No summary available.
መጋቢት 9 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- የኮልፍ ቀራኒዮ ክ/ከተማ መሬት አስተዳደር ባለስልጣን - ነ/ፈጅ ወ/ሕይወት ደምሰው ቀረቡ ተጠሪዎች፡- ጂ.ኤም.ቲ ኢንዱስትሪያል ኃ/የተ/የግል ማህበር - ጠበቃ አቶ ሙሉጌታ ገብሩ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር በተጀመረበት ፍ/ከ/ፍ/ቤት ተጠሪ እና አመልካች እንደቅደም ተከተላቸው ከሳሽ እና 2ኛ ተከሳሽ የነበሩ ሲሆን 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች የነበሩት ደግሞ የሰበር ክርክሩ አካል ያልሆኑት እንደቅደም ተከተላቸው የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት እና የማረሸ፣ የወገልና የቢላዋ ስ/አ/ህብረት ስራ ማህበር ናቸው።
በ06/07/02 ተሻሽሎ የቀረበው ክስ ይዘትም ከሳሽ በ1ኛ ተከሳሽ ስር ከሚገኘው የፍ/አ/መምሪያ የ3ኛ ተከሳሽ ንብረት የነበረ ድርጅት በጨረታ ገዝቶ መረከቡን፣ ይሁን እንጂ ከ3ኛ ተከሳሽ የሚፈለግ የካፒታል ዕድገት ግብር ካለ እንዲገለፅ ከ1ኛ ተከሳሽ ለተፃፈለት ደብዳቤ 2ኛ ተከሳሽ በወቅቱ ምላሽ ባለመስጠቱ፣ 1ኛ ተከሳሽም የ2ኛ ተከሳሽን መልስ ሳይጠብቅ እና ግብሩን ሳይቀንስ ተራፊውን ገንዘብ በሙሉ ለ3ኛ ተከሳሽ በመመለሱና የ3ኛ ተከሳሽ ካርታ ሳይቀርብ ከሳሽ በንብረቱ እንዲበደር ለባንክ ማረጋገጫ በመስጠቱ 3ኛ ተከሳሽ ከግብር ነፃ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃና ካርታ ሳያቀርብ ሙሉ ገንዘብ በመቀበሉ በአጠቃላይ ተከሳሾቹ በአንድነትና በመመሳጠር በፈጸሙት ተግባር ከሳሽ ስሙን አዛውሮ በንብረቱ ለመጠቀምና ብድሩን ለመክፈል አለመቻሉን የሚገልጽ ሆኖ በከሳሽ ላይ የታሰበውን የብድር ወለድ ብር 1,785,539.20 ተከሳሾቹ ለከሳሽ እንዲከፍሉ እንዲወሰን ዳኝነት የተጠየቀበት መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያስረዳል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ክስ የቀረበበትን የወለድ ገንዘብ ለመክፈል ተከሳሾቹ የሕግም ሆነ የውል ግድታ የለባቸውም በማለት ክሱን ውድቅ በማድረግ መዝገቡን ዘግቷል።
ይግባኙ የቀረበለት የፍ/ጠ/ፍ/ቤት በበኩሉ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በፍ/ባለመብት አሰፋ አርጋው እና የፍ/ባለዕዳ በነበረው 3ኛ መ/ሰጪ መካከል በነበረው አፈፃፀም ይ/ባይ የ3ኛ መ/ሰጪ ንብረት የነበረውን ድርጅት በ22/03/99 ዓ/ም በብር 6,700,000 በጨረታ ገዝቶ ገንዘቡን አጠቃሎ ገቢ በማድረግ ድርጅቱን እንደተረከበ ድርጅቱን ለመግዛት ይ/ባይ ከወጋገን ባንክ ጎፋ ቅርንጫፍ ብር 4,265,100 ሲበደር የስም ዝውውሩ ወደ ይ/ባይ ሲፈፀም ካርታውን በቀጥታ ለባንኩ እንዲልክ ለ2ኛ መ/ሰጪ በደብዳቤ የሚያሳውቅ መሆኑን በመግለፅ የፍ/አ/መምሪያ ለባንኩ ማረጋገጫ እንደሰጠ፣ ከ3ኛ ተከሳሽ የሚፈለግ የካፒታል ዕድገት ግብር እንዲገለጽለት 1ኛ መ/ሰጪ ለ2ኛ መ/ሰጪ ደብዳቤ የፃፈው በ09/09/99 ዓ/ም ሆኖ 2ኛ መ/ሰጪ ብር 803,997.33 የካፒታል ዕድገት ተቀንሶ እንዲሰጠው በመጠየቅ ምላሽ የሰጠው ከዘጠኝ ወራት በኋላ በ06/06/2000 ዓ/ም እንደሆነ፣ በዚህ ጊዜ መሀል 3ኛ መ/ሰጪ ተራፊውን ገንዘብ በሙሉ እንደወሰደ፣ በአዋጅ ቁጥር 286/94 አንቀጽ 37 መሰረት የካፒታል ዕድገት ግብር የመክፈል ግድታ የሻጭ በመሆኑ ግብሩ እንደሚፈለግብኝ አላውቅም ነበር በማለት 3ኛ መ/ሰጪ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት እንደልለው 1ኛ መ/ሰጪ ተጨማሪ ጥረት ማድረግ አይገባውም ወይም ግብሩ ላኖር እንደሚችል መገመት የሚቻልበት ሁኔታ አልነበረም ባይባልም ግድፈቱ ሚዛን የሚደፋ እንዳልሆነ በፍ/ቤቶች የሚፈፀም ስህተት በይግባኝ ከሚታረም በስተቀር ለሚደርስ ጉዳት ኃላፊነት አለባቸው የሚባል ከሆነ በሀገሪቱ ምስቅልቅል የሚፈጠር እንደሆነ፣ 2ኛ ከዘጠኝ ወር በኋላ ግብሩ ገቢ እንዲደረግለት ጠይቆ ገንዘቡ ለ3ኛ መ/ሰጪ መለቀቁ ላገለጽለት ለፍ/የመ/ደ/ፍ/ቤት እና ለፍድራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን ደብዳቤ መፃፉ የራሱን ስህተት ግምት ውስጥ እንዳያስገባ ስህተቱን ልሎች መ/ሰጪዎች እንደፈፀሙት በማድረግ መሯሯጡ ተገቢነት እንዳልነበረው በዝርዝር ከገለፀ በኋላ ይ/ባይ ድርጅቱን የተረከበው በመሆኑ መ/ሰጪዎች የባንክ ብድር ወለድ ይክፈሉኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት እንደልለው ይሁን እንጂ ከክርክሩ መረዳት እንደተቻለው ይ/ባይ ግድታውን ሙሉ በሙሉ ተወጥቶ እያለ ስሙ እስካሁን ያልተዛወረለት በመሆኑ 2ኛ መ/ሰጪ የድርጅቱን ባለቤት ስም ወደ ይ/ባይ ያዘውር የካፒታል ዕድገት ግብሩን ብር 803,997.33 ገንዘቡን ከወሰደበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር 3ኛ መ/ሰጪ ለ2ኛ መ/ሰጪ ገቢ ያድርግ 2ኛ መ/ሰጪም ተከታትሎ ገቢ ያስደርግ ይ/ባይ ለዳኝነት የከፈለውን ገንዘብ 2ኛ እና 3ኛ መ/ሰጪዎች በታሪፉ መሰረት ግማሽ ይከፈሉት፣ ቀሪውን ወጪና ኪሳራ ይቻቻሉ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበው የጠ/ፍ/ቤቱ ይ/ሰሚ ችሎት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ላታረም ይገባል በማለት ሲሆን በ24/08/04 አዘጋጅቶ ያቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ በዚህ ጉዳይ ተጠሪ ያቀረበው ክስ በጨረታ አሸንፎ የተረከበውን ድርጅት በአመልካችና በልሎች የስር ተከሳሾች ጥፋት ወደስሙ ማዛወር ባለመቻሉ ከባንክ ለወሰደው ብድር ለብር 1,785,539.20 የወለድ ክፍያ የተዳረገ በመሆኑ ወለዱ ላተካልኝ ይገባል የሚል ሆኖ አመልካች ስም እንዲያዘውር የካፒታል ዕድገት ግብር ከነወለዱ ከስር 3ኛ መ/ሰጪ ተከታትሎ ገቢ እንዲያደርግ በይ/ሰሚው ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ከክሱ ጋር የሚጣጣም መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ይቻል ዘንድ ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የፅሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የይ/ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህም መሰረት ተጠሪ በፍ/ከ/ፍ/ቤት በ06/07/02 ዓ/ም በተፃፈ ማመልከቻ አሻሽሎ ባቀረበው ክስም ሆነ ለይ/ሰሚው ፍ/ቤት ባቀረበው የይግባኝ ማመልከቻ የጠየቀው ዳኝነት የወለድ ክፍያ መሆኑን እና በይ/ሰሚው ፍ/ቤት የተሰጠው ዳኝነት ደግሞ የስም ዝውውር እንዲፈፀም መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያስረዳል። ይሁን እንጂ ተጠሪ በከ/ፍ/ቤትም ሆነ በይ/ሰሚው ፍ/ቤት በነበረው ክርክር ዳኝነት ለጠየቀበት የወለድ ክፍያ ዋንኛ መንስኤ የሆነው በስር ተከሳሾች (መ/ሰጪዎች) ድርጊት ሳቢያ የስም ዝውውሩ ላፈፀም አለመቻል መሆኑን በግልጽ ሲከራከርበት የነበረ በመሆኑ የድርጅቱ የስም ዝውውር ጉዳይ የስር ፍ/ቤቶች ዳኝነት ከጠየቁበት ጉዳይ ውጪ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም በዚህ ረገድ በአመልካች የቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። በልላ በኩል ግን የስም ዝውውሩን እና የካፒታል እድገት ግብሩን ክፍያ መፈፀም ቅደም ተከተል አስመልክቶ በይ/ሰሚው ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ ከገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 አንፃር ተገቢ መሆን አለመሆኑ መጤን የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም መሰረት ማናቸውም በዚህ አንቀጽ ግብር የተጣለበትን የካፒታል ንብረት ዝውውር የመቀበል ወይም የመመዝገብ ወይም በማናቸውም መንገድ ማጽደቅ ስልጣን የተሰጠው ሰው ግብሩ መከፈሉን ሳያረጋግጥ ዝውውሩን እንደማይቀበል እንደማይመዘግብ እና እንደማያፀድቅ በአዋጅ በአንቀጽ 37(7) ስር በግልጽና በአስገዳጅነት ተደንግጐ ይገኛል። የዚህ ዓይነቱ ግልጽ የሕግ ክልከላ ባለበት ሁኔታ ደግሞ የስም ዝውውሩ ከግብር ክፍያው አስቀድሞ ላፈጸም የሚችልበት አግባብ ስለማይኖር በይ/ሰሚው ፍ/ቤት የተሰጠው የአፈፃፀም ቅደም ተከተል ከአዋጁ ድንጋጌ አንፃር መስተካከል የሚገባው መሆኑን ተገንዝበናል።
አመልካች ከስር 3ኛ መ/ሰጪ የካፒታል እድገት ግብሩን ተከትሎ ገቢ እስኪያስደርግ ድረስ የስም ዝውውሩ መዘግየት ጉዳት ያስከትልብኛል የሚል አቋም ኖሮት ተጠሪው ግብሩን ከፍሎ የስም ዝውውሩን የሚያስፈፅም ሆኖ ከተገኘም የከፈለውን የካፒታል ዕድገት ግብር ከስር 3ኛ መ/ሰጪ የማስተካት መብት እንዲኖረው መደረጉን ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፍ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይ/ሰሚ ችሎት በመ/ በ30/06/04 የሰጠው ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሐል።
አመልካች ካፒታል እድገት ግብሩን ይ/ሰሚው ፍ/ቤት በውሳኔው መሰረት ከስር 3ኛ መ/ሰጪ ተከታትሎ ገቢ ካስደረገ በኋላ የስም ዝውውሩን ያስፈጽም በማለት ወስነናል።
ተጠሪ የጉዳዩ መዘግየት ላያስከትልበት የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ያስችለው ዘንድ ግብሩን እራሱ ከፍሎ ከስር 3ኛ መ/ሰጪ ለማስተካት የሚፈልግ ከሆነ የካፒታል እድገት ግብሩን ብር 803,997.33 (ስምንት መቶ ሶስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ከ33/100) ከፍሎ የስም ዝውውሩን እንዲያስፈፅም እና የስር 3ኛ መ/ሰጪም ይ/ሰሚው ችሎት በወሰነው መሰረት ይህንን ገንዘብ ከነወለዱ ለተጠሪ እንዲተካ ወስነናል።
የሰበር ክርክሩን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
በይ/ሰሚው ፍ/ቤት የተሰጠው የወጪና ኪሳራ ውሳኔ አልተነካም።
የአፈፃፀም እግዱ ተነስቷል።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.