No summary available.
ሐምል 06 ቀን 2004 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ነጋ ዱፊሳ አዳነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ይርገዱ አዲሱ - ጠበቃ ይርጉ ሰንበቶ ቀረቡ ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የሚስትነት ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን በዚህ ፍርድ ቤት የአሁኗ አመልካች የሟች አቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ሚስት ናቸው ተብሎ ማስረጃ እንዲሰጥላቸው አመልክተው ፍርድ ቤቱን የአመልካችን በቃለ መሃላ ተደግፎ የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ አመልካች ከሟቹ ጋር በአገር ባህል የተጋቡ ስለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል ምክንያት ሚስትነታቸውን የሚያረጋገጥ ማስረጃ የሰጠ ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች ሟቹ ከተለያዩ ሴቶች ልጆችን የወለዱና አመልካች በ1996 ዓ/ም ከሟቹ ጋር አብረው ከመኖር ውጪ በሀገር ባህል ተጋብተው የኖሩ ያለመሆኑን ገልፀው ለአመልካች የተሰጣቸው የሚስትነት ማስረጃ እንዲሰረዝላቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
ፍርድ ቤቱንም ግራ ቀኙን በመቃወሚያ አቤቱታው ላይ ከአከራከረ እና ማስረጃ ከሰማ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ አመልካች በቀበል የቤተሰብ ቅፅ ላይ ሚስት ተብለው የተመዘገቡ ቢሆንም በቤተዘመድና በማህበረሰቡ ውስጥ እንደ ባልና ሚስት የተቀበሐቸው መሆናቸውን በበቂ ሁኔታ አስረድተዋል ለማለት ስለማይቻል አመልካች ጋብቻ ለመፈጸማቸው የትዳር ሁኔታ እንዳላቸው በማረጋገጥ አላስረዱም የሚሉትን ምክንያቶችን በመያዝ ቀድሞ የሰጠውን የሚስትነት ማስረጃ ሰርዞታል። ከዚህም በኋላ አመልካች የይግባኝ አቤቱታቸውን ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ባል ወይም ሚስት በቀበል ፎርም ላይ ሞልተው ማረጋገጣቸው ራሳቸውን እንደ ባልና ሚስት እየቆጠሩ የሚኖሩ መሆኑ እና ማህበረሰቡም በዚህ መልኩ የተቀበላቸው መሆኑን እንደሚያመላክት የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ ግንቦት 16 ቀን 1998 ዓ/ም በአዋጅ ቁጥር 454/1997 መሰረት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል የሚል ምክንያት በመያዝ ከመቃወሚያው በኋላ የተሰጠውን የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮ አመልካች የሟች አቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ሚስት ናቸው ተብሎ የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል።
ከዚህም በኋላ ተጠሪዎች የሰበር አቤቱታቸውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ከሟች ጋር በባህላዊ የጋብቻ አፈፃፀም ስርዓት ጋብቻ የፈጸሙ እና ይህንኑ የሚያረጋገጥ የሰነድ ማስረጃ በመጥፋቱ ምክንያት ማቅረብ ያልቻሉ ቢሆንም በ1996 ዓ/ም ከሟች ጋር ባደረጉት ስምምነት በቦል ክፍለ ከተማ ቀበል 11 ጽ/ቤት ሁለታቸውም ቀበል ቀርበው በቀበልው ጽ/ቤት ውስጥ በሚገኘው በሟች የግል ማህደር ላይ ባልና ሚስት ፎርም ቅፅ ላይ በባልና ሚስትነት ስማቸው መመዝገቡንና እስከ እለተሞቱ ድረስ አንድ ላይ በመሆን ንብረት ሁሉ ያፈሩ ስለመሆኑ እየታወቀ አመልካች ከሟች ጋር የመሰረቱት ሕጋዊ ግንኙነት የለም ተብሎ በከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት መወሰኑ ያላግባብ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች የሟች ሚስት ተብሎ የመወሰኑን አግባብነት ከሰ/መ/ አንፃር ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በጽሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የተሰጠው ጉዳዩ በአግባቡ ተጣርቶ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ ከሰ/መ/ አንፃር መታየት ያለበት ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ከሟች ጋር ሕጋዊ ጋብቻ መስርተናል የሚሉት በባህላዊ የጋብቻ አፈጻጸም ስርዓት ሲሆን ይህንኑ ያሳያል የሚሉት ሰነድም የጠፋባቸው ስለመሆኑ ገልፀው ከመከራከራቸውም በላይ በ1996 ዓ/ም ግን ከሟች ጋር በክፍሉ ቀበል ጽ/ቤት ቀርበው በባልና ሚስት ፎርም ላይ ቅጹን የሞሉ መሆኑንና ከሟች ጋር በባልና ሚስትነት ይኖሩ እንደነበር በመዘርዘር መሆኑን፣ ተጠሪዎች የአመልካችን ከሟች ጋር ጋብቻ አልፈፀሙም በማለት የሚከራከሩት ለአንድ ወር ከሟች ጋር ከመኖራቸው ውጪ ጋብቻ አልመሰረቱም፣ በባልና ሚስትነትም የሚታወቁ አይደሉም፣ ሟች ልሎች ሴቶች ጋር ህጋዊ ግንኙነት የነበራቸው በመሆኑ ከአመልካቻቸው ጋር በጋብቻ ውስጥ አልነበሩም በማለት መሆኑንና የከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ላሰጥ የቻለው አመልካች ቀድመው ማስረጃ ሲወስዱ ከሟች ጋር በአገር ባህል እንደተጋቡ አድርገው ገልፀው ቆይተው በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር ደግሞ በ1996 ዓ/ም ቀበል ፅ/ቤት ቀርበን ቅፁን ሞልተናል ማለታቸው ቀድሞውንም ጋብቻ ያልፈጸሙ መሆኑን እንደሚያጠራጥር፣ ይልቁንም እንደ ባልና ሚስት ሁነው ይኖሩ እንደነበረ መግለፃቸውን እንደሚያሳይ ጠቅሶ ጋብቻ መኖሩ ተገልጾ ክርክር ባልቀረበበት ሁኔታ ደግሞ ጋብቻ መኖር ያለመኖሩን ማስረዳት አለማስረዳትን መመርመሩ አስፈላጊ አይደለም የሚሉ ምክንያቶችን በመያዝ ስለመሆኑ ከክርክሩ ሂደት ተመለክተናል።
ከዚህ አንፃርም ጉዳዩን መርምረናል። እንደመረመርነውም የአሁን ተጠሪዎች በተቃዋሚነት በጉዳዩ ቀርበው የተከራከሩት የአሁን አመልካች የሟች ሚስት አይደሉም የሚሉበትን ክርክር በማቅረብ ነው። ተጠሪዎች ይህንኑ ክርክር ለማቅረብ የሚያስችላቸውን የእራሳቸው የሚስትነት ማረጋገጫ ማስረጃ አላቀረቡም፣ ወይም ህጋዊ ሚስቶች የተባሉትም ቀርበው አልተከራከሩም። ስለሆነም በዚህ በግራ ቀኙ መካከል በተነሳው ክርክር ለጉዳዩ እልባት መስጠት በጭብጥነት ላያዝ የሚገባው ነጥብ የአሁን አመልካች የሟች አቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ሚስት ላሆኑ የማይችልበትን ፍሬ ነገር እና የሕግ ክርክር ባሁኑ ተጠሪዎች በኩል በሕጉ አግባብ ቀርቧል ወይስ አልቀረበም?፣ ፍርድ ቤቱስ ጉዳዩን በሕጉ አግባብ ማጣራት ነበረበት ወይስ አልነበረበትም? የሚለው ነው። ከዚህ ነጥብ አንፃር ጉዳዩን ስንመለከት ተጠሪዎች ሟች ከልሎች ሴቶች ጋር ጋብቻ መስርቶ ነበር በሚለው ነጥብ ላይ አትኩረው የተከራከሩ ከመሆኑ በቀር የአሁን አመልካች ሚስት ላሆኑ ያልቻሉበትን ክርክርና ማስረጃ ያላቀረቡ መሆኑን የመዝገቡ ግልባጭ ያስረዳል። ምንም እንኳ የእርሷ ሚስትነት ከክርክሩ አካሄድ አኳያ ጥያቄ ውስጥ የገባ ቢሆንም ይህ ግን ፍርድ ቤቱ ራሱ በሚያጣራው ማስረጃ ነጥሮ ላወጣ ይችል የነበረ መሆኑን ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል።
ስለሆነም የአሁን አመልካች የሟች ዘሪሁን ብርሃኑ ሚስት መሆን ያለመሆናቸው ጉዳይ መታየት የነበረበት በቀበልው ውስጥ ተሞልቷል የተባለው ቅጽ አሞላሉ እንድት እንደነበር (ሟችና አመልካች በግንባር ቀርበው መሆን ያለመሆኑ፣ የባልና ሚስት ሁኔታን ላያረጋገጥ የሚችል ማስረጃ በቀበልው ጽ/ቤት ቀርቦ ታይቶ መሆን ያለመሆኑና ልሎች የቀበል ጽ/ቤቱ የሚከተላቸው አሰራሮች ምን ምን እንደሆኑ) ከተጣራ በኋላ መሆን እንደነበረበት ተረድተናል። አንድ ፍርድ ቤት ለጉዳዩ አወሳሰን የጠራ ፍሬ ነገር የልለ መሆኑን ከተገነዘበ ይኸው ፍሬ ነገር እንዲጣራ ተገቢ ነው ያለውን ማጣራት ሁሉ ማድረግ እንደሚችል ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 136፣137፣ 272፣ 327(3)፣ 345 እና ከልሎች ስለማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ደንብ ከተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘትና ዓላማ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። የከተማው ሰበር ሰሚ ችሎት የአመልካች ክርክር ወጥ ያለመሆኑን በመግለጽ ውሳኔ መስጠቱም አጠቃላይ የክርክሩን ይዘትና ፍርድ ቤት እውነትን ለማውጣት በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት ተግባር ያላገናዘበ ሁኖ አግኝተናል። በመሆኑም ጉዳዩ ላወሰን የቻለው በክርክሩ ሂደት ላጣራ የሚገባቸው ነጥቦች ባልተሟሉበት ሲሆን የክርክር ሂደት ሳያሟላ ዳኝነት መስጠት ደግሞ የፍርድ አካሄድ ስርዓት የሚቀበለው ጉዳይ ባለመሆኑ የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን የሚያሟላ ነው። ከዚህ አንጻር ስንመለከተው አመልካች ከሟች አቶ ዘሪሁን ብርሃኑ ጋር በሕግ አግባብ ጥበቃ ላደረግ የሚችል ግንኙነት መኖር ያለመኖሩን በተሻሻለው የፍድራሉ የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 94 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች እንዲሁም በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ በተሰጠው አስገዳጅ የሕግ ትርጉም መሰረት ለመወሰን በቅድሚያ አመልካች የአገር ባህል የጋብቻ ስርዓት የፈፀሙ ስለመሆኑ ያሳያል ያሉት ሰነድ የጠፋ መሆኑን የገለፁ ስለሆነ ይኸው ፍሬ ነገር ተገቢ ነው በተባለው መንገድ ሁሉ እንዲጣራ፣ በ1996 ዓ/ም አመልካች ሟች አቶ ዘሪሁን በቀበልው ጽ/ቤት ፎርም ሲሞሉ ባልና ሚስት ናቸው ተብሎ እንድት ላሞላ እንደቻለና በቅጽ ባልና ሚስት ተብሎ መሞላቱ ስላለው ውጤት የክፍሉ ቀበል መግለጫ እንዲያቀርብ ማድረጉ የዳኝነት አሰጣጥ ስርዓቱ የግድ የሚለው ጉዳይ ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 1879/02 መጋቢት 08 ቀን 2003 ዓ/ም ተሰጥቶ በአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በመ/ ጳጉሜ 01 ቀን 2003 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በአዲስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔም ተፈፃሚነት የለውም ብለናል።
የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 1879/02 ክርክሩን ቀጥሎ ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተመለከተው አግባብ ጉዳዩን አጣርቶ ተገቢ ነው ያለውን ውሳኔ እንዲሰጥበት ጉዳዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(2) መሰረት መልሰንለታል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.