No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 22 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ ሙስጠፋ አሀመድ አመልካች፡- ወ/ሮ እታፈራሁ ፀጋዬ ቀረቡ ተጠራዎች፡-1. ወ/ሮ መሰረት ግርማ ወኪል ሁለተኛ ተጠሪ ቀረቡ 2. ወ/ሮ ፍሬህይወት ግርማ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሳስ 5 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ መስከረም 21 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበችውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዳዩ የውርስ ሀብትና የጋብቻ ወቅት የተፈራ የጋራ ንብረት ክፍያ ጥያቄ የሚመለከት ነው። በስር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪዎች ለስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት የክስ ማመልከቻ ነው። ተጠሪዎች ወላጅ አባታችን አቶ ግርማ ብሩ መጋቢት 24 ቀን 1988 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። እኛም ወራሽነታችን በፍርድ በማረጋገጥ ውርስ እንዲጣራልን አድርገናል። የውርስ አጣሪው ሪፖርት በመዝገብ ህዳር 15 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፀድቋል። አባታችን በጉለል ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ቁጥሩ 076/ሀ/ የሆነ ቤት አላቸው። ተከሳሽ /አመልካች/ ቤቱን ይዛ ግማሹን እያከራየች ትገኛለች። ስለሆነም ተከሳሽ ቤቱን እንዲለቁና የኪራይ ገንዘብ /ሃያ ሺህ አራት መቶ ብር/ እንዲከፍሉ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት በተከሳሽነት ቀርበው ከሳሾች ክስ ያቀረቡበት የውርስ ንብረት ጥያቄ በአስር ዓመት የይርግ ጊዜ ገደብ ቀሪ ይሆናል። የቤት ቁጥር 076 የሆነው ቤት ባለቤቴ /የከሳሾች አውራሽ/ ከሞተ በኋላ በእርጅና ምክንያት በመፍረሱ በአዲስ መልክ ሃምሳ ሁለት ቆርቆሮ ጣራውን በአዲስ መልክ ሰርቼ የምጠቀምበት የግል ንብረቴ ነው በማለት ተከራክራለች
የስር ፍርድ ቤት በውርስ ማጣራቱ ቤቱ የአቶ ግርማ ብሩ መሆኑ ተረጋግጧል። የቤቱ ስመ ሀብትም በከሳሾች አውራሽ በአቶ ግርማ ብሩ ስም ነው። ስለዚህ ተከሳሽ በጉለል ክፍለ ከተማ ቀበል 11 ወረዳ 09 ቁጥሩ 076/ሀ/ የሆነውን ቤት ለከሳሶች ያስረክቡ የቤቱን /አስር ሺህ ሁለት መቶ ብር/ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፐርሰንት ወለድ ጋር ተከሳሽ ለከሳሾች ይክፍሉ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርባለች የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ቤቱ የመልስ ሰጭዎች /ተጠሪዎች/ አውራሽ መሆኑ በውርስ ማጣራት ሂደት ተረጋግጧል። የውርስ አጣሪው ሪፖርት በፍርድ ቤት ፀድቋል። ስለዚህ የስር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው በማለት አፅንቶታል።
አመልካች መስከረም 28 ቀን 2004 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ከተጠሪዎች አውራሽና ወላጅ አባት ጋር ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ ተጋብተን ስንኖር ሁለተኛ ተጠሪን ወልጃለሁ አመልካች የሟች አቶ ግርማ ብሩ ሚስት መሆኔና ተጠሪዎች ደግሞ የሟች ልጆችና ወራሾች መሆናቸው በመዝገብ ቁጥር 376/88 ጥር 6 ቀን 1989 ዓ.ም በፍርድ ቤት ውሣኔ ተረጋግጧል። ተጠሪዎች ወራሽነታቸውን ካረጋገጡ ከአስራ ሶስት ዓመት በኋላ በ2002 ዓ.ም ውርስ እንዲጣራላቸው ጠይቀው እኔም ይህንን ጥያቄ በመቃወም እስከ ፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችሎት ተከራክሬ የውርስ ማጣራቱ የአንቺን መብት የሚነካ አይደለም ተብሎ ውሣኔ ተሰጥቷል። አመልካች የአከራካሪው ቤት ግማሽ ባለንብረት ስለመሆኔ ከሟች ባለቤቴ ጋር የተሰጠን የጋራ የቦታ ማረጋገጫ ሰነድ የሚያሳይ ሲሆን ንብረቱም በጋብቻ ወቅት የተፈራ የጋራ ሀብት ነው። ስለዚህ ተጠሪዎች የንብረት ታስረክበኝ ጥያቄ እያቀረቡ የጋራ ባለሀብትነት መብቴን በማለፍ ንብረቱን ለተጠሪዎች እንዳስረክብ የተሰጠው ውሣኔ የተሻሻለውን የቤተሰብ ሕግ ድንጋጌዎችና የፍታብሕር ሕግ ቁጥር 1845 የሚጥስ በመሆኑ በሰበር ታይቶ እንዲታረምልኝ በማለት አመልክታለች።
ተጠሪዎች በበኩላቸው ታህሳስ 2 ቀን 2005 ዓ.ም በሰጡት መልስ አመልካች የውርስ አጣሪው ቤቱ የሟች ግርማ ብሩ የግል ንብረት ነው በማለት የቀረበውን ሪፖርት በማፅደቅ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመቃወም እስከ ፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ድረስ ተከራክረው ክርክራቸው ውድቅ ተደርጎባቸዋል። ይህ ከሆነ ቤቱ የጋራ ሀብት ነው በማለት የምታቀርበው የሕግ መሰረት የለውም። ቤቱም በጋብቻ የተፈራ ሣይሆን ሟች ከአባቱ በስጦታ ያገኘው ንብረት ነው። ጉዳዩ ክርክር ሲደረግበት የቆየ በመሆኑ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች ታህሳስ 22 ቀን 2004 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርባለች።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን የክስ መቃወሚያና የፍሬ ጉዳይ ክርክር ውድቅ በማድረግ ቤቱን ለተጠሪዎች እንድታስረክብ የሰጡት ውሣኔ ተገቢነት ያለው መሆኑን አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን ተጠሪዎች የሟች አቶ ግርማ ብሩ ውርስ እንዲጣራላቸው ለፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ አመልካች አቅርበው የነበረውን መቃወሚያና ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ብይን ይዘት መመርመር ያስፈልጋል። በዚህ መዝገብ አመልካች የቤት ቁጥር 076 የግል ቤቴ ነው። ውርስ እንዲጣራ የቀረበው ጥያቄም በአስር ዓመት ይርጋ ቀሪ ነው የሚል የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱ ተጠሪዎች ያቀረቡት የውርስ ይጣራልን ጥያቄ ነው።
ውርስ ሲጣራ የውርስ አጣሪው ወራሾች ኑዛዜ፣ የሟች ዕዳና ንብረት መለየት እንጂ በሶስተኛ ወገኖች የመፋለም መብትን የሚያሳጣ ውሣኔ መስጠት አይችልም የውርስ አጣሪው ስራ ውርስ ማጣራት እንጂ የአሁኑ የመቃወም አመልካች ንብረት ወይም ቤት አይደለም ብሎ በዚህ መዝገብ በቤት ቁጥር 076 ላይ የተሰጠ ውሣኔ የለም” ስለዚህ በውርስ አጣሪ ሪፖርት ላይ የመቃወም አመልካች መብት ላነካ የሚችል ውሣኔ ያልተሰጠ በመሆኑ የመቃወም አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ አልተቀበልነውም በማለት ጥር 20 ቀን 2002 ዓ.ም ትዕዛዝ ሰጥቷል። አመልካች ይህንን ትዕዛዝ በመቃወም ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበው የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ ሰኔ 9 ቀን 2003 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው፣ በሰበር ችሎት የሚታይ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም ተብሎ በሰበር መዝገብ ታህሳስ 9 ቀን 2004 ዓ.ም ሶስት ዳኞች በተሰየሙበት የሰበር ማጣሪያ ችሎት ትዕዛዝ ተሰጥቶበታል።
No topics extracted.