No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ኮንቴክ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ጠበቃ አለልኝ ምህረቱ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ወልዱ ህሉፍ - ጠበቃ ሰለሞን ገ/ሚካኤል ጋር ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮም ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዳዩ ከስነ-ስርዓት ክርክር ጋር ተያይዞ የቀረበ ሲሆን ክርክሩም የተጀመረው በፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት በአሁኑ አመልካች ድርጅትና የድርጅቱ ባለአክሲዮኖች በሆኑት ልሎች 2 ሰዎች ከሳሽነት ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ። ጥር 24 ቀን 2005 ዓ/ም በተፃፈ የክስ አቤቱታ አመልካችና የአመልካች ድርጅት ባለአክሲዮኖች በሆኑት አቶ ሳልህ ሁሴንና ወ/ሮ አለም ካሣ በጋራ በመሆን በተጠሪ ላይ ያቀረቡት የክሱ ይዘት ባጭሩ ተከሳሽ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ሆኖ በሰሩበት ወቅት ያለአግባብ ያባከኑት የድርጅቱን ገንዘብ ብር 3,641,052.04 እንዲከፍሉ እንዲወሰንባቸውና እንዲሁም ተከሳሹ በድርጅቱ ባለአክሲዮንነት ማዋጣት ከሚጠበቅበት የአክሲዮን ድርሻ ውስጥ ገቢ አድርጐ የተገኘው ብር 516,744.56 በመሆኑና በዚህ የተነሳም የማህበሩ ካፒታል ወደ ብር 4,442,616.36 ብቻ ቀንሶ በመገኘቱ የማህበሩ ባለአክሲዮኖች የአክሲዮን ድርሻ እያንዳንዳቸው ባደረጉት ካፒታል ልክ እና እንዲሁም የማህበሩ ጠቅላላ ካፒታልም በተከፈለው ልክ ብቻ ነው ተብሎ እንዲወሰንላቸው ዳኝነት የተጠየቀበት ሲሆን ተጠሪም ቀርቦ ለከሱ በሰጠው መልስ የተለያዩ መከራከሪያ ነጥቦችን በማቅረብ ተከራክሯል።
ፍ/ቤቱም ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ሰኔ 8 ቀን 2003 ዓ/ም በዋለው ችሎት የማህበሩን ካፒታል እና የባለአክሲዮኖቹን የአክሲዮን ድርሻ መጠን ጋር በተያያዘ የተጠየቀው ዳኝነት በፍ/ቤት የሚወሰን አይደለም በማለት በዚህ ረገድ ተጠሪ ያቀረበውን መቃወሚያ ወይም መከራከሪያ ነጥብ በመቀበል ያለፈ ሲሆን ተጠሪ በስራ አስኪያጅነት ኃላፊነታቸው አባክነዋል የተባለውን የድርጅቱን ገንዘብ በተመለከተ ግን ምክንያቶቹን በበለጠ በመተንተንና ግልፅ በማድረግ ክሳቸውን አሻሽለው እንዲያቀርቡ ሲል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ልሎች ከሳሾች ከክሱ በመቅረት የአሁኑ አመልካች ብቻ ሐምል 21 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ የክስ አቤቱታ ከሱን አሻሽያለሁ በማለት ለፍ/ቤቱ ያቀረበ ሲሆን ይህ ተሻሽሎ የቀረበ ነው የተባለው የክሱ ይዘትም ባጭሩ ተከሳሹ ያልከፈሉትን የአክሲዮን ድርሻ ወይም ዋጋ ብር 2,438,255.44 ና እንዲሁም በስራ አስኪያጅነታቸው ዘመን ያባከኑትን የድርጅቱን ገንዘብ ብር 5,488,693.84 ከህጋዊ ወለድ ጋር ታስቦ እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ የሚል ሲሆን ተጠሪም በበኩሉ ክሱ በፍ/ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት ተሻሽሎ አለመቅረቡንና ልሎች ክርክሮችንም በማንሳት መልሱን ሰጥቷል። ቀጥሎም ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ በ15/8/2004 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተሻሽሎ የቀረበው ክስ ፍ/ቤቱ በ8/10/2003 ዓ/ም ከፈቀደው ውጪ መሆኑን ፍ/ቤቱ ለመገንዘብ ችሐል በማለት የተከሳሽን መቃወሚያ በመቀበል ከሳሽ ፍ/ቤቱ በ8/10/2003 ዓ.ም በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ክሱን አሻሽሎ ያቅርብ በማለት ብይን ሰጥቷል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሁኑ አመልካች በ15/8/2004 ዓ/ም የተሰጠው ብይን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 320(2) መሰረት እንዲታረምለት ጉዳዩን እንዲያይ ለተመራለት ልላ ችሎት አቤቱታ በማቅረቡና ችሎቱም በቀረበው አቤቱታ ላይ ተጠሪም የበኩሉን መልስ እንዲሰጥበት ካደረገ በኋላ ጉዳዩን በመመርመር አመልካች ሐምል 21 ቀን 2003 ዓ/ም አሻሽሎ ባቀረበው ክስ የካፒታል መጠን ይወሰንልኝ የሚለውን ጥያቄ ያስቀረ ከመሆኑም በላይ በልላ በኩል ከተከሳሽ የሚጠይቀውን ዳኝነትም በዝርዝር አብራርቶ ያቀረበ በመሆኑና የገንዘብ መጠኑም ቢሆን ጨምሮ መቅረቡ ፍ/ቤቱ ክሱ እንዲሻሻል ትዕዛዝ ሲሰጥ የገንዘብ መጠኑ ከፍ ብሎ እንዳይቀርብ የገደበው ባመሆኑና ይህም ወደፊት ተከሳሹ ይጠየቅበታል? ወይስ አይጠየቅበትም? ተብሎ የሚመረመር እንጂ ከወዲሁ ክሱ እንደገና ይሻሻል ተብሎ ትዕዛዝ የሚሰጥበት ሆኖ ባለመገኘቱ ቀድሞውንም ፍ/ቤቱ በራሱ አነሳሽነት ተሻሽሎ እንዲቀርብ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የቀረበ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ሚያዝያ 15 ቀን 2004 ዓ/ም የሰጠውን ብይን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 320(2) መሰረት ላታረም የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ መሰል ስህተቶችም ለማረም እንደሚቻል የሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ የህግ ትርጉም የሰጠበት በመሆኑ በአመልካች ተሻሽሎ የቀረበው ክስ ተቀባይነት ያለው ነው በማለት ሐምል 21 ቀን 2003 ዓ/ም ተሻሽሎ በቀረበው ክስ ክርክሩ ይቀጥል ሲል ትዕዛዘው ሰጥቷል።
የአሁኑ ተጠሪም ይህንኑ ትዕዛዝ በመቃወም ይግባኝ አቤቱታውን ለፍድራሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በማቅረቡና ችሎቱም ግራ ቀኙ ቀርበው በጉዳዩ ላይ እንዲከራከሩ ካደረገ በኋላ የፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት በ15/8/2004 ዓ/ም እራሱ የሰጠውን ብይን ለጉዳዩ አግባብነት የልለውን የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 320(2) ድንጋጌን መነሻ በማድረግና ያለስልጣኑ መሻሩ ተገቢ አይደለም በማለት ለይግባኝ አቤቱታ መቅረብ መነሻ የሆነውን ትዕዛዝ በመሻር ክርክሩ ሚያዝያ 15 ቀን 2004 ዓዓም በዋለው ችሎት በፍ/ቤቱ በተሰጠው ብይን መሰረት ይቀጥል በማለት ጉዳዩን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 341 መሰረት ወደ ፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመመለስ ወስኗል።
No topics extracted.
አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታም በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟልና ስህተቱ ይታረምልን የሚል ሲሆን አቤቱታውም ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል በመባሉ ተጠሪም ቀርቦ የበኩሉን መልስ የሰጠበት ሲሆን አመልካችም የመልስ መልሱን ሰጥቶበታል።
የጉዳዩ አመጣጥና ይዘት አጠር ባመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 6 ቀን 2004 ዓ/ም በሰጠው ትዕዛዝ አስቀድሞ ሚያዝያ 15 ቀን 2004 ዓ/ም በዋለው ችሎት እራሱ ሰጥቶ የነበረውን ብይን መለወጡ ወይም መሻሩ በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ መመልከቱ አስፈላጊ ሳይሆን መጀመሪያውኑ ሰኔ 6 ቀን 2004 ዓ/ም በፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤቱ በተሰጠው ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ ይቻላል? ወይስ አይቻልም? የሚለውን ነጥብ በጭብጥነት ይዘን ጉዳዩን መርምረናል።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 320(4) ስር የተመለከቱትን የሰው መታሰርና የንብረት ማጣት ጉዳይ የሚመለከቱ ልዩ ሁኔታዎች ካላጋጠሙ በስተቀር በማናቸውም ፍ/ቤት ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜና ከስረ-ነገሩ ፍርድ በፊት በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው ማናቸውም ትዕዛዝ በተሰጠ ጊዜ በትዕዛዙ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ እንደማይቻል ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 320(3) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ ይቻላል። በተያዘው ጉዳዩም የፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 6 ቀን 2004 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ በባህሪው የሰውን መታሰርና የንብረት ማስተላለፍን ወይም ማዛወርን የሚመለከት ትዕዛዝ አይደለም። ይህ ከሆነ ደግሞ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 320(4) ስር የተደነገገው ከተያዘው ጉዳይ ጋር አግባብነት እና ግንኙነት የልለው በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም ማለት ነው።
በልላ በኩል ይህ የፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 6 ቀን 2004 ዓ/ም በዋለው ችሎት ድምዳሜ ላይ ደርሶ በውጤት ደረጃ የሰጠው ትዕዛዝ የአሁኑ አመልካች (የስር ከሳሽ) ሐምል 21 ቀን 2003 ዓ/ም አሻሽሎ ባቀረበው ክስ መሰረት በፍሬ-ጉዳይ ላይ ክርክሩ በግራ ቀኙ መካከል ቀጥሎ ክሱ ይሰማ የሚል ሲሆን ይህ ትዕዛዝም ከስረ-ነገር ፍርድ በፊትና የጉዳዩ መሰማት በግራ ቀኙ መካከል ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ የተሰጠ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው ትዕዛዝ (interlocutory order) ነው ከሚባል በስተቀር በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ወይም እልባት የሰጠ ነው ላባል የሚችል አይደለም። የትዕዛዙ ይዘትና ባህሪይ ይህ ከሆነ ደግሞ ተጠሪ በትዕዛዙ ላይ ቅሬታ ካለውም በስረ-ነገሩ ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ይህንን ቅሬታም ጨምሮ በአንድ ላይ በማጠቃለል ይግባኙን ያቀርባል እንጂ ክርክሩ ቀጥሎ ባለበት ሁኔታ በየጊዜው በሚሰጠው ጊዜያዊ አገልግሎት ባለው ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ በፍ/ብ/ስ/ሰ/ህ/ቁ 320(3) መሰረት የተከለከለ ነው። ስለሆነም የፍድራል ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በትዕዛዙ ላይ በተጠሪ የቀረበለትን የይግባኝ አቤቱታ በዚህ ምክንያት ውድቅ ማድረግ ሲገባው ይህንን አልፎ ይግባኙን በመቀበል ማስተናገዱና ወደ ክርክር ጉዳዩ ገብቶ ውሳኔ መስጠቱ የስነስርዓት ህጉን የተከተለ ባለመሆኑ በውሳኔው ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል።
በመሆኑም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፍድራሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በመ/ በ21/8/2005 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የፍድራሉ ከፍ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ ሰኔ 6 ቀን 2004 ዓ/ም የሰጠው ትዕዛዝ ጊዜያዊ አገልግሎት ያለው (interlocutory order) በመሆኑ በትዕዛዙ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ የሚቻል አይደለም ብለናል።
በፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩ ከቆመበት ጀምሮ እንዲታይ ብለናል። ይፃፍ።
የሰበር ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል፣ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።