No summary available.
መጋቢት 10 ቀን 2005 ዓ/ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ ሙስጠፋ አሕመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ አቶ ሰለሞን ፍቅሬ ተጠሪዎች፡-
መዝገቡን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ በባንክ የቁጠባ ሂሣብ ውስጥ ያለው ገንዘብ ለማንም ሣይከፈል ታግዶ እንዲቆይ ተብሎ በፍ/ቤቱ የተላለፈው የእግድ ትእዛዝ ፀንቶ በሚቆይበት ጊዜ በገንዘቡ ላይ ወለድ ይታሰብበታል? ወይንስ አይደለም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ በዚህ ሰበር ችሎት ተመርምሮ ተገቢው ምላሽ እንዲሰጥበት በማለት የቀረበ ነው።
ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 እና 359 መሰረት ለፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ባቀረበው የመቀወሚያ ማመልከቻ መነሻነት ነው። የመቃወሚያ ማመልከቻ ይዘቱም የይግባኝ መ.ቁ.
58449 በሆነው ላይ በተጠሪዎች መካከል በነበረው የንብረት ክፍፍል ክርክር መነሻነት የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ሐምል 26 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ2ኛ ተጠሪ ስም በተከፈተው የቁጠባ ውስጥ ያለው ገንዘብ ለማንም ሣይከፈል እንዲቆይ በሚል አረጋግጠው የእግዱ ትእዛዝ መነሻነት ባንኩ ገንዘቡን በዝግ ሂሣብ ውስጥ እንዲቀመጥ አድርጓል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ችሎቱ በተጠሪዎች መካከል ሲካሄድ በነበረው ክርክር ላይ ታህሣስ 8 ቀን 2003 ዓ.ም ውሣኔ ሲሰጥ ከሐምል 26 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ፍ/ቤቱ የእግድ ትእዛዝ መሰረት ወደ ዝግ ሂሣብ ውስጥ የገባው ገንዘብ ላይ ጭምር ወለድ ታስቦበት ከነወለድ እንዲከፈላቸው በሚል የተሰጠው ውሣኔ መብቴን ስለነካው በዝግ ወይም ተካፋይ ሂሣብ ውስጥ በተቀመጠ ገንዘብ ላይ ወለድ ስለማይታሰብ ገንዘቡ ወደ ዝግ ሂሣብ ከገባበት ሐምል 26 ቀን 2002 ዓ.ም ጀመሮ ባለው ጊዜያት ወለድ ሣይታሰብበት ዋናው ገንዘብ ብቻ ይከፈላቸው በሚል ውሣኔው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 360 /2/ ስር በተመለከተው መልኩ ተሻሽሎ ወይም ታርሞ እንዲሰጥ ዳኝነት ጠይቋል።
ለተጠሪዎችም ጥሪ ተደርጎ ሁለቱም ተመሣሣይነት ባለው መልኩ በገንዘቡ ላይ ወለድ የማይታሰብበት በቂና ሕጋዊ ምክንያት ስለልለ የቀረበው መቃወሚያ ማመልከቻ ውድቅ እንዲደረግላቸው በመከራከር መልሣቸውን ሰጥተዋል።
ጉዳዩን የተመለከተው የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ፍ/ብ/ይ/ሰሚ ችሎቱም ግራ ቀኙን ሰምቶ ጉዳዩን ከመረመር በኃላ ቁጠባ ሂሣብ ውስጥ ያለው ወጪ ሆኖ ለጊዜ እንዳይከፈል የእግድ ትእዛዝ ከመስጠት በስተቀር አመልካች እንደሚለው ገንዘቡን ከቁጠባ ሂሣብ ወጥቶ በዝግ ወይም ተከፋይ ሂሣብ ውስጥ እንዲቀመጥ በሚል የሰጠሁት ትእዛዝ ስለልለ በገንዘቡ ላይ ወለድ የማይታሰብበት ምክንያት የለም በማለት የቀረበውን የመቃወም ማመልከቻ ሣይቀበል ቀርቷል። አሁን በአመልካች የቀረበው የሰበር አቤቱታ ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ሲሆን ይዘቱም ባጭሩ ሲቀመጥ በገንዘቡ ላይ የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ በውጤት ደረጃ ገንዘቡ በዝግ ሂሣብ እንዲቀመጥ እንደማለት መሆኑ ግልጽና የማያሻማ ጉዳይ ነው። አመልካችም ይህንኑን በመረዳት ገንዘቡን በዝግ ሂሣብ እንዲቀመጥ በማድረጉና በዝግ ሂሣብ በተቀመጠ ገንዘብ ላይ ደግሞ አመልካች ወለድ አስቦ ለመክፈል የሕግም ሆነ የውል ግድታ ሣይኖርበት በዝግ ሂሣብ የተቀመጠ ገንዘብ ከነወለዱ ታስቦ ይከፈል ተብሎ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ውሣኔው ታርሞ በጥያቄያችን መሰረት ይወሰንልኝ የሚል ነው። አቤቱታውም ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ላቀርብ ይገባል በመባሉ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎ ቀርበው የበኩላቸውን መልስ የሰጡበት ሲሆን አመልካችም የመ/መልስ ሰጥቶበታል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
እንደመረመርነውም በገንዘቡ ላይ የእግድ ትእዛዝ ከተሰጠበት ሐምል 26 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጊዜያት አመልካች ከነወለዱ አስቦ ገንዘቡን ለተጠሪዎች ላከፍል ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለው አከራካሪ ነጥብ በጭብጥነት ተይዞ ምላሽ ላሰጥበት የሚባው ሆኖ አግኝተነዋል።
እንግዲህ ከክርክር ሂደቱ መገንዘብ እንደተቻለው በ2ኛ ተጠሪ ስም በአመልካች ባንክ በተከፈተ የቁጠባ ሂሣብ ውስጥ ያለው ገንዘብ ለማንም ሣይከፈል ታግዶ እንድቆይ ተብሎ የእግዱ ትእዛዝ መተላለፍ የተረጋገጠ ፍሬ-ነገር ከመሆኑም በሻገር ይህ ስለመሆኑ በግራ ቀኙም አይካድም። አመልካችም ይህንኑ የተረጋገጠውን ፍሬነገር መነሻ በማድረግ በአጽኖት እየተካራከረ ያለው በፍ/ቤት የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ አጠቃላይ ይዘቱ ከፍ ሲል እንደገለፀው ቢሆንም ወይም ቃል በቃል ሲነበብ ገንዘቡ ወደ ዝግ ሂሣብ ተዛውሮ እንዲቀመጥ በሚል የሰፈረ ባይሆንም ገንዘቡ ለማንም ሣይከፈል ታግዶ ይቆይ በሚል አገላለጽ መተላለፉ በራሱ ገንዘቡን ማንም እንዳያንቀሣቅሰው ወይም ማንም እንዳይጠቀምበት ወይም በተለመደው አባባል በዝግ ሂሣብ እንዲቀመጥ የሚያደርግ ወይም ውጤት ያለው ትእዛዝ በመሆኑና ይህንኑ መነሻ አድርገን በዝግ ሂሣብ እንዲቀመጥ በተደረገ ገንዘብ ላይ ወለድ ላታሰብ አይገባም በሚል ይከራከራል።
No topics extracted.
ተጠሪዎችም በበኩላቸው ገንዘቡ ወደ ዝግ ሂሣብ ተዛውሮ እንዲቀመጥ በፍ/ቤቱ የእግድ ትእዛዝ ያልተሰጠ በመሆኑና አመልካች በራሱ በተሣሣተ ትርጉም በተከፋይ ሂሣብ /payable account/ እንዲቀመጥ ያደረገውን በፍ/ቤቱ የእግድ ትእዛዝ መነሻነት ወለዱን ለመክፈል አስመሰሎ የሚያቀርበው ክርክር ውድቅ ላሆን ይገባል በሚል ይከራከራሉ።
እንዲህ ከግራ ቀኙ እየቀረበ ያለው ክርክር አንድ ቁጠባ ሂሣብ ውስጥ ያለው ገንዘብ እንድትና በምን አይነት ሁኔታዎች ወደ ዝግ ወይም ተከፋይ ሂሣብ እንዲቀመጥ ላደረግ ይችላል የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ላይ መፍትሕ ከመስጠቱ በፊት ሙያዊ አስተያየት ወይም ማብራሪያ በጉዳዩ ላይ እንዲሰጥበት ማድረጉ የግድ ይላል ተከራካሪ ወገኖች የሚከራሩበት ነጥብ ከክርክሩ ልዩ ባህሪይ የተነሣ የልዩ አዋቂ ምስክርነትና የባለሙያን ማብራሪያ የሚያስፈልገው ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን በዚህ አኳኃን እንዲጣራ ማድረግ እንደሚገባው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 136/1/ ሥር ተመልክቷል። በያዝነው ጉዳይም ከፍ/ቤት የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ገንዘቡን በዝግ ሂሣብ እንዲቀመጥ ውጤት ያለው ነው ወይም አይደለም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ የባንክ ባለሙያዎች አስተያየት ሙያዊ ማብራሪያ የሚያስፈልግ በመሆኑ እንደሁኔታው ከብሕራዊ ባንክና እንዲሁም በዚህ ረገድ ያለው የልሎች የግል ንግድ ባንኮች የታወቀና የተለመደ ልማድ ባካተተ መልኩ ተገቢው ሙያዊ አስተየየት እንዲሰጥበት በማድረግ በጉዳዩ ላይ ውሣኔ መስጠት ሲገባው ታልፎ መወሰኑ ወይም በክርክሩ ሂደት አግባብነት ያላቸው ፍሬ-ነገሮች ሣይጣሩ ታልፎ በመወሰኑ በጉዳዩ ላይ የተሟላ ዳኝነት ተሰጥቷል ለማለት አልተቻለም በመሆኑም በክርክር አመራር ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ውሣኔ
የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ.ቁ. 58449 ሐምል 30 ቀን 2004 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፍ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መዝገቡን አንቀሣቅሶ ግራ ቀኙን በማስቀረብ ሐምል 26 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትእዛዝ ቁጠባ ሂሣብ ውስጥ የነበረው ገንዘብ ወደ ዝግ ወይም ተከፋይ ሂሣብ ተዛውሮ እንዲቀመጥ የማድረግ ውጤት ያለው መሆን አለመሆኑን እንደሁኔታው በብሕራዊ ባንክ ባለሙያና ተገቢ ሆኖ ከተገኘም ከልሎች ንግድ ባንኮችም ሙያዊ አስተያየት ወይም ማብራሪያ እንዲሰጥበት በማድረግና ጉዳዩን በሥነ-ሥርዓት ሕጉ አግባብ በማጣራት ተገቢውን ውሣኔ እንዲሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት በመመለስ ወስነናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻሉ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፣ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።