No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ቄስ ዳንኤል አርኬ ከጠበቃ ሙሉጌታ ዱላ ጋር ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የኮልፍ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ - አልቀረበችም።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የይግባኝ አቤቱታ የማቅረቢያ ጊዜ አልፏል ወይስ አላለፈም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ በግራ ቀኙ መካከል በተደረገው ክርክር ከተረጋገጠውና ይህንኑ የተረጋገጠውን ጉዳይ መነሻ አድርጎ ይግባኝ ሰሚው የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለዚሁ ጭብጥ ከሰጠው የመጨረሻ ዳኝነት ጋር አገናዝበን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
በዋናው ጉዳይ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ፍርድ ሰጥቶ ግራ ቀኙን ካሰናበተ በኋላ የአሁኗ ተጠሪ ግንቦት 21 2004 ዓ.ም በተፃፈ አቤቱታ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 208 መሰረት በጠየቁት ዳኝነት መሰረት ፍርድ ቤቱ የአሁን አመልካችን ሳይጠራ ጉዳዩን እንደገና ተመልክቶ ግንቦት 22 ቀን 2004 በጥያቄው መሰረት ዳኝነት የሰጠበት ስለመሆኑ፤
እንዲሁም ይህ መዝገብ ከተዘጋ በኋላ ትዕዛዝ የተሰጠ በመሆኑ የአሁን አመልካች በፍርድ አፈፃፀም መምሪያ በኩል ሐምል 13 ቀን 2004 ዓ.ም የደረሰው ስለመሆኑ የአሁን ተጠሪ ማስተባበያ ያቀረበበት በመሆኑና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም እነዚህኑ ፍሬ ነገሮች መነሻ አድርጎ ዳኝነት የሰጠበት እንደመሆኑ መጠን እነዚህ ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ፍሬነገሮች የተረጋገጡ ጉዳዮች ናቸው።
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የቀረበለትን የይግባኝ ማስፈቀጃ ጥያቄ በይግባኝ ከተመለከተ በኋላ ለአሁን አመልካች የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ዳኝነት ከደረሳቸው ጊዜ ጀምሮ ሲታሰብ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው ከማለፉ በፊት 9 ቀን የነበራቸው ከመሆኑ አንፃር በዚህ በዘጠኝ ቀን ጊዜ ውስጥ የይግባኝ አቤቱታ አዘጋጅቶ የይግባኝ አቤቱታውን ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ለማቅረብ በቂ ጊዜ የነበራቸው ሆኖ እያለ በዚህ ጊዜ ውስጥ ሳያቀርቡ ምክንያት አለኝ ይፈቀዳልኝ በሚል ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል።
ሆኖም ከላይ እንደተጠቀሰው የይግባኝ አቤቱታ ላቀርብልኝ ይገባል በማለት የአሁን አመልካች ጥያቄ ያቀረቡበት ዳኝነት የተሰጠው መዝገብ ከተዘጋ በኋላ እንደገና ከተንቀሳቀሰ በኋላ ስለሆነ፤
በዚህ አኳኋን ተንቀሳቅሶ በታየው ጉዳይ ላይ የአሁን አመልካች የበኩላቸውን ክርክር ማቅረብ ይችሉ ዘንድ የመደመጥ መብታቸው እንዲከበር ጥሪ ያልተደረገላቸው ከመሆኑም በላይ መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ ተንቀሳቅሶ ዳኝነት የተሰጠበት ስለመሆኑ እርሷ በጊዜው እንዲያውቁት አልተደረገም።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ የተቀመጠው የ60 ቀን የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ታሳቢ የሚያደርገው ተከራካሪው ባሉበት ውሳኔ መስጠቱን ወይም ለውሳኔ የሚያበቃ ክርክር የተደረገ መሆኑን ተረድቶ ቀርቦ ለመከታተል እና የዳኝነቱን ውጤት ለመስማትም ሆነ ለማወቅ ያልፈለገውን ወይም ደግሞ የተከራካሪው የመደመጥ መብት ይከበር ይቻል ዘንድ በሕጉ በተዘረጋው መረዳት መሰረት በአግባቡ ጥሪ ተደርጎለት በጥሪው መሰረት ክርክሩን በአግባቡ ለመምራት ያልቻለ እንደሆነ የይግባኝ አቤቱታ ማቅረቢያ ጊዜው ውሳኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ይህ የ60 ቀን ጊዜ መታሰብ ያለበት ስለመሆኑ ነው።
በዚህ ጉዳይ የአሁን አመልካች ሳይጠራ ዳኝነት የተሰጠ በመሆኑ አመልካች ሳይጠራ ግንቦት 22 ቀን 2004 ዓ.ም የተዘጋው መዝገቡ ተንቀሳቅሶ ዳኝነት የተሰጠ መሆኑን እንዲያውቀው በጊዜው ያልተደረገ መሆኑ እስከተረጋገጠ ጊዜ ድረስ ይህ በሕጉ በተቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ተጠቃሚ ላሆን እንዳልቻለ ተገንዝበናል። በዚህ ሕጉ ታሳቢ አድርጎ ባስቀመጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ተጠቃሚ ላሆን እንደሚቻል ከተረጋገጠ ደግሞ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው በቂ ነበረ ወይስ አልነበረም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ ዳኝነቱ መሰጠቱን ከተረዳበት ጊዜ ጀምሮ ከቀረው ዘጠኝ ቀን አንፃር በማየት ዘጠኝ ቀን የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ ያስችል ነበር አልነበረም ከሚለው አንፃር ላታይ የሚገባው አይደለም።
አመልካች በሕጉ ከተሰጠው የ60 ቀን የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ውስጥ 51 ቀን በፍርድ ቤቱ በተፈፀመው ሥነ ሥርዓት ጉድለት ሳቢያ የባከነበት መሆኑ እስከተረጋገጠ ጊዜ ድረስ አመልካች የይግባኝ ማስፈቀጃ አቤቱታ የቀረው የዘጠኝ ቀን ጊዜ በቂ መሆኑና አለመሆኑ መለኪያ ላሆን የሚገባ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም መዝገቡ ከተዘጋ በኋላ የአሁን አመልካች ስለመንቀሳቀሱም ሆነ የመደመጥ መበቱ እንዲከበር ሳይጠራ ዳኝነቱ መስጠቱ እየታወቀ በዚህም ምክንያት በሕጉ በተሰጠው የ60 ቀን የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ተጠቃሚ ላሆን የሚችልበት አግባብ ላጠበቅ እንዳልልቻለ እየታወቀ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይህንኑ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳያስገባ በቀረው የዘጠኝ ቀን ጊዜ ብቻ ተወስኖ ይህ ዘጠኝ ቀን በጉዳዩ ላይ የይግባኝ አቤቱታ ለማቅረብ በቂ ነበር ወይስ አልነበረም?
No topics extracted.
ከሚለው ማነፃፀሪያ አኳያ ብቻ ተመልክቶ ማስፈቀጃው ተቀባይነት የለውም በሚል የሰጠው ዳኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
ይግባኝ ሰሚው የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የይግባኝ ማስፈቀጃውን ጉዳይ ተመልክቶ በኮ/መ/ በቀን 7/5/2005 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የአሁን አመልካች በሕጉ በተሰጠው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ለመጠቀም በሚያስችላቸው ደረጃ የተሰጠ ዳኝነት በመሆኑ ይህ ዳኝነት መሰጠቱን ከተረዳበት ጊዜ ከሐምል 13 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ የይግባኝ አቤቱታ እስካቀረቡበት ጊዜ ድረስ ሲሰላ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜው እንዳለፈባቸው ስለማይቆጠር በጉዳዩ ላይ የይግባኝ አቤቱታቸውን አቅርበው እንዲያሰሙ ላፈቀድ ይገባል ብለናል፡ ተፈቅዷል።
በዚህ በሰበር ደረጃ ግራ ቀኙ ያደረጉት ክርክር ላስከተለው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ።