No summary available.
ሰኔ 03 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ቴዎድሮስ አማረ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አዲሱ ፍሰሃ ጠበቃ አቶ አባቡ ሞላ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የቀረበው የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአላማጣ ምድብ ችሎት በመዝገብ ህዳር 19 ቀን 2ዐዐ5ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትና የሰበር ችሎት መጽናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዲሽርልኝ በማለት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት አላማጣ ምድብ ችሎት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበው ክስ ነው። ተጠሪ ሟች ወ/ሮ አስካለ አርአያ መስከረም 1ዐ ቀን 1993ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። ሟች ተወላጅና እናትና አባታቸው የልሉ በመሆኑ በእናት መስመር የተከሣሽ/ አመልካች/ እናት የሆነችው ወ/ሮ አረጋነሽ አርአያ በእናት መስመር የእናቷ ልጅ የሆነችው ወ/ሮ ብርታንጉ ፋንታዬ ወራሾች መሆናቸው በወፍላ ወረዳ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 0793 02- 06-1993ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ተረጋግጧል። ወ/ሮ ብርታንጉ ፋንታዬ የሟች አስካለ አርአያ ወራሽ መሆኑን ካረጋገጠች በኋላ ከዘጠኝ ዓመት በኋላ ህዳር 28 ቀን 2ዐዐ1ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። እኔ የሟች ብርታንጉ ፈንታዬ ተተኪ ወራሽ መሆኔ የሰቆጣ ወረዳ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 46ዐ9 ታህሣስ 16 ቀን 2ዐዐ1ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ተረጋግጧል። ስለሆነም አውራሽ ወ/ሮ ብርታንጉ ፈንታዬ ከሟች አስካሉ አርአያ በኮረም ከተማ ዐ1 ቀበል ከሰራችው ሁለት ክፍል ቤት የሚደርሳት አንድ ክፍል ቤት ተከሣሽ እንዲያስረክበኝና ስመ ንብረቱ እንዲዛወርልኝ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል።
አመልካች በተከሣሽነት ቀርቦ ከሣሸ ተጠሪ ከዚህ በፊት በኮረም ወረዳ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦብኝ የወረዳው ፍ/ቤት ጥር 2 ቀን 2ዐዐ4ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቶበታል።
ስለዚህ ጉዳዩ በፍርድ ያለቀ ስለሆነ በድጋሚ ላቀርቡብኝ አይገባም የሚል ልሎች መከራከሪያዎችን አቅርቧል። የአላማጣ ምድብ ችሎት የኮረም ከተማ ፍርድ ቤት ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም የተጠሪንና የአመልካችን ክርክር ከሰማ በኃላ የተከሣሽን /የተጠሪን/ ክስ ውድቅ በማድረግ ውሣኔ የሰጠ መሆኑ ገልፆ የከሣሽ /ተጠሪ/ መኖሪያ አማራ ክልል ሰቆጣ ከተማ የተከሣሽ መኖሪያ ትግራይ ኦፍላ ወረዳ መሆኑ ተረጋግጧል። በአዋጅ ቁጥር 25/1985 አንቀጽ 5/2/ መሰረት ስልጣኑ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሆኑ የኮረም ወረዳ ፍርድ ቤት በልለው የዳኝነት ስልጣን የሰጠውን ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ ጉዳዩ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት ታይቶ እንዳይወሰን የሚገድብ አይደለም በማለት የአመልካችን መቃወሟያ ውድቅ አድርጎታል። የአመልካቾችና የተጠሪን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኃላ አመልካች አንድ ክፍል ቤት ለተጠሪ እንዲያካፍል ውሣኔ ሰጥቷል። ይህ ውሣኔ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትና የሰበር ችሎት ፀንቷል።
አመልካች ታህሣስ 19 ቀን 2004 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የኮረም ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በይግባኝ ሣይሻር የአላማጣ ምድብ ችሎት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 5/1/ ድንጋጌ በተዛባ መንገድ በመተርጐም ያቀረቡኩትን የመጀመሪያ የፍርድ መቃወሚያ በማለፉ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ተጠሪ በሟች አስካለ አርአያ ጋር ምንም አይነት ዝምድና የልለው በመሆኑ የውርስ ንብረት አንዲካፈል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩሉ የካቲት 27 ቀን 2005 ዓ.ም በተፃፈ መልስ አውራሽ ቀደም ብላ ሟች አስካለ አርአያን ወራሽ መሆኗን አረጋግጣለች የኮረም ወረዳ ፍርድ ቤት ጥር 5 ቀን 2004 ዓ.ም ከሥር ነገር የዳኝነት ስልጣኑ ውጭ በማየት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ አለመሆኑን በማየት ዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአላማጣ ምድር ችሎት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ተከራክሯል። አመልካች መጋቢት 25 ቀን 2005 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የሥር የክርክሩ አመጣጥና በዚህ ሰበር ችሎት ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አላማጣ ምድብ ችሎት ቀደም ሲል በኮረም ወረዳ ፍርድ ቤት ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፣ ስልጣን ባለው ፍርድ ቤት የተሰጠ አይደለም በማለት ተጠሪ ያቀረበለትን ክስ በማየት የሰጠውን ውሣኔ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትና የሰበር ችሎት ማፅናታቸው የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ ጉዳዩን መርምረናል።
ጉዳዩን እንደመረመርነው ተጠሪ አመልካች የሟች አስካለ አርአያ የውርስ ንብረት የሆነውንና በኮረም ከተማ የሚገኘውን ቤት እንዲያካፍለው በኮረም ከተማ ምድብ ችሎት ክስ አቅርቦ፣ የኮረም ከተማ ምድብ ችሎት የተጠሪን /የከሣሽንና/ የአመልካችን /የተከሣሽን/ ክርክር ህዳር 10 ቀን 2004 ዓ.ም ከሰማ በኋላ የከሣሽን ክስ ውድቅ በማድረግ ጥር 2 ቀን ዓ.ም ብይን የሰጠ መሆኑን የከፍተኛው ፍርድ ቤት የአላማጣ ምድብ ችሎት ያረጋገጠው ፍሬ ጉዳይ ነው። በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 79 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት የዳኝነት ስልጣን ያለው የኮረም ከተማ ምድብ ችሎት ተጠሪ አመልካች ቤቱን እንዳካፍለው ያቀረበውን ክስ በማየት ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 320/1/፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 314፣ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 327 እና ልሎች አስገዳጅ የስነ ስርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ ቀርቦበት አልተሻረም ወይም አልተለወጠም። ተጠሪ የኮረም ወረዳ ምድብ ችሎት በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 5/2/ የተደነገገውን በመተላለፍ፣ በሁለት ክልል ኗዋሪዎች መካከል የተነሣውን ክርክር በማየት ውሣኔ መሰጠቱ የሕገ መንግስቱን አንቀጽ 80 ንዑስ አንቀጽ 4 የሚቃረን ስለሆነ በይግባኝ ታይቶ እንዲሻርለት ስልጣን ላለው ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ፣ የኮረም ምድብ ችሎት ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ ያላሻረ በመሆኑ ውሣኔው በጉዳዩ ላይ የመጨረሻና አስገዳጅነት ያለው መሆኑ የሚቀርበት ምክንያት የለም።
የኮረም ምድብ ችሎት ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በሕግ ከተሰጠው የስረ ነገር የዳኝነት ስልጣን ውጭ የሆነ ጉዳይ በማየት የሰጠው ቢሆንም፣ ይህ ውሣኔ በይግባኝ ታይቶ እንዲታረም ካልተደረገ በስተቀር በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 212 በጉዳዩ ላይ አስገዳጅነት ያለውና የመጨረሻ ውሣኔ ነው።
በመሆኑም የኮረም ምድብ ችሎት ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት በይግባኝ ወይም በሰበር ታይቶ ባልተሻረበት ሁኔታ በዚያው ጉዳይ ተጠሪ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አላማጣ ምድብ ችሎት በመዝገብ ያቀረበው ክስ የፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ የሚቃረን በመሆኑ ተቀባይነት የልለው ነው። የአላማጣ ምድብ ችሎት በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 5/1/ የተዛባ ትርጉም መስጠት የኮረም ምድብ ችሎት ቀርቦ ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም በፍርድ ባለቀና ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ያልተሻረ ሆኖ እያለ ተጠሪ ያቀረበውን ክስና ክርክር በማየት ሚያዝያ 8 ቀን 2005 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ከላይ የጠቀስናቸውን የሕግ ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትና የሰበር ችሎት የአላማጣ ምድብ ችሎት የፈፀመውን የሕግ ስህተት ሣያርሙ ማለፋቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአላማጣ ምድብ ችሎት በመዝገብ የሰጠው ውሣኔና የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመዝገብ የሰጠው ትዕዛዝ የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰበር መዝገብ የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
ጉዳዩ በኮረም ከተማ ምድብ ችሎት ጥር 2 ቀን 2004 ዓ.ም በፍርድ ያለቀ በመሆኑ ተጠሪ ይህንን ውሣኔ ለይግባኝ ወይም በልላ የፍርድ ማረሚያ ሥርዓት ሣያሽር ልላ ክስ ማቅረብ አይችልም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 511 መሰረት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻሉ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.