No summary available.
መጋቢት 24 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ረታ ቶሎሣ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቱል።
ጉዳዩ የንጽህና አቃዎችን ለመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋም አቅርቦት ውልን መሰረት አድርጐ የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በጋሞ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው።የተጠሪ ክስ ይዘትም የአሁኑ አመልካች በ2001 ዓ.ም የበጀት አመት ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ መደበኛ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውል የንጽህና እቃዎች ግዥ ጨረታ በአዲስ ዘም 67ኛ አመት ቁጥር 337 ነሐሴ 17/2000 ዓ.ም. ታትሞ በወጣው ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቶ የአሁኑ ተጠሪ ተወዳድረው የተሻለ ዋጋ አቅራቢ መሆናቸው ተረጋግጦ የአሁኑ አመልካችም የተጠሪን አሸናፊነትን በቁጥር /42 በቀን 13/02/2001 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ የገለፀላቸው መሆኑን ተጠሪ በአስር ቀናት ውስጥ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 10% ብር 63,468.50 (ስልሳ ሶስት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ምስንት ብር ከሀምሳ ሳንቲም) የአሁኑ አመለካች በስሙ ባስከፈተው ባንክ ሂሳብ ገቢ እንዲደረግ እና በሚሰጠው ኘርግራም መሰረት የአሁኑ ተጠሪ እቃዎችን እንዲያቀርቡ ውል እንዲፈጽሙ ያዘዛቸው መሆኑን በዚህም መሰረት ተጠሪ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትናዉን ገንዘበ ሕዳር ዐ2 ቀን 2001 ዓ/ም በውል በመፈፀም አስይዘው በውሉ መሰረት ለአሁኑ አመልካች ብር 634,685.00 (ስድስት መቶ ሰላሳ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ አምስት ብር) የሚያወጣ የንጽህና እቃዎችን አቅርበው አመልካችም ገቢ በማድረግ ዋጋውን የከፈላቸው መሆኑን ከዚህ በተጨማሪ አመልካች ተጠሪን ጠቅላላ የጨረታውን ዋጋ 25% ማለትም የብር 333,155.00 (ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ አምስት ብር) እቃ እንዲያስገቡ አዝዟቸው በዚሁ ትእዘዝ መሰረት የእቃ ግዥ መጠየቂያ ቀርቦ በአመልካች መስሪያ ቤት በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ተፈርሞና ደብዳቤው ተሰጥቶ የብር 333,155.00 ዋጋ ያለው እቃ ተጠሪ ገዝተው ለአመልካች በማቅረብ ንብርቱን ለአመልካች በሞድል 19 ጣምራ በሆነው ገቢ አድርገው ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን የአመልካች ማስሪያ ቤት የእቃ ግዥ ንብረት አስተዳደር ክፍልም እቃውን ቆጥሮ ከተረከበ በኋላ ለአመልካች መስሪያ ቤት ፋይናንስ መመሪያ እቃውን ስለመረከቡ ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑንና በውሉ መሰረት ክፍያ አንዲፈፀምላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም አመልካች ፈቃደኛ ያልሆነ መሆኑን ዘርዝረው አመልካች ብር 333,155.00 ከተለያዩ ወጪና ኪሣራ እንዲከፍል ይወስንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስ ሕዳር ዐ2 ቀን 2001 ዓ.ም የተደገው ውል የራሱን ፍጻሜ ያገኘ በመሆኑ ለክሱ መሰረት ላሆን እንደማይገባ ተጠሪ የማይመጥን እቃ እንዲያስገባ የአመልካች ተቋም የበላይ ኃለፊ በየጽሑፍ ደብዳቤ ያላዘዙ መሆኑንና ተጠሪ ከበታች ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር የልታዘዘ ግዢ በሕገ ወጥ መንገድ በመነገድ ወደ ተቋሙ እንዲገባ መደረጉን ያለጨረታ ግዥ እንዲፈፀም የሚደረገውም በፋይናንስ ደንብ ቁጥር 17/1989 አንቀጽ 68(2(ሀ)) ላይ እንደሰፈረው የመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ በጣም አስቸኳይ በሆነና ቢዘገይ በመስሪያ ቤቱ ላይ ከባድ ችግር የሚፈጥርና የመስሪያ ቤቱ የስራ አፈፃፀም ላይ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን በማመን በጽሑፍ ስረጋገጥ ብቻ እንጂ በልላ ሰው ትእዛዝ ያጨረታ ግዥ መፈፀም እንደልለበት መደንገጉን ተቋሙ ለጨረታ ኮሚቴ ማቅረብ ሳያስፈልግ በግዥ ፈፃሚ አካላት የበላይ ኃላፊ ውሳኔ መግባት የሚችለው ለአንድ ጊዜ እስከ ብር 30,000.00 ብቻ መሆኑን የፍድራል መንግስት የግዥ አፈፃፀም መመሪያ እንደሚያዝና የንብረት አስተዳደር የእቃ ግዥ ጥያቄ አቅርቦም በዚሁ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ ግዥው የመንግስትን ግዥ መመሪያ በመጠበቅ እንዲፈፀም መታዘዙን ሆኖም አግባብነት የልለውን ጥቅም ለተጠሪ ለማስገኘት አስበውና አቅደው ከመንግስት ግዥ መመሪያ ውጨ አቶ ቶማስ ወልዱ ተጨማሪ ጽሑፍ ያስገባ በመሆኑ ስለእቃው አገባብ በግላቸው ከሚጠየቁ በስተቀር አመልካችን የሚያስጠይቅ ሕጋዊ ውል የልለ መሆኑን እቃው ያላገባብ የገባ መሆኑን አቶ ቶማስ ወልዱ ተረድተው ለስራ ወጪ እንደሆነ መግለፁንና ይህ ግለሰብ ከአቶ ብዙነህ ደሞዝ ጋር ሁነው ባጠፉት ጥፋት ለተጠሪ ከሚጠየቁ በስተቀር አመልካችን እንደማያስጠይቀው ግለሰቦቹ ወደ ክሱ እንዲገቡ ተደርጐ ክርክሩ እንዲመራና ከሕግ ውጪ ወደ ዩኒቨርሲቲው የገቡት እቃዎችም ብልሽት ቢደርስባቸዉ አመልካች ተጠያቂ ላሆን ስለማይችል ተጠሪ የመጋዝን ኪራይ ከፍለው እቃዎችን እንዲረከቡ እንዲደረግና እንዲሁም በቀድሞው ውል መሰረት ፈሳሽ ሳሙና ባለአራት ላትር በጀርካን ሆኖ ዋጋው ብር 60,000.00 ሆኖ እያለ ያለአግባብ ወደ ላትር በመለወጥ የአንድ ላትር ዋጋ ብር 60,000.00 በማስላት ከፍተኛ የመንግስት ገንዘብ ወጪ መሆኑን ተደርሶበት ያለ ሆኖ በድጋሚ በማጭበርበር ጥቅም ለማግኘት ክስ መመስረቱ ተገቢነት የልለው መሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ አመልካችን ለክሱ ኃላፊ በማድረግ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ገንዝበ ከዳኘነት ወጪ ከ7% የጠበቃ አበል ጋር ለተጠሪ እንዲከፍል ወስኗል። በዝሀ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለደቡብ ብሄር በሄረሰቦችና ሕዝቦች ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችሎት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ጉዳዩ ተመርምሮ በድምጽ ብልጫ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ በመጽናት ይግባኙ ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው፣፡ የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ከተጠሪ ጋራ በህዳር ዐ2 ቀን 2001 ዓ.ም ተደርጐ ከተፈፀመው ውል ውጪ የካቲት ዐ3 ቀን 2001 ዓ.ም በተጨማሪነት ተደረገ የተባለው ውል ከመንግስት ግዥ መመሪያ ውጪ ተጠሪ ከአመልካች ተቋም የበታች ሰራተኞች ጋር በመመሳጠር ያደረጉትና በሕጉ አግባብ ያልፀደቀ ሆኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች በአመልካችና በተጠሪ መካከል ውል አለ በማለት ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ አመልካች ለተጠሪ እንዲከፍል መወሰናቸው የላግባብ ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዚሀ ችሎት ላታይ የሚገባው መሆኑ ታምኖበት እንዲቀርብ ከተደረገ በኋላ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጐላቸው ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሁፍ እንዲከራከሩ የተደረገ ሲሆን የከርክራቸው መሰረታዊ ይዘትም በስር ፍርድ ቤት ካቀረቡት ክርክር ጋር ተመሳሳይነት ያለው መሆኑን ተመልከተናል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ስሆን ይህ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም በስር ፍርድ ቤት አመልካች ወደ ክርክሩ እንዲገቡ የጠየቃቸው ሰራተኞች ወደ ክርክሩ ሳይገቡ ውሳኔ መስጠቱ ስነ ስርዓታዊ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካችና ተጠሪ በሕጉ አግበብ ስለመደረጉ ክርክር ያልቀረበበትና ህዳር ዐ2 ቀን 2001 ዓ.ም ያደረጉትን የንጽህና እቃዎች ግዥ ውል ፈፃሚ እንዲያገኝ አድርጉው አሁን እያከራከራቸው ያለው የካቲት 03 ቀን 2001 ዓ.ም ተደረገ የተባለው የንጽህና እቃዎች ውል መሆኑን ይህ ውል በቀድሞው ውል ጠቅላላ ብር 634,685.00 ( ስድስት መቶ ሰላሳ አራት ሺህ ስድስት መቶ ሰማንያ አምስት ብር) ዋጋ 25% ማለትም የብር 333,155.00 (ሶስት መቶ ሰላሳ ሶስት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ አምስት ብር) እቃ እንዲያስገቡ ተጠሪ በአመልካች ታዝዘው በዚሁ ትእዛዝ መሰረት የእቃ መጠየቂያ ቀርቦ በአመልካች መስሪያ ቤት በሚመለከታቸው ኃላፊዎች ተፈርሞና ደብዳቤው ተሰጥቶ የብር 333,155.00 ዋጋ ያለው እቃ ተጠሪ ገዝተው ለአመልካች በማቅረብ ንብረቱን ለአመልባች በሞድል 19 ጣምራ በሆነው ገቢ አድርገው ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑንና የአመልካች መስሪያ ቤት የእቃ ግዥ ንብረት አስተዳደር ክፍልም እቃውን ቆጥሮ ከተረከበ በኋላ ለአመልካች መስሪያ ቤት ፋንናንስ መመሪያ እቃውን ስለመረከቡ ማረጋገጫ የሰጠ መሆኑን ተጠሪ ጠቅሰው የሚከራከሩ ቢሆነም ይህ ሁሉ የሆነው ግን የአመልካች መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ በመንግስት የግዥ መመሪያ መሰረት ተገቢውን ትእዛዝ አድራጐቱን ፈፀሙ ለተባሉት የበታች ሰራተኞች አስተላልፈው ስለመሆኑ ያለመረጋገጡን ነው። የበታች ፍርድ በቶች አመልካችን ለክሱ ተጠያቂ ያደረጉት እነዚህ ፍሬ ነገሮች መኖራቸውን አረጋጋጠው የአመልካች ሰራተኞች ከአመልካች ጋር ባላቸው የሥራ ግንኙነት መሰረት የደረሱበትን ኪሣራ ወይም ጉዳት አመልካች ላጠይቅ የሚችለው ሰራተኞቹን እንጂ ከተጠሪ ጋር መከራከሪያ ላያደርገው አይችልም በሚል ምክንያት መሆኑንም ውሳኔው የሚሳይ መሆኑን ተረድተናል።
በመሰረቱ አንድ ውል የሕግ ጥበቃ የሚያገኘው በሕጉ አግባብ የተቁቋመ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1731 ድንጋጌን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1678(ለ) ድንጋጌ ጋር በጣምራ ስናነብ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።
ውሉ ሕጉን በሚቃረን መልኩ የተቋቋመ መሆኑ እየተረጋገጠና ውሉን ተዋውሐል የተባለ ተዋዋይ ወገንም ውሉ ሕጋዊ አይደለም በማለት ክርክር እያቀረበ በውሉ እንዲገደድ ማድረግ የመዋዋል ነፃነትን መሰረታዊ መርህ የሚጥስና ፍላጐቱንና ፈቃዱን ያልሰጠ ሰው ግድታውን እንዲወጣ በማድረግ ልላኛው ተዋዋይ ነኝ የሚል ወገንም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም እንዲያገኝ የማድረግ ውጤት የሚስከትል ከመሆኑም በላይ በተለይ እንዲህ አይነቱን ግድታ እንዲወጣ ጥያቄ የቀረበው በመንግስ መስሪያ ቤት ከሆነ የመንግስት ግዥን ስርአት ለመስያዝ የወጣውን ሕግ ውጤት አልባ የሚያደርግ መሆኑ የሚታመን ነው። አንድ የመንግስት ሰራተኛ በሕጉ የተሰጠው ኃላፊነትና ተግባር እያለ ከዚሁ ኃላፊነትና ተግባር አድማስ ውጪ ባደረገው ግንኙነት በተቋሙ ግድታ የሚያስከትል ተግባር ፈጽሞ ከተገኘም ኃላፊነቱን ላወስድ የሚገባው እንዲ አይነቱን ተግባር ያከነወነው ሰራተኛ በግሉ ከሚሆን በስተቀር ተቋሙ ላሆን የሚችልበት አግባብ የለም። አንድ የመንግስት መስሪያ ቤተ ለሰራተኛው ተግባር ኃላፊነት ላህረው የሚችለው በሰራተኛው የተፈፀመው ጥፋት የሥራ ጥፋት ሆኖ ሲገኝ ሲሆን አንድ ጥፋት የስራ ጥፋት ነው ተብሎ የሚወሰደውም ጥፋት አድራጊው በዚህ ጥፋት ላይ የወደቀው በቅን ልቡና በስልጣኑና ለስራው ክፍል መልካም ያደረገ መስሎት የፈፀመው መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑና ከዚሀ ውጪ በሆነ በማናቸውም ልላ ጉዳይ ግን ጥፋቱ እንደግል ጥፋት ሁኖ እንማሚቆጠር የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2126 እና 2127(1) እና (2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያስረዳሉ። ጥፋቱ በቅን ልቦና ያልተፈፀመ መሆኑም በተቃራኒ ማስረጃ ላረጋገጥ እንደሚችልና ተቃራኒ ማስረጃ ካልቀረበ ግን የራተኛው አሰራር በቅን ልቦና እንደተሰራ በሕጉ ግምት እንደሚወሰድበት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2127/3/ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ ያሳያል። ከላይ የተመለከቱት የሕግ ጉዳዮች በፍርድ ተገቢውን አልባት የሚሰጥባቸው ደግሞ በክርክሩ የግድ ተካፋይ የሆነው ወገኖች በከርክሩ እንዲሳተፉ ተደርጐ ጉዳዩ በተገቢው ማስረጃ በጥንያቄ ሲጣራ ነው።
በመሰረቱ በአንድ ጉዳይ ላይ ክስ ሲቀርብና የክሱም ምክንያት የብዙ ሰዎችን መብትና ጥቅም የሚነካ ወይም ኃላፊነት ያለበትና ግድታውን ላወጣ የሚገባው የትኛው ወገን መለየት የግድ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከእነሱ አንዱ ወይም ከፊሉ ክስ በቀረበ ጊዜ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በጉዳዩ ላይ በሚሰጠው ውሳኔ ወይም ፍርድ መብትና ጥቅም የሚነካ ወይም ግድታው በሕጉ አግባብ እንዲወጣ ላደረግ የሚችል ሲሆን በክሱ ውስጥ ተካፋይ ያልሆኑ ሰዎች የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
39/1/ እና 40/2/ ድንጋጌዎች ይዘት ያስገነዝባል። በሕጉ አግባብ ተጠያቂ የሚሆን ወገንም የክርክሩ ተሳታፊ እንዲሆን ማድረግ የሚመነጨው ከዚህ አግባብ ስለመሆኑ ተጠቃሽ ድንጋጌዎችን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 36/5/ ጋር ተጣምረው ሲነበቡ የሚያገነዝቡን ጉዳይ ነው። እነዚህ ወገኖች ተካፋይ ሳይሆነ የሚሰጠው ውሳኔ ወይም ፍርድ ውጠት የማይኖረው ስለመሆኑም የተጠቃሽ ድንጋጌዎች መንፈስ ያሰረዳል። በመሆኑም በክሱ መግባት ያለበት ተከሳሽ የሆነ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የክርክሩ ተካፋይ እንዲሆንና በቀረበው ክስና መልስ መከላከያውን እንዲያቀርብ ላያዘው የግድ የሚል ስለመሆኑ ሥነ ሥርዓቱ የሳያል። በክርክሩ ውስጥ የግድ ተካፋይ መሆን የሚገባቹው ወገኖች ማለት ደግሞ ክስ በቀረበበት ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ ጥቅማቸው መብታቸው ወይም ግድታቸው የሚነካ፡ በክርክሩ ውስጥ ተካፋይ ያልሆኑ ሰዎች ስለመኖቸውም ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 40 ድንጋጌ ይዘት የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። ድንጋጌው ክርክሮች ወደፊት እንዳይነሱ በማድረግ የወጪ ጊዜና ጉልበትን ብክነት በመቆጠብ አፋጣኝ ዳኝነት የመስጠትን የስነ ስርዓት ሕጉን መሰረታዊ አላማ ያገናዘበ ነው ተብሎ ይታሳባል።
ወደተያዙው ጉዳይ ስንመለስም ተጠሪ ውሉ የተገባው በመንግስት ግዥ መመሪያ ቁጥር 17/1989 አንቀጽ 68(2)(ሀ)) ድንጋጌ መሰረት በአመልካች መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ የጽሑፍ ትእዛዝ የተላለፈ ትእዛዝ መኖር ያለመኖሩን በተመለከተ ከአመልካች ሰራተኞች ጋር ተደረገ የሚሉት የቀድሞ ውልን መነሻ በማድረግ ሕጋዊ ስርዓትን የተከተለ ስምምነት አለ የሚሉ ሲሆን በዚህ ረገድ በአመልካች በኩል የቀረበው ክርክር ደግሞ ውሉ ላይ መጻፃፎች እንዲኖሩ ያደረጉት ሰራተኞች ከተጠሪ ጋር ተመሳጥረው ያደረጉት ተግባር እንጂ ሕጋዊ አይደለም በማለት በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት በመጥቀስ ተከራክሯል። አመልካች የተቋሙ ሰራተኞች ተግባሩን የፈፀሙት ከተጠሪ ጋር ተመሳጥረው ነው በማለት የሚያቀርበው ክርክር ሰራተኞቹ ወደ ክርክሩ እንዳገቡ ተደርጐ የግራ ቀኙ ማስረጃ ተሰምቶ ጉዳዩ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2126 እና 2127 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ እንዲሁም ክርክሩ በተነሳበት ጊዜ ተፈፅሚነት የነበረውን የመንግስት የግዥ መመሪያ ድንጋጌዎች ጋር ተዛመዶ ዳኝነት የማሰጥበት እንጂ አመልካች ከወዱሁ በሰራተኞቹ የግል ጥፋትም ቢሆንም እንኳን ሃላፊነቱ የአመልካች ነው በማለት ውሳኔ መስጠቱ ሕጋዊ አካሄዱን በተከተለ የተደረሰ መደምደሚያ አይደለም። የአመልካች ሰራተኞች ተግባሩን የፈፀሙት ከቅን ልቦና በመነጨ ሁኔታ ነው? ወይስ ከዚሀ ውጪ ነው? ተጠሪስ የእቃዎቹን አቅርቦት ለአመልካች የፈፀሙት ከሰራተኞቹን የመመሳጠር ተግባር ፈጽመው ነው ወይስ ሕጋዊ አንድ ጠንቃቃ ነጋድ ላያደርገው የሚገባውን ጥንቃቄ አድርገው የንገድ ስራው የግድ የሚለውን አካሄድ ተከትለው ነው? የእቃቹ አቅርቦት ከተጠሪ ጋር የነበረውን የቀደመ ግንኙነት መሰረት አድርጐ እንዲከናወን የተጠሪ ተቋም የበላይ ኃላፊ ለሰራተኞቹ በሕጉ አግባባ ያሰተላለፉት እትዛዝ አለ ወይስ የለም? የተላለፈ ትእዛዝ አለ ከተባለም ሰራተኞቹስ ስራውን ያከናወኑት በበላይ ኃላፊ ትእዛዝ መሰረት መሆን ያለመሆኑ ለትክክለኛ ፍርድ አሰጣጥ ተገቢውን ማጣራት ማድረግን የሚጠይቁ ሲሆን ይህ ሁሉ መከናወን ያለበት ግን ሰራተኞቹን የክርክሩ ተሳታፊ በማድረግ የመደመጥ መብታቸውን በማስከበር እና የፍታ ብሄር ስነ ሥርዓት ሕጉን አይነተኛ አላማ በማገናዘብ ልላ ክርክር ወደፊት እንዳይነሳ የሚያደርግ የክርክር አመራርት ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ ነው። ሲጠቃለልም የስር ፍርድ ቤቶች ተገቢ ባልሆነ የክርክር ደረጃ አመልካች ለሰራተኞቹ ተግባር ጭምር ኃላፊነቱን ላወስድ ይገባል በሚል ምክንያት የአመልካች ሰራተኞች የሆነት አቶ ቶማስ ወልድ አቶ ብዙነህ ደመወዝ የተባሉት ግለሰቦች ወደ ክርክሩ ይግበልኝ የሚለውን የአመልች ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ነው ለማለት አልተቻለም ። ስለሆነም እነዚሀ ግለሰች ወደ ክርክር ሳይገቡ የተሰጠው ውሳኔ ሥነ ሥርዓታዊ ባለመሆኑ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ ሆኖ አለነም። በዚሀም ምከንያት በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ላታረም የሚገባው ነው።
በጋሞ አከባቢ ከተፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ነሐሴ 14 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በደበ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት ዐ3 ቀን 2004 ዓ.ም በድምጽ ብልጫ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ሙሉ በሙሉ ተሽሯል።
የአመልካች ተቋም ሰራተኞች የሆነትና ከእቃው አቅርቦት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ነበራቸው የተባሉ አቶ ቶማስ ወልድና አቶ ብዚነህ ደመወዝ በክርክሩ ውስጥ የግድ ተካፋይ መሆን ያለባቸው መገኖች በመሆኑ ለቀረበው ክስና መልስ መከላከያቸውን እንዲያቀርቡ የጋሞ አከባቢ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰጥቶ ጉዳዩን እንደገና በመመልከት ተገቢውን ውሣኔ እንዲሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.