No summary available.
ግንቦት 6 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ዋላያ የቆዳ ማለስለሻ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ጠበቃ አቶ አይሸሹም መድፉ በመዝገብ ቤት እሰማለሁ በማለታቸው ዛሬ አልቀረቡም ተጠሪዎች፡- አቶ ደረጀ ውለታው - ተጠሪም በተመሳሳይ ምክንያት አልቀረቡም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ አንድ ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ ለደረሰ የአካል ጉዳት ካሳ ክፍያ እንዲከፈለው በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 96(1) አግባብ አሰሪውን ያለጥፋት በስራ ክርክር ችሎት ከሶና አስፈርዶ ክፍያውን ከተቀበለ በኋላ በዚያው ጉዳት የአሰሪውን ጥፋት መነሻ በማድረግ የጉዳት ካሳ ክፍያ ከውል ውጪ ባለው ህግ ድንጋጌዎች መሰረት በተጨማሪ እንዲከፈለው በፍ/ብሕር ችሎት ክስ ለማቅረብ የሚያስችል የህግ አግባብ መኖር አለመኖሩን የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፍድራሉ መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ ተከሳሽ በመሆን ነበር።
የተጠሪ ክስ ይዘትም በአመልካች ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ በመስራት ላይ እያለ አራት የቀኝ እጅ ጣቶች እና ሦስት የግራ እጅ ጣቶች በማሽን የመቆረጥ የአካል ጉዳት እንደደረሰበትና ጉዳቱም የደረሰው በአሰሪው ጥፋት መሆኑን በመግለፅ እና በዚህ ምክንያት ላከፈለው የሚገባው የጉዳትና ሞራል ካሣ ክፍያ በድምሩ ብር 335,680 አመልካች እንዲከፍለው እንዲወሰንለት ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። አመልካችም ቀርቦ ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ አሁን ክስ ባቀረቡበት የአካል ጉዳት ካሣ ክፍያ ከዚህ ቀደም በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 96(1)፣ 97 እና 109 ድንጋጌዎች መሰረት በስራ ክርክር ችሎት ክስ አቅርቦና በዚሁ መሰረት ብር 24,000 አስፈርዶ ገንዘቡን በአፈፃፀም ከተቀበለ በኋላ በዚያው ጉዳት ተጨማሪ የጉዳት ካሣ ክፍያ ጥያቄ ለማቅረብ የማይችል መሆኑን በመጀመሪያ መቃወሚያነት ያቀረበ ሲሆን በፍሬ-ነገር ደረጃም ጉዳቱ የደረሰው በአመልካች ጥፋት ባለመሆኑ ካሣ የመክፈል ኃላፊነት የልለበት መሆኑንና በድጋሚ የቀረበው የክስ አቤቱታም የህግ መሰረት እንደልለው በመግለፅ ክሱ ውድቅ ተደርጎ ላወሰን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ አሁን የቀረበው ክስ ከከዚህ ቀደሙ ክስ ጋር ጭብጣቸው የሚለያይ ነው በሚል ምክንያት የቀረበውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ መደረጉን ከገለፀ በኋላ ፍሬ-ነገር ክርክሩን አስመልክቶ አሰሪው ተጠሪ በሚሰራበት ማሽን ላይ ተገቢ የጉዳት መከላከያ መሣሪያ ባለመግጠሙ እና በአሰሪው ጥፋት ጉዳቱ የደረሰ ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል በማለት አመልካች ለደረሰው ጉዳት ኃላፊ ነው ሲል ከወሰነ በኋላ የጉዳት ካሣ መጠኑን በተመለከተም ተገቢ ነው ባለው አኳኋን አስልቶ ባጠቃላይ ብር 139,219.9 አመልካች ለተጠሪ ይክፈል በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ቀርበው እንዲከራከሩ ከተደረገ በኋላ የበታች ፍ/ቤት ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል። አሁን የቀረበው የሰበር አቤቱታም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ሲሆን መሰረታዊ ይዘቱም ለሁለቱም ክሶች ብቸኛ ምክንያት የሆነውና በተጠሪ ላይ ለደረሰው የአካል ጉዳት ካሣ ክፍያ በስራ ክርክር ችሎት ተወስኖለት በአፈፃፀም ካሳውን የተቀበለ ሲሆን ሆኖም ግን በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 96(3) ድንጋጌ አግባብ የጉዳት ካሣ ጥያቄ የማቅረብ መብት የተሰጠው ሰራተኛው ከፍ/ብሕር ህጉና ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ህጉ አንዱን በመምረጥ በአሰሪው ላይ ያለጥፋት ኃላፊነት ወይም በጥፋት ላይ በተመሰረተ በአንዱ ክስ የማቅረብና እንዲካስ እንጂ ያለጥፋት ክስ አቅርቦ ካሣውን ከተቀበለ በኋላ በዚያው የአካል ጉዳት በጥፋት ላይ በተመሰረተ ኃላፊነት ድጋሚ የጉዳት ካሣ ለመጠየቅ አይደለም። የአንቀጽ 96 ንዑስ አንቀጽ 3 በአዋጁ ውስጥ እንዲካተት የተደረገው በሰራተኛው ላይ የደረሰው ጉዳት በአሰሪው ጥፋት ከሆነ ለሰራተኛው ላከፈለው የሚገባ የካሣ መጠን በአዋጁ አንቀጽ 109 ስር በተወሰነው እንዳይገደብ ለማድረግ ነው። በመሆኑም ድንጋጌው ተፈፃሚ ላደረግ የሚገባው ከፍ ሲል በተገለፀው መልኩ ሆኖ ሳለ የበታች ፍ/ቤቶች ለድንጋጌው የሰጡት ትርጉም ከድንጋጌው አነጋገር ጋር የማይሄድ ከመሆኑም በላይ አንድ ተጎጂ ለአንድ ጉዳት ሁለት ጊዜ ካሣ የመጠየቅና ሁለት ጊዜ ካሣ የማግኘት መብት አለው በማለት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ከበቂ ኪሣራና ወጪ ክፍያ ጋር ተሽሮ እንዲወሰንለት በመጠየቅ አመልክቷል። አቤቱታውም ተመርምሮ ተጠሪ አንድ ጊዜ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ያለጥፋት ኃላፊነት በአመልካች ላይ በስራ ክርከር ችሎት ክስ አቅርቦ እና አስፈርዶ የጉዳት ካሳ ክፍያውን ከተቀበለ በኋላ በዚያው ጉዳት እንደገና አሰሪውን በጥፋት ላይ በተመሰረተ ኃላፊነት በፍ/ብሕር ክርከር ችሎት ልላ ክስ አቅርቦ የጉዳት ካሳ እንዲከፈል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪም ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ግራ ቀኙ በፅሁፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
በመሰረቱ አንድ ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ ጉዳት ከደረሰበት አሰሪው ጥፋት ባይኖርበትም ለደረሰው ጉዳት ካሣ የመክፈል ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 96(1) ድንጋጌ ስር የተመለከተ ሲሆን የካሣ መጠኑም በህጉ በተቀመጠው ስልት መሰረት የሚከፈል ስለመሆኑ ከተጠቃሹ አዋጅ አንቀጽ 109 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። ይህንን የጉዳት ካሣ ዳኝነት ጥያቄ ተቀብሎ እና አይቶ ውሳኔ ላሰጥ የሚገባው አካልም የሥራ ክርክር ችሎት እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 138(1)(ሰ) ድንጋጌ ስር ተለይቶ የተቀመጠ ጉዳይ ነው።
በልላ በኩል ጉዳቱ በሰራተኛው ላይ ላደርስ የቻለው በአሰሪው ጥፋት ምክንያት የተነሳ እንደሆነ ሰራተኛው የጉዳት ካሣ ክፍያ ጥያቄውን አግባብ ባለው ህግ መሰረት መጠየቅ እንደሚችል ከተጠቃሹ አዋጅ አንቀጽ 96(3) ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ የሚቻል ሲሆን በዚህ ንዑስ አንቀጽ አግባብ መሰረት የሚቀርብ የጉዳት ካሳ ክፍያ ጥያቄም በፍትሐብሕር ክርክር ችሎት ታይቶ ላወሰን እንደሚገባ የሚታወቅ ጉዳይ ነው። ይሁን እንጂ የተጠቃሹ አዋጅ እና አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ ተፈፃሚነት ላኖረው የሚችለው ሰራተኛው በህጉ የተመለከቱትን መብቶች በአግባቡ እና በቅጡ በትክክል ተገንዝቦ እንደየጉዳዩ ሁኔታ ዓይነት እና አግባብነት በተሻለ ሁኔታ የሚጠቅመውን የመብት አድማስ አውቆ በመለየት ተገቢው መብቱ ከመነጨበት ህግ አግባብ አንፃር ለማቅረብ ሲችል ነው።
ሰራተኛው ከደረሰበት ጉዳትና ከጉዳቱ አፈፃፀም በመነሳት ከሁለቱ የአሰሪ ኃላፊነት መንገዶች ውስጥ አንዱን ብቻ በመምረጥ አሰሪውን ያለጥፋት ወይም የአሰሪውን ጥፋት መሰረት ባደረገ ኃላፊነት ክሱን ከወዲሁ ለይቶ የተሻለ መብቱ ከመነጨበት ህግ አኳያ ከሚያቀርብ በስተቀር በአዋጁ አንቀጽ 96(1) እና 96(3) ስር የተመለከቱትን መብቶች ሁለቱንም በማፈራረቅ እንደፈለገ እንዲጠቀም ለማስቻል ታስቦ እና ተፈልጎ አይደለም። በተጨማሪም አንድ ሰው ክሱን መስርቶ ዳኝነት በሚጠይቅበት ጊዜ በክስ አቤቱታው ላይ የሚጠይቀውን መብት የሚያቋቁሙለትን ትክክል የሆኑትንና የሚታዩትን ተጨባጭ ፍሬ-ነገሮችን ብቻ ገልፆ በማስፈር ክስ ማቅረብ እንዳለበት ከፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 80(2) ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻል ሲሆን ይህ በክስ አቤቱታው ላይ ተገልፀው የሚቀርቡት ፍሬ-ነገሮችም እውነት ስለመሆናቸው በአቤት ባዩ መረጋገጥ እንዳለበት እንዲሁ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 92 ድንጋጌ ስር ተመልክቷል።
የክስ አመሰራረት እና አቀራረብን አስመልክቶ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህጉ ከተደነገጉት አግባብነት ካላቸው ከፍ ሲል ከተገለፁት መገንዘብ የሚቻል ሲሆን ከዚህ አኳያ ደግሞ አንድ ሰራተኛ አንድ ጊዜ በስራ ላይ የደረሰበት ጉዳትን መነሻ በማድረግ አንድ የአሰሪውን ያለጥፋት ኃላፊነት ላያስከትሉ የሚችሉ ፍሬ-ነገሮችን በመግለፅ በልላ ጊዜ ደግሞ ያንኑ ጉዳት በሚመለከት የአሰሪውን በጥፋት ላይ በተመሰረተ ኃላፊነት የሚያስከትሉ ፍሬ-ነገሮችን እንደፈለገ እና በዘፈቀደ በመግለጽ የተለያየ ዓይነት ክሶችን ለማቅረብ፣ በክርክር አመራር ስርዓት የሚደገፍ እና ተቀባይነት ያለው ድርጊት አይደለም። ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም ተጠሪ ለዚህ ክርክር መነሻ በሆነው ጉዳት መነሻነት አመልካችን ያለጥፋት ለጉዳቱ ኃላፊ በሚያደርገው አኳኋን በስራ ክርክር ችሎት ክስ አቅርቦ እና የአካል ጉዳት ካሳ ክፍያውን ብር 24,000 አስፈርዶ በአፈፃፀም መቀበሉ ይታወቃል። ይህ ከሆነ ደግሞ ከፍ ሲል በተገለፀው መልኩ በልላ ጊዜ በድጋሚ ያንኑ ጉዳት በሚመለከት በጥፋት ላይ በተመሰረተ ኃላፊነት የጉዳት ካሳ ክፍያ ከውል ውጪ ባለው ህግ ድንጋጌዎች መሰረት በፍትሐብሕር ችሎት ታይቶ እንዲወሰንለት ያቀረበው ክስ ተገቢነት የለውም ምክንያቱም ጉዳዩ በልላ አኳኋንና መልክ ይዞ ቢሆንም አስቀድሞ ቀርቦ ውሳኔ እንዳገኘ የሚቆጠር ነው። የመጨረሻ ውሳኔ ስላገኙ ጉዳዮች የሚያወሳው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5 ድንጋጌ ይዘት አድማሱ በግልጽ በተወሰኑ ጭብጦች ላይ ብቻ ሳይሆን በተከራካሪ ወገኖች ቢነሱ ኖሮ ላወሰኑ ይችሉ በነበሩ ጭብጦች ሁሉ ላይም ጭምር በመሆኑና ከዚህ አኳያ ተጠሪ በኋላ ላይ ያቀረበው የክስ ጭብጥም አስቀድሞ እንደቀረበ እና ውሳኔ እንዳገኘ ጉዳይ የሚቆጠር በመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 5(2) አንፃር በድጋሚ ላቀርብ አይችልም። በመሆኑም የበታች ፍ/ቤቶች በድጋሚ የቀረበውን የጉዳት ካሳ ክፍያ ጥያቄ ተቀብለው እና አይተው አመልካች ለተጠሪ ብር 139,219.9 እንዲከፍል በፍድራሉ መ/ደ/ፍ/ቤት ውሳኔ መሰጠቱም ሆነ ይሄው በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቱም መታረም ሲገባ መፅናቱ ከፍ ሲል በተገለፁት ምክንያቶች ሁሉ በአግባቡ እና ስነ-ስርዓታዊ ባለመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በመሆኑም ተከታዩን ወስነናል።
በፍድራሉ፤ መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ መስከረም 20 ቀን 2004 ዓ/ም ተወስኖ በፍድራሉ ከፍ/ፍ/ቤት መ/ ሚያዝያ 18 ቀን 2004 ዓ/ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት በድምፅ ብልጫ ተሽሯል።
ተጠሪ በህጉ ከተቀመጡት አማራጮች የላቀውን ጥቅም ወይም መብት የሚያስገኝለትን በመለየት የጉዳት ካሳ ጥያቄውን ማቅረብ ሲገባው በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 96(1) ድንጋጌ መሰረት ጥያቄውን በስራ ክርክር ችሎት አቅርቦና አስፈርዶ የካሳ ክፍያውን ከተቀበለ በኋላ እንደገና ያንኑ ጉዳይ በሚመለከት ከውል ውጪ ኃላፊነት በሚያስከትሉ ድንጋጌዎች አግባብ ያቀረበው ሁለተኛ ክስ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ተጠሪ በአዋጁ አንቀጽ 96(1) ድንጋጌ አኳኋን የጉዳት ካሳ ክፍያ ጥያቄ በስራ ክርከር ችሎት አቅርቦና አስፈርዶ የተቀበለ በመሆኑ ልላ ተጨማሪ የሚከፈለው የጉዳት ካሳ ክፍያ የለም ብለናል።
የሰበር ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.