No summary available.
የካቲት 28 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- የአቀቂ ቃላት ክ/ከተማ ወረዳ 5 ንግድና ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ተጠሪዎች፡- ሃምሳ አለቃ ታምራት ከበደ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዳዩ ከንግድ ስራ ፈቃድ ማገድ ጋር ተያይዞ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ከርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በአ/አበባ ከተማ መስተዳድር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረተው ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ በአቃቂ ቃላት ክ/ከተማ ወረዳ 5 ክልል ውስጥ ባለኝ የመኖሪያ ቤት ይዞታዬ ላይ የመኪና ማቆሚያ ንግድ ስራ ህጋዊ ፍቃድ ተሰጥቶን እየሰራሁ እያለሁ ተጠሪ በቁጥር 415/2004 ታህሳስ 23 ቀን 2004 ዓ/ም በተፃፈ ማስጠንቀቂያ እየሰራህ ያለው የንግድ ስራ ከፀጥታ ከጤና እና ከአካባቢ ብክለት አንፃር በአካባቢ ጥበቀ ላይ ከፍተኛ ችግር እያደረሰ ነው በሚል ምክንያት የንግድ ፍቃድን ለማገድ ሁከት ስለፈጠረብን የተፈጠረው ሁከት እንዲወገድለት ዘንድ ዳኝነት ጠይቋል። ተጠሪም ቀርቦ በሰጠው መልስ በአዋጅ ቁ 686/2002 ዓ.ም አንቀጽ 37/ሀ/ መሰረት እግድ መስጠቱ ህጋዊ እርምጃ በመሆኑ የቀረበው የሁከት ይወገደልኝ አቤቱታ ተገቢነት የልለው በመሆኑ ክሱ ወድቅ ተደርጎ እንዲሰናበት በመጠየቅ መልስ ስጥቷል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የከተማ መ/ደ/ፍ/ቤትም የተጠሪ መኪና ማቆሚያ ንግድ ስራ በአካባቢው የጤናም ሆነ ብክለት ላይ ችግር ማስከተሉ በማስረጃ ሳይደገፍ የንግድ ስራ ፈቃዱ በአመልካች መታገዱ የሁከት ተግባር በመሆኑ የተፈጠረው ሁከት ይወገድ ሲል ወስኖል አመልካችም ይህን ውሣኔ በመቃወም ቅሬታውን ለከተማ መስተዳደሩ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ጸንቷል። እንዲሁም አቤተታውን ለከተማው መስተዳድር ሰበር ሰሚ ችሎት ያቀረበ ቢሆንም አሁንም ተቀባይነት አላገኘም።
ሐምል 24 ቀን 2004 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ አመልካች ያቀረበው የሰበር አቤቱታም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ሲሆን ይዘቱም ባጭሩ አመልካች በአዋጅ ቁ 686/2002 አንቀጽ 37/1/ሀ/ መሰረት ተጠሪ የፈጠረው ችግር አስኪታረም ድረስ የንግድ ስራ ፈቃዱን ማገዱ በህግ የተሰጠን ስልጣን ሲሆን ይህም በተሰጠን ስልጣን መሰረት ሀላፊነትና ግድታችን መወጣት እንጂ የሁከት ተግባር ላባል የማይችል በመሆኑ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ተሸሮ የተፈጠረ ሁኩት የለም ተብሎ እንዲወሰንላቸው ዘንድ ጠይቋል። አቤቱታውም ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ላቀርብ የገባል በመባሉ ተጠሪ ቀርቦ የበኩሉን መልስ የሰጠ ሲሆን አመልካችም የመ/መልሱን ሰጥቶበታል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ከርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመርነውም የንግድ ምዝገባና ፈቃድ ጋር በተያያዘ ጉዳይ የሚመለከተው የአስተዳደር አካል አስተዳደራዊ እርምጃን በሚወስደበት ጊዜ በተወሰደው አርምጃ መብቴ ተነክቷል። የሚል ሰው ካለ መብቱን በምን አይነት ሰርዓት እና መንገድ ላያስከብር ይችላል? የሚለው ነጥብ በቅድሚያ ታይቶ የምላሽ የሚሻ ሆኖ ተገኝቷል።
ይህን ጉዳይ በተመለከተ አግባብነት ያለው ህግ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 686/2002 ሲሆን አዋጅ አንቀጽ 61ም በአስተዳደራዊ አርምጃዎች ላይ ቅሬታ ስለማቅረብ በሚለው የድንጋጌው ርዕስ ስር በዚህ አዋጅ መሰረት በመዝገቢው መስሪያ ቤት ወይም አግባብ ባለው ባለስልጣን አስተዳደራዊ እርምጃ የተወሰደበት ሰው ላኖረው ከሚችለው ቅሬታ ጋር በተያያዘ በህግ ጉዳዮች ላይ ብቻ ለመደበኛ ፍ/ቤት አቤቱታ ላያቀርብ ይችላል በሚል በግልጽ ተመልክቷል። ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መንፈስ ደግሞ መረዳት የሚቻለው በህግ ጥያቄዎች ላይ ብቻ ካልሆነ በስተቀር የፍሬ ነገር ክርከርን በሚመለከት መደበኛ ፍ/ቤቶች ተቀብለው ለማየት ስልጣን ያለተሰጣቸው መሆኑን ነው። ከህግ አተገባበር ጋር በተያዘ የተፈጠረ ስህተት ካለ እሱን በተመለከተ ብቻ ተቀብለው ከማረም ውጭ የፍሬ ነገር ክርክርችን በማስረጃ አጣርተው ውሳኔ ለመስጠት ስልጣን የለችውም በተያዘው ጉዳይም ሁከት ይወገደልኝ በሚል የቀረበውን የክሱን ፍሬ ነገር በተመለከተ የስር ፍ/ቤቶች ግራ ቀኙን በማከራከርና በማስረጃ በመጣራት የሰጡት ውሳኔ ከፍ ሲል በተጠቀሰው ምክንያት የህግ መሰረት ያለው አይደለም በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች በዚህ ጉዳይ የፍሬ ነገር ጉዳይን በሚመለከት አከራክረው የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለገኘን ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በዚህ ጉዳይ የአ/አበባ አስተዳደር መ/ደ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚና ሰበር ሰሚ ችሎቱ የሰጡት ውሣኔዎች በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሸሯል።
መደበኛ ፍ/ቤቶች ከንግድ ምዝባና ፈቃድ ጋር በተያዘ የሚነሱ የፍሬ ነገር ክርክሮችን አይተው ለመወሰን ስልጣን የላቸውም።
ተጠሪ የህግ ጉዳይን ወይም ጥያቄን በተመለከተ ብቻ በአዋጅ ቁ 686/2002 61 መሰረት ስልጣን ላለው መደበኛ ፍ/ቤት አቅርቦ መብቱን ለማስከበር ይህ ውሳኔ አይከለክለውም።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርከር ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ወጪና ኪሣራ ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.