሰረታዊ የሕግ ሥህተት ተፈፅሟል ሲባል ብቻ ውሣኔዎችን የሚመለከት በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ለውሣኔዎቻቸው መሰረት ያደረጉዋቸውን ፍሬ ነገሮች ትክክለኛነት ወደማጣራት ወይም ግራ ቀኙ ያቀረቡዋቸውን ማስረጃዎች ወደ መመዘን አልሄደም፣ይልቁንም እነዚህን በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች እንዳሉ በመውሰድ የተረጋገጠው ፍሬነገር በተጠሪ የቀረበውን ክሱ የሚያቋቁም መሆን አለመሆን የሚመለከተውን የሕግ ነጥብ ተመልክቷል።
ከሥር ፍ/ቤት መዝገብ መረዳት እንደቻልነው ተጠሪ የትራንስፖርትና የኮንስትራክሽን ዲዛይን አክሲዩን ማህበር የምህንድስና ኃላፊ ሁነው ሲሰሩ አከራካሪውን ሪግ ከውሉ ውጪ የቀረበ ስለመሆኑ በሚመለከተው ኮሚቴ ተረጋግጦ እያለና ተገቢ ያልሆነ ቃል ጉባኤ ከልሎች የማኔጅመንት ኮሚቴ አባለት ጋር ሁነው ይዘው የርክክብ ደብዳቤ በመጻፍ ለአቅራቢው ክፍያው እንዲፈፀም አድርገው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 407(1(ሀ)(ለ) በሚፃረር ሁኔታ በመንግስት ጥቅም ላይ ጉዳት አድርሰዋል የሚል ነው።
በፍርዱ ሂደት ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ሪጉ በውሉ በተመለከተው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ያልመቅረቡንና ተጠሪም ሆነ ልሎች አብሯቸው የተከሰሱት የድርጅቱ ኃላፊዎች እውቀት የነበራቸው መሆኑ በማስረጃ ማረጋገጡን የገለፀ ሲሆን በዚህ ረገድ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የተለየ ድምዳሜ የልለው መሆኑን ከውሳኔው ግልባጭ ተገንዝበናል።የርክክብ ደብዳቤ ላፃፍ የቻለው መሰረታዊ ምክንያትም ይሄው በማሽኑ ላይ ያለው ችግር ታውቆ አቅራቢው ድርጅት ችግሩን እንዲያስተካክል የድርጅቱ ተወካይ ባለበት ውይይት ተደርጎ በአስራ አምስት ወራት ውስጥ ችግሩን እንደሚያስተካከል ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ ስለመሆኑም በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል።ይህ ችሎትም ይህ የተጠሪ አድራጎት በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በተጠቀሰው ድንጋጌ መስፈርት ጋር በማያያዝ ትክክል መሆን አለመሆኑን ተመልክቷል። ከላይ እንደተገለፀው ተጠሪ እቃው እንደውሉ የሚቆፍር መሆኑ ተፈትሾ እና ተረጋገጦ ርክክብ ይፈፀም የሚል ሀሳብ በማኔጅመንቱ ስብሰባ ሲያቀርቡ የሳባ ኢንጀነሪግ ተወካይ አቅራቢው ድርጅት የማስሞከር ግድታ እንድለለበት በመግለፃቸው በዋስትናው ጊዜ አስራ አምስት ወራት ውስጥ ጉድለት ካለ አስተካክላለሁ በማለታቸው የእቃው ርክክብ እንዲፈፀምና የአክሴፕታንስ ሰርቲፊኬት ለመስጠት ስምምነት ተደርሶ ተጠሪውም ስምምነቱ ላይ መድረሳቸው፣ተጠሪ ከሚመሩት የዲዛይን መመሪያ በ14/11/1998 ዓ/ም በተፃፈ የውስጥ ማስታወሻ ማሽኑ አዲስነቱ ተረጋግጧል፣ገቢ ይሁን ተብሎ በመፃፉ የመልካም አፈጻጻም ዋስትና ገንዘብ (Perfomance bond) ለአቅራቢው ድርጅት ከተለቀቀለት በኋላ ሪጉ ሲፈተሸ በውሉ የተገለጸውን የ158 ሜትር ጥልቀት እንደማይቆፍር በፍሬ ነገረ ደረጃ መረጋገጡን ነው።
እነዚህ ፍሬ ነገሮች በግልጽ የሚያሳዩት ተጠሪ የሪጉን አዲስነት ከማረጋገጥ ጀምሮ የአስራ አምስት ወራት የዋስትና ጊዜ ውስጥ ጉድለቱ እንዲስተካከል የአቅራቢው ድርጅት ተወካይ ያቀረበው ሃሳብ ተጠሪው ጭምር ተሳታፊ በሆኑበት ኮሚቴ ተቀባይነት አግኝቶ የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ገንዘብ ለአቅራቢው እንዲለቀቅ የሚያደርግ ተግባር እስከተፈፀመባቸው ሂደቶች ውስጥ በቀጥታ ተሳታፊ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።እነዚህ ፍሬ ነገሮች ተጠሪው የመወሰን ስልጠን የነበራቸው መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው።የወንጀል ሕጉ አንቀፅ 420 ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው የመወሰን ሥልጣን የልላቸውና የሙያ ግልጋሎት የመስጠት ኃላፊነት ባለቸው ሰዎች ነው።እነዚህ ሰዎች በአንቀጽ 407 አግባብ የሚጠየቁት ግልፅ በሆነ ሁኔታ አንድን ሰው ለመጥቀም ወይም ራሳቸውን ለመጥቀም በማሰብና ኃላፊዎቻቸውን ለማሣሣት የፈፀሙት ጉልህ ተግባር መኖሩ ሲረጋግጥ ነው።ይህ እስካልተረጋገጠ ድረስ በሥልጣን አላግባብ የመገልገል ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው ላጠየቁ አይገባም። ስለሆነም በአንቀጽ 420 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ መሰረት ተጠሪው የሙያ ተግባሩንና ሥራው በአግባቡና በጥንቃቄ ባለመፈፀሙ ምክንያት በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ላባሉ የሚችሉበት አግባብ የለም።የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤተ ይግባኝ ሰሚ ችሎት በዚህ ረገድ የደረሰበት ድምዳሜ ተገቢነት ያለው ሁኖ አላገኘነውም።
የተጠሪ አድራጎት የሚሸፈንበት ድንጋጌ ስንመለከትም አመልካች በአንቀጽ 407 ስር ላሆን በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የሚያገኘው ሁኖ አልተገኘም።ምክንያቱም ከተጠሪ ጋር የተከሰሱት ግለሰቦች በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ በሆኑት ታይቶ አድራጎታቸው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1(ሀ) እና 411(1(ሀ)(ለ) ድንጋጌዎች ስር ጥፋተኛ የተባሉ በመሆኑና ውሳኔዎቹ ላይ አመልካች ቅር በመሰኘት ለሰበር ሰሚ ችሎት አቤቱታ ቢያቀርብም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ተብሎ በመ/ በሆኑ መዛግብት የመጨረሻ ፍርድ ያገኙ በመሆኑ ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 4፣41 እንዲሁም ከኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 25 ድንጋጌዎች አኳያ በሕግ ፊት እኩል ሁኖ የመታየት መብት አንፃርም ሆነ የወንጀል አድራጎቱን የበለጠ የሚሸፈነው ድንጋጌ አንቀጽ 407 ሳይሆን 411(1(ሀ)(ለ) ሁኖ ተገኝቷልና።
በወንጀል ሕጉ አንቀፅ 411 ሥር ወንጀል የሚያቋቁሙት ድንጋጌዎች የሚገኙት በንኡስ አንቀፅ (1) (ሀ)፣ (ለ) እና (ሐ) ነው። ማንኛውም በዚህ አንቀፅ ሥር የተከሰሰ ሰው በዚህ አንቀፅ ሥር ከተመለከቱት ውስጥ የትኛውን ወንጀል እንደፈፀመ በግልፅ በሚያመለክት ሁኔታ ክስ ላቀርብበትና ላከላከል ይገባል።ተጠሪ የዲዛይን መምሪያ ኃላፊ ሁነው የሪጉን አዲስነት ተረጋግጧል በማለት ማስረጃ እንዲቀርብ ማድረጋቸውም ሆነ የዋስትናውን ጊዜ በተመለከተ በአቅራቢው ድርጅት ግድታ ላይ ውሳኔ ሲሰጥ ተሳትፈው ከውሉ ውጪ በሆነ ሁኔታ ስምምነት ላይ መደረሳቸው ሲታይ የመንግስት ሥራን በማይመች አኳኋን መምራታቸውን የሚያሳይ ነው።
ከላይ ከተገለጹትና በስር ፍርድ ቤቶች ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች አንፃር ለጉዳዩ አግባብነት ያለውና ላጠቀስ ይገባ የነበረው አንቀፅ 411(ሐ) መሆኑን ተገንዝበናል። በዚህ አንቀፅ መሰረት የወንጀል ተጠያቂነት የሚከተለው ደግሞ ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የማይገባ ጥቅም ለማግኘት ወይም ለማስገኘት በማሰብ፣ሥልጣኑን ወይም ኃላፊነቱን ተጠቅሞ በጠቅላላው በሥራው ሥልጣን መሰረት በአደራ የተሰጠውን ወይም ላጠብቀውና ላከላከለው የሚገባውን የሕዝብ ወይም የመንግስት ጥቅም የሚጐዳ ተግባር በማናቸው ዘድ የፈፀመ እንደሆነ” ነው።
የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 411 አንድን ሰው ጥፋተኛ የሚያደርገው በሕጉ የተቀመጡት መስፈርቶች ተሟልተው ሲገኙ ነው።ክሱ ላይ እንደተገለፀው አንዱ መሟላት ያለበት መስፈርት በዚሁ አንቀፅ የተከሰሰው ሰው የማይገባ ጥቅም ለራሱ ወይም ለልላ ለሦስተኛ ወገን ለማስገኘት መንቀሳቀሱ ነው። አሁን በያዝነው ጉዳይ ተጠሪ ሪጉ አዲስ ነው በማለት ርክክቡ እንዲፈፀም የአክሴፕታንሰ ሰርቲፊኬት መፃፋቸው ጥፋት ነው የተባለ ሲሆን የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ገንዘብም በዚህ ደብዳቤ መነሻ ለአቅራቢው ድርጅት መከፈሉ ተረጋግጧል።ይህ ደግሞ በስራቸው ሥልጣን መሰረት በአደራ የተሰጣቸውን ወይም ላጠብቁትና ላከላከሉት የሚገባውን የሕዝብ ወይም የመንግስት ጥቅም የሚጐዳ ተግባር መፈፀማቸውን የሚያሳይ ነው።በመሆኑም ተጠሪ ጥፋተኛ ላባሉ የሚገባው በአንቀጽ 411(1(ሐ)) ስር ሆኖ ስለአገኘነው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በተጠሪ ላይ የሰጠውን የጥፋተኝነት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(ለ-2)) እና በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 113/2/ መሰረት በመለወጥ ተጠሪ በወንጀል ህግ አንቀፅ 411(1(ሐ)) ስር የተመከተውን ድንጋጌ የተላለፈ ነው በማለት የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥተናል።
የቅጣቱን መጠን በተመለከተ በልሎች የተጠሪ ግብረአበሮች የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቅጣት ሲወስን ወንጀሉ ከውል አፈፃጸም ጋር ተያይዞ የተፈጸመ መሆኑንና ውሉም እንዲፈርስ የተደረገ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ አስገብቶ በቅጣት አወሰሳን መመሪያው አንቀፅ 13(2) መሰረት ላጣል የሚገባው ዝቅተኛ የወንጀል ደረጃውን ያገናዘበ ቀላል እስራት ቅጣት ላሆን እንደሚገባ፣በቅጣት አወሳሰን መመሪያው አንቀጽ 13(3) መሰረት የቅጣት መነሻና መድረሻ መካከል ያለውን ቅጣት ርዝመት ለአራት እኩል ተካፍሎ የሚመጣው ዝቅተኛ ወንጀል ደረጃ የቅጣት ፈቅድ ስልጣን ከአንድ አመት እስከ አንድ አመት ስድስት ወር ቀላል እስራት የሚያስቀጣ መሆኑን፣ይህም ፍቅድ ስልጣን በቅጣት አወሰሳን መመሪያ አባሪ አንድ ከእርከን 7 ስር የሚሸፈን መሆኑን ግንዘቤ ውስጥ አስገብቶ እያንዳንዱ አጥፊ በግል ያቀረበውንና ሕጋዊ የቅጣት ማቅላያ ምክንያት በመቀበል ተገቢ ነው ያለውን እስከ ስድስት ወር ቀላል እስራት እና ብር 1000.00 የገንዘብ መቀጮ ቅጣት ያስተላለፈ በመሆኑ ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረታዊ አላማ ጋር ተገናዝቦ ሲታይ በተጠሪ ላይ የሚጣለው የቅጣት መጠንም ከላይ በግብረ አበሮቹ ላይ ቅጣት ሲወሰን ተፈፃሚ የሆነውን አካሄድ ላከ,ተል የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል።ከዚህ አንፃር ጉዳዩን ስንመለከተው ተጠሪ ላቀጡ የሚገባው በቀላል እስራት በመሆኑና ቀላል እስራት ደግሞ ከአስር ቀን እስከ ሶስት አመት ሚደርስ ስለሆነ በመመሪያው አንቀጽ 13(3) መሰረት መነሻና መድረሻው መካከል ያለውን ቅጣት ርዝመት ለአራት እኩል ተካፍሎ የሚመጣው ዝቅተኛ ወንጀል ደረጃ ቅጣት ፍቅድ ስልጣን ከአንድ አመት እስከ አንድ አመት ከስድስት ወር ቀላል እስራት የሚያስቀጣ ነው።በዚህ ፍቅድ ስልጣን ያለው ቅጣት በመመሪያው አባሪ አንድ እርከን ሰባት ስር የሚሸፈን ነው።በአቃቤ ሕግ በኩል የቀረበ የቅጣት ማክበጃ ምክንያት የልለ ሲሆን ተጠሪ ሪኮርድ የልለባቸው፣የቤተሰብ አሰተዳደሪ እና የዲስክ መንሸራተት በሽታ ያለባቸው መሆኑ በፍድራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቅጣት ማቅላያነት የተያዙ ምክንያቶች ስለሆኑ ይህ ችሎትም የሚቀበላቸው በመሆኑ ሶስቱ የቅጣት ማቅላያ ምክንያቶች ሲያዙ እርከኑ ወደ እርከን አራት ይወረዳል።በዚህ እርከን የፍርድ ቤቱ ፍቅድ ስልጣን ደግሞ ከአራት ወር እስከ ሰባት ወር እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ ተጠሪ ላቀጡ የሚገባው በስድስት ወር ቀላል እስራት ነው በማለት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 195(2)(ለ-2) መሰረት የበታች ፍርድ ቤቶችን የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በማሻሻል ፍርድ ሰጥተናል።
ሲጠቃለልም የተጠሪ አድራጎት የሚሸፈነው በአቃቤ የሕግ ማመልከቻ በተጠቀሰው ድንጋጌ ወይም በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርደ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በተጠቀሰው ድንጋጌ ሳይሆን በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 411(1(ሐ)) ድንጋጌ በመሆኑና ቅጣቱም ከዚህ ድንጋጌ አንጻር የሚጣል በመሆኑ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በከፊል መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አሻሽለናል።በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል፡ ው ሣ ኔ
በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ታህሳስ 11 እና 26 ቀን 2004 ዓ/ም፣በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ ህዳር 06 ቀን 2005 ዓ/ም የተሻሻለው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(ለ)) መሰረት አሻሽለናል።
የተጠሪ አድራጎት የሚሸፈነው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 32(1(ሀ)(ለ) እና 411(1(ሐ)) ድንጋጌ ስር ነው ብለናል።ቅጣቱን በተመለተከተም ተጠሪ ላቀጡ የሚገባው በጉዳዩ ላይ የታሰሩት ማናቸውም ጊዜ የሚታሰብላቸው ሁኖ በስድስት ወር ቀላል እስራትና በብር 1000.00 ነው ብለናል።
ተጠሪ በዚህ ችሎት እንዲቀጡ ከተወሰነባቸው የእስራት ጊዜ በላይ በጉዳዩ ላይ የታሰሩ መሆኑ ስለተረጋገጠ የእስራት ዋራንት እንዲጻፍ ተገቢ ሁኖ አልተገኘም፣የገንዘብ መቀጮውን በተመለከተ ግን ተጠሪ ያልከፈሉትን ቀሪ ገንዘብ ካለ አመልካች ተከታተትሎ ገቢ እንዲያስደርግ ብለናል።
No topics extracted.