No summary available.
ህዳር 06 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል አዳነ ንጉሴ መኰንን ገ/ሕይወት ተኽላት ይምሰል አመልካች፡- ወ/ሮ ራኬብ መለሰ ተጠሪ፡- የፍድራል ዐቃቤ ሕግ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ በወንጀል ጉዳይ ለመንግስት እንዲወረስ ከተወሰነው ከአንድ አጥፊ ንብረት ውስጥ ለቤተሰብ ህይወትና መተዳደደሪያ ላውል የሚገባው ድርሻ ላሸፍናቸው የሚገባቸውን የወጪ አይነቶችንና መጠናቸውን የሚመለከት ነው። ለክርክሩ መነሻ የሆነው የአሁኑ ተጠሪ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የመ/ በሆነውና ታህሳስ 13 ቀን 2002 ዓ.ም.
በተሰጠው የወንጀል ጉዳይ የፍርድ ባለመብት በመሆኑ በወንጀል ጉዳዩ 3ኛ ተከሳሽ የነበሩትና አጥፊነታቸው ተረጋግጦ ንብረታቸው ለመንግስት ውርስ እንዲሆን የተወሰነባቸው የፍርድ ባለእዳ የሆኑት አቶ ጌቱ ወርቁ ንብረቶችን አይነታቸውን ዘርዝሮ ለመንግስት ገቢ እንዲሆኑ የአስከፈተው የአፈጻጸም ማመልከቻ ነው።የአፈፃፀም መዝገብ የተቀበረለት የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፍርድ ባለእዳው ጉዳዩ ላይ መልስ እንዲሰጡበት ያደረገ ሲሆን የአሁኗ አመልካች በአፈጻጸም መዝገቡ ላይ ሰኔ 09 ቀን 2003 ዓ.ም. በተጻፈ የመቃወሚያ ማመልከቻ አቅርበዋል። ፍርድ ቤቱም በዋናው የወንጀል ጉዳይ ላይ አቶ ጌቱ ወርቁ በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ መሆናቸው በመረጋገጡ ምክንያት ሀብታቸው /ንብረታቸው/ በመንግስት እንዲወረስ ፍርድ ማረፉን፣በፍርዱ ላይ የልጆቹና የሶስተኛ ወገኖች መብት የተጠበቀ መሆኑንና እነዚህ መብቶች ከታዩና ከተመረመሩ በኋላ የአቶ ጌቱ ወርቁ ግማሽ ድርሻ ላይ የሚቀነሰው ከተቀነሰ በኋላ ተራፊ የሆነው ድርሻው ለመንግስት ውርስ እንዲሆን ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ዘርዝሮ የአሁኗ አመልካች ሚስት በመሆናቸው ግማሽ ድርሻቸው እንዲጠበቅላቸው የፍርድ አፈጻጸሙን የያዘው ችሎት የወሰነ ሲሆን የልጆቹን መብት በተመለከተም በዋናው የወንጀል ጉዳይ ለተቀረው የቤተሰብ ሕይወትና መተዳደሪያ ወይም አስፈላጊ ለሆኑት የእለት ምግብና ለኑሮአቸው መደገፊያ የሆኑ ልዩ ልዩ ገቢዎች ላወረሱ እንደማይችሉ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 98(1(ለ)) መደንገጉንና ይህም በፍርድ አፈጻጸም ሂደትም የፍርድ ባለእዳ ልጆች መብት የተጠበቀ መሆኑንና የፍርድ ባለእዳው የእድሜ ልክ ፍርደኛ ቢሆንም በልጆች አስተዳደግ ላይ በሕጉ የተጣለባቸውን ግድታ ላወጡ እንደሚገባ እንደሚያስገነዝብ ፍርድ ቤቱ መረዳቱን ጠቅሶ ለህምክና፣ ለትምህርት፣ ለትራንስፖርት የስድስት ወር ወጪአቸው ላወረስ እንደማይገባ እንዲሁም ለመጠለያ፣ ለልብስና ለምግብ የሚያስፈልጋቸው ወጪ ለልጆቹ ሕይወትና መተዳደሪያቸው ወይም አስፈላጊ የሆኑ የእለት ምግብ ፣ለኑሮአቸው መደገፊያ አስፈላጊ በመሆናቸው ልጆቹ ራሳቸውን እስከሚችሉ ማለትም አስራ ስምንት አመት እስከሚሞላቸው ድረስ ወጪዎቹ ላወረሱ እንደማይገባ፣ የከፍተኛ ትምህርት ወጪ ተብሎ የቀረበው ግን በማስረጃ ያልተደገፈ በመሆኑ ተቀባይት እንደልለው ገልጾና ለህክምና የስድስት ወር ወጪያቸው በወር ብር 1500.00 ሲታሰብ ለእያንዳንዳቸው ብር 900.00፣ የትምህርት ክፍያ የስድስት ወር ወጪ ለእያንዳንዱ ልጅ ብር 6243.00፣የትራንስፖርት ወጪ ብር 1000.00 ላሆን እንደሚገባና በአንድ ልጅ ለ6 ወር ብር 3000.00 ላሆን እንደሚገባ፣ለልብስና ለቀለብ የቀረበው ወጪም በወር ለአንድ ልጅ ብር 1500.00 ላሆን እንደሚገባና ስልቱም ልጆቹ አስራ ስምንት አመት እስከሚሞላቸው ላታሰብ እንደሚገባ ገልጾ ለምስጋና ጌቱ ለልብስና ለቀለብ ብር 190,500.00፣ለአማንድ ጌቱ ደግሞ ብር 217,500.00 በጠቅላላ የሁለቱ ልጆቹ ወጪ ብር 428,286.00 እንደሚሆን እና የፍርድ ባለእዳ የሆኑት አቶ ጌቱ ወርቁ ከወጪው ግማሹን የመሸፈን ግድታ እንደአለባቸው ደምድሞ ብር 214,143.00(ሁለት መቶ አስራ አራት ሺህ አንድ መቶ አርባ ሶስት ብር) ለመንግስት ውርስ ከሚሆነው ከፍርድ ባለእዳው ንብረት ላይ እንዲቀነስ ሲል ወስኗል። በዚህ የውሳኔ ክፍል የአሁኗ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱቱ መሰረታዊ ይዘትም አመልካች ያቀረቡት የቅድሚያ ግዥ መብት መታለፉ ያላግባብ ነው፣የልጆች የትምህርት፣ የሕክምናና የትንስፖርት ወጪ የስድስት ወር ብቻ ታስቦ ልላው ተቀባይነት ማጣቱ ከልጆቹ መብትና ጥቅም አንፃር ያልታየ ነው በማለት ዘርዝረው ውሳኔው እንዲታረም ዳኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም የአመልካች የቅድሚያ መብት የመታለፉና የልጆቹ የህክምና፣ የትምህርትና የትራንስፖርት ወጪ ለስድስት ወር ብቻ እንዲታሰብ የመደረጉን አግባብነት ከወ/መ/ሕ/አንቀፅ 98(1(ለ)) ድንጋጌ አኳያ ለመመርመር ተብሎ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦም ግራ ቀኙ በፅሑፍ ተከራክረዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብት ካለቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን ለችሎቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የፍርድ ባለእዳው ንብረት እንዲወርስ በወንጀል ችሎት ውሳኔ ያረፈበት መሆኑና የሶስተኛ ወገኖችና የልጆች መብት ግን የተጠበቀ መሆኑ በዋናው ፍርድ ጭምር የሰፈረ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት ያረጋገጠው ጉዳይ መሆኑን፣አመልካች የፍርድ ባለእዳ ባለቤት ሲሆኑ እንዲወረስ በተወሰነው ንብረት ላይ ግማሽ ድርሻ ያላቸው መሆኑና በፍርድ አፈፃፀም ጊዜ አቤቱታ ላያቀርቡ የቻሉት መብታቸው እንዲጠበቅላቸውና የልጆቹ የቀለብ፣የልብስ፣ የትምህርት ፣የህክምና እና ትራንስፖርት ወጪ ለመንግስት ውርስ ከሚሆነው የፍርድ ባለእዳው ግማሽ ድርሻ ላይ እንዲቀነስላቸው መሆኑን፣የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን ግማሽ ድርሻ የጠበቀላቸው ቢሆንም ስለቅድሚያ ግዥ ጥያቄ ግን በትዕዛዙ ላይ ያሰፈረው ነገረ የልለ ሁኖ የልጆችን የትምህርት፣ የህክምና እና የትራንስፖርት ወጪ ግን ለስድስት ወር ብቻ እንዲታሰብላቸው፣ ቀለብና ልብስ ግን እድሜአቸው አካለ መጠን እስከሚደርሱ ድረስ በወር ብር 1500.00 እንዲታሰብላቸው ስልት ይዞ የወሰነ መሆኑን ነው።
እኛም ጉዳዩን በሚመለከተው መልኩ ተመልክተናል።
አመልካች ያቀረቡን የቅድሚያ መብት ጥያቄ በተመለከተ፡- አመልካች ለጥያቄአቸው መሰረት ያደረጉት ከፍርድ ባለእዳ ጋር ያላቸውን የጋራ ባለሃብትነት መብት ነው። ይህ መብት መሰረቱ ጋብቻ መሆኑ የተረጋገገጠ ሲሆን የክርክሩ ምንጭ የወንጀል ጉዳይ በመሆኑ ይህንኑ የሚገዛው ቀጥተኛ ሕግ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 98(ለ(መ)) ሁኖ የሶስተኛ ወገኖች መብት የሚጠበቅበትን አግባብ ከሚደነግግ በስተቀር እነዚህ ወገኖች በንብረቱ ላይ የቅድሚያ ግዥ መብት ላሰጣቸው እንደሚገባ በግልጽ አይደነገግም። ይሁን እንጂ ተጠሪ የአመልካች የቅድሚያ መብት ጥያቄ ቢጠበቅላቸው ተቃውሞ የልለው መሆኑን በስር ፍርድ ቤት አስተያየት የሰጠ ከመሆኑም በላይ በዚህ የሰበር ደረጃም በጉዳዩ ላይ ተቃውሞ የልለው መሆኑን የመልሱ ይዘት ያሳያል። እንዲህ ከሆነ አመልካች የቅድሚያ ግዥ መብት የማይጠበቅበት ሕጋዊ ምክንያት የልለ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ጥያቄ በዝምታ ማለፋቸው ተገቢ ሁኖ አልተገኘም።
የልጆችን የትምህርት፣የህክምና እና የትራንስፖርት ወጪን በተመለከተ ፡-በዚህ ረገድ የበታች ፍርድ ቤቶች በአመልካች የቀረበውን መጠን የተጋነነ መሆኑን አስልተው ተገቢ ነው ያሉትን መጠን ለይተው ወስነዋል። የወንጀለኛውን ንብረት መወረስን በተመለከተ የሚደነግገው የወንጀል ህግ አንቀፅ 98(3(ለ)) ስር ቢያንስ ለስድስት ወር ጊዜ ወይም ፍርድ ቤቱ ልዩ ሁኔታዎችን አይቶ ይገባል ብሎ በሚገምተው ምክንያት ለተገለጸና በቂ አስተያየት ላሰጠው ተገቢ በሆነ ውሳኔ ከዚህ ለሚበልጥ ጊዜ ለተቀጪው ቤተሰብ ሕይወትና ለመተዳደሪያቸው ወይም አስፈላጊ የሆኑት የእለት ምግብና ለኑሮአቸው መደጐሚያ የሆኑ ልዩ ልዩ ገቢዎች ሲሆኑ እንዳይወረሱ ለማድረግ እንደሚገባ ሕጉ ያሳያል። ከዚህ ድንጋጌ አቀራረፅ፣ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው የተቀጪው ቤተሰብ ሕይወትና መተዳደሪያ ወይም አስፈላጊ የሆኑት የእለት ምግብና ለኑሮአቸው መደገፊያ የሆኑ ለልዩ ልዩ ገቢዎች የሚሆኑትን የወንጀለኛውን ንብረቶች ለመንግስት ውርስ እንዳይሆኑ ለማድረግ የሚቻለው ቢያንስ የስድስት ወራት ጊዜአትን መነሻ አድርጎ መሆኑን፣ከዚህ ወራት በላይ ደግሞ እንደነገሩ ሁኔታ መወሰን የሚችልበት አግባብ መኖሩን ነው። በመሆኑን ፍርድ ቤቱ ከስድስት ወራት ላላነሰ ጊዜ እንዲወስን ሕጉ ግድታ ከሚጥልበት በስተቀር ከዚህ በላይ ለሆነው ጊዜ ወይም ለማንኛውም ጉዳይ የተቀጪው ንብረት ከውርስ ቀሪ እንዲሆን ለማድረግ የማይቻል መሆኑን ሕጉ ያሳያል።
የሕጉ መሰረታዊ ዓላማም ጥፋት ያልሰሩ የተቀጪው ቤተሰቦች ያላግባብ እንዳይጎዱ መጠበቅና ወንጀለኛው በተገቢው መንገድ እንዲታረም እና ቅጣቱ ልላውን እንዲያስተምር በማድረግ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 87 እና 1 ስር የተመለከተውን ለማሳካት ነው ተብሎ ይታሳባል።
በመሆኑም የወ/ሕ/አንቀጽ 98(3((ለ)) ድንጋጌ በፍርድ ቤቱ ላይ የሚጥለው ግድታ አነስተኛ የጊዜ ገደብ ስድስት ወር ከመሆኑ ውጪ ለተቀጪው ቤተሰብ ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ለረዥም ጊዜአት እንዲሆኑ እንዲታሰቡ አይደለም።
ለስድስት ወር የተያዘው ወጪ መጠን ያነሰ ነው የሚለው የአመልካች የቅሬታ ነጥብ ሲታይ በማስረጃ የሚነጥርና ይህንኑ ለማድረግ በሕግ ስልጣን የተሰጣቸው ፍርድ ቤቶች የሚያከናውኑትና በፍቅድ ስልጣናቸው (Discretionary power) ስር የሚወድቅ እንጂ ይህ ችሎት በኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 መሰረት በተሰጠው የመሰረታዊ ህግ ስህተት የማረም ስልጣን ስር የሚወድቅና የመሰረታዊ ህግ ስህተት መመዘኛን የሚያሟላ ሁኖ አልተገኘም። አመልካች ቅሬታቸቸውን ከሕጻናቱ የትህምርት እና የህክምና ሕገ መንግስታዊ መብት ጋር አያያዝው ያቀረቡት ቅሬታ ሲታይም ህጻናቱ ከአባታቸው ድርሻ የስድስት ወር ወጪ እንዲያገኙ በመደረጉ ምክንያት ብቻ ይኼው የትምህርትና የህክምና መብታቸው አደጋ ላይ የሚድቅበት አጋጣሚ ወደፊት የሚከሰት መሆኑን የሚጠቁሙ መነሻ የክርክር ነጥቦችን በማስረጃ ያመላከቱበት ሁኔታ የልለ መሆኑን የስር ፍርድ ቤት የክርክሩ ሂደት በግልፅ የሚያሳየው ጉዳይ ሁኖ ስለአገኘን የአመልካች ቅሬታ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ አይደለም ብለናል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም አመልካች የበታች ፍርድ ቤቶች የትምርት፣የህክምና እና የትራንስፖርት ወጪ ለህጻናቱ ለስድስት ወር ብቻ እንዲታሰብ ማለፋቸውን ገልፀው በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር የወንጀል ሕጉን አንቀፅ 98(3(ለ)) ድንጋጌን ይዘትና መንፈስ እንዲሁም ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት በሕጉ ተለይቶ የተሰጠውን ስልጣን አድማስ ያላገናዘበ ሁኖ ስለአገኘን ቅሬታውን የምንቀበለው ሁኖ አልተገኘም። ሲጠቃለልም ከላይ በተመለከቱት ሕጋዊ ምክንያቶች መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፍድራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 20 ቀን 2003 ዓ/ም ተሰጥቶ በፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 21 ቀን 2004 ዓ/ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ተሻሽሐል።
አመልካች የግማሽ ድርሻ በሆኑባቸው ንብረቶች የቅድሚያ ግዥ መብት ቢያገኙ ተጠሪ ተቃውሞ የልለው መሆኑን የገለጸ በመሆኑ ይኼው መብታቸው እንዲጠበቅላቸው ብለናል።
የልጆችን የትምህርት፣የሕክምና እና የትራንስፖርት ወጪን በተመለከተ የበታች ፍርድ ቤቶች ለስድስት ወር ብቻ እንዲሆን ማሰባቸው ከወንጀል ሕጉ አንቀፅ 98(3(ለ)) ድንጋጌ አንጸር ሲታይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም።
No topics extracted.