No summary available.
የካቲት 12 ቀን 2005 ዓ.ም ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ረታ ቶሎሣ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡-
ጉዳዩ ከቦታ ማስለቀቅ ጋር ተያይዞ የተነሳ የካሳ ክፍያ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን የተጀመረውም የአሁኖቹ አመልካቾች በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ባቀረቡት ክስ ነው። የክሱም ይዘት ባጭሩ ተከሳሽ በሚተዳደርበት የከተማ ቦታ ኪራይ ደንበ መሰረት ለሆቴል አገልግሎት የሚውል 3250 ካ.ሜ ቦታ ለ1ኛ ከሳሽ እና የ2ኛ ከሳሽ አባት ለሆኑት ለአቶ ጥጋቡ ሸጎዕ በውል ሰጥቶ እንደነበረ በዚሁ ቦታ ላይ ግንባታውን በከፊል አከናውነው ከፊሉ ደግሞ በግንባታ ኦዲት ላይ እያለ ተከሳሽ አቅም ስለልላችሁ ቦታውን አስረከቡ በማለት በ18/05/01 በተፃፈ ደብዳቤ እንዳስታወቀቸው እነርሱም ጉዳዩ የተጓተተው በአቶ ጥጋቡ ሸጎዕ ሞት ምከንያት ከውርስ ማጣራት ጋር ተያይዞ መሆኑን ለተከሳሽ እንደገለጹ እና በተጠየቁት መስረት የፋይናንስ አቅማቸውን የሚያመለክት ማስረጃ ለተከሳሽ እንዲያቀርቡ ለግንባታው ከብር አንድ ሚላዮን በላይ ወጪ እንዳደረጉና ተከሳሽ ተገቢውን ምላሽ ላሰጧቸው እንዳልቻሉ የሚገለፅ ሆኖ በሂደት እያለሙት የነበረውን ቦታ ተከሳሽ እንዲመልስላቸው የማይመልስ ከሆነ ደግሞ ያወጡትን ወጪ ብር እንድ ሚላዮን ከተዛማጅ ወጪዎች ጋር እንዲመልስላቸው ውሳኔ እንዲሰጣቸው ዳኝነት የተጠየቀባቸው ነው። ተከሳሽ በበኩሉ የቦታ ማስለቀቅ እና የካሳ ጉዳይን ፍ/ቤቱ በመጀመሪያ ደረጃ ስልጣን ማየት ስለማይችል መዝገቡን ዘግቶ ያስናብተን በማለት መቀወሚያ ከቀረበ በኋላ ፍሬ ጉዳዩን በተመለከተ ከሳሾቹ ሆቴል እና የነዳጅ ማደያ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ገንብተው አገልግሎት ላይ ለማዋል ውል ገብተው ቦታውን በ1994 ከተረከቡ በኋላ አስከ 1999 ዓ.ም ደረስ የተወሰኑ ክፍሎችን ከመስራት በስተቀር በገቡት ግድታ መሰረት ግንባታውን አጠናቀው ስራ ላይ ባለማዋላቸው በ1999 ስራውን እንዲያቆሙ እንደታዘዙ እና ቀጥሎም እንዲያስረከቡ እንደተደረገ ይህ እርምጃም የተወሰደው ለከተማ አስተዳደሩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት እንደሆን እና ቦታው በጨረታ ለልሎቹ ባለሀብቶቹ ላተላለፍ እንደሆነ በመግለጽ ተከራክሮአል።
ፍ/ቤቱም መቃወሚውን ውድቅ አድርጎ የግንባታው ዋጋ በባለሙያ እንዲገመት ካደረገ በኋላ ተከሳሽ የግንባታውን ወጪ ብር 618,815.93 ለከሳሾች ይክፈል ከዚህ በኋላ ቦታውን ከነግንባታው ይረከብ በማለት ውሳኔ ሰጥቶአል።
ሁለቱም ወገኖች በውሳኔው ቅር በመሰኘት ያቀረቡትን ይግባኝ የመረመርው የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በበኩሉ ክርክሩን ከሰማ በኋላ ከፍተኛ ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው የከተማ ቦታን በኪራይ ስለመያዝ እንደገና ለመደንገግ በክልሉ በወጣው ደንብ ቁጥር 19/1995 አንቀጽ 13/2/ መሰረት የቦታ ማስለቀቅ እና የካሳ ክፍያ ጉዳይን በመጀመሪያ ደረጃ ለማየት የሚያስችል ስልጣን ሳይኖው ነው በማለት ውሳኔውን በሁለቱም መዝገቦች የሻረው ሲሆን የጠቅላይ ፍ/ቤቱ ሰበር ችሎትም የቀረበለትን አቤቱታ ዘግቶ አስናብቶአል።
አመልካቾች አቤቱታ ያቀረቡት የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይ/ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመባቸው በመሆኑ ላታረሙ ይገባል በማለት ሲሆን ይህንኑ ክርክራቸውን በ12/11/04 አዘጋጅተው ባቀረቡት የተሻሻለ አቤቱታ ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ የሰጠው በልለው ስልጣን ነው ተብሎ በበላይ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት በክርክሩ ከተጠቀሰው ደንብ ቁጥር 19/1995 አንቀጽ 13/2/ አንፃር ለመመርመር ጉዳዩ ለሰበር ክርክር እንዲቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሑፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ የሰጠው ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ለማየት ስልጣን ሳይኖረው ነው በሚል የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔን በመሻር የሰጠው ውሳኔ እና ከዚህ ውሳኔ የቀረበለትን አቤቱታ ዘግቶ በማስናበት የጠ/ፍ/ቤቱ ሰበር ችሎት የሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት መሆን አለመሆኑን መርምረናል።
በዚህም መሰረት ከላይ እንደተጠቀሰው የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይ/ሰሚ እና ሰበር ችሎቶች አከራካሪ ሆኖ የቀረበው ጉዳይ በይግባኝ ካልሆነ በስተቀር በቀጥታ በፍ/ቤት ላታይ የሚችል አይደለም በማለት ለሰጡት ውሳኔ መሰረት ያደረጉት የከተማ ቦታን በኪራይ ስለመያዝ እንደገና ለመደንገግ በክልሉ የወጣውን ደንብ ቁጥር 19/1995 ሆኖ በተለየም የደንቡን አንቀጽ 13/2/ ደንጋጌ ነው። ተጠሪው ይዞታውን ለአመልካቾቹ በኪራይ የሰጠው ሆቴል እና ነዳጅ ማደያ ገንብተው በሁለት ዓመት ውስጥ አገልግሎት ላይ እንዲያውሉ ግድታ በማስገባት መሆኑ እና የተጀመረውን ግንባታ አቁመው ይዞታውን እንዲያስረከቡ ያደረገው ደግሞ ግንባታውን በተባለው ጊዜ አጠናቀው አገልግሎት ላይ አለማዋላቸውን እና የአቅም ውስንነት የታየባቸው መሆኑን በምክንያትነት በመጥቀስ መሆኑ በክርክሩ ተረጋግጦአል። የተጠሪ እርምጃን በመቃወም በመሆኑ የደንቡ አንቀጽ 13 ድንጋጌ በተያዘው ጉዳይ ላይ ተፈፃሚነት ያለው መሆን አለመሆኑ ላጤን የሚገባው ሆኖ ተገኝቶአል። በመሰረቱ ደንቡ የሚደነግገው ሁለቱ ጉዳዮችን ነው። የመጀመሪያው አስተዳደሩ የከተማ ቦታ በኪራይ ስለሚሰጥበት ሁኔታ እና ከኪራይ ይዞታ ጋር ተያይዞ በአስተዳደሩ እና በኪራይ በለይዞታዎች መካከል ስለሚኖረው አጠቃላይ ግንኙነት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የከተማ ቦታን ስለማስለቀቅ ሆነ ቦታ እንዲለቁ በሚደረጉ ባለይዞታዎች እና በአስተዳደሩ መካከል ስለሚኖረው አጠቃላይ ግንኙነት ነው። ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የከተማ ቦታውን እንዲለቅ የማስቀለቀቂያ ትዕዛዝ የተሰጠው ባለይዞታ በማስለቀቅ ትዕዛዙ ላይም ሆነ በከሳ ጉዳይ ላይ ቅሬታ የሚኖረው ከሆነ የዚህ ዓይነቱ ቅሬታ የሚስተናገድበትን ስርዓት ጨምሮ ከቦታ ማስለቀቅ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በደንቡ ተደንግገው የሚገኙት ከአንቀጽ 13 ጀምሮ ነው። የደንቡ አንቀጽ 13/2/ የሚደነግገውም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የከተማ ቦታን ከማስለቀቅ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ቅሬታዎን በቀጥታ ለፍ/ቤት ክስ ላቀርብባቸው የማይቻል መሆኑን ነው።
በተያዘው ጉዳይ አመልካቾቹ ቦታውን እንዲያስረከቡ ተጠሪ የወሰነው ቦታው ለሕዝብ ጥቅም ተፈልጉአል በማለት ሳይሆን አመልካቾቹ በገቡት ግድታ መሰረት ግንባታውን በተገቢው ጊዜ አጠናቀው ለአገልግሎት አላበቁም የፋይናንስ አቅም ችግርም ታይቶባቸዋል በማለት ነው። እንዲህ ከሆነ ደግሞ በደንቡ ከአንቀጽ 13 እስከ 16 ያሉት ድንጋጌዎች በጉዳዮ ላይ ተፈፃሚ ላደረጉ የሚችሉበት አግባብ አይኖርም። የተያዘው ጉዳይ የኪራይ ይዞታ ማቋረጥን የሚመለከት በመሆኑ ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸው ደንቡ አንቀጽ 10 እና 11 ድንጋጌዎች ናቸው። እነዚህ ድንጋጌዎች ደግሞ የኪራይ ይዞታ ማቋረጥን አስመልክቶ አስተዳደሩ በሚወስዳቸው እርምጃዎች ላይ ባለይዞታው ቅሬታ ሲያድርበት ጉዳይ ላታይ ስለሚችልበት የደኝነት መድረክ የሚገልጹት ነገር የለም። ጉዳዩ በፍርድ ላወስን የሚገባው እስከሆነ እና ጉዳዩን ለማየት በሕግ በግልጽ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ልላ አካል እስከልለ ደረስ ደግሞ አመልካቾቹ ጉዳያቸውን በቀጥታ ለፍ/ቤት አቅርበው ፍትሕ ከማግኘት የሚታገዱበት ሕጋዊ ምክንያት አይኖርም።
የኢ.ፊ.ዲ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 37/1/ እና 79/1/ እንዲሁም የፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 4 ድንጋጌዎችም ይህንኑ የሚያስገነዝቡ ናቸው።
ሲጠቃለል ጉዳዩ በቀጥታ ለፍ/ቤት ላቀርብ አይችልም በማለት በስር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መስረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቶአል።
ው ሣ ኔ
የት/ብ/ክ/ከመንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይ/ሰሚ ችሎት በመ/ በ04/04/04 እና በመ/ በ04/04/04 የሰጠው ውሳኔ እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመ/ በ03/08/04 የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ጉዳዩ በቀጥታ ለፍ/ቤት ክስ ላቀርብበት የሚችል መሆኑን እና የመቀል ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጉዳዩን አስተናግዶ ውሳኔ የሰጠው በዚሁ አግባብ መሆኑን በመገንዘብ ሁለቱን የይግባኝ መዝገቦች አንቀሰቅሶ በዋና ጉዳይ ውሳኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዳዩ በፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ 341/1/ መሰረት ወደ ክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይ/ሰሚ ችሎት እንዲመለስ ወስነናል። የውሳኔው ግልባጭ ይላክለት።
የሰበር ክርክሩን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዝገቡ ተዘግቶአል።
No topics extracted.