No summary available.
መጋቢት 27 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ዘካሪያስ ገ/ጻዲቅ አለማየሁ ተጠሪ፡- የፍድራል ዐቃቤ ሕግ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ አንድ ሰው በአንድ የወንጀል ጉዳይ በድጋሚ ክስ ላቀርብበት አይገባም ላባል የሚችልበት ሕጋዊ አግባብ የሚመለከት ነው።ክርክሩ የተጀመረው በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁነ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ የመሰረተው ክስም በሁለት ምድብ የተከፈለ ነው።አንደኛው ክስ አመልካች ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለማግኘት አስቦ በቦል ክፍለ ክተማ ቀበል 10 ውስጥ የሚገኘውን ንብረትነቱ የኦቶ ታደሰ ሙለታ መኖሪያ ቤት የሆነውን ከተከራየ በኋላ ካርታ ላሳድስላችሁ ብሎ በውክልና ከወሰደ በኋላ ቤቱን ለመሸጥ ሺል በመታወቁ የተሰጠው ውክልና ተነስቶ ክስ ቀርቦበት ይህ ቤት እንዳይሸጥ፣እንዳይለወጥ በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት, አግድ ተሰጥቶ እያለ ግንቦት 16 ቀን 2002 ዓ/ም ሐሰተኛ ሰነድ የእግድ ትእዛዝ አዘጋጅቶ እግድ እንዲነሳ ከአደረገ በኋላ የግል ተበዳይ ታደሰ ሙለታ ውክልና የተሰጠው በማስመሰል በሐሰተኛ ውክልና በመገልገል ቤቱን በብር 1,030,000.00(አንድ ሚላዩን ሰላሳ ሺህ ብር) ለወ/ሮ ሰናይት ብርሃኑ ግንቦት 30 ቀን 2002 ዓ/ም ሽጦ ለግል ጥቅም በማዋል በ1996 ዓ/ም የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 696(ሐ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ከባድ ማታለል ፈፅሟል የሚል ሲሆን ሁለተኛ ክስ ደግሞ በሐሰተኛ ሰነዶች በመገልገል የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 378 ድንጋጌን ተላልፏል የሚል ነው።የአሁኑ አመልካችም ክሱን ክዶ በመከራከሩ አቃቤ ሕግ አሉኝ ያላቸውን ስድስት የሰው ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቦ ክሱን ማስረዳቱን ፍርድ ቤቱ ከተገነዘበ በኋላ የአመልካችን የመከላከል መብት በመጠበቅ የመከላከያ ማስረጃዎችን ሰምቷል።ከዚኅም በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን መርምሮ አመልካች በክሱ መሰማት ጊዜ ቀድሞ በጉዳዩ ላይ ተከሰው በነፃ የወጡ መሆኑን የገለጹ መሆኑን የተረዳ መሆኑን ጠቅሶ በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን የመከራከሪያ ነጥብ ቀድሞ አመልካች ተከሰው ነጻ የወጡበት ጉዳይ በኋላ ከቀረበባቸው ክስ ጋር ልዩነት ያለው ነው በማለት በሚል ምክንያት ውድቅ ያደረገው ሲሆን ዋናውን ጉዳይ በተመለከተም አመልካች በመከላከያ ማስረጃዎች የአቀቤን ማስረጃዎችን ያላስተባበለ መሆኑን በመግለጽ የመከላከያ ማስረጃዎችን ውድቅ በማድረግ አመልካችን በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሰው በቀረቡት ሁለቱም ድንጋጌዎች ስር ጥፋተኛ አድርጎታል።ቅጣቱን በተመለከተም የግራ ቀኙን የቅጣት አሰተያየት በመቀበል ከፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ጋር አገናዘቦ መመልከቱን በመግለፅ ለሁለቱም ክሶች በድምሩ በ17(አስራ ሰባት)አመት ፅኑ እና በብር 40,000.00(አርባ ሺህ) የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችሎት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም።የአሁኑ የሰበር አቡቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም በጉዳዩ ላይ ቀድሞ ክስ ቀርቦበት በነፃ ተለቀው በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የነፃ መለቀቁ ውሳኔ ጸንቶ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ይህንኑ አልፈው አመልካችን በድጋሚ ክስ ቀርቦ በመቀበል ተጠያቂ በማድረግ መወሰናቸው በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 23 ስር የተመለከተውን የሚጥስ ነው በማለት መከራከሩንና በዚህ ምክንያት የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ እንዲሻር ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ቀድሞ በፍድራል መጀረመያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ; ክስ ቀርቦበት በነጻ ተሰናብቶ ይኼው ውሳኔ በመ/ በይግባኝ ቀርቦ በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጸንቶ ባለበት ሁኔታ ሁኔታ በድጋሚ ክሰ ቀርቦበት በወንጀል ተጠያቂ የመባሉትን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪም ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካለቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን ለሰበር ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ለአሁኑ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በአመልካች ላይ የተሰጠው በ1996 ዓ/ም በወጣው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 696(ሐ) እና 378 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የወንጀል ድርጊቶቹን መፈፃማቸው ተረጋግጧል ተብሎ መሆኑን፣አመልካች በነፃ ተሰናብቼአለሁ በማለት የሚከራከሩበት ጉዳይ ደግሞ አንቀጽ 678 ስር የተመለከተውን ተላልፈዋል ተብሎ ክስ ቀርቦባቸው የነበረ መሆኑን፣በሁለቱም ክሶች የቤቱ ባለንብረት የተባሉትና ለክርክሩ ምክንያት የተባለው የቤት ሕጋዊ ባለንበብት የሆኑት ግለሰብ አቶ ታደሰ ሙለታ የተባሉት መሆናቸውን፣አመልካች በነጻ ወጡ የተባለበት የወንጀል ድርጊት ዝርዝር ይዘቱ ሲታይም አመልካቹ ያግባብ ለመበልፀግ ሳይሆን የንብረቱን ባለቤት በንብረቱ እንዳጠይቀምበት ለማድረግ በማሰብ ታህሳስ 30 ቀን 2002 ዓ/ም በቦል ክፍለ ከተማ ቀበል 08/09 ልዩ ቦታው የቦል ክፍለ ከተማ መስተዳደር ግቢ ውስጥ የግብለ ተበዳይ አቶ አጋ ሙሉታ በሰጡት ህጋዊ ውክልና ተጠቅሞ የቤት የሆነውን ኦርጂናል የቤት ካርታ ወስዶ ባለመመለሱ የግል ተበዳይ ንብረትነቱ የአቶ ታደሰ ሙሉታ የሆነውን በውክልና የሚያስተዳድሩበትን ኦርጅናል የቤት ካርታና ፕላን ህዳር 15 ቀን 2002 ዓ/ም ከወሰደ በኋላ የግል ተበዳይ መልስልኝ ሲሉት ባለመመለሱ በልላ ሰው ሃብት ያላግባብ መገለገል ወንጀል ፈጽሟል የሚል መሆኑን፣የአሁኑ ክስ ግን በሐሰተኛ ሰነድ የአቶ ታደሰ ሙሉታን ንብረት በመሸጡ ከባድ የማታላል ወንጀል ፈጽሟል፣በሐሰተኛ ሰነድም ተገልግለጓል የሚል ሁኖ ድርጊቶቹ የተፀሙበት ጊዜና ሁኔታ ቀድሞ ቀርቦ ከነበረው ክስ ጋር የተለያዩ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ በኢ.ፍ.ዲ.ሪብላክ ሕገ መንግስት የወንጀል መርህ ተደርገው ከተደነገጉት መብቶች አንዱ አንድ ሰው በአንድ የወንጀል ድርጊት ክስ ቀርቦበት የመጨረሻ በሆነ ውሳኔ ጥፋተኛነት ተረግጋግቶ በተቀጣበት ወይም በነፃ በተለቀቀበት ወንጀል እንደገና መከሰሰና መቀጣት የልለበት መሆኑን የሚደነግግው አንቀጽ 23 ይገኝበታል።ይህ መርህ በ1996 ዓ/ም በወጣው የኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ የወንጀል ሕግ ውስጥም በአንቀጽ 2(5) ስር በግልጽ ተመልክቷል።በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 9(4) መሰረት የአገሪ የህግ አካል በተደረጉ አለምአቅፍ ስምምነቶች ውስም የሲቭልና የፖለቲካ መብቶች ስምምነት በአንቀጽ 14 ስር ያስቀመጠው ድንጋጌ ይህንኑ ያረጋግጣል።በመሆኑም ይህ መብት በሕግ ጥበቃ የተደረገለት መሆኑ ግልጽ ሲሆን መብቱን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ በሕጉ የተቀመጡት መመዘኛዎች መሟላታቸውን ማረጋገጥ የግድ ይላል።አንድ ሰው በድጋሚ ልከሰስ አይገባም ብሎ ለመከራከር በሕጉ ይዘትና መንፈስ መሰረት መሟላት ያለባቸው ሕጋዊ መሰፈርቶች ተከሳሹ በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት አግባብነት ባለው የወንጀል ሕግና የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ መሰረት ተከሶ የነበረ መሆኑና ቀድሞ በተከሰሰበት የወንጀል ድርጊት የመጨረሻ በሆነ ፍርድ ጥፋተኛ ሆኖ የተቀጣ ወይም በነፃ የተለቀቀ መሆን በሚገባ መረጋገጥ ስለመሆናቸው ከመርሁ ይዘትና መንፈስ የምንረዳው ጉዳይ ነው።የዚህ መርህ ዓይነተኛ አላማም ዜጎች በአንድ የወንጀል ድርጊት በተደጋጋሚ በሚቀርብ ክስ ስጋት ውሰጥ ከመኖር ነጻ እንዲሆኑ ማድረግ ነው ተብሎ ይታሰባል።በልላ በኩል መርሁ ተግባራዊ ሲደረግ በሕጉ የተቀመጡት መመዘኛዎችን በጥንቃቄ በማየት የተከሳሹን መብት ተገቢ በሆነ ሁኔታ ለማስከበር ከማስቻሉም በላይ አጥፊዎች ከወንጀል ድርጊት ነጻ እንዳይወጡና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግና የወንጀል ሕጉን ዓላም በሚያሳካ መልኩ ተግባራዊ መደረግ ያለበት መሆኑ የሚታመን ነው። ስለሆነም ከላይ የተመለከቱትን ሕጋዊ መመዘኛዎችንና ዓላማዎችን መሰረት በማድረግ ጉዳዩን መመልከቱና ዳኝነት መስጠቱ ተገቢነት ይኖረዋል።
የአመልካችን ጉዳይ ከዚህ አንፃር ስንመለከተው በቀድሞው ክስ የመጨረሻ ፍርድ ተሰጥትቶ አመልካች በነፃ የተሰናበቱ መሆኑን የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መ/ና የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመ/ የሚያረጋግጡት ሀቅ ሲሆን በእነዚህ መዛግብት የታዬው ጉዳይ አመልካች የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 678 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በልላ ሰው ሃብት ያላግባብ መገልገል ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተከሰሱትና በኋላም ፍርድ ቤቶቹ በማስረጃ አልተረጋገጠም በማለት ተጠሪን ነፃ ያደረጉበት ምክንያት አመልካች የወሰዳቸው የቤት ካርታዎች በሽያጭና በብድር ውል መያዣነት መሆኑን ተረጋግጧል በሚል ነው።ይህም የሆነው በክሱ ላይ የተጠቀሳን የባለቤትነት ደብተር ካርታና ፕላን እንዲያወጡ እንዲረከቡ ውክልና ሰጪው ለአመልካች ውክልና መስጠታች በመረጋገጡ፣የቤቱ ባለቤት ከባለቤታቸው ጋር በመሆኑን ቤቱን ለአመልካች በመሸጣቸውና በአሁኑ አመልካችና በአቶ ታደሰ ሙለታ የገንዘብ ብድር ውል ተደርጎና በፍርድ ቤት አመልካቸ አቶ ታደሰ ሙለታን በመክሰስ በመ/ የካቲት 17 ቀን 2002 ዓ/ም ለአሁኑ አመልካች የተፈረደላቸወ መሆኑን በሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጧል በማለት ፍርድ ቤቶቹ ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸው ምክንያት ነው።ባሁኑ ጉዳይ አመልካች የተከሰሱት የግል ተበዳይ ቤት እንዳይሸጥ፣እንዳይለወጥ በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍድ ቤት በመ/ እግድ ተሰጥቶ እያለ ግንቦት 16 ቀን 2002 ዓ/ም በሐሰተኛ ሰነድ የእግድ ትዕዛዝ በማዘጋጀት እግዱ እንዲነሳ ከአደረገ በኋላ የግል ተበዳይ የአቶ ታደሰ ሙለታ ወክልና የተሰጠው በማስመሰል በሐሰተኛ ውክልና በመገልገል ቤቱን ግንቦት 30 ቀን 2002 ዓ/ም ሸጠዋል በሚል ነው።ስለሆነም አመልካች ቀድመው በግል ተበዳይ ላይ የፍትሓ ብሕር ክስ አቅርበው የነበሩ መሆኑ ቢረጋገጥም በፍርድ ቤት የተሰጠውን እግድ ግን ለውጠዋል፣እግድ የተነሳ መሆኑን የሚሳይ ማስረጃም ሐሰተኛ ነው በማለት አቃቤ ክስ መመሰረቱን በግልጽ የምንረዳው ጉዳይ ነው።አመልካች ከግል ተበዳይ ወሰዱ የተባሉትና ስለመኖሩ በመ/ በቀረበው የወንጀል ክስ ተረጋግጧል የተባለው የውክልና ሰነድም በጥር ወር 2002 ዓ/ም ውስጥ መሻሩ አሁን እያከራከረ ባለው የወንጀል ጉዳይ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ ሲሆን አመልካች በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 678 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል ተብሎ በአቃቤ ሕግ በስር ፍርድ ቤት ክስ የቀረበባቸውም የካቲት 17 ቀን 2002 ዓ/ም ስለመሆኑ በፍ/መ/ደ/ፍርድ ቤት መ/ ጋር ተያይዞ ካለው የክስ ማመልከቻ ተመልክተናል።እግዲህ የግል ተበዳይ ቤት የተሸጠው በሐሰተኛ የፍርድ ቤት እግድ ማንሻ ትዕዛዝና የውክልና ስልጣን ስለመሆኑ በሰው ምስክርነትም ሆነ በፎረንሲክ ምርምራ ውጤት ማስረጃዎች በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል። በቀደመው ክስ አመልካች የግል ተበዳይን በቤቱ እንዳይገለገል አድርጓል የተባለው የቤቱን ካርታ ላመለስ አልቻለም ተብሎ ሲሆን በሁለተኛው ክስ ግን ሐሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት የግል ተበዳይን ቤት ሽጧል በሚል ነው። በግንቦት 3ዐ ቀን 2002 ዓ.ም ወይም በፊት አመልካች የግል ተበዳይን ቤት በሕጋዊ መንገድ የገዙት ስለመሆኑም አልተረጋገም።በመሆኑም አመልካች አሁን የቀረበበት ክስ ዝርዝር ይዘቱ፣የድርጊቱ አፈጻጸም እና ጥሰት ተደርጎበታል የተባለው የግል ተበዳይ የመብት አድማስ ቀድሞ ክስ ከቀረበበት ጉዳይ ዝርዝር ይዘት ጋር የማይገናኝ ሁኖ አግኝተናል።በዚህም ምክንያት በአንደ ጉዳይ በድጋሚ በወንጀል የተከሰሱ መሆናቸውን ገልጸው ያቀረቡት ቅሬታ ተቀባይነት የሚሰጠው ሁኖ አላገኘንም።
የወንጀል ድርጊቶችን አፈጻጸም በተመለከተ አመልካች ግልጽ የሆነ የሰበር ቅሬታ ያላቀረበቡት ቢሆንም ፍሬ ነገሩን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርደ ቤቶች በሚገባ ያረጋገጡት ጉዳይ በመሆኑና ለዚህ ችሎት በኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ከተሰጠው ስልጣን አንፃር ሲታይም የተለዬ ድምዳሜ የሚያዝበት ሁኖ አልተገኘም።አመልካች ከመንግስት መስሪያ ቤቶች ያልወጡትን ሰነዶችን ከመንግስት መስሪያ ቤቶች እንደወጡ በማስመሰል፤በሐሰተኛ መንገድ በማዘጋጀት የግል ተበዳይን ቤት የሸጡ መሆናቸው በአንቀፅ 696(ሐ) ስር የተመለከተውን መተላለፋቸውን የሚያሳይ ሲሆን ይህንኑ ቤቱን ለመሸጥ አድራጎት ጥቅም የዋሉት ሐሰተኛ ሰነድ መሆኑ ደግሞ ይኼው አድራጎት በተገቢው ድንጋጌ በተደራቢነት የሚያስጠይቃቸው መሆኑን ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 699 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።ስለሆነም አመልካች በአንቀጽ 696(ሐ) እና 375 ድንጋጌዎች ስር ጥፋተኛ መባላቸው ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(2)፣58 እና ከወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 141 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አንጻር ሲታይ ተገቢ ሁኖ አግኝተነዋል።ቅጣቱን በተመለከተም አመልካች ጥፋተኛ የተባሉባቸው ድንጋጌዎች ከሚያስቀጡት የቅጣት መጠንና ከቅጣት አጣጣል መርሆዎች እንዲሁም ከፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቅጣት አወሳሰን መመሪያ አንጻር ሲታይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት የሚቻል ሁኖ አልተገኘም።ሲጠቃለልም በጉዳዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሕዳር 21፣ታህሳስ 02 ቀን 2004 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ መስከረም 30 ቀን 2005 ዓ/ም የጸናው የጥፋተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2(ሐ)) መሰረት ሙሉ በሙሉ ፀንቷል።ለማረሚያ ቤቱ ይፃፍ።
አመልካች በአንድ የወንጀል ድርጊት ድጋሚ አልተከሰሱም ብለናል።
No topics extracted.