No summary available.
ጥር 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ ረታ ቶሎሣ አዳነ ንጉሤ አመልካች፡- ወጋገን ባንክ አ.ማ ነ/ፈጅ ሰላማዊት አዳነ ቀርቧል ተጠሪ፡-
ወ/ሮ ሰላማዊት ጥላሁን ቀርበዋል።
አቶ ነጋሲ በርሕ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የፍርድ አፈፃፀም ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በት/ብ/ክ/መንግስት የአክሱም ዞን ማእከላዊ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ባቀረበው የፍርድ አፈፃፀም ማመልከቻ መነሻነት ነው። በዚያ ፍ/ቤት አመልካች የፍርድ አፈፃፀም ከሣሽ በመሆን ተጠሪዎች ላይ በፍ/ቤት ላስፈረደው ውሣኔ አፈፃፀም እንዲውልለት በ1ኛ ተጠሪ ስም ተመዝግቦ በተሽከርካሪ ሰ.ቁ. 3-27506 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪ ተይዞ በሀራጅ ተሽጦ እዳው እንዲከፈለው ፍ/ቤቱን ጠይቋል። ፍ/ቤቱም ተጠቃሹ ተሽከርካሪ በሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት በኩል እንዲታገድ ትእዛዝ ሲያስተላለፍ ተሽከርካሪዋ ቀደም ብላ በፍድራል የመ/ደ/ፍ/ቤት በልላ ምክንያት የታገደች መሆኑ በጽሑፍ ተገልፆለታል። ከዚህ በኃላ ተሽከርካሪዋ ቀደም ብላ በልላ ፍ/ቤት የእግድ ትእዛዝ የተሰጠባት የአፈፃፀም ከሣሽ (የአሁኑ አመልካች) ጭምር በጉዳዩ ተከራካሪ ወገን በሆነበት መዝገብ ላይ መሆኑን ፍ/ቤቱ ተገንዝቤያለሁ በማለት ይህ ቀደም ብሎ የተሰጠው እግድ ሣይነሣ ተሽከርካሪዋን ሽጦ ለፍርድ አፈፃፀሙ ማዋል ስለማይችል የአፈፃፀሙ ከሣሽ ልላ የንብረት ዝርዝር እስከሚያቀርብ ድረስ ለጊዜው መዝገቡን በመዝጋት ትእዛዝ ሰጥተዋል። አመልካች በዚህ ትእዛዘ ባለመስማማት ይግባኙን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢቀያርብም ተቀባይነት አላገኘም። የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንን ትእዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሐምል 13 ቀን 2004 ዓ.ም በተፃፈ ማመልከቻ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ይዘትም ባጭሩ ተሽከርካሪዋ ላይ የቅድሚያ መብት አለኝ የሚል ወገን ሣይኖር ፍ/ቤቱ በራሱ በልላ ፍ/ቤት የተሰጠው እግድ ሣይነሣ እንዲሸጥ ማዘዝ አይቻልም በማለት የሰጠው ትእዛዝ አግባብነት የልለው መሆኑን፣ በተሽከርካሪዋ ላይ ከአመልካች የቀደመ መብት ያለው 3ኛ ወገን ስለመኖሩ አልተረጋገጠም እንጂ ቢኖርም ይህ መኪናዋ እንዳትሸጥ የሚከለክል አለመሆኑን መኪናዋንም በዋስትና ይዘን በዚህ ምክንያት ከማንም በፊት ያሣገደው አመልካች ሆኖ እያለ በልላ ፍ/ቤት የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ሣይነሣ በመኪናዋ ላይ ውሣኔውን ማስፈፀም አይቻልም መባሉ ከሕግና ሥነ ሥርዓት ውጪ በመሆኑ ትእዛዙ ተሽሮ አፈፃፀሙ በመኪናው ላይ እንዲቀጥል እንዲታዘዝላቸውና ወጭና ኪሣራ እንዲከፈላቸው ጭምር ጠይቋል።
አቤቱታውም ተመርምሮ ለሰበር ችሎት ላቀርብ ይገባል በመባሉ ተጠሪዎች ቀርበው መልስ ሰጥተዋል። ይዘቱም አመልካች መኪናዋን በዋስትና በመያዝ ለተጠሪ አበድሮ የነበረው ገንዘብ መኪናዋን የገዛት አቶ ደረጀ ወንድሙ የሚባል ከፍሎ ካጠናቀቀ በኃላ አመልካች የመኪናዋን ላብሬ ላያስረክበው ፊቃደኛ ባለመሆኑ የፍድራል መ/ደ/ፍ/ቤት መ.ቁ. 179925 በሆነው ላይ አመልካች መኪናዋን በዋስትና ይዞ ያበደረው ገንዘብ የተከፈለው በመሆኑ የመኪውን ላብሬ እዳውን ለከፈለውና መኪናውን ለገዛው ሰው እንዲያስረክብ ተወስኖበታል። ላብሬውንም በፍድራል የመ/ደ/ፍ/ቤት አፈፃፀም መ.ቁ. 195425 በሆነው ላይ አመልካች መኪናውን ለገዛው ሰው በፍርድ ቤት ትእዛዝ አስረክቧል። ይህ ውሣኔና ትእዛዝ በሕግ አግባብ ባልተሻረበት ሁኔታ አመልካች ከቅን -ልቦና ውጪ እያቀረበ ያለው ክርክር ውድቅ ተደርጎ በቂ ኪሣራ ተቆርጦላቸው እንዲሰናበቱ የሚል ነው። አመልካችም የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከለይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የግራ ቀኙን ክርክር የሰበር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔና አግባብነት ካላቸው ድንጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
እንደመረመርነውም ለክርክሩ መነሻ የሆነችው መኪና ላይ ቀደም ብሎ በልላ ፍ/ቤት የተሰጠው የእግድ ትእዛዝ ሣይነሣ መኪናዋን እንድትሸጥ ማድረግ አይቻልም መባሉ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝተናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ እንደሚቻለው ለክርክሩ መነሻ የሆነችው መኪና ፍርዱን የሚያስፈጽመው ፍ/ቤት ከሰጠው የእግድ ትእዛዝ ቀደም ብሎ በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት አመልካች ራሱ የክርክሩ ተካፋይ በሆነበት መዝገብ ላይ የታገደች መሆኑ በአመልካች አልተካደም። ይህ ደግሞ በሕጉ አግባብ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ተከራክሮ ያጣውን ወይም የተከለከለውን መብት ከሕግ ስነ-ሥርዓትና ቅን -ልቦና ውጭ በሆነ አኳኃን ፍርዱን በሚያስፈጽመው ፍ/ቤት ለመጐናፀፍ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ተገቢነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። አሁን ባለው ሁኔታ መኪናዋ ለፍርዱ አፈፃፀም ተከብራና ተይዛ የምትሸጥበት የሕግ አግባብ ላኖር አይችልም።
No topics extracted.
ይህ ከወዲሁ የሚታወቅ ከሆነም ፍ/ቤቱ በመኪዋ ላይ መብት አለን የሚሉ ወገኖችን ክርክር የግድ የሚጠብቅበት ሁኔታም አይኖርም።
በተጨማሪም መኪናዋን ቀደም ብዬ ከማንም በፊት በዋስትና ይዣለሁ የሚለው ክርክርም ቢሆን በሥር ፍ/ቤት ያልተነሣ ክርክር ከመሆኑ ባሻገር ይህም ቢሆን በዚህ መዝገብ ላይ ላነሣ የሚገባው ክርክር ሣይሆን አመልካች ራሱ የክርክሩ ተካፋይ በነበረበት የፍድራሉ መ/ደ/ፍ/ቤት መዝገቦች ላይ ላነሣ የሚገባው ክርክር ነው ሲጠቃለል በሥር ፍ/ቤቶች ትእዛዝ ላይ የተፈጠረ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስላላገኘን ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በዚህ ጉዳይ የአክሱም ዞን ማእከላዊ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 17188 ሚያዚያ 26 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝና እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ.ቁ. 52873 ሰኔ 19 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችሎት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኙ ያወጡትን ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻሉ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ብለናል።