No summary available.
ጥቅምት 07 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ነ/ፈጅ ፍሬው ሃይሉ ቀረቡ ተጠሪ፡- 1.አቶ ቶላ መገርሣ ቀረቡ 2.አቶ ታምራት ኃይል **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የስራ ግድታን ባለመወጣት በወንጀል ጥፋተኛ የተባለ የሲቪል ሰራተኛ በጥፋቱ ምክንያት የመንግስት ንብረት መጥፋቱ ሲረጋገጥ በሕግ ፊት ስላላው የፍትሐብሕር ሓላፊነትን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቸው ባሁኑ ተጠሪዎች ላይ በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡-ተጠሪዎች በአመልካች መስሪያ ቤት በጥበቃ ሰራተኛነት በማገልገል ላይ ሳሉ በአራዳ ክፍለ ከተማ ቀበል 01/02 አካባቢ ከሚገኘው የአመልካች መጋዝን በሚያዚያ 21 ቀን 2002 ዓ.ም. ልላት የጥበቃ ተረኛ በነበሩበት ወቅት የአመልካች የሆኑ መለያቸው 70 168 PR የሆኑ እያንዳንዳቸው ብር 1977.39 የሚያወጡ አስራ ሶስት ብሪጅስቶን ጎማዎችን ያጠፉ መሆኑንና ተጠሪዎችም የስራ ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት ሳቢያ ለፈፀሙት ወንጀል በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተብለው የተቀጡ መሆኑን ገልፆ ተጠሪዎች የጎማዎቹን ዋጋ ብር 25,706.07 (ሃያ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ስድስት ብር ከዜሮ ሰባት ሳንቲም) ባልተነጣጠለ ኃላፊነት እንዲከፍሉ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስም በአመልካች መስሪያ ቤት በጥበቃ ስራ ተቀጥረው በሚሰሩበት ጊዜ ንብረቶቹን ለስራ የተረከበው ግለሰብ ልላ መሆኑን ፣በወንጀል ጉዳይ የመሰከሩት ምስክርም እቃው ጠፋ በተባለበት ወቅት ያልነበሩና ያላዩ መሆናቸው መታወቁን፣መጋዝኑ ዝግ ሁኖ ማደሩ መረጋገጡን፣የገንዘብ መጠኑ ከፍ ያለ በመሆኑ በሰው ማስረጃ ላረጋገጥ እንደማይችል፣በርክክብ ሰነዱም ለተተኪ የጥበቃ ሰራተኞች በሰላም ማስረከባቸውንና ክሱም በማስረጃ ያለመደገፉን ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ተጠሪዎች በወንጀል የተቀጡ ስለመሆኑ ቢረጋገጠም ጠፉ የተባሉትን ንብረቶች የወሰዱ ስለመሆኑ የወንጀል ውሳኔው እንደማያሳይ፣ንብረት ቢጠፋ ተጠሪዎች የጠፋውን ንብረት ለአመልካች ለመክፈል የተደረገ ስምምነት ወይም ውል የልለ መሆኑና በጠፉት ንብረቶች ተጠሪዎች የበለፀጉበት ሁኔታ ስለመኖሩ የሚያሳይ ማስረጃ አለመቅረቡን በምክንያትነት ይዞ ተጠሪዎችን ከክሱ በነጻ አሰናብቷቸዋል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪዎች የስራ ግድታቸውን ባለመወጣት በወንጀል ጥፋተኛ ሁነው ተገኝተው እያለና የወንጀል ድርጊቱ በተፈፀመበት ጊዜ ደግሞ ጎማዎቹ መጥፋታቸው ተረጋግጦ እያለ ተጠሪዎች ለፍትሐ ብሕር ክሱ ኃላፊነት የለባቸውም ተብሎ ክሱ ውድቅ መደረጉ ያላግባብ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለሰበር ችሎቱ እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎችም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙኝ ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ምላሽ የሚያስፈልገው የጉዳዩ ጭብጥ ተጠሪዎች በአመልካች መስሪያ ቤት በጥበቃ ሰራተኛነት በማገለገል ላይ ሳሉ ጠፉ ለተባሉ ጎማዎች የስራ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም በማለት በወንጀል ከተቀጡ በኋላ ተጠሪዎች የጠፉትን ጎማዎች ግምት እንዲከፍሉ በቀረበባቸው ክስ ጎማዎቹን ወስደው ባለመበልጸጋቸው ወይም ጎማዎቹ ቢጠፉ ለመክፈል ከአመልካች ጋር ያደረጉት ውል ባለመኖሩ የሚከፈሉት ግድታ የለም ተብሎ መወሰኑ ተገቢ መሆን ያለመሆኑን የሚመለከት ነው።
ተጠሪዎች ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ጎማዎች መጥፋታቸውና የስራ ግድታቸውን ባለመወጣት በወንጀል የተቀጡ ስለመሆኑ ሳይክዱ ለጎማዎቹ ግምት ኃላፊነት የለብንም በማለት የሚከራከሩት ንብረቶቹን ስለመረከባችን የሚያሳይ ማስረጃ የለም፣መጋዝኑም አልተሰበረም፣ለወንጀሉ ጉዳይ ምስክርነት የሰጠው ግለሰብም ጉዳዩን ሳይመለከት ነው የመሰከረው የሚሉትን ምክንያቶችን በመጥቀስ ነው።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ በክሱ የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍሉ አይገባም ወደሚል ድምዳሜ መድረስ የቻለውም የወንጀሉ ውሳኔ ተጠሪዎችን ጎማዎቹን ስለመውሰዳቸው አይሳይም፣ ንብረቶቹ ሲጠፉም ለመክፈል ስምምነት ውል የለም፣ እንዲሁም ተጠሪዎች ስለመበልፀጋቸው የሚያሳይ ማስረጃ አልቀረበም በሚሉ ምክንያቶች ነው።
ይሁን እንጂ ተጠሪዎች አከራካሪ እቃዎቹን ለአመልካች መስሪያ ቤት እስከሚያስረክቡ ጊዜ ድረስ በጥበቃ ላይ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ በንብረቶቹ ላይ ለሚደርስ ማናቸውም ጉዳት፣ብልሽት ወይንም መጥፋት በኃላፊነት ተጠያቂ ላሆኑ ስለሚችሉ ይህ ችግር እንዳይከሰት ተገቢውን የጥበቃ ስራ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ይታመናል። አንድ ሰራተኛ ከአሰሪው መስሪያ ቤት ለስራ እቃዎቹን ሲረከብ የሚፈርመበት ዋናው ምክንያትም ይህንኑ ግድታውን ካልተወጣ ኃላፊነት ላከተልበት ስለሚገባውና የእቃዎቹን ግምት በማወቅ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲወጣ ለማስቻል እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 515/1999 እና በልሎች አግባብነት ያላቸው ሕጎች የተካተቱት ድንጋጌዎች ይዘት፣መንፈስና ዓላማ ያስገነዝባል። በልላ በኩልም ተጠሪዎች የአመልካችን ንብረቶች ያሉበትን መጋዝን ሲጠብቁ በመጋዝኑ ውስጥ ያሉት እቃዎች እንዳይጠፉ፣እንዳይሰረቁም ሆነ ልላ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የሚጠበቅባቸው በሥራ ሰዓት ሲሆን ንብረቶቹ በሥራ ሰዓት ከተጠሪዎች ጥንቃቄ ጉድለት ውጪ በሆነ ምክንያት ወይም ከሥራ ሰዓት ውጭና በተጠሪዎች እጅ ባልነበሩበት ጊዜ የጠፉ ስለመሆኑ የማስረዳት ሸክም አለባቸው። ይህንኑ ግድታቸውን የተወጡ ስለመሆኑ ደግሞ ከላይ እንደተገለጸው የበታች ፍርድ ቤቶች በፍሬ ነገር ደረጃ ማስረጃን መዝነው ያረጋገጡት ጉዳይ አይደለም። ይልቁንም አመልካች ተጠሪዎች የስራ ግድታቸውን ሳይወጡ ቀርተው በወንጀል ጥፋተኛ ተብለው የተቀጡ ስለመሆኑ የሚሳይ የውሳኔ ግልባጭ ያቀረበና ተጠሪዎቹም ቢሆኑ በወንጀል ጉዳይ ላይ የምስክርነት ቃል የሰጠውን ምስክር ጉዳዩን አይውቅም ብለው ከመከራከራቸው ውጪ በወንጀል ጉዳይ የተሰጠው ውሳኔ በስርአቱ መሰረት መለወጡን ገልጸው አልተከራከሩም። እንዲህ ከሆነ ተጠሪዎች የስራ ግድታቸውን ባለመወጣት ጎማዎቹ እንዲጠፉ ስለማድረጋቸው በወንጀል ችሎት ውሳኔ መረጋገጡን በቀላሉ መገንዘብ የምንችለው ጉዳይ ነው። ቀጥሎ መታየት ያለበት አቢይ ነጥብ በወንጀል ችሎት የተሰጠ ውሳኔ በፍትሐ ብሕር ክርክር ጊዜ ስላላው የማስረጃነት ዋጋ ነው። እንደሚታወቀው በወንጀል ጉዳይ የሚቀርበው ማስረጃ እና በፍትሃብሕር ጉዳይ የሚቀርበው ማስረጃ የሚመዘኑበት መርህ የተለያየ ነው። በወንጀል ጉዳይ የሚቀርበው ማሰረጃ የሚመዘነው ጥብቅ በሆነ መንገድ ሲሆን በፍትሐብሄር ጉዳይ የሚቀርበው ማስረጃ ደግሞ ከተከራካሪ ወገኖች መካከል የተሻለ ያስረዳ የትኛው ወገን ነው? የሚለው መለኪያ ተይዞ የማስረጃው ክብደት የሚለይበት ስርአት በመሆኑ የማስረጃ አመዛዘኑ መርህ ከወንጀል ጉዳይ የማስረጃ አመዛዘን መርህ የላላ ነው። እነዚህ ተቀባይነት ባለቸው የማስረጃ ሕግ ደንቦች የሚታወቁ የማስረጃ አመዛዘን መርሆች አንዱ በልላው ላይ ስላለው ውጤት ሲታይም በፍትሃብሕር ሕጋችን ቁጥር 2149 ስር የተመለከው ድንጋጌ ምላሽ ይሰጠናል። ይኸውም በፍትሃብሕር በኩል ጥፋት ተደርጎአል ብሎ ለመወሰን በወንጀል ፍርድ ተከሳሹ ነፃ መለቀቁ ወይም በወንጀል አያስከስሰውም ተብሎ መበየኑ ዳኞቹን አያግዳቸውም በሚል ሓይለ ቃል በያዘ መንገድ ተቀምጧል። የዚህ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዝበው ከወንጀል ክስ ነጻ መሰናበት የፍትሐብሕር ተጠያቂነትን ቀሪ የማያደርገው መሆኑን ነው። የድንጋጌው ተቃራኒ ንባብ ሲታይም በወንጀል ጥፋተኛ የተባለ ሰው በፍትሐብሕር ተጠያቂ መደረግ ያለበት መሆኑን ያስረዳል። ይህም በወንጀል ጉዳይ የሚቀርበው ማስረጃ በጥብቅ መንገድ የሚመዘን እስከሆነ ድረስ የላላ የማስረጃ ምዝና ስርዓትን ለሚጠይቀው የፍትሃብሕር ጉዳይ በቂ ዋጋ እንደአለው ተደርጎ መወሰድ አለበት የሚለው የማስረጃ ሕግ ደንብ መሆኑን የሚያሳየን ነው። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች በወንጀል ጉዳይ የተሰጠውን ውሳኔ ይዘት ከላይ ከተመለከተው ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ አንፃር ሳያገናዝቡ መወሰናቸው ያላግበብ ሁኖ አግኝተናል። ተጠሪዎች ስለመበልጸጋቸውና ንብረቶቹ ሲጎድሉ ለመክፈል ስምምነት ያለማድረጋቸው ከሃላፊነት ነፃ ለማድረግ በምክንያትነት መጠቀሱም በአመልካች ላይ በሕጉ ያልተጣሉ ግድታዎች በመሆኑ ተቀባይነት ያላቸው አይደሉም። በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዳዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ህዳር 22 ቀን 2004 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 14 ቀን 2004 ዓ/ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪዎች የስራ ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት በአመልካች ጎማዎች ላይ ላደረሱት ጉድለት በአንድነትና በነጠላ ብር 25,706.07 (ሃያ አምስት ሺኅ ሰባት መቶ ስድስት ብር ከዜሮ ሰባት ሳንቲም) እንዲከፍሉ ብለናል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.