No summary available.
ሰኔ 21 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ገ/ማሪም ገ/መድህን ቀረቡ ተጠሪ፡- ጣዕመ ወ/ስላሴ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የቤት ይለቀቅልኝ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ጉዳዩ የተጀመረው በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። ክርክሩ የተጀመረው ተጠሪ በአመልካች እና በስር 1ኛ ተከሳሽ ሻለቃ ኃይለማርያም ኃ/ስላሴ ላይ የካቲት 17 ቀን 2001 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ መነሻ ነው። የተጠሪ ክስ ይዘትም በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 20 ቀበል 19 ክልል ቁጥር 513 የሆነውና የካርታ በሚል የሚታወቅ ቤት ባለቤት መሆናቸውን ለ1ኛ ተከሳሽ ቤቱን እንዲያስተዳድሩ እንዲያከራዩ በሚል የውክልና ስልጣን የተሰጣቸው ቢሆንም ቤቱን ወደ ልላ ሰው የማስተላለፍና ስልጣን እንዳልተሰጣቸው 1ኛ ተከሳሽ የተሰጣቸውን ስልጣን ሽፋን በማድረግ ሐምል 10 ቀን 1992 ዓ/ም በተፃፈ ውል አማካኝነት ቤቱን ለአሁኑ አመልካች በብር 148,000.00/አንድ መቶ አርባ ስምንት ሺህ ብር/ የሸጡ መሆናቸውን አሁኑ አመልካች በዚህ የመሸጥ የመለወጥና የማስተላለፍ ሥልጣን በማያካትተው የውክልና ሰነድ ወይም ህገ ወጥ ሰነድ አማካኝነት ቤቱን መግዛታቸውን ገልፀው የሽያጭ ውል ሕገ ወጥ ነው ተብሎ እንዲፈርስ እንዲሁም ውሉን ተከትሎ የተከናወኑት ተግባራት ዋጋ አልባ ናቸው እንዲባሉ ቤቱን የአሁን አመልካች ለቀው እንዲያስረክቧቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁን አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክሮችን አቅርበዋል። አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረቡት ፍርድ ቤቱ ጉዳን ለማየት ሚያስችለው ስልጣን የልለው መሆኑን ተጠሪ የክስ ምክንያት የልላቸውና ክሱን ለማቅረብም መብት ወይም ጥቅም የልላቸው መሆኑን የተጠሪ የዳኝነት ጥያቄ በሁለት ዓመት ይርጋ የሚታገድ መሆኑን ሚገልፅ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ ካርታው የተሰረዘ መሆኑን በሕጉ አግባብ የተደረገ ቤት ሽያጭ ውል ላፈርስ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያትዬልለ መሆኑንና ተጠሪ የውጭ ሀገር ዜጋ በመሆናቸው የማይንቀሳቀስ ንብረት በኢትዮጵያ ውስጥ ለመያዝ ህጋዊ መብት የልላቸው መሆኑንና ልሎች ነጥቦችን ዘርዝረው ተከራክረዋል።
ጉዳዩ በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፍድራል መጀመሪ ደረጃ ፍርድ ቤትም በመጀመሪ ደረጃ መቃወሚያነት ተጠሪ ያቀረቧቸውን ነጥቦች ሙሉ በመሉ ውድቅ አድርጎ አልፎ ፍሬ ጉዳዩን መርምሮ የቤት ሽያጩ ውሉ ሕጋዊ አይደለም በሚል ምክንያት ፈራሽ ነው በማለት ቤቱን ተጠሪ ላረከቡ ይገባል ሲል ወስኗል።
የአሁኑ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኃላ የተጠሪ የዳኝነት ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1808 መሰረት ውል እንዲፈርስ ጥያቄ የሚቀርብባቸው ውሎች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1810 መሰረት በሁለት ዓመት ይርጋ የሚታገዱ ናቸው። ተጠሪ የካቲት 17 ቀን 2001 ዓ.ም ክሱን የመሰረቱት ሐምል 14 ቀን 1992 ዓ/ም የተደረገው የሽያጭ ውል እንዲፈርስላቸው በመሆኑና ጊዜ ሲሰላም የሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ ያለፈበት በመሆኑ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። ከዚህም በኃላ ተጠሪ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ችሎት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኃላ ችሎቱ ጉዳዩ በይርጋ የታገደ አይደለም በማለት የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ ሽሮ በፍሬ ጉዳዩ ላይ ውሳኔ እንዲሰጥበት ሲል ጉዳዩን ለፍድራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት መልሶ ልኮለታል። ጉዳዩ የተመለሰለት የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን የፍሬ ጉዳይ ክርክርን መርምሮ የስር ፍርድ ቤት ውሉ ፈራሽ ነው ቤቱን አመልካች ለተጠሪ ላያስረክቡ ይገባል በማለት የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አፅንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች በመንግስት መመሪያ መሰረት በሚመለከተው አካል ፊት ቀርቦ ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ፈራሽ ነው ተብሎ መወሰኑ በጊዜው የወጣው የመንግስት መመሪያ የውሉን ይዘትና ለጉዳዩ መቅረብ ያለባቸውን ማስረጃዎችን አይነትና የአቀራረባቸውን ስርዓት እንዲሁም ማስረጃዎቹን ይዘት ያላገናዘበና በጉዳዩ ላይ የክርክሩ የግድ ተሳታፊ ላሆን ይገባው ነበረውን ወገን ወደ ክርክሩ እንዲገባ ሳይደረግ ክረክሩ የተመራበት ለተጠሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ግንቦት 07 ቀን 2001 ዓ.ም የወጣው መመሪያ ያስቀመጠው መፍትሕ መሰረት ያላደረገ መሆኑን ዘርዝረው የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ተሸሮ የቤትሽያጭ ውሉ ላፈርስ አይገባም ተብሎ እንዲወሰንላቸው ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
No topics extracted.
አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችሎቱ እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው በሰጡት መልስም የቤት ሽያጭ ውሉ በመንግስት መመሪያ መሰረት የተደረገ ስለመሆኑ ያልተረጋገጠና በመንግስት መመሪያ ተደርጓል ቢባል አንኳን መመሪያው ሕጉን ለማውጣት ስልጣን ባለው አካል የወጣ ባለመሆኑ የህግ አቋም የልለውና የውክልና ሕግ መርህዎችን የሚፃረር በመሆኑ ተቀባይነት ላሰጠው የማየይገባ መሆኑን ዘርዝረውና የአመልካች መከራከሪያ ነጥቦች ድግግሞሽ ያለባቸው ስለመሆኑ ገልፀውና የህግ መሰረት የልላቸው መሆኑን ያሳያሉ የሚሐቸውን ምክንያቶች ጠቅሰው በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ላፀና ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካች በበኩላቸው የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር መልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከለይ የተመለከተው ሲሆን በበኩላችንም አቤቱታው ለሰበር ችሎቱ ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ መርምረናል። ጉዳዩ ለሰበር ሲቀርብ የተያዘው ጭብጥ አከራካሪው ቤት ላሸጥ የቻለው የውክልና ሰነዱንም መሰረት አድርጎ ሳይሆን በምንግስት በወጣ መመሪያ ነው እየተባለና ይህንንም መመሪያ አመልካች ከመልሳቸው ጋር እንደማስረጃ ሳያቀርቡ በመቅረታቸው ብቻ ይሄ ታልፎ የሽያጭ ውሉ ተሰረዞ አመልካች ቤቱን ለተጠሪ መልሰው ያስረክቡ ተብሎ መወሰኑ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ነው።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ሀምል 10 ቀን 1992 ዓ/ም ከተጠሪ ወኪል ከተባሉት ከሻለቃ ሀብተማሪያም ሀብተስላሴ ጋር ያደረጉት መኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል ስምምነት በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት የተደረገ መሆኑን መስከረም 25 ቀን 1993 የተደረገው ውልም በተመሳሳይ አካል ፊት የተደረገ መሆኑን የክልል መስተዳደር ጽ/ቤት በቁ/አመ/አ.አ 73 በ18/8/1992 ዓ/ም ለውልና ማስረጃ ጽ/ቤት በፃፈው ደብዳቤ ኤርትራዊያን ከሀገር ሲወጡ ንብረታቸውን የመጠበቅ የማስተዳደር የመሸጥ የመሳሰሉት የውክልና ሰነዶች/ማስረጃዎች/ ያሐቸው ሰዎች መሸጥ መለወጥ ይችላሉ የሚል ይዘት ያለው መሆኑን ተጠሪ ኤርትራዊ መሆናቸውና ለወኪላቸው ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችል ስልጣን ያልሰጡ መሆኑን የተረጋገጠ መሆኑን በቁጥር ቀ2/ጠ67/61/92 በቀን 10/10/92 በተፃፈ ደብዳቤ ተጠሪ በአከራካሩው ቤት ጥር 13 ቀን 1974 ዓ/ም የወሰዱት የካርታ ለተወካያቸው ሳይሰጡ ከሀገር የወቱ በመሆናቸው ከሚመለከተው አካል ተረጋግጦ በመቅረቡ ምክንያት ተጠሪ የወሰዱት ካርታ እጃቸው ላይ እንዳለ በማምከን ለአሁኑ አመልካች ሆነ አዲስ ካርታ ሰኔ 09 ቀን 1992 ዓ/ም የተሰጣቸው መሆኑን ከሚመለከተው አካል የተፃፈ የሰነድ ማስረጃ መቅረቡን ሐምል 10 ቀን 1992 ዓ/ም በውልና ማስረጃ በተደረገው የስምምነት ሰነድ ይዘቱ ሲታይ የውሉን አላማ የኤርትራዊያን ቤት ወኪሎች የሆኑት ወኪል የሆኑበትን ቤት ሽጠው ገንዘቡን በዝግ ሂሳብ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ በክልል 14 ቢሮ ቁጥር 20 የተጠሪ ወኪል ተጠርተው በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ቤቱን ለመሸጥ መሆኑንና ወኪሉ የወኪል አድራጊያቸው ባለቤት መጥተው ቢከራከሩ ወይም ያገባኛል ቢሉ ሁሉንም ነገር በኃላፊነት የሚመልሱ መሆኑን በመግለፅ ፊርማቸውን ማስቀመጣቸውንና የቤቱን ዋጋ በወቅቱ የተከፈለውን የገንዘብ መጠንና ቀሪው ገንዘብ የሚከፈልበትን ሁኔታ እንዲሁም ልሎች የገዥንና ሻጭን መብትና ግድታዎችን በዝርዝር የያዘ መሆኑን የሚያስገነዝብ መሆኑን ነው።
እንግዲህ ከላይ የተገለጹት ነጥቦች በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡ ሲሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሽያጭ ውሉ ላፈርስ ይገባል በማለት ላወስኑ የቻሉት አመልካች ቤቱ የተሸጠው በመንግስት ትዕዛዝና መመሪያ መሆኑን ገልፀው ቢከራከሩም ለጉዳዩ ለማስረጃነት የቀረቡት የውል ሰነዶች አያሳም እንዲያውም ወኪሉ ቤቱ የእኔ ነው ባይ ወይም ተከራካሪ ወገን ቢመጣ የመመለስ ኃላፊነቱ የውል ሰጪው ነው በሚል የስምምነት ግድታ የተቀመጠ መሆኑ ቤቱ የተሸጠው በመንግስት ትዕዛዝ ሳይሆን የተጠሪ ወኪል በራሳቸው ፈቃድ ተነሳስተው መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው የሚል ምክንያት በመያዝ ነው። ይሁን እንጂ ሐምል 10 ቀን 1992 ዓ/ም የተደረገው ውል እንደከፍተኛው ፍርድ ቤት ድምዳሜ በመንደር የተደረገ ሳይሆን በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት የተደረገ ከመሆኑም በላይ እንደተጠቀሰው ይዘቱ ወኪሉ በክልል 14 ቢሮ ቁጥር 20 ተጠርተው በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት ሽያጩን ያከናወኑ መሆኑን በግፅ የሚያሳይ ነው። ይህ የሰነዱ ይዘት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2005 እና አዋጅ ቁጥር 334/1995 አንቀፅ 2(1) ፤ 4(1) እና 5(1(ሀ) መሰረት ተቀባይነት የማያገኝበት ሕጋዊ ምክንያት የልለ ሲሆን ውሉን ያረጋገጠው አካልም ኤርትራዊያን ከሀገር ሲወጡ ቤት ለመሸጥ የሚያስችል ስልጣን ለተወካቻቸው ባይሰጡም ተወካዩቹ የማስተዳደር መጠበቅና የመሳሰሉ የውክልና ሰነዶችን ቢይዙም ንብረቶቹን መሸጥ መለወጥ የሚችሉ መሆኑን ከአዲስ አበባ መስተዳደር ሚያዝያ 18 ቀን 1992 ዓ/ም የተላለፉትን መመሪያ መሰረት አድርጎ ስምምነቱን ማረጋገጡን ሁለቱም ሰነዶች አንድ ላይ ሲታ የሚያስገነዝቡን ጉዳይ ነው። ይህ ሁኔታ ሲታይም የተጠሪ ወኪል ተግባሩን የፈፀሙት ቤቱን ለመሸጥ የሚያስችላቸው ሕጋዊ ውክልና አለኝ በሚል ሳይሆን በጊዜው በነበረው ነባራዊና አስገዳጅ ሁኔታ ውስጥ ሁነው መሆኑንና አመልካች ደግሞ ይህንኑ በማየትና በመገንዘብ ስምምነቱ ውስጥ የገቡ መሆኑን የሚያስረዳ ነው። የተጠሪ ነባር የባለቤትነት ካርታ በሚመለከተው አካል መሰረዙ ከላይ ከተጠቀሰው የክልል 14 መስተዳድር መመሪያና ውሉ በውልና ማስረጃ ፊት ቀርቦ ከመደረጉና ሕጋዊ ነው ተብሎ ከመረጋጡ ጋር ተዳምሮ ሲታይ አመልካች ተገቢውን ጥንቃቄ አድርገው ግዢውን የፈፀሙ መሆኑን የሚያሳይ ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች የመንግስት መመሪያ ስለመኖሩ አመልካች ማስረጃ አላቀረቡም በማለት የያዙት ድምዳሜ ከላይ የተጠቀሰውን ውል ይዘት ያላገናዘበ ከመሆኑም በላይ ለውሳኔ አሰጣጥ አስፈላጊ ከሆነም በራሳቸው አነሳሽነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 145(1) እና 345(1)(ለ) ድንጋጌዎች አግባብ ማስቀረብ ይችሉ የነበረ ጉዳይ ነው። ከሁሉም በላይ ግን የውሉ ሰነድ ይዘት በግልፅ ሽያጩ በመንግስት አስተዳደር አካል ትዕዛዝ የተከናወነ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ ይሄው የሰነዱ ይዘት ለጉዳዩ ተቀባይነት ያለውና ተግባሩ በአስተዳደር አካሉ ትዕዛዝና መመሪያ የተፈፀመ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው። ስለሆነም የበታች ፍ/ቤቶች ሽያጩ በመንግስት አስተዳደር አካል ትዕዛዝ ወይም መመሪያ መሰረት የተከናወነ መሆኑ የሚያሳይ ማስረጃ አልቀረበም በማለት የደረሱበት ድምዳሜ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሐምል 10ቀን 1992 ዓ.ም. እና መስከረም 25 ቀን 1993 ዓ.ም. የተደረጉትን ውሎችን ይዘትና መንፈሳቸውን ለውሎች መደረግ ከሚመለከተው አካል ለዚሁ ውል አረጋጋጭ አካል ሲተላለፉ የነበሩትን ደብዳቤዎችን ይዘት ያላገናዘበ ነው። በመሆኑም የተጠሪ ወኪል ውክልናውን መሰረት አድርገው ሽጠዋል በማለት በአመልካች ክርክር ባልቀረበበትና በወቅቱ በነበረው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ምክንያት በመንግስት አስተዳደር አካል በተወሰደው እርምጃ መሰረት ወደ ግብይት የገቡት ዜጎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ የፈፀሙት ተግባር መሆኑ እስከታወቀ ድረስ ጉዳዩ በወቅቱ ከነበረው ልዩ ሁኔታ ታይቶ በራሱ ዳኝነት ከሚያገኝ በስተቀር የውክልና ህግ መርህዎች መሰረት ተደርገው ተግባራቸው ህጋዊ ጥበቃ የሚነፈግበት አግባብ ላኖር አይገባም። በወቅቱ የተወሰደውን እርምጃ በመገንዘብም በወቅቱ የተከናወኑትን ተግባራትና መፍትሕ ለመስጠት የሚያስችል መመሪያ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ግንቦት 7 ቀን 2001 ዓ/ም ወጥቶ ስራ ላይ መዋሉም መንግስት በማመን የግዥ ተግባር ያከናወኑትን ዜጎች ዋስትና ለመስጠት ነው ተብሎም ይታሰባል። በዚህ መመሪያ መሰረት ከሀገር እንዲወጡ ተደርገው የነበሩ ኤርትራዊያ በመንግስት አስተዳደር ንብረታቸው ተሽጦ በዝግ ባንክ አካውንት የተቀመጠ ገንዘብ ካላቸው ማስረጃ ሲያቀርቡ ካለወለድ ገንዘባቸውን በብር እንዲያገኙ እንደሚደረግ በአንቀፅ 4(2) ስር በግልፅ ሰፍሯል። በመሆኑም ተጠሪ ከሀገር ወጥተው የነበሩ ኤርትራዊ መሆናቸውንና አመልካች ለቤቱ የከፈሉት ገንዘብ ብር 148,000.00(አንድ መቶ አርባ ስምንት ሺህ) በኢትጵያ ንግድ ባንክ ፊኒፊኔ ቅርንጫፍ በዝግ ሂሳብ መቀመጡና የባንክ ደብተሩም በአዲስ አበባ መስተዳደር መቀመጡን አመልካች ጠቅሰው ላቀረቡት ክርክር በተጠሪ በኩል ማስተባበያ ክርክር ያልቀረበበትና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሐ/ቁጥር 234(1(ሰ)፤235 እና 83 ድንጋዎች እንደታመነ የሚቆጠር በመሆኑ ተጠሪ ያላቸው መፍትሕ ይህንኑ ገንዘብ መቀበል እንጂ የቤት ሽያጩ እንዲፈርስ ማስደረግና ቤቱን የመረከብ መብት አይደለም። ሲጠቃለልም አመልካች በመንግስት አስተዳደር አካል በተላለፈው መመሪያ መሰረት ተገቢውን ጥንቃቄ አድርገው የገዙትና ለበርካታ አመታት ሲጠቀሙበት የነበረውን ቤት ውሉ ፈርሶ ለተጠሪ ላያስረክቡ የሚገደዱበት ሕጋዊ ምክንያት ስላላገኘን የበታች ፍርድ ቤቶች የክርክሩን ልዩ ባህርይና በጉዳዩ ላይ የቀረቡትን የውል ሰነዶችን ይዘታቸውን በአግባቡ ሳይመለከቱ ለጉዳ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት የልለለውን ውክልና ሕገ መርህዎችንና በአመልካች ላይ መመሪያውን ለማስረጃነት ማቅረብ ግድታን ሕጉ ባልጣለበት አግባብ የሽያጭ ውሉ ፈራሽ ነው በማለት መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሁኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ህዳር 04 ቀን 2002 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ነሐሴ 18 ቀን 2004 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሸሯል።
አከራካሪው ቤት ላይ የተደረገው የሽያጭ ውል ላፈርስ አይገባም አመልካች ቤቱን ለተጠሪ እንዲያስረክቡ ላገደዱ አይገባም ብለናል።
ተጠሪ ያላቸው መፍትሄ የቤቱን ሽያጭ ገንዘብ ብር 148,000.00(አንድ መቶ አርባ ስምንት ሺህ ብር) በኢትጵያ ንግድ ባንክ ፊኒፊኔ ቅርንጫፍ ከሚገኘው የዝግ የሂሳብ አካውንት መውሰድ ነው ብለናል።
ለክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
የማይነበብ የአመስት ዳኞች ፊርማ አለበት፤