No summary available.
ሰኔ 17 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አሕመድ አመልካች፡- አቶ ባዘዘው ይሁን የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የአ/ብ/ክ/መንግስት ዐ/ሕግ የቀረበ የለም መዝገቡን መርምረን ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ በሕግ የፀና ንግድ ፍቃድ ሣይኖረው መነገድ ወንጀልን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአ/ብ/ክ/መንግስት በአዊ ብሕረሰብ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ጃዊ ወረዳ ፍ/ቤት ነው። በተጠሪ የቀረበበት ክስም አመልካች የንግድ ምዝገባ ፈቃድ አዋጅ ቁ. 686/2002 አንቀጽ 60/1/ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ሚያዚያ 22 ቀን 2003 ዓ.ም ከለላቱ በግምት 11፡30 ሲሆን ፈንደቀ ከተማ ልዩ ስሙ መናኸሪያ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ አመልካች ባልታደሰ የንግድ ፈቀድ ሁለት ማደበሪያ የፍየልና የበግ ቆዳ በሕዝብ ማመላለሻ መኪና በኪስ ውስጥ ይዞ ላወጣ ሲል የትያዘ ስለሆነ በፈፀመው የፀና የንግድ ፈቃድ ሣይኖረው መስራት ወንጀል ተከሷል የሚል ሲሆን አመልካችም ቀርቦ ክሱ ከተነበበለት በኃላ ቆዳውን ይዤ ተገኝቻለሁ ነገር ግን ሕጋዊ ፈቃድ ስላለኝ ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል።
ዐ/ሕግም እንደ ክሱ ያስረዱልኛል ያላቸውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም የቀረበውን የሰው ምስክር ሰምቶ ጉዳዩን ከማስረጃ ጋር በማገናዘብ ከመረመረ በኃላ አመልካች እንደ ክሱ ባልታደሰና በማያገለግል ንግድ ፊቃድ ተጠቅሞ የበግ እና የፍየል ቆዳ ሲነግድ በመያዙ የተመሰከረበት በመሆኑ ክሱን ላከላከል ይገባል በማለት ትእዛዝ ተሰጥቷል። አመልካቹም በበኩሉ ክሱን ለመከላከል አቅርቦ ያሰማቸው የመከላከያ ምስክሮች አመልካች ንግድ ፈቃድ የነበረው መሆኑ እንጂ ንግድ ፈቀዱ የታደሰ ይሁን አይሁን ለይተው የማያቁ መሆናቸውን በመግለጽ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። በመጨረሻም ጉዳዩን የተመለከተው ፍ/ቤት ጉዳዩን ከመረመር በኃላ አመልካች ወንጀሉን አለመፈፀሙን በመከለከያ ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ በተከሰሰበት የሕገ ድንጋጌ ሥር ጥፋተኛ ነው በማለት ከወሰነ በኃላ ቅጣትን በተመለከተም የግራ ቀኙን የቅጣት ሃሣብ ተቀብሎ ከመረመር በኃላ በ7 ዓመት ጽኑ እስራት እና በብር 150,000 የገንዘብ መቀጮ ይቀጣ ሲል ውሣኔ ሰጥቷል እንዲሁም ቆዳው የተሸጠበት ገንዘብም ብር 2,432 ለመንግስት ገቢ አንዲሆን ትእዛዝ ተሰጥቷል።
አመልካችም በተሰጠው ውሣኔ ላይ ቅር በመሰኘት ለአዊ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት ይግባኙን ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 195/1/ መሰረት ተቀባይነት አላገኘም በመቀጠልም አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለክልሉ ሰበር ችሎት አቅርቦ ችሎቱም ግራ ቀኙ ቀርበው እንዲሰሙ ካደረገ በኃላ በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጠውን የጥፋተኝነት ውሣኔ በማጽናት ቅጣቱን በተመለከተ ግን በ3 ዓመት ተኩል ጽኑ እስራት እና 5000 ብር መቀጮ በማሻሻል ወስኗል፡ አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታም ይህንኑ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው የቅጣት ውሣኔ ላይ የሕግ ግድፈት መፈፀሙን በመግለጽ እስከ አሁን የታሰርኩት ራሱ ከበቂ በላይ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ከጥፋቱና ቅጣቱ በነፃ አንድሰናበት ይወሰንልኝ የሚል ነው አቤቱታውም ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት ቀርቦ ላታይ ይገባል በመባሉ ተጠሪም ቀርቦ የበኩሉን መልስ ያቀረበ ሲሆን አመልካችም የመ/መልሱን ሰጠቶበታል።
የጉዳዩ አመጣጥ ይዘት አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር የሰበር አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት ይቻላል ወይስ አይቻልም? የሚለውን ነጥብ በጭብጥነት ተይዞ ምላሽ ላሰጥበት የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክር ሂደት መገንዘብ እንደተቻለው አመልካች የፀና የንግድ ሥራ ፈቀድ ሣይኖረው በቆዳና ልጦ ንግድ ሥራ ተሰማርቶ ተገኝቷል በሚል የተከሰሰበትን ድርጊት መፈፀሙን ሣይክድ ነገር ግን ድርጊቱን ላፈጽም የቻለው የተጠቀሰውን የንግድ ሥራ ላያሰራ የሚችል የንግድ ሥራ ፈቀድ ያለው በመሆኑ ጥፋተኝነት እንደልለበት በመግለጽ የተከራከረ መሆኑን ተረድተናል ሆኖም ግን አመልካች አለኝ የሚለው የቆዳና ልጦ ንግድ ሥራ ፈቃድ በአዋጅ ቁ. 686/2002 አንቀጽ 2/10/ እና 36 ድንጋጌዎች ይዘት አኳያ በሕግ በተቀመጠው የግዜ ገደብ ውስጥ ያለቅጣትም ሆነ በቅጣት የታደሰ ባለመሆኑ /የማያገልግል ፈቃድ በመሆኑ/ የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ ነው ለማለት የሚቻል አይሆንም በሕጉ አግባብ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ሣይኖረው በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ የተገኘ ሰው ደግሞ የፀና የንግድ ሥራ ፈቃድ እንደልለው ተቆጥሮ በወንጀል ኃላፊ ሆኖ እንደሚቀጣ በአዋጅ አንቀጽ 60/1/ ስር ተደንግጓል በመሆኑም በዚህ ረገድ በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጠው የጥፋተኝነት ውሣኔ የሚነቀፍ ሆኖ አላገኘንም።
በልላ በኩል ቅጣትን አስመልክቶ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት የተሰጠው የቀጣት ውሣኔም ቢሆን አመልካች ተላልፏል ተብሎ ጥፋተኛ የተባለበት የሕግ ድንጋጌ የሚያስቀጣው ከ7 ዓመት እስከ 15 ዓመት ጽኑ እስራት እና እንዲሁም በብር 150,000 እስከ 300,000 የገንዘብ መቀጫ ቢሆንም ችሎቱ የአመልካቹን የግል ሁኔታ የቀድሞ ባህሪውን የወንጀሉን አፈፃፀም እና እንዲሁም የወንጀሉን ክብደት እና ቅለት በማገናዘብ በፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በወጣው የወንጀል ቅጣት አወሣሰን መመሪያ አኳያ በማስላት በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ቅጣት በማሻሻል በ3 ዓመት ተኩል 3½/ ጽኑ እስራት እና በብር 5,000 የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ መወሰኑ የሚነቀፍ እና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ባለመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበው የሰበር አቤቱታም ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ውሣኔ
195/2//ለ//2/ መሰረት ፀንቷል።
ይፃፍ።
No topics extracted.