No summary available.
ጥር 03 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሳ አዳነ ንጉሴ አመልካች፡- ወጋገን ባንክ ነ/ፈጅ ጌጡ ፀጋዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዐ/ህግ ሜሮን አንማው ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ በጉምሩክ ወንጀል ጥፋተኝነቱ የተረጋገጠበት የአሽከርካሪ ባለቤት ወይም አሽከርካሪ በቅጣት ረገድ ተሽከርካሪው በመንግሥት እንዲወረስ ውሳኔ ከተሰጠበትና የወንጀል ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት ተሽከርካሪው በባንክ መያዣነት መያዙ ከተረጋገጠ በሕግ ፊት ቅድሚያ ላጠበቅ የሚገባው በወንጀሉ ጉዳይ ተሽከርካሪው ውርስ እንዲሆን የተሰጠው ውሳኔ ነው ወይስ ወይም የመያዣ መብቱ ነው? የሚለውን የሕግ ጥያቄ የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በመቀል ከተማ ማዕከላዊ ፍ/ቤት ሚያዚያ 01 ቀን 2002 ዓ.ም ጽፎ ባቀረበው የክስ ማመልከቻ ነው። በክሱ ላይም ንብረትነቷ የአቶ በርሕ ሓጎስ አድሃና የሆነች የኮድ ቁጥር 3-29644 አ.አ አይሱዚ የጭነት መኪና አቶ ብርሕ ሓጎስ ከከሳሽ ባንኩ ሲበደሩ መኪናዋን አስይዘው ብር 90,000.00 /ዘጠና ሺህ/ መበደራቸውንና በየወሩ ብር 2,905.00 እየከፈሉ ክፍያውን በማቋረጣቸው መኪናዋ በፎርክሎጀር ሕግ መሰረት ተሸጣ ለእዳው የሽያጭ ገንዘቡ ገቢ እንዲሆን በፍድራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን ትዕዛዝ የተሰጠባት መኪና ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን የመቀል ቅርንጫፍ ጠይቆ መኪናዋ ቦንዳ ጭና በመገኘቷ የተወረሰች መሆኑን ለባንኩ የገለፀላቸው መሆኑን ገልጾ በመኪናው ላይ ከማንኛውም ወገን ቅድሚያ ያለው በመሆኑ መኪናውን ተጠሪ እንዲያስረክብ ይወሰንለት ዘንድ ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። ተጠሪ ለአመልካች ክስ በሰጠው መልስም ንብረትነቷ የአቶ በርሕ ሐጎስ አድሃና የሆነች ኮድ 3-29644 አ.አ አይሱዚ መኪና ባለንብረቱ በገንዘብ ተከሶ በፍድራል ሰበር ሰሚ ችሎት እንደሚገኝ፣ የመኪናዋ ባለቤት አቶ በርሕ ሓጎስ አድሃና መስከረም 28 ቀን 2002 ዓ.ም ጣልቃ ገብተው ወጋገን ባንክ በቁጥር 126/ተሰአ/2002 በ3/2/02 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በማይጨው ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሲከራከር ቆይቶ በፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ5/02/2002 ዓ.ም በመ/ ተጠቃሹ መኪና በተጠሪ እጅ ላቆይ እንደሚገባ መወሰኑን ገልጾ በመከራከሩ ፍርድ ቤቱ በፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የተያዘው ጉዳይ እልባት እስከሚያገኝ ድረስ መዝገቡን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 197/2/ መሰረት አቆይቶ ሰበር ሰሚ ችሎቱ ግንቦት 05 ቀን 2003 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ውሳኔ መስጠቱን የስር ፍ/ቤት ከተገለፀለት በኋላ የተዘጋውን መዝገብ ሲያንቀሳቅስ የአሁኑ ተጠሪ መልሱን ለማሻሻል ጥያቄ አቅርቦ ፍርድ ቤቱም ፈቅዶለት ተጠሪ አሻሽሎ ባቀረበው መልሱ ላይ የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አከራካሪዋ መኪና በወንጀሉ ጉዳይ ለመንግሥት ውርስ እንድትሆን የወሰነ መሆኑንና ይህ ደግሞ አመልካች በመኪናዋ ላይ መብት የልላቸው መሆኑን የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሶ በመጨረሻ ፍርድ ባለቀ ጉዳይ ላይ ክሱ መቀጠል የለበትም ሲል ተከራክሯል። የአሁኑ አመልካችም ጉዳዩ የተለያየ ስለሆነ የመጨረሻ ፍርድ አግኝቷል ላባል የሚችልበት አግባብ የልለ መሆኑን ጠቅሶ የመያዣ መብቱ ቅድሚያ እንዲጠበቅለት ተከራክሯል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍ/ቤትም ጉዳዩን መርምሮ ለክርክሩ ምክንያት የሆነችው መኪና በጉምሩክ ወንጀል ምክንያት ለመንግሥት ውርስ እንድትሆን በፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመጨረሻ ፍርድ የተሰጠባት መሆኑን በምክንያትነት ይዞ በመኪናዋ ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 244/2/መ/ መሰረት ልላ ክርክር የሚቀርብባት አግባብ የለም ሲል ክሱን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 32/2/፣ 244/2/ለ/መ/ ድንጋጌዎች ጠቅሶ ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ብይን አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለትግራይ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ብይን በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም መኪናዋ ለባንክ ብድር ለመያዣነት የተሰጠች ሆኖ እያለ ከመያዣው በኋላ ለተፈፀመው የወንጀል ድርጊት ለመንግሥት ውርስ እንድትሆን መወሰኑ ለቅድሚያ መብት ጥያቄው ጉዳዩ ቀድሞ በፍርድ ያለቀ ነው ለማለት የማያስችል መሆኑን ዘርዝሮ የበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ አንድ ጉዳይ ቀድሞ ፍርድ ያረፈበት ነው ለማለት መሟላት የሚገባቸውን መመዘኛዎችንና የመያዣ መብትን በተመለከተ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ይዘት ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት መከራከሩን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች በብድር መያዣነት የያዘው ተሽከርካሪ የኮንትሮባንድ ወንጀል የተፈፀመበት በመሆኑ እንዲወረስ ቀደም ሲል በመወሰኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 32/2/፣ 244/2/ለ/መ/ መሰረት አመልካች ልላ ክስ ማቅረብ አይችልም ተብሎ በስር ፍ/ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 3059/2/ እና ከወንጀል ሕጉ አንቀጽ 98/3/መ/ እና አዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀጽ 95/2/ ድንጋጌዎች አንፃር ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ ተደርጓል። ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በሰጠው መልስም አመልካች የመያዣ መብት ላጠቀም የሚችለው በፍትሐብሕር ጉዳዮች እንጂ በወንጀል ጉዳዮች ያለመሆኑንና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 418 መሰረት በማይጨው ከፍተኛ ፍ/ቤት በተከፈተው መዝገብም ጥያቄ አቅርቦ ተቀባይነት ሲያጣ ቆይቶ የመጨረሻ ፍርድ ሲሰጥ የቅድሚያ መብትን መሰረት አድርጎ ክስ መመስረቱ ሕጋዊ አካሄድ ያለመሆኑን ዘርዝሮ በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም ሲል ተከራክሯል። አመልካች በበኩሉ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሒደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ አመልካች ለአቶ በርሕ ሓጎስ መስከረም 02 ቀን 1997 ዓ.ም በተደረገና በተወሰነ ጊዜ በሚከፈል የብድር ውል ብር 90,000.00 /ዘጠና ሺህ ብር/ ሲሰጥ ንብረትነቱ የተበዳሪው የሆነውንና አሁን ክርክር ያስነሳውን ቁጥሩ 3-29644 የሆነውን አይሱዙ ተሽከርካሪ በአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን በመያዣነት ማስመዝገቡን፣ ይህ ሆኖ እያለ ግን መኪናው የኮንትሮባንድ እቃ በ24/06/2001 ዓ.ም ጭኖ በመገኘቱ የንብረቱ ባለቤት የሆነው አቶ በርሕ ሓጎስ በተጠሪ መስሪያ ቤት ዓቃቤ ህግ በትግራይ ክልል ደቡብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የወንጀል ክስ ቀርቦባቸው ክርክሩ እስከ ፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ድረስ ከተካሄደ በኋላ ሰበር ሰሚ ችሎቱ በመ/ በሆነው መዝገብ ግንቦት 05 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችሎት አቶ በርሕ ሓጎስ ላይ የተጣለውን የሶስት አመት ቀላል እስራትና የብር 5,000.00 የገንዘብ መቀጮ በማጽናት መኪናውን በተመለከተ ደግሞ ለመንግሥት ውርስ እንድትሆን የታች ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በማሻሻል የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠ መሆኑን፣ አመልካች በፍድራል ሰበር ሰሚ ችሎት የወንጀሉ ክርክር ሲካሄድም አመልካች በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ይፈቀድለት ዘንድ ጥቅምት 16 ቀን 2002 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ ጠይቆ የነበረ መሆኑን ሰ/መ/ ከተያያዘው አቤቱታ የተረጋገጠ መሆኑንና አመልካች በስር ፍ/ቤት በመ/ ያቀረበውና ለአሁኑ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ክስ የፍትሐብሕር ክርክርን መሰረት ያደረገ መሆኑን ነው።
እንግዲህ ከዚህ የክርክር ሒደት በቀላሉ መገንዘብ የሚቻለው አከራከሪዋ መኪና ለብድር መያዣነት አመልካች የያዛት የወንጀል ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት መሆኑንና ተጠሪም የአመልካች ክርክርና የዳኝነት ጥያቄ ሥነ ሥርታዊ አይደለም የሚለውን ጥብቅ ክርክር ከማቅረቡ ውጪ በመኪናዋ ላይ አመልካች በሕጉ አግባብ ያቋቋመው የመያዣ ውል የለም በማለት የማይከራከር መሆኑን ነው። በመሆኑም ምላሽ የሚያስፈልገው የሕግ ጥያቄ በመያዣ የተያዘ ተሽከርካሪ ከመያዣው በኋላ በኮንትሮባንድ ወንጀል ምክንያት ለመንግሥት ውርስ እንዲሆን በፍ/ቤት የመጨረሻ ፍርድ ከአረፈበት ባለመያዣው በተሽከርካሪው ላይ ያለው መብት በምን አግባብ ላከበር ይገባል? የሚለው ነው።
በመሰረቱ በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ በሕግ አግባብ የተቋቋመ የመያዣ መብት በሕግ ጥበቃ የሚደረግለት ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር የፍ/ሕ/ቁጥር 2828፣2857/1/ እና 3059 ስር ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዘት የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። በሕግ አግባብ የተቋቋመው የመያዣ ውል መኖሩ ከተረጋገጠ ደግሞ ይኼው መብት ያለው ሰው ከልላው ሰው የቀደመ መብት ያለው መሆኑን የተጠቃሾቹ ድንጋጌዎች ጣምራ ንባብ ያስረዳል። የፎርክሎዝር ሕጎቻችን ሲታዩ ደግሞ ባንክ በመያዣ የያዛቸውን ንብረቶች እዳው ሳይከፈለው በቀረ ጊዜ የ30 ቀን ማስጠንቀቂያ ለተበዳሪው በመስጠት ያለማንም ጣልቃ ገብነት በመያዣ የያዘውን ንብረት በመሸጥ ገንዘቡን ገቢ ማድረግ እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 97/90 አንቀጽ 3 ላይ ተመልክቷል። ከዚህም ልላ መያዣ የተቀበለ ባለገንዘብ ከመያዣው ሽያጭ ዋጋ ከልሎች ባለገንዞቦች ቀድሞ የመቀበል መብት እንዳለውም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2857/1/ ላይ ተደንግጓል።
ከእነዚህ ድንጋጌዎች አንጻር አመልካች ለብድር አከፋፈል በመያዣነት በያዛቸው ንብረቶች ላይ የቀደምትነት መብት እንዳለው መገንዘብ ይቻላል።
በልላ በኩልም የወንጀል ሕጉን በመተላለፍ ለሚፈፀም ድርጊት ወንጀሉ የተፈፀመበት ንብረት ለመንግሥት ውርስ እንዲሆን ቢወሰንና ይኼው ለመንግሥት ውርስ እንዲሆን የተወሰነበት ንብረት በመያዣ የተያዘ መሆኑ ቢረጋገጥ የመያዣ መብት ያለው ሰው መብት በምን አግባብ ላከበር እንደሚችል የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 98 ድንጋጌ በግልጽ የሚያስቀምጠው ድንጋጌ የለም። የኮንትሮባንድ ወንጀሎችን በተመለከተ በልዩ ሁኔታ የሚገዛው አዋጅ ቁጥር 622/2001 ወይም ይህ አዋጅ ሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ተፈፃሚነት ያላቸው ሕጐችም ቢሆኑ በዚህ ረገድ ግልጽ ድንጋጌ ይዘው አናገኛቸውም። በሕጉ ማዕቀፍ ያለው ሁኔታ በዚህ መልክ ግልጽ ያልሆነ ከሆነ ደግሞ በልሎች የሕግ ማዕቀፎች ስር ያለውን አግባብ በመመልከት ጉዳዩን እልባት መስጠት ተገቢ ስለመሆኑ ተቀባይነት ካላቸው የህግ አተረጓጎም ደንቦች የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።
የአሰሪና ሰራተኛን ጉዳዩ በሚመለከት በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት በቅጥር ላይ ከተመሰረተ የሥራ ግንኙነት የሚመነጭ የሰራተኛ የክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ወይም የእዳ ክፍያ ጥያቄ ቅድሚያ እንደሚኖረው በአንቀጽ 167 ላይ ተመልክቷል። የዚህ የሕግ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የሚያሳየው በቅጥር ላይ ከተመሰረተ የሥራ ግንኙነት የሚመነጭ ማንኛውንም የሰራተኛ የክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ወይም የእዳ ጥያቄ ቅድሚያ እንደሚሰጠው የተደነገገ እንደመሆኑ መጠን የልሎች ገንዘብ ጠያቂዎች አቋም ተራ ገንዘብ ጠያቂዎች /ordinary creditors/ ወይንም እንደ አመልካች በመያዣ ብድር የሰጠ ባለገንዘብ /secured creditors/ ሆኑም አልሆኑ የሰራተኛው የክፍያ ጥያቄ ከማናቸውም የክፍያ ጥያቄ ቅድሚያ እንደሚሰጠው ስለተደነገገ ከባንክ ጭምር ቅድሚያ መብት ያላቸው ሰራተኞች መሆናቸውን የሚያሳይ ሲሆን በዚህ የሕግ ማዕቀፍ የሕግ አውጪው ለማሣካት ያሰበው የሰራተኞች ክፍያ ጥያቄዎች ከሰራተኛው የዕለት መተዳደሪያ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ሰራተኛው ለሕይወቱ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንዲያገኝ ማድረግ ስለመሆኑ ይታመናል። ልላው የሕግ ማዕቀፍ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 ሲሆን በዚህ አዋጅ አንቀጽ 80 ስር እንደተመለከተው ዋስትና የተሰጣቸው የልሎች አበዳሪዎች የቅድሚያ መብት እንደተጠበቀ ሆኖ የግብር ሰብሳቢው መብት ግብር የመክፈል ግድታ ባለበት ሰው ሐብት ላይ ከማናቸውም ልሎች እዳዎች የቀደምትነት መብት ይኖረዋል በማለት ተደንግጎ እናገኛለን።
ይህም የሚያሳየው ከግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት ሁሉ የመያዣ መብት ያላቸው ሰዎች ቅድሚያ መብት እንዳላቸው የሚያስገነዝብ ነው። በልሎች የሕግ ማዕቀፎች ያለው አጠቃላይ ሁኔታ ከላይ የተገለፀው ሲሆን በወንጀል ሕጉ ላይ ለመንግሥት እንዲወረስ ውሳኔ በሚሰጥበት ንብረት ላይ የመያዣ መብት ስላላቸው ሰዎች መብት ግን በግልጽ የተመለከተ ድንጋጌ የለም።
ይሁን እንጂ ከላይ እንደተገለፀው የወንጀል ሕጉን አይነተኛ ዓላማ ከመያዣ ሕጎች መሰረታዊ ዓላማ እና አዋጅ ቁጥር 622/01 አንቀጽ 91/2/ ድንጋጌ ጋር በማገናዘብ ለጉዳዩ እልባት መስጠት ተገቢ ይሆናል። የመያዣ ውል መሰረታዊ ዓላማ የንግድ እንቅስቃሴ ዋስትና እንዲኖረው ማስቻል መሆኑ የሚታመን ሲሆን የወንጀል ሕጉ ደግሞ ለጠቅላላው ሕዝብ ሰላምና ደህንነት መሆኑ የሚታመን ነው። ባንኮች የሕዝብ መብትና ጥቅም ያላቸው ተቋማት መሆናቸው ክርክር የሚቀርብበት ጉዳይ አለመሆኑ የሚታመን ነው። የገቢዎችና የጉምሩክ ባለሥልጣን በሕግ ተለይቶ የተሰጠው ስልጣን ጠቅለል ተደርጎ ሲታይ የአገሪቱ የገቢ ማሰባሰብ ስርዓት ሕጋዊ እንዲሆን ማስቻል መሆኑ አዋጅ ቁጥር 578/200 እና ልሎች አግባብነት ያላቸው የግብር እና ታክስ ህጐች ይዘትና መንፈስ የሚያስገነዘበን ጉዳይ ነው። ስለሆነም በአዋጅ ቁጥር 286/1994 አንቀጽ 80 ድንጋጌ ስር መያዣ ያላቸው ሰዎች ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት ቅድሚያ መብት ያላቸው መሆኑ በግልጽ ከተደነገገ ግብር አስገቢ መስሪያ ቤት ሕጉን ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቃሴ አጥፊዎችን በፍ/ቤት ሲያስቀጣና አጥፊዎች ወንጀሉን የፈፀሙባቸውን ንብረቶች በሕጉ አግባብ ለመንግሥት እንዲወረሱ በሕጉ አግባብ ከተወሰነ በዚህ ንብረት ላይ መብት ያላቸው ሰዎች መብት ንብረቱ በወንጀል ምክንያት ለመንግሥት ገቢ እንዲሆኑ መወሰኑ ብቻ መያዣ ያላቸው ሰዎች መብት ዋጋ የሚያጣበት የህግ አግባብ የልለ መሆኑ የሕግ አውጪው ሐሳብ መሆኑን የተለያዩ የሕግ ማዕቀፎች አንድ ላይ ሲታዩ የሚያስረዱን ጉዳይ ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም አመልካች በአከራካሪው ንብረት ላይ ከወንጀል ድርጊቱ በፊት ሕጋዊ የሆነ የመያዣ መብት ያቋቋመ ስለመሆኑ ክርክር ያልቀረበበት ጉዳይ በመሆኑና ይኼው መብት ከመያዣው በኋላ ተበዳሪው በፈፀመው የወንጀል ድርጊት ውጤት አልባ የሚሆንበት ሕጋዊ አግባብ ላኖር ስለማይገባ የአመልካች መብት ከተጠሪ ክስና ሕጋዊ ውጤት ቅድሚያ ጥበቃ ላሰጠው ይገባል። የስር ፍ/ቤቶች ጉዳዩን ከዚህ አቅጣጫ በማየት እልባት መስጠት ሲገባቸው ለጉዳዩ አግባብነት የልላቸውን ድንጋጌዎች በመጥቀስ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ሆኖ አልተገኘም። ልላው እልባት ላሰጠው የሚገባው ጉዳይ የተጠሪ መብት በምን አግባብ ላከበር ይገባል የሚል ነው። የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት ግለሰብ በተሽከርካሪው የኮንትሮባንድ ወንጀል መፈፀማቸው ከተረጋገጠ የውርስ ትዕዛዝ ላሰጥ የሚገባው በተሽከርካሪው ላይ ስለመሆኑ ሕጉ ያሳያል። በመሆኑም የመያዣ መብት ያለው ወገን መብቱን ቀድሞ እንዲያስከበር ከተደረገ ከመያዣ ባለመብቱ የሚተርፈው የንብረቱ ግምት ወይም በወንጀሉ ምክንያት እንዲወረስ የተባለው ንብረት በመያዣው ውል መነሻ ሙሉ በሙሉ በመያዣ ሰጪው የሚያወድ ከሆነ ተራፊው የመያዣ ንብረቱ ግምት ለመንግሥት የማይመለስበት ወይም ተራፊ ከልለ ደግሞ ውርስ እንዲሆን በወንጀል ጉዳይ ተወስኖበት የነበረው የንብረቱ ግምት ይህል ድረስ በአጥፊው ልላ ንብረት ላይ መንግሥት አፈጻጽሙን እንዲቀጥል የማይደረግበት አግባብ ላኖር አይገባም። ምክንያቱም አጥፊው በወንጀል ተግባሩ አትራፊ ላሆን አይገባውምና። በመሆኑም አመልካች የሚፈልገውን የብድር እዳ የአከራካሪው መኪና ዋጋ ሸፍኖ የሚተርፍ ገንዘብ ካለ ተራፊውን ገንዘብ ለመንግሥት እንዲወረስ ማድረጉ ወይም የሚተርፍ ነገር ከልለው ንብረቱ ይወረስ ተብሎ በተወሰነበት ጊዜ በነበረው ግምት ያህል በልላ የወንጀል ድርጊቱ አጥፊ የግል ንብረት ላይ አፈፃፀሙን እንዲቀጥል ማድረጉ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል።
ሲጠቃለልም የመያዣ መብት የተቋቋመበት ተሽከርካሪ በኮንትሮባንድ ተግባር ለመንግሥት ውርስ እንዲሆን ውሳኔ ከተሰጠ መያዣ ሰጪው ቅድሚያ መብት ያለው በመሆኑና ይሄው መብቱ ላከበርለት የሚገባ መሆኑን መገንዘብ ስለሚቻል አመልካች በአከራካሪው ንብረት ላይ የቅድሚያ መብት ስላለኝ በዚህ ንብረት ላይ የወንጀል ውርስ አፈፃፀሙ ላቀጥል አይገባም በማለት ያቀረበውን አቤቱታ የስር ፍ/ቤቶች ሳይቀበሉት መቅረታቸው በአግባቡ ስላልሆነ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
የበታች ፍ/ቤቶች በጉዳዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአቶ በርሕ ሓጎስ አድሃና የሆነች የኮድ ቁጥር 3-29644 አ.አ አይሱዚ የጭነት መኪና የኮንትሮባንድ ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት በአመልካች በሕግ አግባብ የመያዣ መብት የተቋቋመባት መሆኑ ስለተረጋገጠ ለብድር ገንዘቡ መመለሻ ቅድሚያ ልትውል ይገባል ብለናል። በተበዳሪው ላይ አመልካች የሚፈልገው የብድር መጠን ከመኪናው ዋጋ በታች ከሆነ ተራፊው ገንዘብ ለመንግሥት ውርስ እንዲሆን፣ መኪናው ላይ የሚመለስ ወይም ተራፊ ገንዘብ ከልለ ደግሞ መንግሥት መኪናው ይወረስ ተብሎ በወንጀል ጉዳይ ውሳኔ በተሰጠበት ጊዜ የነበረውን ዋጋ ያህል ከአቶ በርሕ ሓጎስ አድሃና የግል ንብረት ላይ አፈፃፀሙን ቀጥሎ ተጠሪ ለመንግሥት ገንዘቡን ገቢ ማስደረግ ይችላል በማለት ወስነናል።
የክርክሩን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
No topics extracted.