No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 21 ቀን 2006 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሤ አመልካቾች፡-
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሁን የሰበር አመልካቾች የክስ አቤቱታ አቅራቢነት የተጀመረው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። አመልካቾች የካቲት 12 ቀን 2004 ዓ/ም አሻሽለው በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት የክስ አቤቱታ አመልካቾችና 1ኛ ተጠሪ የሟች አቶ ብርሃኑ ገ/ማሪያም እና የወ/ሮ ፀዳለ በዳዳ ወራሾች መሆናችን በድሬዳዋ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረጋግጦ የወራሽነት ማስረጃ ወስደን የውርስ ንብረቶች ተጣርተው ሪፖርቱም ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ የጸደቀ ቢሆንም 1ኛ ተጠሪ ቀደም ሲል እውነተኛ ወራሽና ተወላጅ ሳይሆኑ የወሰዱት የወራሽነት ማስረጃ ከህግ ውጪ አሳስተው የወሰዱ መሆኑ ተረጋግጦ የተሰረዘ በመሆኑ በተሰረዘ ወራሽነት ማስረጃ ከሟቾች ወራሾች ጋር የውርስ ሀብት ላከፋፈሉ ስለማይገባ የውርስ ሀብቶችን ከወራሾች ጋር እንዲከፋፈሉ የተሰጠው ትዕዛዝ ይሰረዝልን ብለዋል።
ተጠሪዎችም በሰጡት መልስ፡- አመልካቾች 1ኛ ተጠሪ የሟቾች ልጅ መሆኗን አምነው የወራሽነት ማስረጃ እንዲሰጣቸውም ሆነ የውርስ ሀብቶች እንዲከፋፈሉ ለፍርድ ቤት ሲያመለክቱ ቆይተው የሟቾች ልጅ እና ወራሽ አይደለችም በሚል ዳኝነት እንደገና እንዲታይ ያቀረቡት አቤቱታ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/6(1)(ሀ)የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ስለማያሟላ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል።
የድሬዳዋ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በሰጠው ብይን፡- አመልካቾችና 1ኛ ተጠሪ የሟች ብርሃኑ ገ/ማሪያም እና ወ/ሮ ጸዳለ በዳዳ ልጆች ስለመሆናቸው አንድ ላይ ወራሽነታቸው ተረጋግጦ የውርስ ንብረቶች ተጣርተው የአጣሪው ሪፖርት ቀርቦ ስለትክክለኛነቱ ወራሾቹ በሰጡት አስተያየት በመስማማታቸው ከጸደቀና የፍርድ ቤቱ የውሳኔ አካል ሆኖ እንዲፈጸም ትዕዛዝ ከተሰጠ በኋላ ዳኝነት እንደገና እንዲታይ ያቀረቡት አቤቱታ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/6 ስር ከተደነገጉት ሁኔታዎች ውጪ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ሲል ውድቅ አድርጓል።
አመልካቾችም በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ብይን ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ወገኖች ካከራከራቸው በኋላ በሰጠው ፍርድ፡- ይግባኝ ባዮች ቀርቦ የነበረውን ክስ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/91 መሰረት በማሻሻል በ12/08/2004 ዓ/ም የተጻፈ የክስ አቤቱታ ቢያቀርቡም የክስ አቤቱታቸውን አሻሽለው እንዲያቀርቡ የተፈቀደላቸው ስለመሆኑ የስር ፍርድ ቤት መዝገብ አያመላክትም።
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ አቤቱታቸውን አሻሽለው እንዲያቀርቡ ሳይፈቅድላቸው ያቀረቡት የክስ አቤቱታ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/91 ስለአቤቱታ አቀራረብ ከተደነገገው ውጪ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፣በልላ በኩል ይግባኝ ባዮች በ25/04/2004 ዓ/ም እና በ12/06/2004 ዓ/ም ያቀረቡኣቸው አቤቱታዎች ጥቅምት 09/2004 ዓ/ም የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲሻሻልላቸው የጠየቁባቸው ቢሆንም አቤቱታዎቹ በመዝገቡ ላይ የመጨረሻ ውሳኔና ትዕዛዝ ተሰጥቶ ከተዘጋ በኋላ የቀረቡ በመሆናቸው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/6 አንጻር የሚታዩ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በዚሁ የሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር መሰረት በማየት ውደቅ ማድረጉ ተገቢ ነው ሲል አጽንቷል።
አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡትም በሥር ፍርድ ቤቶች ብይን/ፍርድ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን የቅሬታ ነጥቡም ሲጠቃለል፡-አመልካቾች በህጉ አግባብ ተገቢውን የዳኝነት ክፍያ ከፍለን በ12/06/2004 ዓ/ም ባቀረብነው ቀጥታ የክስ አቤቱታ ተጠሪዎች በተሰረዘ የወራሽነት ማስረጃ መሰረት የያዙትን የውርስ ንብረቶች እንዲመልሱ እንዲወሰንልን ዳኝነት ጠይቀን ሳለ ፍርድ ቤቶቹም የክሱን አርዕስት፣ተከራካሪ ወገኖችንና የክሱን ማስረጃ ዝርዝር እንዲሁም በክሱ አቤቱታ የተጠየቀውን ዳኝነት በማየት በፍ/ህ/ቁ/ 999 መሰረት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ መስጠት ሲገባቸው ጉዳዩ እንደገና ዳኝነት እንዲታይ በሚል እንደቀረበ በመቁጠር የክስ አቤቱታችንን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/6 መሰረት መርምረው ውድቅ ያደረጉት ተገቢነት የለውም የሚል ነው።
ተጠሪዎች በበኩላቸው በሰጡት መልስ፡- ጉዳዩ እልባት አግኝቶ በተዘጋ መዝገብ ላይ የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 91(1)ን በመጠቅስ አመልካቾች የውርስ ሀብቱ ይመለስልን ሲሉ ያቀረቡትን አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤቶች በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/ 6(1) መሰረት በመመርመር ውድቅ ያደረጉት ህግን መሰረት ያደረገ ነው፣አመልካቾች ያቀረብነው አቤቱታ ላታይ የሚገባው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/6(1) ሳይሆን በፍ/ህ/ቁ/999 መሰረት ነው ቢሉም በፍ/ህ/ቁ/999 መሰረት የሚቀርብ ጉዳይ አዲስ ክስ ቀርቦ አዲስ ዳኝነት የሚሰጥበት እንጂ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠበት መዝገብ ተንቀሳቅሶና በፍ/ሥ/ሥ/ህ ቁ 91 መሰረት የክስ አቤቱታ ተሻሽሎ የሚወሰን ባለመሆኑ የሰበር አቤቱታቸው ውድቅ ላደረግ የሚገባ ነው ሲሉ ተከራክረዋል።
No topics extracted.
አመልካቾችም ለተጠሪዎች መልስ የመልስ መልስ በማቅረብ ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም፡-አመልካቾች ያቀረቡትን የክስ አቤቱታ የስር ፍርድ ቤቶች ውድቅ ያደረጉት በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካቾችና 1ኛ ተጠሪ የሁለቱም ሟቾች ወራሾች ስለመሆናቸው እንዲወሰንላቸው በጋራ ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ወራሽነታቸው በፍርድ ቤት ተረጋግጦ መወሰኑንና የሟቾች የውርስ ሀብቶች እንዲጣሩ ተደርጎ ተጣርተው ከቀረቡ በኋላ የአጣሪው ሪፖርት ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርቦ ስለመጽደቁና ክፍፍሉም እንዲፈጸም ታዞ መዝገቡ ጥቅምት 09 ቀን 2004 ዓ/ም መዘጋቱን የስር ፍርድ ቤቶች በውሳኔያቸው ካሰፈሩት መገንዘብ ተችሐል።
አመልካቾችም መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ በታህሳስ ወር 2004 ዓ/ም ለመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በጻፉት አቤቱታ ለ1ኛ ተጠሪ የተሰጣቸው የወራሽነት ማስረጃ የተሰረዘ በመሆኑ ተጠሪዋ ከውርስ ሀብቱ ¼ኛ እንዲካፈሉ የተሰጠው ትዕዛዝ ተሽሮ ለአመልካቾች እንዲደርሳቸው በተወሰነው የውርስ ሀብት ድርሻ ላይ እንዲጨመርላቸው ጠይቀው የተጠሪዋን መልስ ፍርድ ቤቱ ከተቀበለ በኋላ መዝገቡ ለምርመራ ተቀጥሮ ባለበት አሁን ለክርክሩ መነሻ የሆነውን የክሱን አርዕስት በፍ/ህ/ቁ/999 መሰረት የአመልካቾችን የውርስ ድርሻ ለማስለቀቅ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/91 መሰረት ተሻሽሎ የቀረበ የክስ አቤቱታ የሚል አቅርበዋል። ይህን ተሻሽሎ ቀረበ የተባለውን የክስ አቤቱታ ፍርድ ቤቶቹ የመረመሩት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/6(1) መሰረት መሆኑንም ከውሳኔያቸው መገንዘብ ችለናል።
የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 91 ተከራካሪ ወገኖች አቤቱታቸውን ወይም የመከላከያ መልሳቸውን ላያሻሽሉ ወይም ላለውጡ ስለሚችሉበት አግባብ የሚደነግግ ነው። በዚህ ድንጋጌ በንዑስ ቁጥር 1 እንደተመለከተው አቤቱታ ወይም ክርክር ለመሻሻል ወይም ለመለወጥ የሚቻለው በተካራከሪ ወገኖች ጥያቄ ወይም ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ሲያዝ ሲሆን ተከራካሪ ወገኖቹም አቤቱታቸውን ወይም ክርክራቸውን አሻሽለው ወይም ለውጠው ላያቀርቡ የሚችሉት የክሱ መሻሻል ወይም የክርክሩ መለወጥ ነገሩን በይበልጥ የሚያብራራ ወይም ትክክለኛ ፍትህ ለመስጠት ይረዳል ብሎ ፍርድ ቤቱ ሲገምት ብቻ ነው። አቤቱታውን ለማሻሻል ወይም ክርክሩን ለመለወጥ የሚቻለውም በጉዳዩ ላይ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ ስለመሆኑ በዚሁ በንዑስ ቁጥር ተመልክቷል። በዚህ በተያዘው ጉዳይ ግን አመልካቾች አቤቱታቸውን አሻሽለው ለማቅረብ እንዳልተፈቀደላቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍርድ የሚያመላክት ከመሆኑም ልላ አቤቱታቸውን ያቀረቡትም በጉዳዩ ላይ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥቅምት 09 ቀን 2004 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቶ መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ ስለመሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር በመሆኑ አቤቱታው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 91 መሰረት የሚስተናገድ አይሆንም።
የስር ፍርድ ቤቶች ይህን አቤቱታ የመረመሩትም በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/6 መሰረት ሲሆን ድንጋጌው ለጉዳዩ አግባብነት ያለው መሆን አለመሆኑን መመርመር ይገባል።
በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/6 (1)(ሀ) መሰረት ጉዳዩ እንደገና እንዲታይ የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት የሚኖረው የመጨረሻው ፍርድ ወይም ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ የተሰጠው በሐሰት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ሰነድ ወይም ሀሰተኛ የምስክርነት ቃልን ወይም መደለያን ወይም ወንጀል ጠቀስ የሆነ ተግባርን መሰረት በማድረግ ሲሆን አቤት ባዩም ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት አስፈላጊውን ትጋት አድርጎ ለማወቅ አለመቻሉን ማስረዳት የሚጠበቅበት ከመሆኑም በላይ በፊደል (ለ) እንደተጠቀሰውም እነዚህ የተዘረዘሩት ተግባሮች መፈጸማቸው ቢገለጽ ኖሮ ለተሰጠው ፍርድ መለወጥ ወይም መሻሻል በቂ ምክንያት ላሆኑ ይችሉ እንደነበር አቤት ባዩ የማስረዳት ኃላፊነት አለበት።
በዚህ በተያዘው ጉዳይ አመልካቾች በክስ አቤቱታቸው የገለጹት 1ኛ ተጠሪ እውነተኛ ወራሽ ሳይሆኑ የወሰዱት የወራሽነት ማስረጃ በፍርድ ቤት ውሳኔ የተሰረዘባቸው በመሆኑ የተቀበሉትን የውርስ ሀብት ድርሻ ለአመልካቾች እንዲለቁ በፍ/ህ/ቁ/999 መሰረት ይወሰንልን የሚል ነው። ከዚህ የክስ አቤቱታው ይዘትም መረዳት የሚቻለው አቤቱታው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/6(1)(ሀ) እና (ለ) የተመለከቱትን ሁኔታዎች አለመያዙንና በውርስ ህግ ድንጋጌዎች መሰረት መቅረቡን ነው። በፍ/ህ/ቁ 996 (1) ወራሽ የሆነ ሰው ለሟቹ ወራሽ መሆኑንና ከውርሱ ላይ የሚያገኘውን ድርሻ የሚያመላክት የወራሽነት የምስክር ወረቀት እንዲሰጠው ለፍርድ ቤት ማመልከት የሚችል ሲሆን የተሰጠው የወራሽነት ምስክር ወረቀትም በፍ/ህ/ቁ/998(1) በተመለከተው ሁኔታ ላሰረዝ ይችላል። በልላ በኩል በፍ/ህ/ቁ/999 በተደነገገው መሰረት አንድ ሰው ዋጋ ያለው የወራሽነት ማስረጃ ሳይኖረው ውርሱን ወይም ከውርሱ አንዱን ክፍል በእጁ ያደረገ እንደሆነ እውነተኛው ወራሽ ወራሽነቱ እንዲታወቅለትና የተወሰዱበት የውርስ ንብረቶች እንዲመለሱለት የወራሽነት ጥያቄ ክስ ማቅረብ እንደሚችል ተመልክቷል። የአመልካቾች አቤቱታም 1ኛ ተጠሪ እርግጠኛ ወራሽ ሳይሆኑ የወራሽነት ማስረጃ በመያዝ የውርስ ሀብት ድርሻ ስለያዙ እንዲመልሱ ይወሰንልን የሚል እስከሆነ ድረስ የዳኝነት ክፍያ በታሪፉ መሰረት ከፍለው በፍ/ህ/ቁ/999 እንደተጠቀሰው አዲስ ክስ ከሚያቀርቡ በስተቀር የውርስ ሀብት ተጣርቶ ክፍፍሉ እንዲፈጸም ተወስኖ የተዘጋውን መዝገብ በማንቀሳቀስ እንዲከራከሩ የሚፈቅድ የፍ/ሥነ ሥርዓት ህግ ድንጋጌ የለም።
በመሆኑም አመልካቾች የውርስ አጣሪ ሪፖርት ለፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርቦ ከጸደቀና የንብረት ክፍፍል እንዲደረግ ታዞ ድርሻቸውን ወሰደው መዝገቡ ከተዘጋ