No summary available.
ግንቦት 23 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ አዳነ ንጉሴ አመልካቾች፡-
ወ/ት ፍሬወይኒ አለም በ VC ቀርባለች።
ወ/ት ሣምራዊት አለም
አቶ በረከት አለም፡ አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ አለም መሐሪ ጠበቃ አቶ ምናስቦ ገብሩ ቀርቧል።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ ከንብረት ግምት ክፍያ ጋር ተያይዞ የቀረበ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው ያሁኑ ተጠሪ በአመልካቾች ላይ በት/ብ/ክ መንግስት አዲግራት ወረዳ ፍ/ቤት በመሰረተው ክስ መነሻነት ነው። የክሱ ይዘትም ተጠሪ ከወ/ሮ አለምነሽ ተ/ብርሃን ጋር በትዳር ተሳስሮ በመኖር ላይ ሳሉ በመካከል ለስራ ወደ ምዕራብ ትግራይ ሄዶ በቆዩበት ወቅት አመልካቾች የተጠሪን የመጥፋት ውሣኔ በማሳወጅና ከዚያ በኋላም ውርስ እንዲጣራ በማድረግ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን በተጠሪ ስም ተመዝግቦ የነበረው ግምቱ ብር 80,000 የሆኑ 4 ክፍል ቤቶች ግማሹ ድርሻ ወደ ባለቤታቸው ስም ቀሪውን የተጠሪ ግማሽ ድርሻ ደግሞ ወራሾች ለሆኑት ወደ አመልካቾች ስም በማዘጋጃ ቤት በኩል ተላልፎ እንዲመዘገብ ተደርጓል። ይሁን እንጂ ተጠሪ አሁን ለስራ ከሄድኩበት ተመልሼ አመልካቾች የሰጡትን የመጥፋት ውሣኔም ስላስነሳው በዚህ ምክንያት ተወርሶና ወደ አመልካቾች ስም ተላልፎ የነበረው የቤቱ ግማሽ ድርሻዬ ወይም ንብረቴን እንዲመልሱልኝ በማለት ዳኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። ያሁኑ አመልካቾች /የስር ተከሣሾች/ በበኩላቸው ቀርበው ለክሱ በሰጡት መልስ የቤቱ ግምት ብር 80,000 ሳይሆን ከ200,000 በላይ መሆኑንና ከመጥፋቱ በፊት በተጠሪ ስም የነበረው ባዶ መሬት ብቻ መሆኑንና የባዶ መሬት ባለቤት ደግሞ መንግስት እንጂ ተጠሪ ባለመሆኑና ተጠሪ ከጠፋ በኋላ በባዶ መሬቱ ላይ ሀብታችን አፍስሰን የሰራነውን ቤት ከ 18 ዓመት በኋላ መጥቶ ላጠይቅ እንደማይገባ በመጀመሪያ መቃወሚያነት የተከራከሩ ሲሆን ፍሬ-ጉዳዩን በተመለከተም ቤቱ በባዶ መሬት ላይ በእኛ በአመልካቾች መሰራቱ ታውቆ በህጋዊ መንገድ ወደ ስማችን የተዛወረ በመሆኑ የተጠሪ አይደለም። ሆኖም ግን ባዶ መሬቱ ለተጠሪ ላሆን ይገባል ከተባለም ቤቱ በባለሙያ ተገምቶና በግምቱ መሰረት ክፍያ እንዲፈፀምላቸው ተከራክሯል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ወረዳ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር 5 የአመልካቾች ምስክሮች ሰምቶ በተጠሪ በኩል ከቀረቡት ሰነድ ማስረጃዎች ጋርም በማገናዘብ ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ምንም እንኳ ቤቱን የሰሩት አመልካቾች ስለመሆናቸው በእነሱ በኩል ቀርበው በተሾሙት ምስክሮች ቢነገርም ከዚህ ቀደም ውርሱ በአመልካቾች እንዲጣራ ሲደረግ ቤቱ የተጠሪ እንደሆነ በውርስ አጣሪ ሪፖርቱ ላይ የተገለፁ በመሆኑና አሁን ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ ቤቱ የአመልካቾች ነው በማለት የቀረበው ክርክር እርስ በራሱ የሚጣረስ በመሆኑ ክርክሩ ተቀባይነት የልለው በመሆኑ ለክርክሩ መነሻ የሆነውና ወደ አመልካቾች ስም የተላለፈው ሁለቱ ክፍል ቤቶች ለተጠሪ ይመለስ በማለት ወስኗል።
የአሁኑ አመልካቾችም በተሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ አቤቱታቸውን ለምስራቃዊ ዞን ማዕከላይ ፍ/ቤት አቅርበውና ግራ ቀኙም ቀርበው እንዲከራከሩ ከተደረገ በኋላ ክርክር የተነሳበት ቤት በአመልካቾች መሰራቱ ተረጋግጦ ሳለ አመልካቾች ያለ ምንም ግምት ክፍያ ቤቱን ለቀው ለተጠሪ ላመልሱ ይገባል በማለት የተሰጠው ውሣኔ አለአግባብ መሆኑን ከገለፁ በኋላ ተጠሪ በባለሙያ ተገምቶ በቀረበው ግምት መሰረት የቤቱን ግምት ብር 160,482.765 ለአመልካቾች ከከፈሉ በኋላ ቤቱ ተመልሶለት በስሙ እንዲመዘገብ በማለት የወረዳ ፍ/ቤቱን ውሣኔ በማሻሻል ወስኗል።
ተጠሪ በበኩሉ ይህንን ውሣኔ በመቃወም የይግባኝ አቤቱታውን ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርቦ ግራ ቀኙ ቀርበው እንዲከራከሩ ከተደረገ በኋላ አመልካቾች የቤቱ ግምት እንዲከፈላቸው ያቀረቡት ክስ ወይም የተከሣሽ ከሳሽነት ክስ በልለበትና እንዲሁም በአመልካቾች የተከፈለ የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ ሳይኖር ተጠሪ ራሱ ዳኝነት ከፍሎ ባስከፈተው መዝገብ ላይ ብር 160,482.765 እንዲከፈላቸው በዞኑ ፍ/ቤት መወሰኑ ስነ-ስርዓታዊ አይደለም በማለት ይህንን በሚመለከት የተሰጠውን የውሣኔ ክፍል ሽሮ ሆኖም ግን ንብረቱ ለተጠሪ ላመለስ ይገባል በማለት በበታች ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ውሣኔ /የውሣኔ ክፍል/ በማፅናትና አመልካቾችም በቦታው ላይ ሀብታቸውን አፍስሰናል የሚሉ ከሆነ ይህንን በህጉ አግባብ የመጠየቅ መብታቸው የተጠበቀ መሆኑን በመግለፅ ውሣኔ ሰጥቷል።
No topics extracted.
አመልካቾች ደግሞ በተራቸው በክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የተሰጠውን ውሣኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ሰበር ችሎት ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታው በድምፅ ብልጫ ተቀባይነት አላገኘም።
አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታም ይህንኑ በክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ተወስኖና በክልሉ ሰበር ችሎት ድምፅ ብልጫ የፀናውን በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም በአንድ በኩል ንብረቱ ለተጠሪ ይመለስ እየተባለ በልላ በኩል ደግሞ እኛ አመልካቾች የንብረታችንን ግምት ከሳችሁ ጠይቁ በማለት የተሰጠው ውሣኔ ጊዜና ጉልበት ከማባከን ውጪ ልላ ለውጥ ስለልለው ውሣኔው ተሽሮ በፍ/ብ/ህ/ቁ 171/1/ ድንጋጌ መሰረት ያፈሰስነው ሀብት ግምታችን እንዲከፈለን ይወሰንልን በማለት አመልክተዋል። አቤቱታውም ተመርምሮ ለሰበር ችሎት ቀርቦ ላታይ ይገባል በመባሉ ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ የበኩሉን መልስ የሰጠበት ሲሆን አመልካቾችም የመ/መልሳቸውን ሰጥተውበታል።
የጉዳዩ አመጣጥና ይዘት አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሣኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል። እንደመረመርነውም የሰበር አቤቱታ በቀረበበት ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል ለማለት ይቻላል? ወይስ አይቻልም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ተይዞ ላመረምር የሚገባ ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክር ሂደቱ መገንዘብ እንደሚቻለው ከሳሽ የነበረው የአሁን ተጠሪ ከፍ ሲል እንደተገለፀው ዳኝነት ጠይቆ እየተከራከረ ያለው ወደ አመልካቾች ዞሮ የነበረው ንብረቴ ይመለስልኝ በማለት ነው። አመልካቾችም በበኩላቸው ንብረቱ ለተጠሪ የሚመለስ ከሆነ በቦታው ላይ ያፈሰስነው ሀብት በባለሙያ ተገምቶ ግምቱ ላከፈለኝ ይገባል የሚል መከራከሪያ ነጥብ በማቅረብ እየተከራከሩ ያሉ መሆናቸውን መገንዘብ ችለናል። ሆኖም ግን አመልካቾች በስር ፍ/ቤት ተከሳሾች እንደመሆናቸውና እነሱም በበኩላቸው ከተጠሪ የሚጠይቁት መብት ካላቸው በህጉ አግባብና በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 234/1/ /ረ/ መሰረት ከመከላከያ መልሳቸው ጋር የዳኝነት አገልግሎት ክፍያ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 215/2/ ስር እንደተመለከተው በመፈፀም በተከሳሽ ከሳሽነት ክስ የተጠቀሰው የቤቱ ግምት እንዲከፈላቸው በሚል የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ የለም። በዚህ አግባብ ተሟልቶ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ በለልበት ደግሞ ዳኝነቱ ላሰጥ አይችልም።
በልላ በኩል ከፍ ሲል እንደተገለፀው የአመልካቾች ክርክር የቤቱ ግምት እንዲከፈላቸው ይወሰንልን በማለት ከመከራከር ውጭ ጨርሶ ቤቱንም ልናስረክብ አይገባም የሚል አይደለም። ጥያቄያቸው ይህ ከሆነ ደግሞ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም ሆነ ሰበር ችሎቱ ግምቱ ላከፈላቸው አይገባም በሚል ውሣኔ የሰጡ ሣይሆን ይህ የዳኝነት ጥያቄቸው በዳኝነት አካሉ ተቀባይነት አግኝቶ ላስተናገድ የሚገባው መጀመሪያውኑ በህጉ አግባብ ስርዓቱን ጠብቆ ሲቀርብ መሆኑን በማለት ነው። አመልካቾችም እራሳቸው ይህንኑ መሆኑን ተረድተው ይህ አከራካሪው የቤቱ ግምት እንዲከፈላቸው በተጠሪ ላይ ስልጣን ላለው ፍ/ቤት አዲስ ክስ ማቅረባቸውን ተጠሪ ለሰበር አቤቱታ መልሱን ሲሰጥ ጠቅሶ ባቀረበው ክርክር ላይ ምንም ያሉት ነገር የለም ይህ ደግሞ እርግጥም እንደተባለው በዚህ ጉዳይ አዲስ ክስ ያቀረቡ መሆናቸውን በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 234/1/ /ሰ/ እና 235 /2/ ስር እንደተመለከተው እንደመሆኑ ተቆጥሮ የሚወሰድ ይሆናል።
ሲጠቃለል ከፍ ሲል በተገለፁት ምክንያቶች የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አመልካቾች የዳኝነት አገልግሎት ፈፅመው ዳኝነቱንም በስርዓቱ ባላቀረቡበት ሁኔታ ይህ የተጠቀሰው የቤቱ ግምት ብር 160,482.765 ተጠሪ ራሱ ዳኝነት ከፍሎ ባስከፈተው መዝገብ ላይ ላወሰንላቸው አይገባም በማለት ተወስኖ በሰበር ችሎቱም በድምፅ ብልጫ እንዲፀና በማለት በተሰጠው ትአዛዝ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አላገኘንም በመሆኑም ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መ/ ጥቅምት 26 ቀን 2005 በዋለው ችሎት ተወስኖ በክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት መ/ ህዳር 17 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት በትእዛዝ የፀናው በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
አመልካቾች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም።
በዚህ መዝገብ ላይ ተሰጥቶ የነበረው የአፈፃፀም እግድ ተነስቷል። ይፃፍ።
የሰበር ክርክር ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።