No summary available.
የካቲት 29 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ረታ ቶሎሣ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ ዩሐንስ በቀለ ጠበቃ መረሣ ፍስሃ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- የቦንጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤት 1. ዐ/ህግ ታመነ ታደሰ ቀረቡ 2. ዐ/ህግ ኬሮ ወ/ሚካኤል ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የከተማ ክልል ይዞታ ለማስለቀቅ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም ለፍርድ ቤት የቀረበ ክስ ተጠሪ ሳይጠራ ውድቅ በመደረጉ ምክንያት የቀረበ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የአመልካች ክስ በቦንጋ ከተማ ካላቸው ይዞታ ውስጥ ተጠሪ ትርፍ ይዘሃል በሚል ምክንያት እንዲለቁ እያደረጋቸው መሆኑን ጠቅሰው ይህንኑ እንቅስቃሴ ተጠሪ በፍርድ ኃይል እንዲያቆሙ እንዲደረግላቸው ዳኝነት የጠየቁ ሲሆን ጉዳዩ የቀረበለት የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የአሁኑ ተጠሪ ሳይጠራ የአመልካች ክስ በትርፍነት የያዙትን ቦታ እንዲለቁ ሲጠየቁ ይህንኑ ለማድረግ አልችልም በሚል የቀረበና ከማዘጋጃ ቤቱ ስልጣን ውጪ ነው በሚል ምክንያት መዝገቡን ዘግቶታል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች ይግባኛቸው ለከፋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱ ተጠሪን ሳይጠራ አመልካችን ብቻ በመስማት ጉዳዩን በመመርመር አመልካች ንብረታቸው ከሕግ ውጪ መውደሙን ቤት፣ ቡና፣ አታክልት፣ ባህር ዛፍ፣ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል ይህንን ያጠፋው ማዘጋጃ ቤቱ ነው ከስር ክሱን ንብረቱን ገምቼ አላቀረብኩም ከስር የከሰስኩት በሁከት ይወገድ ነው የከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዳዩን አላይም በማለት የዘጋው ያላግባብ ነው እየተጠየቀ ያለው በህጋዊ መንገድ ሰርቼ ላገኘሁት ግምት ላከፈለኝ ይገባል ብዬ ነው በማለት ጉዳዩን አመልካች እንዳብራሩት በመመዝገብ ይግባኛቸውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ዘግቶባቸዋል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካች የሰበር አቤቱታቸውን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አቅርበው ችሎትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪን ጠርተው ጉዳዩን በማስረጃ ሳያጣሩ መዝጋታቸው ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችሎቱ ላታይ ይገባዋል ተብሎ በመታመኑ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጐለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በጸሁፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪን ሳይጠሩ የአመልካችን ክስ መዝጋታቸው ስነ ስርዓታዊ ነው ወይስ አይደለም የሚለው በጭብጥነት የሚታይ ሁኖ አግኝተነዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች በከተማው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክሰ ሲመሰርቱ በሁከት ይወገድልኝ ስለመሆኑ በይግባኝ ሰሚው የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያስመዘገቡ ሲሆን በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ደግሞ በንብረት ግምት መሰረት የካሳ ይከፈለኝ ክስ ሳያቀርቡ ጥያቄአቸው ለንብረታቸው ካሳ ይከፈለኝ በማለት አቤቱታ እያሰሙ ያሉ መሆኑን ያረጋገጡ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ አንድ ክስ ለፍርድ ቤት የሚያቀርብ ሰው ክሱን የሚያቀርበበት ስርዓት በሕጉ የተዘረጋ ሲሆን ክሱ የቀረበለት ፍርድ ቤትም ልላኛውን ወገን ከመጥራቱ በፊት ክሱ ህጋዊ ፎርማላቲ ያሟላ መሆን ያለመሆኑ መመርመር ያለበት መሆኑን ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 33፣80፣222፣225፣226፣ እና 231 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። እነዚህ ድንጋጌዎች በህጉ መሰረት ያልቀረበ ክስ ተከሳሽ የሆነውን ተከራከሪ ወገን መጥራት ሳያስፈልግ ላዘጋ የሚችልበት አግባብ መኖሩን የሚያሳዩ ናቸው። በህጉ አግባብ መቅረቡ ከተረጋገጠ ደግሞ የግራ ቀኙ የመስማት መብት በሕጉ አግባብ መጠበቅ ያለበት መሆኑን 223፣234፣241 እና ተከታይ ድንጋጌዎች ያሳያሉ።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም አመልካች ክስ ሲመሰርቱ ትርፍ ቦታ መያዛቸውን ተረድተው ለመልቀቅ ፈርመው ለማዘጋጃ ቤቱ ማሳወቃቸውን የከተማው መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያረጋገጠው ጉዳይ ሲሆን ይህም በትርፉ ቦታ ጥቅም ወይም መብት የልላቸው መሆኑን በመነሻነት የሚያሳይ ሲሆን አመልካች ቦታውን ልለቅ አይገባም ሲሉ ቆይተው ጥያቄአቸው የካሳ ይከፈለኝ ጥያቄ መሆኑን በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አረጋግጠዋል። የካሳ ይከፈለኝ ጥያቄ ደግሞ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 225 መሰረት የዳኝነት ተከፍሎበት ያልቀረበ መሆኑን የክርክሩ ሂደት ያሳያል።
No topics extracted.
በመሆኑም አመልካች የክስ አቀራረባቸውን በሕጉ በተዘረጋ ስርዓት መሰረት አስተካክለው ሳያቀርቡ ወጥነት በልለው አኳኋን የጠየቁትን ዳኝነት እየቀሩ የመሰማት መብቴ ሳይከበር ክሴ ተዘግቷል በማለት የሚያቀርቡት ክርክር የሕግ መሰረት የልለው ነው። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን ክስ የዘጉት አግባብ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 33/2/፣222፣225፣226 እና 231/1/ሀ// አንፃር ሲታይ የሚነቀፍ ባለመሆኑ በጉዳዩ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የደቡብ ብሕር ብሕረሰቦችና ሕዝቦች ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በጉዳዩ ላይ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ትዕዛዝ በማጽናት በመ/ ሐምል 19 ቀን 2004 ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ ጸንቷል።
የአመልካች ክስ ውድቅ የተደረገው የክስ አቀራረብ ሰርዓቱን አሟልቶ ባለመቅረቡ በመሆኑ ተገቢ ነው ብለናል።
አመልካች ሕጋዊ መብታቸውን መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡት የካሳ ክፍያ ጥያቄ ካለ ይህ ውሳኔ አያግዳቸውም ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።