No summary available.
የካቲት 12 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ኢትዩ ቴልኮም VC በትክክል ላሥራ ሰላልቻለ መቅረብ ማረጋገጥ አልተቻለም።
ተጠሪ፡-
ጉዳዩ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የቀረበውን የደመወዝ ጭማሪና የቦነስ ክፍያ ጥያቄን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁን ተጠሪዎች በአሁን አመልካች ላይ በድሬዳዋ ከተማ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ላይ ሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት ክስ መነሻ ነው የተጠሪዎች ክስ ይዘትም ከቀድሞ የኢትዮጵያ ቴልኮሙንኬሽን ኮርፖሬሽን እና በሰራተኛ ማሕበር መካከል በ1999 ዓ/ም በተፈረመ የሕብረት ስምምነት መሰረት ከሐምል 01 ቀን 2001 ዓ/ም አስከ ሰኔ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ለሰሩበት ከሐምል 01 ቀን 2002 ዓ/ም ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪ እንዲሁም በጰጉሜ 2002 ዓ/ም ለሰራተኛ የተደረላቸውን የቦነስ ክፍያ አመልካች እንዳልከፈላቸው ገልፀው እንዚህን ክፍያዎች እንዲከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክሮች አቅርቧል። አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያነሣቸው ነጥቦች ጉዳዩ በአዲስ አበባ አሰሪና ሰራተኛ ጉሣይ ወሣኝ ቦርድ እየታየ ባለበት ሁኔታ በድጋሚ ልላ ቦታ ክስ መቅረቡ ያለአግባብ መሆኑን፣ ተጠሪዎች የመክሰስ መብት የልላቸው መሆኑን እና ክሱ በስድስት ወር ይርጋ የሚታገድ መሆኑን ገለፆ የተከራከረባቸው ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ደግሞ ተጠሪዎች ለክሱ መሰረት ያደረጉት የሕብረት ስምምነት የተፈጻሚነት ጊዜው ያላበቃለት በመሆኑ ለደመወዝና ለልሎች ጥቅማጥቅሞች ተፈፃሚ የሚሆንበት የህግ አግባብ የልለ መሆኑን ተጠሪዎች የደመወዝ መጠናቸውና ይገባናል የሚሉትን ጭማሪና ቦነስ መጠኑን ለይተው ያለማቅረባቸው የአመልካችን የመከላከል መብት የሚያጣብብ ከመሆኑም በላይ ከዳኝነት አሰጣጡም አመቺ ያለመሆኑን አመልካች በበጅት አመቱ የአግልግሎት ጥራትና ምርታማነቱን ከፍ ያደረገ ስለመሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ክፍያዎቹ የሚጠየቁበት አግባብ የልለ መሆኑንና በህብረት ስምምነቱም የክፍያዎቹ ጥያቄዎች የሚፈፀሙት ከማህበሩ ጋር አመልካች በሚያደርገው ድርድር እንጂ በሰራተኞች ቀጥታ ጥያቄ ያለመሆኑን ዘርዝሮ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ቦርድም የአመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦችን ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎ አመልካችን ለክሱ ኃላፊ በማድረግ ለተጠሪዎች ከሐምል 01 ቀን 2002 ዓ/ም ጀምሮ የደመወዝ ጭማሪ እንዲያደርግ ክፍያውም በህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 18 መሰረት እንዲፈፀም ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የቦርዱ ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ጉዳዩ በይርጋ የሚታገድ ሁኖ እያለ መታለፉም ሆነ የህብረት ስምምነቱ ተፈጻሚነቱ ያበቃ ሁኖ እያለ ለክፍያዎቹ ጥያቄ ተፈፃሚ እንዲሆን መደረጉ ያላግባብ መሆኑን የደመወዝ ጭማሪ የሚደረገው አመልካች የአገልግሎት ጥራት እድገትና አመታዊ የትርፍ ገቢ ከተገኘ ስለመሆኑ በህብረት ስምምነቱ በግልጽ ተቀምጦ እያለና ይህ ስለመሆኑ ተጠሪዎች አግባብነት ባለው የስነድ ማስረጃ ሳያረጋገጡ መሆኑን ዘርዝሮ ውሳኔው እንዲሻር ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች የተጠቀሰውን የደመወዝ ጭማሪ ለተጠሪዎች ይክፈል ተብሎ በአስሪና ሰራተኛ ጉዳይ ውሳኝ ቦርድ የመወሰኑንና በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የመጽናቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸውም 1ኛ፣2ኛ፣84ኛ እና ከ86ኛ እስከ 93ኛ፣ 6ኛ፣7ኛ 8ኛ፣27ኛ፣ 53ኛ.55ኛ፣61ኛ 69ኛ፣74ኛ 81ኛ፣ 85ኛ 94ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች ቀርበው መልሳቸውን በጽሑፍ ያቀረቡ ሲሆን 5ኛ፣ 9ኛ፣ 19ኛ፣29ኛ፣ 31ኛ፣ 38ኛ፣46ኛ፣ 48ኛ፣ 53ኛ፣ 56ኛ፣ 69ኛ፣ 73ኛ፣ 74ኛ79ኛ 81ኛ፣ 82ኛ፣ 84ኛ፣8 5ኛ ተራ የተጠቀሱት ተጠሪዎች መጥሪያ በህጉ አግባብ ደርሷቸው ባለመቅረባቸው በጽሑፍ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፏል። ልሎች ተጠሪዎችም በህጉ አግባብ ጥሪ ተደርጎላቸው ያልቀረቡ በመሆኑ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፏል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመውም ለጉዳዩ አግባብነት ያለው የይርጋ ጊዜ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162/1/ ስር የተመለከተው ነው? ወይስ በዚሁ አንቀጽ ንዑስ ቁጥር ሶስት ስር የተመለከተው ነው? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ክስ ላመሰረቱ የቻሉት አመልካች በ1999 ዓ/ም በወጣው የድርጅቱ የሕብረት ስምምነት መሰረት በ2001 ዓ/ም የበጀት አመት ከሐምል 01 ቀን 2002 ዓ/ም ጀምሮ ላከፈል የሚገባቸውን የደመወዝ ጭማሪ በጳጉሜ 2002 ዓ/ም ለሰራተኞች ያደረገውን ቦነስ አልከፈለንም በሚል ምክንያት ሲሆን አመልካች የተለያዩ የመቃወሚያ የክርክር ነጥቦችን ከማቅረቡም በተጨማሪ የደመወዝ ጭማሪ የሚከፍልበትን ስርዓትና የህብረት ስምምነቱን የተፈፀሚነት ጊዜ ጠቅሶ ኃላፊነት የለብኝም ሲል ተከራክራል። ቦርዱም ሆነ ይግባኙን የተመለከተው ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካች ክርክር ውድቅ ያደረጉት የሕብረት ስምምነቱ በልላ እስከሚተካ ድረስ ተፈፃሚ እንዲሆን የድርጅቱና የማህበሩ ተወካዮች ሚያዚያ 30 ቀን 2001 ዓ/ም ተስማምተው የፈረሙበትና በማህተም ያረጋገጡት ማስረጃ እንዲሁም ስምምነቱ ለሰራተኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለምዝገባ ቀርቦ ጸድቆ የተመዘገበ ስለመሆኑ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግንቦት 02 ቀን 2001 ለሁለቱም ወገኖች በአድራሻ የፃፈላቸው ደብዳቤ ፎቶ ያስረዳል በሚል ምክንያት መሆኑንና ህብረት ስምምነቱ ተፈፃሚ እንዲሆን ግራ ቀኙ ከተሰማሙ ደግሞ ሕጋዊ አይደለም በማለት የቀረበው የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የልለው መሆኑን በመግለጽ መሆኑን ከውሳኔው ግልባጭ ተገንዝበናል። እኛም ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ ተመልክተናል።
አመልካች የተጠሪዎች የደመወዝ ጭማሪና የቦነስ ክፍያ በይርጋ የታገደ ነው በማለት የሚከራከረው የአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 162/3/ ስር የተጠቀሰውን ስድስት ወር ጊዜ በመጥቀስ ነው። ቦርዱም ሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረጉት ለጉዳዩ አግባብነት ያለው በአዋጁ አንቀጽ 162/1/ ስር የተጠቀሰው የአንድ አመት ጊዜ ነው በሚል ምክንያት ነው። ይህ ችሎትም ጉዳዩን ሲመለከት የተጠሪዎች ክስ ለቦርዱ የቀረበው ሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ/ም ሁኖ የዳኝነት ጥያቄው መሰረት የሆነው ደግሞ የደመወዝ ጭማሪ ነው። ይህ የደመወዝ ጭማሪ የሚደረገውም አመልካች ደርጅት በ2001 ዓ/ም የበጀት አመት የአግለግሎት ጥራት እድገትና አመታዊ ትርፍ ግብ ሲመታ ስለመሆኑ አመልካች ራሱ ጠቅሶ የሚከራከርበት የድርጅቱ የሕብረት ስምምነት በግልጽ የሚያሳየው ጉዳዩ ነው። እንግዲህ ከዚህ የህብረት ስምምነት ይዘት እና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው የደመወዝ ጭማሪ የድርጅቱን የበጀት አመት የጥራት እድገትና የትርፍ ግብ መምታትን መሰረት ያደረገ መሆኑን ሲሆን የድርጅት የበጀት አመት በግልጽ አንድ አመት መሆኑ ከመጠቀሱም በላይ የድርጅቱ የጥራት እድገትና ትርፍ መኖሩ የሚረጋገጠው ደግሞ ከበጀት አመቱ መጠናቀቅ በኋላ መሆኑ እሙን ነው። ስለሆነም የድርጅቱ የጥራት እድገትና ትርፍ ግብ መምታቱ የሚረጋገጠውና የደመወዝ ጭማሪውም በዚሁ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ከሆነ ተጠሪዎች ጥያቄውን ማቅረብ የሚችሉት የበጀት አመቱ በተጠናቀቀ እና የደመወዝ ጭማሪውን ለማስገኘት የሚያስችለው ሁኔታ መሟላቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑ እሙን ነው። አከራካሪው ጉዳይ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሚቆጠረው የይርጋ ጊዜ ርዝማኔ ነው። ይኼውም ጊዜው ስድስት ወር ነው ወይስ አንድ አመት ነው የሚለው የህግ ጥያቄ በአግባቡ ላለይ ይገባል።
ከላይ እንደተጠቀሰው በግራ ቀኙ የቀረበው ሙግት የስራ ክርክርን የሚመለከት ነው። ለክርክሩ አግባብነት ያለው ሕግም የአዋጅ ቁጥር 377/96 ነው። ይህ የአዋጅ ቁ.377/96 በክፍል አስር ምእራፍ አንድ አንቀጽ 162- 166 በሚገኙት ድንጋጌዎች ስር ስለ ይርጋ ደንብ ደንግጓል። የአዋጅ ቁ.377/96 የመብት ጥያቄዎች ለሚቀርቡበት የጊዜ ገደብ በአንቀጽ 162 ስር ደንግጓል። ከመነሻው የተጠቀሰው አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /1/ በዚህ ሕግ ወይም በልላ ሕግ በተለየ ሁኔታ እስካልተወሰነ በስተቀር ጉዳዩን ማቅረብ ከሚቻልበት ቀን አንስቶ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ካልቀረበ የመብቱ ጥያቄ በይርጋ እንደሚታገድ አመልክቷል። ይህ ድንጋጌ የጉዳዩ የይርጋ ጊዜ መቆጠር የሚጀምረው ጉዳዩን ለማቅረብ ከሚቻልበት ጊዜ አንስቶ መሆኑን ይጠቅሳል። እንዲሁም በሕግ የተለየ የጊዜ ገደብ ያልተደረለት ጉዳይ ሁሉ አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ላቀርብ እንደሚገባው በመደንገግ አጠቃላይ የሆነ የጊዜ ገደብ አስቀምጧል። በተጨማሪም ይኸው የአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 162 በንዑስ አንቀጽ /2/ ፣/3/ እና /4/ ላይ ሕጉ የተለየ የይርጋ ጊዜ የወሰነላቸው የአቤቱታ አይነቶች ለይቶ አመላክቷል። የአዋጁ አንቀጽ 162 የተለየ ይርጋ ጊዜ ከወሰነላቸው የመብት ጥያቄዎች ውስጥ የመጀመሪያ የሆነው አንቀጽ 162/2/ “ሰራተኛው የስራ ውሉ ከሕግ ውጭ ተቋርጦብኛል በማለት ወደ ሥራው ለመመለስ የሚያቀርበው ክስ ውሉ በተቋረጠ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ይታገዳል” በማለት ደንግጓል። በልላ በኩልም የስራ ውልን መቋረጥ ምክንያት አድርጎ ሰራተኛው በአሰሪው ላይ አላያም አሰሪው በሰራተኛው ላይ የሚያነሳው የክፍያ ጥያቄ የስራ ውሉ ተቋረጠ በስድስት ወር ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ እንደሚታገድ በዚሁ አንቀጽ 162/4/ ላይ ተደንግጓል። በግልፅ እንደሚታየው የመጀመሪያው ድንጋጌ የስራ ውሉን መቋረጥ ሕጋዊነት በመቃወም ወደ ስራዬ ልመለስ ይገባል የሚል ሰራተኛ ይህን ጥያቄውን ለማቅረብ የሶስት ወር ጊዜ ብቻ እንዳለው ያስገነዝባል። ሁለተኛው ድንጋጌ ደግሞ የስራ ውልን መቋረጥ መነሻ አድርገው የሚቀርቡ ማናቸውም አይነት የክፍያ ጥያቄዎች በስድስት ወር ጊዜ ውስጥ የተገደቡ መሆናቸውን ያመላክታል። በተጨማሪም ከእነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች አቤቱታ አቅራቢው ስራ ውሉ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ በመብቱ መጠቀም የሚችል መሆኑን መረዳት ይቻላል። ልላው የአዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 162 የተለየ የይርጋ ጊዜ የወሰነለት የአቤቱታ በንዑስ አንቀጽ /3/ ላይ ተመልክቷል። ይኸውም “ሰራተኛው የሚያቀርበው ደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓትና የልሎች ክፍያዎች ጥያቄ መጠየቅ ከሚገባው ጊዜ ጀምሮ እስከ ስድስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ….” መቅረብ እንደሚገባውና ይሄ ካልሆነ በይርጋ እንደሚታገድ ተደንግጓል። ከድንጋጌው መረዳት እንደሚቻለው ይህን አንቀጽ ተመስርቶ የሚቀርብ የመብት ጥያቄ በአሰሪውና በሰራተኛው መካከል የተፈፀመው የስራ ውል ፀንቶ በአለበት ሁኔታ ሰራተኛው ከአሰሪው የሚጠይቀው ክፍያ የሚመለከት እንጂ የግድ የስራ ውሉን መቋረጥ ተከትሎ የሚነሳ አይደለም። በተጨማሪም የስድስት ወሩ የይርጋ ጊዜ አንደመብቱ መብሰል እየታየ ላወሰን የሚገባው ወይም መብቱን መጠየቅ/ላጠይቅ/ ይገባ ነበር የሚሰኝበት እለት ተመስርቶ መቆጠር የሚጀምር እንጂ ውስን መነሻ ጊዜ የተቀመጠለት አይደለም። ይኽ አንቀጽ 162/3/ ሰራተኛው አሰሪውን ደመወዝ፣ የትርፍ ሰዓትና ልሎችም ክፍያዎችን ላጠይቅ የሚችልበትን ውስን ጊዜ ያስቀመጠ ቢሆንም የስራ ውልን መቋረጥ ለይርጋው ጊዜ አቆጣጠር እንደመነሻ ባለመወሰዱ ከአንቀጽ /2/ እና /4/ ይለያል። እንዲሁም የድንጋጌው ይዘት ሲታይ ክፍያዎቹ ስራ በመስራት የሚገኙ መሆናቸውን ይገልፃል። በመሆኑም ልሎች ክፍያዎች የሚለው የድንጋጌው ሐረግ የሚያሣየው ሰራተኛው ስራውን በመስራት ላያገኝ የሚችላቸውን ክፍያዎች ስለመሆኑ የድንጋጌው አቀራረጽ ያሣያል። ከድንጋጌው ውስጥ “...የልሎችም ክፍያዎች..” ወይም “.. 0thher payments ~ የሚለው ሐረግ ጠቅላላ ቃል መሆኑ ግልጽ ሲሆን እንዲህ በሆነ ጊዜ ቃሉን ሕግ አውጪው የተጠቀመው ምንን ለማመላከት ነው? የሚለውን ጥያቄ ማንሣቱ ተገቢ ሲሆን የሕግ አተረጓጎም መርሆዎችን መሰረት በማድረግም ምላሹን ማግኘት ይቻላል። በዚህም መሰረት ከጠቅላላው ቃል በፊት የተዘረዘሩት የቃላት ዝርያ የሚያሣዩትን ሁኔታ በመመልከት ጠቅላላ ቃል ልሎች ያልተዘረዘሩትን ተመሣሣይ ዝርያ ያላቸውን ቃላት ለመጠቀም ታስቦ የተቀመጠ ነው በሚል እንደሚተረጎም ተቀባይነት ያላቸው የሕግ አተረጓጎም መርሆዎች ያስገነዝባሉ። በመሆኑም ደመወዝ የትርፍ ሰዓት ክፍያዎች በመርህ ደረጃ ስራ ሲሰራ የሚከፍሉ የክፍያ ዓይነቶች ሲሆኑ በድንጋጌው የገባው የልሎች ክፍያዎች ሐረግም ይዘቱና መንፈሱ ሲታይ በዚህ መልክ ለሰራተኛው የሚገቡትን የክፍያ አይነቶችን የሚገልጽ ነው። ይርጋውም ሰራተኛው የተጠቀሱትን ክፍያዎች ይጠይቅ ይገባው ነበር ከሚሰኝበት ጊዜ ይነሣና ምናልባትም የሥራ ውሉ ተቋርጦ እንኳ ቢሆን ይኸን ከግምት ውስጥ ያስገባና እስከ ስድስት ወር ድረስ መቆጠሩ ይቀጥላል። እንግዲህ በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 162 መሰረት አንድ የሥራ ክርክር ጉዳይ የተለየ የይርጋ ጊዜ የተቀመጠላቸውን የመብት ጥያቄዎች የሚመለከት ከሆነ ከንዑስ አንቀጽ /2/ እስከ /4/ የተጠቀሱትን የሦስት ወይም ስድስት ወራት የጊዜ ገደብ አክብሮ የቀረበ ላሆን ይገባዋል። በእነዚህ ድንጋጌዎች ሥር የማይሸፈን ከሆነ ደግሞ ንዑስ አንቀጽ /1/ በተመለከተውና በአንፃሩም ሰፊ በሆነው የአንድ ዓመት የጊዜ ወሰን ውስጥ አንዲቀርብ ያስፈልጋል። በልላ በኩል ደግሞ ይህ የይርጋ ጊዜ የተወሰነበት የአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 162 ሰራተኛውና አሰሪው አንዱ ከልላቸው የመብት ጥያቄዎችን የሚያቀርቡበትን ሁኔታ ብቻ በመጥቀስ የተደነገገ መሆኑን ከአንቀጾቹ መገንዘብ ይቻላል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም ተጠሪዎች እንዲከፈላቸው የጠየቁት ክፍያ ስራ በመስራት የአመልካችን ድርጅት እቅድና ግብ ሲያሳኩ የሚገኙት ክፍያ የሚመለከት እንጂ አመልካች ስራ ባይሰራ ቢቀርም በህብረት ስምምነቱ መሰረት ላፈከላቸው የሚገባውን ጥቅማ ጥቅም የሚመለከት አይደለም። እንዲህ ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162/3/ ስር በተመለከተው ድንጋጌ ልሎች ክፍያዎች በማለት የተቀመጠው ሐረግ እንደተገለፀው ሰራ በመስራት ሰራተኛው የሚያገኛቸውን የክፍያ አይነቶች የሚሸፍን እንጂ በሕብረት ስምምነቱ ስራ ከመስራት ውጪ የሚገኙትና የተጠበቁትን ክፍያዎችን የሚሸፈን አይደለም። በመሆኑም ለጉዳዩ አግባብነት ያለው የይርጋ ጊዜ በአዋጁ አንቀጽ 162/1/ ሥር የተመለከተው የአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ሣይሆን በአንቀፁ ንዑስ ቁጥር ሶስት ድንጋጌ ስር የተቀመጠው የስድት ወር ጊዜ በመሆኑና ይህ የስድስት ወር ጊዜ ገደብም የአመልካች የበጀት ዓመት የተጠናቀቀበት ወይም ድርጅቱ የአገልግሎት ጥራት እድገትና ምርታማነቱን ግቡን ማሣካቱን ከአረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ ላቆጥር የሚገባው በመሆኑ ተጠሪዎች በዚህ ረገድ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው የአንድ አመት ይርጋ ነው በማለት ከመከራከራቸውም ውጪ ስድስት ወር ያላለፈው መሆኑን ገልጸው ያልተከራከሩ በመሆኑ ወይም የአመልካች የበጀት አመት ሰኔ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ተጠናቅቆ ተጠሪዎች ክስ ያቀረቡት ሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም መሆኑን የክርክሩ ሂደት በግልጽ ስለሚያሳይ አመልካቾች ያቀረቡት የዳኝነት ጥያቄ በስድስት ወር የይርጋ ጊዜ የታገደ ነው።
ሲጠቃለልም ቦርዱም ሆነ የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ከላይ በተዘረዘረው ምክንያት አግባብ መመልከት ሲገባቸው ለጉዳዩ አግባብነት ያለው የአንድ አመት ይርጋ ነው በማለት የሰጡት ውሳኔ በተጠሪዎች የተጠየቀው የዳኝነት ጥያቄ ስራ ከመስራትና የድርጅቱን እቅድና ግብ ከማሳካት ጋር የተያያዘ የክፍያ አይነት መሆኑን ሳያገናዘቡ የተሰጠ በመሆኑ በዚህ ረገድ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የፈጸሙ ሁኖ ስላአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ውሣኔ
በድሬዳዋ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ጥቅምት 07 ቀን 2004 ዓ.ም ተሰጥቶ በፍደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ሚያዝያ 04 ቀን 2004 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348 (1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪዎች በአመልካች ላይ ያቀረቡትና እንዲከፈላቸው የተወሰነው የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 162 (3) መሰረት በስድስት ወር የጊዜ ገደብ የታገደ ነው ብለናል።
አመልካች ክፍያውን ላከፍል አይገደድም ብለናል።
No topics extracted.