No summary available.
ታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሤ ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- የቀይ ሽብር ሰማዕታት ወዳጆችና ቤተሰቦች ማህበር ጠበቃ አቶ ታዬ ወጂ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ኤላያስ አሰጋኸኝ ጠበቃቸው አቶ ያለልኝ ተሾመ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዳይ በአሁኑ የሰበር ተጠሪ ከሳሽነት የተጀመረው በፍ/ከ/ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ አመልካችም 1ኛ ተከሳሽ፣የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ደግሞ 2ኛ ተከሳሽ ነበር። ከሳሽ የካቲት 16 ቀን 2002 ዓ/ም ያቀረበው ክስ 1ኛ ተከሳሽ በቀይ ሽብር ሰለባ የሆኑትን ሰዎች ለማሰብ ሐውልት ለማሰራት የሐውልት ኪነ ቅርጽ አወዳድሮ ለመምረጥ ባወጣው ጨረታ ተወዳዳሪ በመሆን ያዘጋጀሁትን ቅርጽ በ1990 ዓ/ም ያስረከብኩ ቢሆንም ተከሳሹ ቅርጹን ከተረከበ በኋላ ማሸነፍ አለማሸነፍን ሳይገልጽልኝ እያመላለሰኝ ከቆየ በኋላ የራሱ ቅርጽ እንደሆነ በማስመሰል ለመገናኛ ብዙኃን ያሰራጨ በመሆኑ፣ 2ኛ ተከሳሽም የቅርጹን ምስል የያዙትን 60,000 ቴምበሮች በማሳተም አንዱን በብር 3.00 በመሸጥ ብር 180,000 የሰበሰበ ስለሆነ ተከሳሾቹ የከሳሽን የፈጠራ መብት በመጣስ ከቅርጹ ማግኘት የሚገባኝን ብር 100,000 በማሳጣት የብር 280,000 ጉዳት ያደረሱብኝ ስለሆነ የሂላና ጉዳት ብር 150,000 ጨምረው በድምሩ ብር 580,000 እንዲከፍሉ ይወሰንልኝ የሚል ነው። ተከሳሾችም ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው ሲሉ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና በአማራጭ በፍሬ ጉዳዩ ላይ መልስ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያውን በ12/04/2003 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በብይን ውደቅ ማድረጉን ከፍርዱ መገንዘብ የተቻለ ሲሆን በፍሬ ጉዳዩ ላይ 1ኛ ተከሳሽ በሰጠው መልስ፡-1ኛተከሳሽ የተቋቋመው በ1995 ዓ/ም ሲሆን ከሳሽ ቅርጹን ሰጥቻለሁ የሚለው በ1990 ዓ/ም በመሆኑ ከከሳሽ የተቀበልኩት ቅርጽ የለም፣በቴምብር የወጣው ቅርጽና ከሳሽ የኔ ነው የሚለው ቅርጽም ይለያያል፣ከከሳሽ ጋር ከውል ወይም ከውል ወጪ የመነጨ ግንኙነት ስለልለን ክሱ ተቀባይነት የለውም፣ ከክሱ ጋር ያቀረባቸው ማስረጃዎችም አግባብነት ያላቸው አይደሉም በሚል ተከራክሯል።
2ኛ ተከሳሽ በበኩሉ በፍሬ ጉዳዩ ላይ በሰጠው መልስ፡- ወጣ ስለተባለው ጨረታ የማውቀው ነገር የለም፣1ኛ ተከሳሽ ቴምብሮች እንዲታተሙለት በሚል ሶስት ምስሎችን በመላኩና ትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴርም እንዲታተሙ ትዕዛዝ በመስጠቱ ታትመዋል፣በታተሙት ቴምብሮች ላይ ያለው ምስልና የከሳሽ ሥራ የሚለያዩ ናቸው፣የካሳው መጠንም የተጋነነ ነው ሲል ተከራክሯል።
ፍርድ ቤቱም በሰጠው ፍርድ፡- የአዲስ አበባ የደርግ አፈናና ጭፍጨፋ ተፋራጆች ሰብአዊ መብት ማህበር የተባለው በቀይ ሽብር ለሞቱት ሰዎች የመታሰቢያ ሐውልት ለማሰራት የወድድር ማስታወቂያ ማውጣቱን፣ከሳሽም በዚሁ ማስታወቂያ መሰረት የሐውልት ቅርጽ ሰርቶ ለማህበሩ ማስረከቡን ፣በማስታወቂያው ከ1ኛ-3ኛ የወጡት አሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት እንደሚሰጣቸውና ከሽልማቱ በኋላ ማህበሩ የቅርጹ ባለቤት እንደሚሆን መገለጹን ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃዎች በፍሬ ነገር ደረጃ መረጋገጡን ፤እንዲሁም ቅርጹን ከከሳሽ የተረከበው የአዲስ አበባ የደርግ አፈናና ጭፍጨፋ ተፋራጆች ሰብአዊ መብት የተባለው ማህበር ቢሆንም በኋላ ግን ቅርጹ የሰማዕታት ሐውልት ግንባታ ማህበር እጅ መቆየቱንና ከሳሽም ቅርጹን በተመለከተ ሲደራደር የነበረው ከዚሁ ማህበር ጋር መሆኑን በ07/11/2000 ዓ.ም. ከተጻፈ ማስረጃ መረጋገጡን፣ተከሳሾችም የከሳሽ ሥራ አዲስ (0riginal) አለመሆኑን በመግለጽ ያቀረቡት ክርክር አለመኖሩንና የተከሳሾች ምስክሮች የከሳሽ ሥራ ባለ ሶስት አውታር መጠን (dimension) መሆኑንና በቴምብሮቹ የታተመው ባለሁለት አውታር ነው ቢሉም 1ኛ ተከሳሽም የከሳሽን ቅርጽ ጨምሮ ሶስት ዲዛይኖችን ለ2ኛ ተከሳሽ እንዲታተሙ በሚል ስለመላኩ መረጋገጡን በፍርዱ ላይ በማስፈር 1ኛተከሳሽም ቅርጹ የከሳሽ መሆኑን እያወቀ የከሳሽ ሥራ የሆነውን ባለ ሶስት አውታር ወደ ባለ ሁለት አውታር በመቀየር ለ2ኛ ተከሳሽ አሳልፎ በመስጠቱና 2ኛ ተከሳሽም ቅርጹን በቴምብሮቹ ላይ በማተሙ 1ኛ ተከሳሽ ለተፈጸመው የቅጂ መብት ጥሰት ሀላፊነት አለበት። 2ኛ ተከሳሽ ግን በራሱ መርጦ የከሳሽ ሥራ የሆነውን ቅርጽ ያላተመና የቅርጽ ምስሉ ሲላክለትም 1ኛ ተከሳሽ የቅርጹ ባለቤት ስለመሆን ስላለመሆኑና የማጣራት ግድታ ያለበት ባለመሆኑ ለክሱ ሀላፊነት የለበትም በማለት አሰናብቶታል።
የካሳ መጠንን በተመለከተም ከሳሽ ከቅርጹ 100,000 ማግኘት የሚችል ስለመሆኑ በማስረጃ ያላረጋገጠ ከመሆኑም ልላ ቅርጹ ለቀይ ሽብር ሰማዕታት በሚል የተሰራ በመሆኑ ለልላ አካል ተሸጦ ገቢ ያስገኛል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም፣ እንዲሁም በጨረታዉ ላሸነፈው ተወዳዳሪ የሚከፈለው የሽልማት ገንዘብ መጠንም ብር 12,900.00 ብቻ በመሆኑ ብር 100,000.00 ማግኘት እችል ነበር ሲል ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም በማለት በአዋጅ ቁጥር 410/1996 አንቀጽ 34(4) መሰረት የሞራል ጉዳት ካሳ መነሻ ብር 100,000.00 እንዲከፍል ወስኖበታል።
የስር 1ኛ ተከሳሽም በከፍተኛው ፍርድ ቤት ፍርድ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፍ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ያቀረበ ቢሆንም ችሎቱ ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/337 መሰረት በመዝጋት ይግባኝ ባዩን አሰናብቶታል።
የሰበር አቤቱታም የቀረበው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ፍርድ እና በፍ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ትዕዛዝ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን አመልካች በዋናነት ያቀረባቸው የቅሬታ ነጥቦችም፡- ተጠሪው ቅርጹን ለአመልካች አስረክቤአለሁ የሚለው በ1990 ዓ/ም ሆኖ ክሱን ያቀረበው ደግሞ በ16/06/2002 ዓ/ም በመሆኑ ክሱ በፍ/ህ/ቁ/1845 መሰረት በ10 ዓመት ይርጋ የሚታገድ ነው በሚል ያቀረብኩትን የመ/ደ/መቃወሚያ ፍርድ ቤቶቹ ውድቅ ያደረጉት ተገቢነት የለውም፣ በቴምብሮቹ ላይ እንዲታተም የተደረገው ተጠሪው የፈጠራ መብት ባለቤትነት አግኝቼበታለሁ ከሚለው የቅርጽ ሥራ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደልለው በባለሙያ ምስክሮች ተረጋግጦ እያለ የተጠሪ ሥራ ነው በሚል ለደረሰው ጉዳት ሀላፊነት አለብህ በሚል የሞራል ካሳ እንድከፍል የተወሰነው ተቀባይነት የለውም የሚሉ ናቸው።
ተጠሪው በበኩሉ በሰጠው መልስ፡- ክስ ያቀረብኩት የቅጂ መብት ተጥሶብኛል በሚል ከህግ የመነጨውን መብት መሰረት በማድረግ ነው እንጂ ከውል በመነጨ መብት መነሻ ባለመሆኑ አግባብነት ያለው በፍትሐብሕር ህጉ ከውል ወጪ ሀላፊነት በተመለከተው ክፍል የተደነገገው የክስ ማቅረቢያ የ2 ዓመት ይርጋ እንጂ ስለውሎች ጠቅላላ ክፍል የተደነገገው በፍ/ህ/ቁ/1845 ሥር የተመለከተው የይርጋ ጊዜ አይደለም ። ክሱም የቅጂ መብቴ ነሐሴ 20 ቀን 2000 ዓ.ም.
ተጥሶብኛል በሚል የካቲት 16 ቀን 2002 ዓ.ም. የቀረበ በመሆኑ የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ ከማለፉ በፊት የቀረበ ነው። በቴምብር ታትሞ የወጣው ባለ ሁለት አዉታር (dimension ) ሲሆን የተጠሪ ደግሞ ባለሶስት አውታር ሥራ ነው በሚል አመልካች ያቀረበው ክርክርም ቢሆን ማንኛውም በምድር ላይ ያለ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ነገር በወረቀት ላይ ወይም በፎቶ ግራፍ ምስል ሲወጣ ከባለሶስት አውታር ወደ ባለሁለት አውታር መቀየሩ ተፈጥሮአዊ በመሆኑ ክርክሩ ተገቢነት የለውም በሚል በከፍተኛውና በፍ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ ህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም የመልስ መልስ በማቅረብ ክርክሩን አጠናክሯል።
የጉዳዩ አመጣጥ ከዚህ በላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም፡- ተጠሪው ያቀረበው ክስ በይርጋ የሚታገድ ነው? ወይስ አይደለም?
ክሱ በይርጋ አይታገድም ቢባል አመልካች ለክሱ ሀላፊነት አለበት? ወይስ የለበትም?
የሚሉትን ጭብጦች ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
አንደኛውን ጭብጥ በተመለከተ ፡- የአመልካች ክርክር ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ስለውሎች በጠቅላላው ክፍል በፍ/ህ/ቁ/1845 ስር የተደነገገው የ10 ዓመት ይርጋ ሲሆን ተጠሪው ቅርጹን ካቀረበበት ከ1990 ዓ/ም ጀምሮ ሲቆጠርም መብቱን ላጠይቅ የሚችልበት የ10 ዓመት የይርጋ ጊዜ አልፏል በሚል ሲሆን ተጠሪው የሚከራከረው ግን የተጣሰው ከህግ የመነጨ መብት እንጂ ከውል የመነጨ መብት ባለመሆኑ ተፈጻሚነት የሚኖረው በፍ/ህ/ቁ/2143(1) ስር ከውል ወጪ ሀላፊነትን በሚመለከት ካሳ ለመጠየቅ የተደነገገው የሁለት ዓመት ጊዜ ሲሆን ይኸው መብት ከተጣሰ ጊዜ ጀምሮ ሲቆጠርም የሁለት ዓመት የክስ ማቅረቢያ ጊዜው አላለፈም በሚል ነው።
ሆኖም ከግራ ቀኙ ክርክር መገንዘብ የተቻለው ቀደም ሲል የነበረው ማህበር ባወጣው ጨረታ መነሻ ተጠሪውም በጨረታው ተወዳዳሪ በመሆን የፈጠራ ሥራውን ማስታወቂያውን ላወጣው ለቀድሞ ማህበር ስለማስረከቡና ማህበሩም ስለመቀበሉ በፍሬ ነገር ደረጃ መረጋገጡን ነው።
የውል አቀራረብና አቀባበል በፍ/ህ/ቁ/1681(1) በተደነገገው መሰረት ፈቃድን በቃል ወይም በጽሁፍ ወይም በተለመዱ ጠቅላላ ምልክቶች ወይም ለውሉ መነሻ ከሆነው ምክንያት የተነሳ ግድታን ለመግባት መፍቀድን በማያጠራጥር አሰራር በማስታወቅ ጭምር የሚደረግ በመሆኑ በተጠሪውና በቀድሞው ማህበር መካከል ግልጽ በሆነ ሁኔታ የተደረገ የጽሁፍ ውል ባይኖርም ፈቃድን በቃል በመግለጽ የውል ስምምነት ተደርጓል ለማለት የሚቻል ከመሆኑም በላይ ማህበሩ የተጠሪውን ሥራ መቀበሉ በመካከላቸው የውል ግንኙነት መመሰረቱን የሚያሳይ ነው። በመሆኑም ከተጠሪው ጋር የተደረገ የውል ስምምነት የለም በማለት አመልካች ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። ተጠሪውም ቢሆን ከአመልካች ጋር ያለው ግኝኑነት በውል ላይ የተመሰረት ሆኖ እያለ ከህግ በመነጨው መብት ላይ አመልካች ጥሰት የፈጸመ በመሆኑ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ይርጋ ጊዜ ከውል ውጪ ሀላፊነት ላኖር ስለሚችልበት አግባብ በፍትሐብሕር ህግ ክፍል የተደነገገው የካሳ ክስ ለማቅረብ የተቀመጠው የሁለት ዓመት የይርጋ ጊዜ ነው በማለት ያቀረበው ክርክርም ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ምክንቶያች የተነሳ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በአመልካችና በተጠሪው መካከል የውል ግንኙነት መኖሩ ከተረጋገጠ ደግሞ ጉዳዩን ስለውሎች በጠቅላላው በተደነገገው ክፍል በሚገኘው በፍ/ህ/ቁ/1845 ይርጋ መሰረት መመርመር ተገቢ ይሆናል። በፍ/ህ/ቁ/1845 ድንጋጌ መሰረት ህግ በልላ አኳን ካልወሰነ በቀር ውሉ እንዲፈጸም ወይም ከላመፈጸሙ የተነሳ ስለሚደርስ ጉዳት ወይም ውሉ እንዲፈርስ መብት ያለው ወገን መብቱን በ10 ዓመት ወስጥ ካልጠየቀ መብቱ ቀሪ እንደሚሆን በግልጽ ተጠቅሷል። በዚህ ጉዳይ የአመልካች የቀድሞ ማህበር የተጠሪውን ቅርጽ የተቀበለው በ1990 ዓ.ም. መሆኑን ከክርክሩ መረዳት የተቻለ ሲሆን ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት እስከ የካቲት 16 ቀን 2002 ዓ.ም. ድረስ ያለው ጊዜ ሲቆጠር ከ10 ዓመት በላይ ነው። እዚህ ላይ ዋናው ምላሽ ማግኘት ያለበት ግን የይርጋው ጊዜ መቆጠር ያለበት ከመቼ ጀምሮ ነው የሚለው ነጥብ ነው። አመልካች ጊዜው መቆጠር ያለበት ተጠሪው ቅርጹን ገቢ ካደረገበት ከ1990 ዓ.ም. ጀምሮ ነው ሲል ተጠሪው ግን መብቱ መጣሱን ያወቅኩት ከነሐሴ 20 ቀን 2000 ዓ.ም. ስለሆነ ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ሲቆጠርም ክስ እስከቀረበበት እስከ የካቲት 16/2002 ዓ.ም. ሁለት ዓመት አላለፈውም በሚል ይከራከራል። ሆኖም የሰማዕታት ሐውልት ግንባታ ማህበር ግንቦት 19 ቀን 2000 ዓ.ም. ለሆነው የመታሰቢያ ቀን ቴምብሮቹ እንዲታተሙ የትራንስፖርትና መገኛኛ ሚኒስቴር ለፖስታ አገልግሎት ድርጅት ደብዳቤ የጻፈው ታህሳስ 02/2000 ዓ.ም. መሆኑን ከቀረቡት ማስረጃዎች በሥር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ሲሆን ተጠሪው ቴምብሮቹ የራሱ የፈጠራ ቅርጽ ምስል ተደርጎባቸው መታተማቸውን ላያውቅ ይችላል ተብሎ የሚወሰደውም ከመታሰቢያው ቀን ማለትም ከግንቦት 19/2000 ዓ.ም. ጀምሮ ሲሆን ተጠሪውም ከውል የመነጨውን መብቱን ላጠይቅ የሚችለው አመልካች በውሉ ግድታ መሰረት ባለመፈጸም መሥራቱን ካወቀበት ቀን ጀምሮ ስለመሆኑ በተመሳሳይ ጭብጥ ይህ ችሎት በሰበር መ/ቁ.67376 በቀን 30/11/2004 ዓ.ም. በዋለው ችሎት አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም ተጠሪው ቅርጹ ለ3ኛ ወገን ተላልፎ ምስሉ በቴምብሮች ወጥቶና ተባዝቶ ለገበያ መዋሉን ካወቀበት ቀን ጀምሮ ያለው ጊዜ ሲቆጠር 10 ዓመት ያላለፈው በመሆኑ አመልካች ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው ሲል ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- በከፍተኛው ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር አመልካች የተጠሪው የፈጠራ ሥራ ባለሶስት አውታር መሆኑንና በቴምብሮቹ ምስሉ ወጥቶ የተባዛው ባለሁለት አውታር ነው በሚል ቢከራከርም ከፍተኛው ፍርድ ቤት በቴምብሮቹ ታትሞ የወጣው ምስል የተጠሪው ኦርጅናል ሥራ መሆኑንና ተጠሪውም ለዚሁ ስራ ባለቤት ስለመሆኑ የግራ ቀኙን ማስረጃዎች በመስማትና በመመዘን በፍሬ ነገር ደረጃ ማረጋገጡን በፍርዱ ላይ የገለጸ ሲሆን በከፍተኛው ፍርድ ቤት የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮችን የፍ/ጠ/ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎትም በመመልከት አጽንቶታል። የፍሬ ነገር ጉዳዮችን የማጣራትና የመመዘን ሥልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶችም ያረጋገጡአቸውን ፍሬ ነገሮችን ይህ ችሎትም የሚቀበላቸው ናቸው። አንድ የመጨረሻ ፍርድ/ውሳኔ ያገኘን ጉዳይ ይህ ችሎት ማረም የሚችለው በፍርዱ/በውሳኔው ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት መኖሩ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ በኢ.ፍ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 80(3)(ሀ) እና አዋጅ ቁ
No topics extracted.