No summary available.
ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ ተስፋዬ ምንዳገኝ ቀረበ ተጠሪ፡-
ጉዳዩ ከጡረታ መብት ጋር የተያያዘ የእድሜ አቆጣጠርንና ውጤቱን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ በአመልካች ኤጀንሲ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች እያንዳንዳቸው ለየብቻቸው ባቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ነው። የአሁኑ 1ኛ አመልካች ኤጀንሲው ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ መስከረም 29 ቀን 2004 ዓ.ም. በቁጥር ጡ/ይ/1/1/870/2004 የሰጠውን ውሳኔ የተቃወሙ ሲሆን የይግባኝ ቅሬታው ይዘትም ከኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክሲዮን ማህበር የሰው ኃይል አስተዳደር መምሪያ ሰኔ 22 ቀን 2003 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ የጡረታ መውጪያ ጊዜን ለማሳወቅ ተብሎ በተፃፈልኝ ደብዳቤ የልደት ዘመንህ እ.ኤ.አ 1944 ተብሎ የተላከና እድሜዬ ለጡረታ የሚደርሰው እ.ኤ.አ ጃኑዋሪ 1/2004 እንደሆነና ያለኝን የአመት እረፍት ከሰኔ 27 ቀን 2003 ዓ.ም. በፊት እንድወስድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኛል፣ ይሁን እንጂ እኔ በዚህ ድርጅት የተቀጠርኩት እ.ኤ.አ በ05/04/71 በመሆኑ ስቀጠር እድሜዬ 17 እንደነበርና የልደት ዘመኔም ሐምል 19 ቀን 1946 ዓ.ም. በመሆኑ በተሰጠኝ ደብዳቤ እንደተመለከተው ከሰባት አመት በፊት ወደ ኋላ ጡረታ መውጣት እንደአለብኝ የሚገልጽ በመሆኑ የጡረታ አበሉና የአገልግሎት ዘመን የሚቀንስ ነው፣ በተቀጠርኩበት ጊዜ የቅጥር ፎርሙ የተሞላው በእንግላዝኛ ቋንቋ ሁኖ በወቅቱ የነበሩት አሰሪዎች የውጪ አገር ዜጎች በመሆናቸው የዘመን አቆጣጠሩ በምን እንደሞሉት የማላውቅ ነበር፣ ጡረታም የምወጣው ወደፊት ሐምል 20 ቀን 2006 ዓ.ም. በመሆኑ የልደት ዘመኑ 1946 ዓ.ም መሆኑ ታውቆልኝ የጡረታ መውጪያ ጊዜ ይስተካከልኝ የሚል ነው። የአሁኑ ሁለተኛ ተጠሪ ለኤጀንሲው ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ይዘት ደግሞ በኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አ.ማ እ.ኤ.አ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም. የተቀጠርኩ ሲሆን በወቅቱ እድሜዬ 20 ዓመት፣ የተወለድኩት ሰኔ 12 ቀን 1944 ዓ.ም. ሁኖ እያለ ከአሰሪ ድርጅቱ የተሰጠኝ ደብዳቤ ከሰባት አመት በላይ ወደ ኋላ ጡረታ መውጣት እንዳለብኝ የሚገለጽ በመሆኑ በጡረታ አበልና በአገልግሎት ዘመኑ ላይ ቅነሳ የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ የትውልድ ዘመኔ እ.ኤ.አ 1944 ሳይሆን እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሰኔ 12 ቀን 1944 ስለሆነ ለጡረታ መውጫ እድሜ ላይ ያልደረስኩ በመሆኑ በተቀጠርኩበት ጊዜ የቅጥር ፎርሙ የተሞላው በእንግላዝኛ ቋንቋና በነበሩት የውጪ አገር አሰሪዎች ሁኖ የዘመኑ አቆጣጠሩ በምን እንደተሞላ የማላውቅ በመሆኑ ታውቆ ትክክለኛው የልደት ዘመኔ ሰኔ 12 ቀን 1944 ዓ.ም. ላያዝልኝ ይገባል የሚል ነው።
የአሁኑ ሶሰተኛ ተጠሪ ያቀረቡት የይግባኝ አቤቱታ ይዘቱ ሲታይም የጡረታ መውጪያ ጊዜ አያያዝ ላይ እንደ አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች ችግሩ የተከሰተበት መንገድ ተመሳሳይ መሆኑን ገልጸው ትክክለኛው የትውልድ ዘመናቸው ነሐሴ 25 ቀን 1943 ዓ.ም. ሁኖ እንዲያዝላቸው ይወሰን ዘንድ ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለተጠሪዎች ይግባኝ በተናጠል በሰጠው መልስም የልደት ዘመን የሚያዘው ሰራተኛው ለስራው ሲቀጠር በሞላው ፎርም ላይ የተመዘገበ የልደት ዘመን መሆኑን ገልጾ የአሁኑ 1ኛ ተጠሪ በጡረታ መለያ ቁጥር ድ/543275 መመዝገባቸውንና የተጠሪ የልደት ዘመን በፎረንሲክ የምርመራ ውጤት መሰረት እ.ኤ.አ 1944 ተወለድኩ ብለው የሞሉና ይህንን የሚቀይር የተሞላ የልደት ዘመን የልለ በመሆኑ ይኼው የልደት ዘመን እንዲያዝላቸው መደረጉን፣ የአሁኑ ሁለተኛ ተጠሪም በጡረታ መለያ ቁጥር ድ/529780 የተመዘገቡና እ.ኤ.አ በ14/1/1972 በሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ላይ እ.አ.አ 1944 የተወለዱ መሆኑን ገልፀው የሞሉ መሆኑን እና ሶስተኛ ተጠሪ በጡረታ መለያ ቁጥር ድ/407412 የተመዘገቡና በእ.ኤ.አ በ4/07/1973 የሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ላይ እ.ኤ.አ 1941 ተወለድኩ ብለው የሞሉና ይህን የሚቀየር የተሞላ የልደት ዘመን የልለ በመሆኑ ይኼው የትውልድ ዘመን እንዲያዝላቸው የተደረገ መሆኑን ዘርዝሮ በሕጉ አግባብ የተከናወነ ተግባር ስለሆነ የኤጀንሲው ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል። ይግባኙ የቀረበለት የኤጀንሲው ጉባኤም ጉዳዩን መርምሮ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የአፈፃጸም መመሪያ ለጡረታ ተግባር የሚያዘው እድሜ በቅድሚያ በተሞላ የስራ መጠየቂያ ወይም የሕይወት ታሪክ መግለጫ ቅጽ ወይም የተያዥ መስጫ ወይም የምዝገባ ቅፅ ላይ የተመዘገበ የልደት ዘመን መሆኑን፣ 1ኛ ተጠሪ በኢትዮጵያ ፐልፕና ወረቀት አክሲዮን ማህበር እ.ኤ.አ. በ05/04/1971 ለስራ ሲቀጠሩ በሞሉት የሕይወት ታሪክ ፎርም ላይ የተመዘገበው የልደት ዘመን ስርዝ ድልዝ ያለው በመሆኑ በኢትዮጵያ ፍድራል ፖላስ የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶሬት በ26/8/2002 በቁጥ ፍሮ/1- 1/31/7452/2002 በተጻፈ ደብዳቤ አባሪ ሆኖ በተላከው የሰነድ የምርመራ ውጤት መግለጫ ላይ በአቶ አበራ ቦከን ስም በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በእንግላዝኛ የልደት ዘመን በሚለው ፊት 1954 በሚል የተጻፉ ቁጥሮች ቀደም ሲል 1944 በሚል ከተጻፈ በኋላ ተደልዘውና ተለውጠው አሁን እንደሚታየው 1954 የተደረገ መሆኑ መረጋገጡን፣ 2ኛ ተጠሪም እ.ኤ.አ.
በ14/1/1972 ለስራ ሲቀጠሩ በሞሉት ፎርም ላይ የልደት ዘመን ስርዝ ድልዝ በመሆኑ በፎረንሲክ ምርምራ ተብሎ በእንግላዝኛ የትውልድ ዘመን በሚለው ቃል ፊት ያለው 1952 በሚል የተፃፉ ቁጥሮች ቀደም ሲል 1944 ከተፃፈ በኋላ ተደልዘውና ተለውጠው አሁን እንደሚታየው 1952 የተደረገ መሆኑን የፍድራል ፖላስ የፎረንሲክ ምርመራ ዳይሬክቶሬት በ26/08/2002 ዓ.ም. በቁጥር ፍሮ/1-1/31/7452/2002 በተፃፈ ደብዳቤ ያረጋገጠ መሆኑን፣ ሶስተኛ ተጠሪን በተመለከተም በእ.ኤ.አ በ4/7/1973 ሲቀጠሩ በሞሉት የህይወት ታሪክ ፎርም ላይ የልደት ዘመን ስርዝ ድልዝ ያለው በመሆኑ በፍድራል ፖላስ የፎረንሲክ ምርምራ በእንግላዝኛ የልደት ዘመን በሚል ከተቀመጠው ቃል ፊት ለፊት 1951 በሚል የተፃፉ ቁጥሮች ቀደም ሲል 1941 በሚል ከተፃፈ በኋላ ተደልዘውና ተለውጠው አሁን እንደሚታየው 1951 የተደረገ መሆኑን በ26/08/2002 ዓ.ም. በቁጥር ፍሮ/1-1/31/7452/2002 በተፃፈ ደብዳቤ መግለፁን በመጥቀስና 1ኛ ተጠሪ ሐምል 12 ቀን በሞሉት የመንግስት የሆኑ ድርጅቶች ሰራተኞች የግል አገልግሎትና የቤተሰብ ሁኔታ መግለጫ ቅጽም ላይ የትውልድ ዘመናቸውን 1946 ዓ.ም. በሚል የመዘገቡት፣ ሁለተኛ ተጠሪም እ.ኤ.አ 1952 በሚል የመዘገቡት፣ ሶስተኛ ተጠሪ ደግሞ 1943 በሚል የመዘገቡት ቅድሚያ እንደልለው ገልፆ የአመልካችን የትውልድ ዘመን አያያዝን በተመለከተ ኤጀንሲው የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽንቶታል። ከዚህም በኋላ የአሁኑ ተጠሪዎች በተናጠል የይግባኝ አቤቱታቸውን ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የአመልካቾች እድሜ ስርዝ ድልዝ ያለው መሆኑ ቢረጋገጠም ማን እና እንድት ላሰረዝ እንደቻለ ሳይረጋገጥ ውሳኔ መስጠት ተገቢ ያለመሆኑና የሕግ ግምቱንም ያልተከተለ መሆኑን ጠቅሶ በጉዳዩ ላይ በይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮ የልደት ዘመኑ በማን እና እንድት እንደተሰረዘ አጣርቶ እንዲወስን በማለት ጉዳዩን መልሶለታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። በእያንዳንዱ መዝገብ ላይ የቀረበው የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በሕግ ተለይቶ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ማረም ሆኖ እያለ ፍሬ ነገሩን ማጣራቱና ማስረጃን መመዘኑ ከስልጣኑ ውጪ መሆኑን እንዲሁም ተጠሪዎች የተወለዱበት ዘመን መጀመሪያ ሲቀጠሩ በትክክል የተሞላና በኋላ ደግሞ የተሰረዘና የተለወጠ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ በኋላ የተሞላውን የትውልድ ዘመን እንድት እንደተሞላና የቀድሞውን ማን እንደሰረዘው እንዲጣራ ማድረግ ለጉዳዩ አወሳሰን አስፈላጊ ያልሆነ ነጥብ መሆኑን ዘርዝሮ ውሳኔው አዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 4(1)፣ 54(1)፣ 56(4) ድንጋጌዎችን ይዘት ያላገናዘበ መሆኑን ዘርዝሮ ውሳኔው ላታረም ይገባል በማለት ዳኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በአዋጅ ቁጥር 714/2003 በአንቀጽ 4(1) መሰረት ለመንግስት ሰራተኛ ለጡረታ የሚያዝ የልደት ዘመን የመንግስት ሰራተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀጠር ያስመዘገበው የልደት ዘመን መሆኑ በግልጽ ተደንግጎ እያለ፣ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ የፍትሐብሕር ችሎት በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 56(4) መሰረት ፍርድ ቤቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተቶችን ብቻ በይግባኝ እንዲያይ ተደንግጎ እያለ በፍሬ ነገር ላይ ጉባኤው ልሎች ማስረጃዎችን እንደገና መርምሮ ውሳኔ እንዲሰጥ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዳዩ ለሰበር ችሎቱ እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎችም ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሑፍ እንዲከራከሩ ተደርጓል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩ ለሰበር ሰሚ ችሎት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎች ሲቀጠሩ በሞሉት የሕይወት ታሪክ ፎርም ላይ ያለው የትውልድ ዘመን ተሰርዞና ተደልዞ የተለወጠና ቅድሚያ የሞሉት የትውልድ ዘመን ስንት እንደነበር በፎረንሲክ ምርምራ መረጋገጡን፣ ተጠሪዎች የትውልድ ዘመኑ ላይ እ.ኤ.አ አቆጣጠር የተሞላ ስለነበር የተከሰተ ችግር እንጂ ቀድሞ ሲሞሉት የነበረውን በመለወጥ የተከሰተ ችግር ያለመሆኑና በቅጥር ጊዜ በነበረው የቋንቋ ችግር መከሰቱን ገልጸው የአመልካች ኤጀንሲ ውሳኔ በጡረታ አበል መጠኑና በአገልግሎት ዘመናቸው ላይ ችግር የሚያስከትልባቸው መሆኑን ጠቅሰው የሚከራከሩ መሆኑን፣ አመልካች በአንፃሩ የተጠሪዎች የትውልድ ዘመን በተገቢው መንገድ ተረጋግጦ እያለ እንድት እንደተሰረዘና ማን እንደሰረዘው ይረጋገጥ ተብሎ በፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት መወሰኑ ያላግባብ መሆኑንና የራሱ እርምጃ በአዋጅ ቁጥር 714/2003 መሰረት የተከናወነ መሆኑን ገልጾ የሚከራከር መሆኑን ነው።
በመሰረቱ ለመንግስት ሰራተኛ ለጡረታ የሚያዝ የልደት ዘመን የመንግስት ሰራተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀጠር በቅድሚያ የመዘገበው የልደት ዘመን መሆኑን አዋጅ ቁጥር 714/2003 በአንቀጽ 4(1) ስር በግልጽ ደንግጓል። ይህ ድንጋጌ የሚያሳየው አመልካች መስሪያ ቤት ለመንግስት ሰራተኞች የጡረታ አበል ውሳኔ የሚሰጠው በአዋጁ መሰረት ሰራተኛው በመጀመሪያ ጊዜ በመንግሰት መስሪያ ቤት ሲቀጠር የሞላውን የልደት ዘመን መሰረት በማድረግ ስለመሆኑ ነው። በተጠቃሹ አዋጅ አዋጁን ለማስፈፀም በተመለከተ መመሪያ የማውጣት ስልጣን ለአመልካች ኤጀንሲ መሰጠቱን በአንቀፅ 60(2) ስር ሰፈሯል። አመልካች በዚህ አግባብም የልደት ዘመንን አያያዝና ልሎች አፈፃፀሞችን በተመለከተ መመሪያ ስራ ላይ ማዋሉም በክርክሩ ሂደት ክርክር ያልቀረበበት ጉዳይ ነው። ኤጀንሲው በአዋጁ ለሚሰጡ ለማናቸውም አበል ብቁ የሚያደርጉ ሁኔታዎች መሟላታቸውን የማረጋገጥና የአበሉን መጠንና አይነት የመወሰን ስልጣን ያለው መሆኑ በአዋጅ አንቀፅ 54(1) ስር በግልጽ የሰፈረ ሲሆን በዚህ ረገድ ውሳኔ ሲሰጥም የራሱን የመረጃ ማህደር፣ በአዋጁ አንቀጽ 53 መሰረት የሚተላለፉን መረጃዎችንና እንደ አግባብነቱ ባለመብቱ የሚያቀርባቸውን ተጨማሪ ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ መሆኑን አንቀጽ 54(2) ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። በኤጀንሲው ማህደርና በሚቀርበው ልላ ማስረጃ ልዩነት ቢፈጠር ደግሞ ተቀባይነት ያለውን ማስረጃ የሚወስነው ኤጀንሲው ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 54(3) ድንጋጌ በግልፅ አስቀምጧል። አዋጁ የኤጀንሲው ውሳኔ በኤጀንሲው ዳግም የሚታይበትን ስርዓት የዘረጋ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታዎችንም በአንቀጽ 55 ስር አስፍሯል። እንዲሁም ኤጀንሲው በሚሰጠው ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ወገን ሁሉ ይግባኙን የሚያቀርበው ለኤጀንሲው ጉባኤ ስለመሆኑ የአዋጁ አንቀጽ 56(1) ይገልፃል።፡ የኤጀንሲው ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ስለመሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 56(4) ስር በግልጽ የተደነገገ ሲሆን የይግባኝ ሰሚው ጉባኤ ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት የሚል ወገን ይግባኙን ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚችልም ይኼው ድንጋጌ ያሳያል። ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኙ የሚቀርበው በፍሬ ነገር ክርክር ወይም በማስረጃ ምዘና ሳይሆን በመሰረታዊ የህግ ስህተት ላይ ብቻ ስለመሆኑ የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ ያሳያል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም አመልካች መስሪያ ቤት የተጠሪዎችን የልደት ዘመን የያዘው ማህደሩን በመመልከትና በማህደሩ የተከሰቱን ችግሮች በማጣራት ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ተረጋግጧል። የፎረንሲክ ምርመራ ውጤትም በተጠሪዎች የህይወት ታሪክ ላይ ቀድሞ የተሞላው ትክክለኛ ዘመን የለየው ሲሆን በኋላ ተሞልቶ የተገኘው ግን የቀድሞው ተሰርዞ የተቀመጠ መሆኑን አረጋግጧል። የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ለጉባኤው እንዲመለስ ያደረገው የትውልድ ዘመኑ በተለያዩ ምክንያቶች ላሰረዝ ይችላል፣ ማህደሩ በአሰሪ እጅ ባለበት ሁኔታ የሰረዘው ማን ነው የሚለው ጥያቄም የሕግ ግምት ነው፣ ተጠሪዎች በኋላ ሞላን የሚሉት ወይም ስርዝ ነው የተባለው የትውልድ ዘመን ቀድሞ እ.ኤ.አ ተሞልቶ ስለነበር ይህንኑ ለማስተካከል ተብሎ ላሆን ይችላል የሚሉትን ነጥቦችን በመያዝ ነው። ይሁን እንጂ እነዚህ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ለውሳኔ መሰረት ያደረጋቸው ምክንያቶች በይዘታቸው ሲታዩ የፍሬነገርና የማስረጃ ምዘና ጉዳዩን የሚመለከቱ ሲሆን ያላግባብ የገባውና በትክክል ሰራተኞቹ ሲቀጠሩ የተሞላው የልደት ዘመን በፎረንሲክ ምርምራ እስከተለየ ድረስ በኋላ የገባውን የልደት ዘመን ማን ሰረዘው፣ እንድት ተሰረዘ የሚለውን ማጣራቱ በተጠሪዎች የጡረታ መብት ውሳኔ ላይ የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት አይኖርም። ምክንያቱም ኤጀንሲው የሰራተኛውን ማህደር በመመርመርና የመብቱ ተጠቃሚ የሚያቀርበውን ማስረጃ መመርምሮ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ የትኛው እንደሆነ ለይቶ መወሰን እንደሚችል በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 54(3) በግልጽ ተደንግጓል። በመሆኑም በፎረንሲክ ምርመራ መሰረት ተጠሪዎች ላያዝልን ይገባል በማለት የሚጠቅሱት የልደት ዘመን በቅጥር ጊዜ የተሞላ ያለመሆኑ ተረጋግጦ እያለና ኤጀንሲውም የተጠሪዎችን አለን የሚሉትን ማስረጃ በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ሳይቀበለው መቅረቱ በተረጋገጠበት ሁኔታ የትውልድ ዘመኑን የሰረዘው ማን ነው?፣ እንድት ተሰረዘ? የሚለው ፍሬ ነገር እንዲጣራ ማድረግ ኤጀንሲው በሕጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ያልተቀበለውን ማሰረጃ እንዲቀበል የማስገደድ ኃይል ያለው ውሳኔ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 56(4) ድንጋጌ መሰረት በሕጉ ተለይቶ የተሰጠው ሥልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ማረም ሁኖ እያለ አመልካች መስሪያ ቤት ፍሬ ነገሩን በማጣራትና ማስረጃን በመመዘን ድምዳሜ ላይ የደረሰበትን የተጠሪዎችን የትውልድ ዘመን እንደገና እንዲጣራ ማድረጉ ያለሥልጣኑ የተሰጠ ውሳኔ ሁኖ አግኝተናል። አንድ ፍርድ ቤት ጉዳዩን መዳኘት ያለበት ደግሞ በሕጉ ተለይቶ በተሰጠው ስልጣን አድማስ ውስጥ መሆኑን የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 9 እና 231 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የሚያሳየን ጉዳይ ነው።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343 ድንጋጌ መሰረት አንድ ጉዳይ ውሳኔውን ለሰጠው አካል እንዲመለስ የሚደረገውም ለውሳኔ አሰጣጥ እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ፍሬ ነገሮች በሕጉ በተመለከተው የማስረጃ አቀራረብና አቀባበል ስርዓት መሰረት ሳይጣሩና የክርክሩ አካሄድ ሳይሟላ ውሳኔ ተሰጥቶ ሲገኝ ስለመሆኑ የድንጋጌው ይዘትና መንፈስ ያሳያል። በዚህ ረገድ የበላይ ፍርድ ቤት መሪ ትዕዛዝ ላሰጥ የሚችለውም በሕጉ ስልጣን ያለው መሆኑ ሲረጋግጥ ነው። የመሰረታዊ ሕግ ስህተት የማረም ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ጉዳዩ በስር ፍርድ ቤት ወይም ዳኝነት መሰል አካል እንዲጣራ ላያደርግ እንደሚችል የመሰረታዊ ሕግ መመዘኛዎች የሚያሳዩን ጉዳይ ሲሆን ይህንን መሪ ትእዛዝ ሲሰጥ ግን ፍሬ ነገሩን ለማጣራትና ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ያለው አካል በፍሬ ነገር ደረጃ በሕጉ አግባብ የደመደመውን ፍሬ ነገር ውድቅ የሚያደርግበት ስልጣን ላኖረው አይችልም። ሲጠቃለልም የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ውሳኔ የአዋጅ ቁጥር 714/2003 አንቀጽ 4(1)፣ 54፣ እና 56(4) ድንጋጌዎችን እንዲሁም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343 ድንጋጌን ይዘትና መንፈስ በአግባቡ ያላገናዘበ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የሰጣቸው ውሳኔዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሸረዋል።
በጉዳዮቹ ላይ የመንግስት ሰራተኞች የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ መስከረም 13 ቀን 2004 ዓ/ም፣ ጥቅምት 25 ቀን 2004 ዓ.ም. የሰጣቸው ውሳኔዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ጸንተዋል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ብለናል።
የዚህ ውሳኔ ግልባጭ ከሰ/መ/ ጋር ይያያዝ ብለናል።
No topics extracted.