No summary available.
ሰኔ 5 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች:- ወ/ሮ ዘምዘም ወንድሙ - ከጠበቃ አትሙት አሰፋ ጋር ቀረቡ ተጠሪ:- አቶ አብዲሰቡር አብዱሰመድ - አልቀረበም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የቀረበው ተመሳሳይ የሆኑ ተከራካሪ ወገኖች በአንድ ዓይነት ወይም ተመሳሳይ የሆኑ ክሶችን በአንድ ፍ/ቤት በመቅረባቸው የተነሳ አንደኛው ወገን ይህን ተገንዝቦ ጉዳዮች ተጣምረው እንዲታዩለት ለፍ/ቤቱ ባመለከተ ጊዜ ፍ/ቤቱ ላፈፅመው የሚገባውን ሥርዓት የሚመለከት ነው።
ለዚህ የሰበር ጉዳይ መነሻ የሆነው የአሁን ተጠሪ ከሳሽ፤ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ የሆኑበትን የብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺ) የብድር ገንዘብ ክርክር ጉዳይ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቄራ ምድብ ችሎት ተመልክቶ በኮ/ በሆነው መዝገብ ላይ በቀን 25/06/2003 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሰጠው ፍርድ ነው።
በዚህ ጉዳይ ከሳሽ የነበሩት የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ ላቀረቡት የብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ) የገንዘብ ብድር ክስ መሰረት አድርገው የጠቀሱት በሁለቱም መካከል ነሐሴ 21 ቀን 1998 ዓ/ም ተደርጓል የተባለውን የገንዘብ ብድር ውል ሲሆን በዚህ ውል ተበዳሪ ገንዘቡን እስከ መስከረም 30 ቀን 2000 ዓ/ም ድረስ በመመለሱ በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ቀበል 02 የሚገኘውንና በቤት ቁጥር B6/14 የተመዘገበውን የኮንዶሚኒየም ቤት በመያዣነት አስይዘዋል። ይሁን እንጂ በውሉ በተገለፀው ጊዜ ገንዘቡን አልከፈለም። ስለሆነም የብድር ገንዘቡን ከህጋዊ ወለድ ጋር እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ በማለት ህዳር 05 ቀን 2001 ዓ/ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ የክስ ምክንያታቸውን ገልፀው ዳኝነት የጠየቁበት ሲሆን፤
የአሁን አመልካችም በተከሳሽነታቸው በዚህ የብድር ውል በተባለው ሰነድ ላገደዱ የማይችሉበትን የፍሬ ነገርና የህግ ክርክር በመጥቀስ ዝርዝር መልሳቸውን ሰጥተውበታል።
በልላ በኩል የአሁን አመልካች መስከረም 02 ቀን 2002 ዓ/ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ ለዚሁ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቄራ ምድብ ችሎት በአሁን ተጠሪ ላይ ባቀረቡት ክስ መነሻ የኮ/ የሆነውን መዝገብ አስከፍተው በኋላም መጋቢት 06 ቀን 2002 ዓ/ም የተሻሻለ ክስ እንዲቀርብ ተደርጎ የክርክሩ መሰማት በዚሁ ፍ/ቤት ቀጥሐል። የአሁን አመልካች በኮ/ በሆነው መዝገብ ላይ ባቀረቡት ክስ የጠቀሱት ዝርዝር ምክንያት የአሁን ተጠሪ ከላይ በአድራሻና በቁጥር የተጠቀሰውንና በዕዳ የደረሰኝን የኮንዶሚኒየም ቤት አስመልክቶ በማስላት ሐምል 12 ቀን 1998 ዓ/ም እና ነሐሴ 21 ቀን 1998 ዓ/ም ተደረገ የተባለውን የሽያጭ ውል፤ ሐምል 21 ቀን 1998 ዓ/ም ተደረገ የተባለውን የሥጦታ ውል እና ነሐሴ 21 ቀን 1998 ዓ/ም ተደረገ የተባለውን የብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) የብድር ውል ያስፈረመኝ ስለሆነና እነዚህም ውሎች በህግ ፊት ላፀና የሚችል ውል ለመያዝ የሚያስፈልጉትን ሁኔታዎች አሟልቶ የተደረጉ ባለመሆኑ ላፈርሱ ይገባል የሚል ነው።
ለዚህም ክስ የአሁን ተጠሪ የፅሁፍ መልስ የማቅረብ መብቱ የታለፈ ቢሆንም፤ ክርክር በሚሰማበት ዕለት ቀርቦ ከአሁን አመልካች ጋር ያደረጉት የብድር ስምምነት በህግ ፊት የፀና ነው የሚሉበትን ምክንያት በመግለፅ ተከራክረዋል።
እነዚህ ሁለት ክሶች በተመሳሳይ ተከራካሪ ወገኖች በአንድ ፍ/ቤት ቀርበው እየተሰሙ ባሉበት ጊዜ በአሁን አመልካች እነዚህ ተመሳሳይ ጭብጥ የሚያስነሱ ተመሳሳይ ጉዳዮች ተጣምረው ላታዩ ይገባል በሚል በማመልከታቸው ፍ/ቤቱ በኮ/መ/ በሆነው መዝገብ ላይ ተከሳሽ የነበሩትን የአሁን ተጠሪን ምስክሮች ዝርዝር ቃል ከተቀበለ በኋላ በቄራ ምድብ 1ኛ ፍ/ብ/ችሎት እየታዩ የሚገኘው የኮ/ የሆነው መዝገብ ቀርቦ ከመ/ ጋር ተጣምሮ እንዲታይ ትዕዛዝ ሰጥቶበታል። ሆኖም የኮ/መ/ቁ “37363” ተብሎ መፃፍ ሲገባው የመጨረሻዋ “3” የምትለው ቁጥር ተሰርዞና ተደልዞ “6” በሚል በመፃፉ ምክንያት እንደ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ይኸው መዝገብ እንዲጣመር አልተደረገም። በዚህም የተነሳ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱ ሁለቱንም ጉዳዮች ጐን ለጐን ሲያይ ከቆየ በኋላ በኮ/መ/ በሆነው መዝገብ የካቲት 25 ቀን 2003 ዓ/ም በዋለው ችሎት የአሁን ተጠሪ ነሐሴ 21 ቀን 1998 ዓ/ም በተደረገው የብድር ውል መሰረት ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) ለአበዳሪ ለአሁን ተጠሪ የመክፈል ግድታ አለባቸው በማለት ሲወስን፤ በኮ/መ/ በሆነው ጉዳይ ደግሞ ይኸው ነሐሴ 21 ቀን 1998 ዓ/ም ተደረገ የተባለው የብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) የብድር ውል እና የመያዣ ውል በህግ ፊት የፀና ውል ሆኖ ባለማግኘቱ ፈራሽ ነው የሚለውንም ጭምር ያካተተ አስቀድሞ ከሰጠው ፍርድ ጋር በተቃራኒ አኳኋን ሰኔ 10 ቀን 2003 ዓ/ም በዋለው ችሎት ወስኗል።
No topics extracted.
በዚህ አኳኋን የተቃረነ ፍርድ መስጠቱን እንደተረዳ በኮ/መ/ የሆነውን መዝገብ ከተዘጋ በኋላ እንደገና በማንቀሳቀስ ቀደም ሲል በክርክር ሂደት ተከስቶ የነበረውን የመዝገብ ቁጥር አፃፃፍ ስህተት ታርሞ ቁጥር “6” በሚል የተፃፈው የመዝገብ ቁጥር የመጨረሻ አኃዝ ቁጥር “3” በሚል ላስተካከል ይገባል በማለት በሰጠው እርስ በእርሱ የተቃረነ ፍርድ ላይ አንዳችም ውጤት ላያስከትል የማይችል ትዕዛዝ ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ/ም እንደሰጠበትም ከሰጠው የትዕዛዝ ዳኝነት ግልባጭ ተረድተናል።
የአሁን አመልካችም ተከሳሽ በነበሩበት በኮ/መ/ በሆነው መዝገብ ላይ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም የይግባኝ አቤቱታውን ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረባቸው ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን ተመልክቶ በመ/ በቀን 04/08/2004 ዓ/ም በዋለው ችሎት ይኸው በኮ/መ/ የተሰጠው ፍርድ በፍሬ ነገርም ሆነ በህግ ረገድ ጉድለት የተገኘበት አይደለም በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት መዝገቡን ዘግቷል።
ለዚህ የሰበር ጉዳይ ምክንያት የሆነውም በዚህ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሰጠው የመጨረሻ ፍርድ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚሉበትን የክርክር ነጥቦች በመጥቀስ ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ሲሆን የአሁን ተጠሪም ይኸው ፍርድ ህጋዊ መሰረት ያለው ነው ላፀና ይገባል በማለት ከእነምክንያቱ ገልፀው ተከራክረዋል።
እንግዲህ የዚህ ጉዳይ መነሻና አመጣጡ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም ለዚህ የሰበር ጉዳይ መነሻና ምክንያት የሆነው ነሐሴ 21 ቀን 1998 ዓ/ም ግራ ቀኙ አድርገውታል የተባለው የብድር ውል ስምምነት ህጋዊ ውጤትን ያስከትላል ወይስ አያስከትልም? የሚለውን አከራከሪ ነጥብ ለጉዳዩ አግባብነት ካላቸው የመሰረተ ህጉ ድንጋጌዎች ጋር አገናዝበን ከማየታችን በፊት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 347(4) እና 182(3) እንደተደነገገው በቅድሚያ ከዚሁ ነሐሴ 21 ቀን 1998 ዓ/ም ተደረገ ከተባለው የብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ) የብድር ውል እና የመያዣ ውል በመነሳት እነዚሁ ሁለት ተከራከሪ ወገኖች በከሳሽነትና በተከሳሽነት በመፈራረቅ አንድ ዓይነት የፍሬ ነገርና የህግ ክርክሩ ጭብጥ በሚያስነሳ ተመሳሳይ ጉዳይ ላይ በአንድ ፍ/ቤት በተለያዩ ክሶች እየተከራከሩ የነበሩ መሆኑ ሲታወቅ በስር ፍ/ቤቶች ላከተሉት የሚገባው ስርዓት ምን ላሆን ይገባ ነበረ? የሚለው ጭብጥ ላታይ የሚገባው ሆኖ ተገኝቷል።
እንደዚህ ባለ ተመሳሳይ ጉዳይ ተመሳሳይ የሆኑ ተከራካሪ ወገኖች በአንድ ፍ/ቤት በተለያዩ ክሶች መከራከራቸው ሲታወቅ ጉዳዩን በመጀመሪያም ሆነ በይግባኝ ደረጃ የተመለከቱት ፍ/ቤቶች እንዚህ ሁለት ጉዳዮች ተጣምረው እንዲታዩ ካላደረጉ በቀር በአንድ ጉዳይ ላይ በተለያዩ አኳኋን ፍርድ ላሰጥ ስለሚችልና በተመሳሳይ ተከራከሪ ወገኖች በሚከራከሩበት ተመሳሳይ ጉዳይ አንድ ፍ/ቤት በተለያዩ ክስ ተቀብሎ በማስተናገዱ ምክንያት የተለያየ ፍርድ መስጠቱ በየትኛውም መለኪያ ቢሆን ፍትሐዊ እና ህጋዊ ካለመሆኑም በላይ በዚህ አኳኋን የተሰጡትንም ፍርዶች ለማስፈፀም አዳጋች ሆኖ ይገኛል።
ይህንንም በመገንዘብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ እንደዚህ ያለ ሁኔታ እንዳያጋጥም ሥርዓት ዘርግቷል። ይኸውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 8(1) ላይ ለክርክሩ መነሻ የሆነው ነገር አንድ አይነት ወይም ተመሳሳይነት ያለው ሆኖ ምላሽ የሚያስፈልገውም የሥረ - ነገር ጭብጥና ተከራከሪ ወገኖችም ተመሳሳይ ሆነው ጉዳዩ በቅድሚያ ሥልጣን ላለው ፍ/ቤት ቀርቦ በመሰማት ላይ እያለ ልላው ፍ/ቤት ይህንኑ አንድ የሆነውን ጉዳይ ተቀብሎ ለመከራከር አይችልም በማለት ተመሳሳይ የሆነው ጉዳይ በአንድ ፍ/ቤትም ሆነ በልላ ፍ/ቤት በቀረበ ጊዜ ክርክሩ ላቀጥል እንደማይገባ አስገዳጅነት ባለው ሁኔታ ደንግጓል። ምናልባትም ይኸው ሥርዓት ሳይፈፀም ተመሳሳይ የሆነውና በተመሳሳይ ተከራካሪ ወገኖች የተነሳው ጉዳይ በተለያየ ክስ አማካኝነት በተለያየ ፍ/ቤት ቀርቦ በመሰማት ላይ የሚገኝ መሆኑ ከታወቀም የክርክሩ ተነጣጥሎ መታየት ለዳኝነት ሥራ አመራር ወይም ለትክክለኛ ውሳኔ አሰጣጥ የማይመች ወይም የማይገባ ሆኖ ስለሚገኝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 11 መሰረት ተጣምሮ መታየት እንደሚኖርበት ወይም በቁጥር 244 እና 245 በተነገረው መሰረት አስፈላጊው ብይን ላሰጥበት እንደሚገባም ተከታይ የሆነውን የማረሚያ ሥርዓት አበጅቷል።
ከዚህም ድንጋጌ ሥር ከተመለከተው “… ለዳኝነት ሥራ አመራር…” የማይመች…” የሚለው ሐረግ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ዓላማው አንድ ክርክሮችን ሥርዓት ባለው መንገድ በመምራት በአፋጣኝ እንዲታዩ በማድረግ ጌዜን፣ ጉልበትን እና ገንዘብን ለመቆጠብ እንደመሆኑ መጠን ተመሳሳይ ጉዳይ በተመሳሳይ ተከራካሪ ወገኖች በአንድ ፍ/ቤትም ሆነ በተለያዩ ፍ/ቤቶች ማቅረብና ቀርቦ እንዲታይ ማድረጉ ከዚሁ መሰረታዊ ከሆነው የሥነሥርዓት ህጉ ዓላማ ጋር የማይስማማ መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን፤ “… ወይም ለትክክለኛ ውሳኔ አሰጣጥ የማይመች ወይም የማይገባ….” የሚለው ሐረግ ደግሞ ተለያይተው ክሶች የመቅረባቸው ውጤት በክርክር አመራር አመቺነት ወይም ጊዜን ወጭንና ድካምን በማስቀረት ላይ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በመጨረሻ በሁለቱም ክሶች ላይ የሚሰጠው ፍርድ ከቶውንም ቢሆን ተመሳሳይ ላሆን ስለማይችል ውጤቱ ትክክለኛ ፍርድ ላሆን የማይችል መሆኑን የሚያመለክት ነው።
የዚሁ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 8 ን ድንጋጌ ሙሉ ለማድረግ በተቀመጠውም በቁጥር 11 ላይ የተመለከተውም ድንጋጌ ይዘትና ሀሳብ ይህንኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉን ዓላማ የተንተራሰ ነው። በተለይም በቁጥር 11(1) ላይ ከአንድ ጉዳይ የመነጩት ክሶች በተመሳሳይ ተከራከሪ ወገኖች በአንድ ፍ/ቤት የቀረቡ መሆኑ ከተረጋገጠ የክርክሩ ደረጃ ምንም ይሁን ምን ክሶች ተጣምረው መታየት እንደሚገባቸው በግልፅ ያመለከተ ሲሆን፤ በቁጥር 11(2) ላይም “…. ማስረጃ መቀበልና ማከራከር ከመጀመሩ በፊት…” በሚል መቼ መጣመር እንደሚገባቸው ጊዜን አስመልክቶ የተቀመጠው ሐረግ በተቻለ መጠን ተከራከሪ ወገኑ ይህንኑ እንደተረዳ ወዲያውኑ ማቅረብ ያለበት መሆኑን ለማስገንዘብ ነው ከሚባል በቀር የአሁን ተጠሪ በዚህ የሰበር ደረጃ ባቀረቡት የፅሁፍ ክርክር እንደገለጹት ምንም እንኳ ክሶች ተለያይተው የቀረቡ መሆኑ ቢታወቅም በሁለቱም ክሶች ላይ የማስረጃ መሰማቱ ሥራ ካለቀ ሁለቱም ጉዳዮች ተነጣጥለው ለየብቻ ታይተው ፍርድ እንዲሰጣቸው ሥርዓቱ ይፈቅዳል ከሚለው ትርጉም የሚያደርስ አይደለም።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 8 እና 11 መሰረት የሚነሱት ክርክሮች በይዞታቸው በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር ሥር የሚታቀፉ በመሆናቸው መቼ መቅረብ እንዳለባቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 234 እንደተደነገገው ማስረጃ ከመሰማቱ በፊት የመከላከያ መልስ በሚቀርብበት ጊዜ ለመሆኑ መደንገጉና፤
ሆኖም በዚህ ጊዜ መቅረብ ሲገባቸው ያልቀረቡት የመቃወሚያ የክርክር ነጥቦች በይዞታቸው ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት የሚያሰናክሉ ሆነው ከተገኙ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በማናቸውም ጊዜ ላቀርቡ እንደሚችሉ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 244(3) ከተደነገገው አንፃር የቁጥር 11(2) ድንጋጌ ይዘት ሲታይ ከላይ የተመለከተውን ትርጉም የሚደግፍ ነው።
በዚህ ጉዳይ ሁለታችንም በልላ ፍ/ቤት እየተከራከርን እንገኛለን ይህ ለሁለተኛ ጊዜ በዚያው ፍ/ቤትም ሆነ በልላ ፍ/ቤት የቀረበው ክስ ከዚህ በፊት ቀርቦ እየተከራከርን ከምንገኝበት ጉዳይ ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ስለሆነም ክርክሩ ላቀጥል አይገባም ወይም ተጣምሮ ላታይ ይገባዋል የሚለው በቁጥር 8 ሆነ 11 መሰረት የሚቀርበው ክርክር ማስረጃ ከመሰማቱ በፊት ያልቀረበ ስለሆነ ክርክርን በአፋጣኝ እና በአነስተኛ ወጭ ለማየት አያስችልም ስለሆነም ጊዜው ካለፈበት በኋላ የቀረበ ስለሆነ ተቀባይነት የለውም የሚያሰኝ የክርክር ዓይነት ሳይሆን ይህ ዓይነት ክርክር መኖሩ እየታወቀ ከታለፈ ትክክለኛ ፍርድን ለመስጠት የማያስችል በመሆኑ ከፍርድ በፊት በማናቸውም ጊዜ እንዲቀርቡ ከሚድረጉት የመቃወሚያ ክርክሮች ዘርፍ የሚመደብ ነው።
የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ቢሆን እነዚህን ሁለት ክሶች ይዘታቸውን ተመልክቶ ተጣምሮ እንዲታዩ አግባብነት ያለውን ትዕዛዝ የሰጡበት እንጂ ማስረጃ ከመሰማቱ በፊት ያልቀረበ ስለሆነ ላጣመሩ አይገባም በሚል ዳኘነት አልሰጡበትም።
በመዝገብ አፃፃፍ ስህተት ሁለቱም ጉዳዮች በተናጠል ታይተው የተለያየ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ እራሱ የሰጠውን ፍርድ እንደይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤቱ የመሻር ስልጣን የልለው በመሆኑ በክርክር ሂደት በመዝገብ አፃፃፍ ጊዜ የተፈፀመውን የቁጥር አፃፃፍ ዝንፈት በማረም ተገድቧል።
ሆኖም የሥር ፍ/ቤት በቁጥር አፃፃፍ ስህተት ምክንያት እንጂ ድሮውንም ተጣምረው ላታዩ የሚገባቸው ተመሳሳይ ጉዳዮች መሆናቸውን ተገንዝቦ ቀደም ሲል ተጣምረው እንዲታዩ በሚል የሰጠውን ትዕዛዝ ተከትሎ ፍርድ ከሰጠም በኋላ ቢሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 208 መሰረት የእርማት ዳኝነት የሰጠበት ጥቅምት 08 ቀን 2004 ዓ/ም ነው። በዚህ ጊዜ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ዳኝነት አልሰጠበትም። የመጨረሻ ዳኝነት የሰጠበት ከ6 ወር በኋላ ነው።
በመሆኑም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 8 እና 11 ድንጋጌዎች አፈፃፀም በሚመለከት በአሁን አመልካች አማካኝነት የይግባኝ መዝገብ ከተከፈተም በኋላ ክርክሩ ሲቀርብለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 345፣ 32(2) እና 244(3) ድንጋጌ አንፃር በማየት የቀረበለትን የይግባኝ መዝገብ ከመዝጋት ይልቅ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 11(3) መሰረት ተገቢውን መፈፀም ይቻል ዘንድ በመ/ የተሰጠው ውሳኔ ደረጃውን ጠብቆ ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መቅረብና አለመቅረቡን መጠባበቅ ይገባው አንደነበረም ተገንዝበናል። ይሁን እንጂ በኮ/መ/ በሆነው ጉዳይ ላይ የአሁን አመልካች በሁለቱም ጉዳዮች ተመሳሳይ ሆነው እያለ በአንድ ፍ/ቤት የተለያየ ፍርድ ላሰጥ የቻለበትን ምክንያት በመግለፅ የተፈፀመው የሥነ - ሥርዓታዊ ግድፈት በይግባኝ ደረጃ እንዲታረም በይግባኝ መዝገብ ማስከፈታቸውን ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ እንዲረዳ አስቀርበን ከተመለከትነው መዝገብ የተረዳን ከመሆኑ በቀር የአሁን ተጠሪ በዚህ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ነሐሴ 21 ቀን 1998 ዓ/ም ተደረገ የተባለው የብድርና የመያዣ ውል ፈራሽ ነው በሚል በመ/ በሆነው መዝገብ ላይ ከታች ወደ ላይ ያቀረቡት ክርክር የለም ክርክር ያቀረቡበትም ለመሆኑ ያቀረቡት ክርክር አልተገኘም። ይህም በመሆኑ ምክንያት በመ/ የተሰጠው ፍርድ ደረጃውን ጠብቆ በቀረበ ክርክር እንደገና ታይቶ ሥልጣን ባላቸው ፍ/ቤቶች እስካልተለወጠ ወይም እስካልተሻሻለ ድረስ የፀና እና ተፈፃሚነት ያለው ፍርድ ነው።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም በይግባኝ መ/ በቀረበለት የይግባኝ ጉዳይ የስር ፍ/ቤት በአንድ ጉዳይና በተመሳሳይ ተከራካሪ ወገኖች የተነሳውን ሁለት የተለያዩ ክሶች ከጉዳዩ አመራር ሥርዓት ውጭ ነጣጥሎ በማየቱ ምክንያት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 8፣ 11፣ 244(3) የተመለከቱትን ሥነ - ሥርዓታዊ ድንጋጌዎች የጣሰ መሆኑንና በማየትና በመ/ የተሰጠውን ፍርድ የአሁን አመልካች ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ ይረዳ ዘንድ በይግባኝ ደረጃ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ የመጨረሻ ዳኝነት ከመስጠቱ በፊት ያቀረቡት ክርክርና ማስረጃ በፍ/ብ/ስ/ስ/ሕ/ቁ 345 የተመለከተውን ሥነ - ሥርዓታዊ ድንጋጌ ምርኩዝ ያደረገና አቤቱታው ከድንጋጌው ትክክለኛ አፈፃፀም ጋር የሚጣጣም መሆኑን ሁሉ ተገንዝቦ በይግባኝ መዝገቡ ላይ ተገቢውን ፍርድ መስጠት እየቻለ በመ/ በሆነው መዝገብ ላይ ብቻ ተወስኖ ሚያዝያ 04 ቀን 2004 ዓ/ም የሰጠው ዳኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
እንዲሁም በመ/ በሆነው መዝገብ ለተነሳው ክርክር መሰረት የሆነው ነሐሴ 21 ቀን 1998 ዓ/ም የተደረገው የብድር እና የመያዣ ውል በህግ ፊት ላፀና የማይችል፤ ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል መሆኑ ተገልፆ ፈራሽነቱ በመ/ የተወሰነ በመሆኑና ይህም ውሳኔ ከታች ወደ ላይ ባለው የክርክር መስመር ታይቶ ያልተለወጠ ያልተሻሻለ ሆኖ በመገኘቱ የመጨረሻ ፍርድ ሆኖ ተገኝቷል። ከዚህም አንፃር ለብር 400,000.00 ብር (አራት መቶ ሺ) ክርክር መሰረት የሆነው የብድር ውል ፈራሽ ሆኖ በመገኘቱ ምክንያት ለዚህ የሰበር ጉዳይ መነሻ የሆነውና በመ/ የካቲት 25 ቀን 2003 ዓ/ም በዚሁ መዝገብ ላይ የአሁን አመልካች ለተጠሪ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺ) ይክፈሉ በሚል የተሰጠውም ፍርድ ዋጋ ያለው እና ተፈፃሚ ላሆን የሚችል ሆኖ ባለማግኘታችን የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ይግባኝ ሰሚው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሚያዝያ 04 ቀን 2004 ዓ/ም በጉዳዩ ላይ የሰጠው የመጨረሻ ፍርድ ተሽሯል።
የአሁን አመልካች ለተጠሪ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) ለመክፈል ግድታ የለባቸውም ብለናል።
የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት መዝገቡ የመ/ በመጣበት አኳኋን ይመለስ።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የተደረገው ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ፡