No summary available.
ታህሳስ 16 ቀን 2006 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ዩቴክ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግ ማህበር - ጠበቃ ረዳኢ ባራኪ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ይህ ጉዳይ የወጭና ኪሣራ አወሣሰን ጉዳይን የሚመለከት ነው። ለወጭና ኪሣራው መነሻ የሆነ የውሳኔ ክፍል ከመስጠቱ በፊት የአሁን 1ኛ ተጠሪ አውራሽ በሆኑት አቶ ፉአድ መሃመድ እና በአቶ አልፍሬድ ፍሪሬቶ መካከል ሐምል 26 ቀን 1991 ዓ/ም በብር 350,000.00(ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) የተደረገን የቤት ሽያጭ ውልን መነሻ ያደረገ ክርክር በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተደርጎ ሻጭ አቶ አልፍሬድ ፍሪሬቶ ቤቱን ለገዥ አቶ ፉአድ መሃመድ እንዲያስረክቡ ህዳር 30 ቀን 2003 ዓ/ም በዋለው ችሎት ውሳኔ አግኝቶ የነበረ ሲሆን የአሁኑ አመልካች ቤቱን ህዳር 30 ቀን 2001 ዓ/ም በሕጋዊ የሽያጭ ውል በብር 2,000,000.00(ሁለት ሚላዩን ብር) ከአሁኑ 2ኛ ተጠሪዎች አውራሽ የገዛው መሆኑን ጠቅሶ ውሳኔን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ተቃውሞ ቀርቧል።ተቃውሞ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ ሻጭ ከአሁኑ አመልካች ጋር ሕጋዊ ሽያጭ ውል አድርጎ እያለ ከቅን ልቦና ውጪ ከአቶ ፉአድ መሃመድ በድጋሚ መሸጣቸው ያላግባብ መሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት የቀድሞውን ውሳኔ በመሻር ቤቱን የአሁኑ አመልካች ላለቅ አይገባም ሲል ወስኗል።ይህ ውሳኔ በበላይ ፍርድ ቤቶች ያልተለወጠ ሲሆን ወጪና ኪሳራን በተመለከተ ደግሞ የአቶ ፉአድ መሃመድ ወራሽ ዝርዝሩን የማቅረብ መብታቸውን ሲጠብቅ የአሁኑን አመልካች ጥያቄ ግን በዝምታ አልፎታል። አመልካች የወጪና ኪሳራ ይተካልኝ ጥያቄ በተመለከተ በዝምታ በመታለፉ ምክንያት ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም።የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ከቅን ልቦና ውጪ ለተደረገ የሽያጭ ውል ለክርክር የተዳረገ መሆኑ እየታወቀ የበታች ፍርድ ቤቶች የወጪና ኪሳራ ዝርዝሩን ማለፋቸው ያላግባብ ነው የሚል ነው።አቤቱታው ተመርምሮም አንደኛ ተጠሪን በተመለከተ ለሰበር ሰሚ ችሎት የሚያስቀርብ የሕግ ነጥብ የለውም ተብሎ የተዘጋ ሲሆን 2ኛ ተጠሪዎችን በተመለከተ ግን ያስቀርባል ተብሎ በመታዘዙ ለተጠሪዎች በሕጉ አግባብ በጋዜጣ ጥሪ ተደርጎላቸው ባለመቅረባቸው በፅሑፍ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፏል።
የጉዳዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምረናል። የዚህን ችሎት ምላሽ የሚያስፈልገው አብይ ጭብጥ አመልካች በ2ኛ ተጠሪዎች አውራሽ ቅን ልቦና ውጪ በሆነ ተግባር ለክርክር የተዳረገ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የወጪና ኪሳራ ጥያቄው በዝምታ መታለፉ በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም?
የሚል ነው።
በመሰረቱ ክርክር ተጠናቆ በፍርድ እንዲቋጭ ሲደረግ ለዚህ ፍርድ ምክንያት የሆነው ክርክር ስላስከተለው ወጭና ኪሣራ ጉዳይ በፍርድ ተካቶ ላወሰን እንደሚገባ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 183 ሥር ተመልክቷል ። ዝርዝር አወሣሰኑም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 462-464 ተደንግጓል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 462 እንደተመለከተው በክርክር ምክንያት የወጣን ወጭና ኪሣራ ማን እንደሚከፍልና ምን ያህል እንደሚከፍል ፍ/ቤቱ በመሰለው ላወስን እንደሚችል ፈቃደ- ስልጣን እንዳለው በግልጽ ተመልክቷል። የዚሁ ድንጋጌ ተከታይ የሆነው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 463 ደግሞ በዚሁ ሕግ የተሰጠው ፈቃደ ስልጣን ተጠቅሞ ፍ/ቤቱ ማን ይክፈል?
የሚለውን በመለየት ከግምት ውስጥ ላገቡ የሚገባቸውን ጉዳዩች ሁሉ ተመልክቶና አረጋግጦ ተረቺ ለረቺ ይክፍል ብሎ ላያዝ እንደሚችል ያሳያል።የወጪና ኪሳራ ድንጋጌዎች መሰረታዊ አላማም ሰዎች ያላግባብ ለክርክር እንዳይዳረጉ መከላከል መሆኑ የሚታመን ነው።ክርክሩ ከሕግ ውጪ የቀረበ መሆኑ ከታወቀ ደግሞ ለክርክሩ ያላግባብ የተዳረገ ወገን በክርክሩ ምክንያት ያወጣውን ወጪና ኪሳራ ለዚሁ የዳረገው ወገን ላተካለት ይገባል ።በእርግጥ የክርክሩ ረቺ የሆነ ወገን ሁሉ ወጪና ኪሳራ ይተካለት ማለት እንዳልሆነ ከድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።ሆኖም አንድ ተከራካሪ ወገን በልላኛው ተከራካሪ ወገን ቅን ልቦና ውጪ በሆነ ተግባር ለክርክር ተዳርጎ መገኘቱ ከተረጋገጠ የወጪና ኪሳራ ጥያቄ ውድቅ ማድረግ የስነ ስርዓት ሕጉ ላያሳካ ከአሰበው ዓላማ ውጪ በመሆኑ የሕግ መሰረት የልለው ነው።በመሆኑም የውጪና ኪሳራ ጥያቄን አስመልክቶ ፍርድ ቤቱ በመጠኑ ላይ በሕጉ ስልጣን የተሰጠው መሆኑና ረቺ ሁልጊዜ ወጪና ኪሳራ እንዲተካለት መደረግ የልለበት መሆኑ ግንዛቤ የሚወሰድበት ቢሆንም ከቅን ልቦና ውጪ ለክርክር የተጋበዘውን ወገን በተመለከተ ግን የክርክሩ ረቺ መሆኑ እስከታወቀ ድረስ ቅን ልቦና ከልለው ወገን በክርክሩ ምክንያት ያወጣውን ወጪ እንዲተካለት ማድረግ ክርክሮች ያላግባብ እንዳይፈጠሩ የማድረግ ውጤት ያለው በመሆኑ ተግባራዊ ላደረግ የሚገባው ነው።
No topics extracted.
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመጣም አመልካች በ2ኛ ተጠሪዎች አውራሽ ከቅን ልቦና ውጪ በሆነ ምክንያት ለክርክሩ መዳረጉን የስር ፍርድ ቤት በውሳኔው በሚገባ ያረጋገጠው ጉዳይ ሲሆን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም በዚህ ረገድ የተለየ ድምዳሜ የልለው መሆኑን የትዕዛዙ ድምዳሜ አስረጅ ነው።በመሆኑም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 463 እና 464 በተመለከተው መሰረት የግራ ቀኙ ክርክር ስላስከተለው ወጭና ኪሣራ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪዎች ለአመልካች የመተካት ግድታ ላኖርባቸው ይገባል።ተጠሪዎች ላተኩ የሚገባው የወጪና ኪሳራ መጠን ደግሞ አመልካች ዝርዝሩን አቅርቦ ግራ ቀኙ ክርክር አድርገውበትና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 462 “………… ምን ያህል ይክፈል………” የሚለውን በሚመለከት በሕጉ ለፍ/ቤቱ የተሰጠውን ፈቃደ ስልጣን ሁሉ በመጠቀም የሚወሰን ሁኖ አግኝተናል።
ከዚህ አንፃር ጉዳዩን ስንመለከተው የስር ፍርድ ቤት አመልከች በ2ኛ ተጠሪዎች አውራሽ ቅን ልቦና መሰረት ባላደረገ ሁኔታ ለክርክር የተዳረገ መሆኑ አረጋግጠው እያለ የወጪና ኪሳራውን ጥያቄ በዝምታ ማለፉም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይህንን የስር ፍርድ ቤት የውሳኔ ክፍል ሳያርም መቅረቱ ወጭና ኪሣራ አወሣሰን ትክክለኛ አፈፃፀም የተከተለ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 14 ቀን 2005 ዓ/ም በአመልካች የቀረበውን ወጪና ኪሳራን አስመልክቶ የሰጠው የውሳኔ ክፍልና በዚሁ የውሳኔ ክፍል አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርቦ በመ/ ሚያዚያ 29 ቀን 2005 ዓ/ም የተሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች የወጪና ኪሳራ ዝርዝሩን ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ የማስወሰን መብት አለው ብለናል።ይፃፍ።
የዚህ የሰበር ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ አመልካች የራሱን ይቻል ብለናል።