No summary available.
ታህሳስ 15 ቀን 200ዓ.ም.
ዳኞች፡ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ግርማ ሰንበት አልቀረቡም ተጠሪ፡- ወ/ሮ አልማዝ ገብረየስ ጠበቃ ወንድወሰን ይልማው ቀረቡ ጉዳዩን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 6 መሰረት በድጋሚ በማየት እንዲያርምልኝ ያቀረብኩትን ማመልከቻ በቂ ህጋዊ ምክንያት የለውም ብሎ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ከዚህ በፊት የአሁን አመልካች/ከሳሽ/ በመሆን ተከራክረዋል አመልካች ተጠሪ የራሳቸው መጸዳጃ ቤት የላቸውም ተከሳሽ ከከሳሽ ጋር የመፀዳጃ ቤት በጋራ በመጠቀም ላይ እያለን ከሳሽ መፀዳጃ ቤቱን በጋራ ለመጠቀም ባለመቻሉ የራሴን መፀዳጃ ቤት ለመገንባት የእድሳት ፈቃድ አውጥተን ከሰራተኞች ጋር ተዋውዬ ቤቱን ማፍረስ ላይ እያለሁ ስራውን እንዳቆም የተደረግሁ በመሆኑ የተፈጠረው ሁከት እንዲወገድና የመፀዳጃ ቤቱን በማደስ ስራውን እንዳጠናቅቅ ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርባ መፀዳጃ ቤቱን የሰራሁት እኔ ነኝ መፀዳጃ ቤቱ የሚገኘው በእኔ ይዞታ ስር ነው በማለት ተከራክራለች ፍርድ ቤቱም የክፍሉን አስተዳደር መፀዳጃ ቤቱ በማን ይዞታ ስር እንደሆነ አረጋግጦ እንዲልክለት ጠይቆ መፀዳጃ ቤቱ በተጠሪ ይዞታ ስር መሆኑን በማረጋገጡ ይዞታው የተጠሪ ነው በማለት ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በጉለል ክፍለ ከተማ የወረዳ 09 አስተዳደር ከዚህ በፊት የሰጠው የባለሙያ ማስረጃ ተገቢነት የልለው መሆኑን አላግባብ የቤት ቁጥር 417 /አመልካች ቤት የጋራ መገልገያ የሆነውን መፀዳጃ ወደ ቤት ቁጥር 418 ያጠቃለላ በመሆኑ ከዚህ በፊት የተፃፈው ደብዳቤ መሻር ያለበት ነው በማለት ጽፏል ስለዚህ ቀደም ተብሎ ተጠሪ የውሳኔ ባለመብት የሆነችው ሀሰተኛን መረጃ መሰረት በማድረግ በመሆኑ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 6 መሰረት ፍርድ በድጋሜ ተይቶ እንዲታረምልኝ በማለት የጉለል ክፍለ ከተማ ቀበል 09 የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት በቁጥር7/ክ/ከ/ወ0 የሰኦ/363/105 ታህሳስ 23 ቀን 2005 ዓ/ም የተፃፈውን ደብዳቤ በመጥቀስ የሰጠውን ማስረጃ በማያያዝ ጥያቄ አቅርቧል የስር ፍርድ ቤት አመልካች ፍርድ እንደገና እንዲታረምለት ያቀረበውን ጥያቄ ለማስረዳት ያቀረባቸው የሰነድ ማስረጃዎች ቀደም ብሎ የተሰጠው ውሳኔ በሀሰተኛና ወንጀል ነክ ተግባሮች በተገኙ የሰነድ ማስረጃዎች መሆኑን የሚያሳይ አይደለም ፍርዱ በድጋሜ የሚታይበት ምክንያት የለም በማለት ሚያዚያ 18 ቀን 2005 ዓ/ም ብይን ሰጥቷል።
አመልካች ሀምል 12 ቀን 2005 ዓ/ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የመጀመሪያው ውሳኔ የተሰጠው በሀሰት ተዘጋጅቶ በተሰጠ ማስረጃ መሰረት መሆኑን የሚሳይ ሰነድ አቅርቤአለሁ ይህም የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 6 መሰፈርት አያሟላም ተብሎ ውድቅ መደረጉ ተገቢነት የልለው ነው በማለት አመልክቷል ተጠሪ መስከረም 13 ቀን 2005 ዓ/ም የመጀመሪያ ውሳኔ የተሰጠው ሀሰተኛና በተጭበረበረ የወንጀል ተግባር መሆኑን የአመልካች ማስረጃ አያሳይም የስር ፍድ ቤት ብይን ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥታለች አመልካች ጥቅምት 4 ቀን 2006 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርባለች።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት የጽሑፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የስር ፍርድ ቤት አመልካች ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የስር ፍድ ቤት አመልካች ከጉለል ከፍለ ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር ያቀረበው ማስረጃ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ አንቀጽ 6/1/ መስፈርት አያሟላም በማለት ውድቅ ማድረጉ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው የስር ፍድ ቤት ይዞታው የተጠሪ ነው ብሎ ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ.ም ለሰጠው ውሳኔ መሰረት የሆነው በጉለል ክፍለከተማ የወረዳ 9 የመሬትናፕሮሰስ ካውንስል የፃፈው ደብዳቤ ቀደም ሲል በሚመለከተው ክፍል በGIS ላይ 9997 ተብሎ የተገለፀው ቦታ የማን ይዞታ እንደሆነ ለማየት የሚያስቸግርና የጋራ መገልገያ መሆኑ ተረጋግጦ የተሰጠውን ውሳኔና የተፃፈውን ደብዳቤ ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባ በመሬት ላይ ይዞታውን /መጸዳጃ ቤቱን/ አመልካችና ተጠሪ በጋራ የሚገለገሉበት መሆኑን የሚደብቅና በቀድሞው የወረዳ 8 ቀበል 11 የቤት ቁጥር 417 ነዋሪ የሆነውን አመልካችን የመፀዳጃና የማብሰያ ቤት ለቤት ቁጥር 418 በማጠቃለል በካርታ ቁጥር 20/11/26812/00 እንዲሰጥ ያደረገ መሆኑን የጉለል ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር አረጋግጦ በደብዳቤ የገለፀ መሆኑን ከስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ተረድተናል።
ይህም ይዞታው የተጠሪ ነው ተብሎ ውሣኔ ለመስጠት መሰረት የሆነው መረጃ እውነታውን የማያሳይና ከዚህ በፊት የተሰጡ አስተዳደራዊ ውሳኔዎችንና የተፃፉ ደብዳቤዎችን አላግባብ በማለፉ የተሰጠ ሀሰተኛ ማስረጃ መሆኑን የሚያሳይ ነው አንድ የመንግስት አካል /ባስልጣን/ እወነተኛውን ሳያጣራ መሰጠት የማይገባውን ሀሰተኛ ማስረጃ ለፍርድ ቤት በመስጠቱ ውሳኔ የተሰጠበት ወገን ማስረጃው ሀሰተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እስካቀረበ ድረስ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 6/1/ መስፈርትን ያላሟላህ ስለሆነ ፍርድ በድጋሜ አይተይልህም መባሉ የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ አንቀጽ 6/1/ መሰረታዊ ዓላማ የሚያሳካ ሆኖ አላገኘውም ምክንያቱም ፍርድ ቤቱ በደጋሚ እንዲታይ የጠየቀው ሰው ሀሰተኛ መረጃ የተሰጠው መንግስት በኃላፊነት ቦታ ላይ ባስቀመጠው ባለስልጣን እና በመንግስት አካል መሆኑን ከማስረዳት አልፎ የመንግስት ባለስልጣን ይህንን ህገወጥ ተግባር የፈፀመበትን ምክንያት እንዲያስረዳ ላጠይቅ የሚገባው እንዳልሆነ ከወንጀል ህጉ አንቀጽ 403 እና አንቀጽ 405 ድንጋጌዎች ከፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 6/1/ ድንጋጌ ጋር በማጣመር በማየት ለመረዳት ይቻላል።
ስለዚህ የስር ፍርድ ቤት ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ/ም ለሰጠው ውሳኔ መሰረት ያደረገው ለክፍሉ አስተዳደር የተፃፈ ደብዳቤ እውነታውን የማያሳይና ሀሰተኛ ማስረጃ መሆኑን የጉለል ክፍለ ከተማ ቀበል 09 አስተዳደር በፃፈው ደብዳቤ የተገለፀ መሆኑ የስር ፍርድ ቤት ፍርዱን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 6/1 መሰረት እንደገና ለማየት በቂና ህጋዊ ምክንያት ያለው ሆኖ አግኝተነዋል ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት ፍርዱን በድጋመ ለማየት በቂ ምክንያት የለም በማለት የሰጠው ብይን መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ወስነናል።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ሚያዚያ 15 ቀን 2005 ዓ/ም የሰጠው ብይን ተሸሯል።
የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 6 መሰረት ጉዳዩን በድጋሜ በማየት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመቀበልና በመስማት እንደዚሁም አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጉዳዩን በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 343/1/ መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጭና ኪሳራ ለየራሳቸው ይቻሉ።
መዝገቡ ተዘግቷል ፤ወደ መዝገብ ቤት ይመስለስ።
No topics extracted.