No summary available.
የሰ/መ/ ህዳር 7 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ መኰንን ገ/ሕይወት ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- ኒያላ ኢንሹራንስ (አ.ማ) ነገረ ፈጅ አቶ ዮሴፍ ገብሬ ቀረቡ ተጠሪዎች-
ጉዳዩ የቀረበው አመልካች የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ስላመለከተ ነው። ጉዳዩ በንብረት ላይ በደረሰ ጉዳት የኢንሹራንስ ሰጭው ያለበትን ኃላፊነት የሚመለከት ነው።
የክርክሩ መነሻ አንደኛ ተጠሪ በሁለተኛው ተጠሪ ላይ ያቀረበው የዳረጐት ክስ ነው። አንደኛ ተጠሪ ቁጥሩ 3-16776 ኢት የሆነው የሁለተኛ ተጠሪ መኪና የመድን ሽፋን የሰጠሁትን የሰልዳ ቁጥር 3-35774 /ኢት/ የሆነ መኪና ግንቦት 9 ቀን 2000 ዓ.ም በመግጨት ጉዳት አድርሶበታል። መኪናውን ለማስጠገን ብር 30,556.52 /ሰላሳ ሺህ አምስት መቶ ሀምሣ ስድስት ብር ከሀምሳ ሁለት ሳንቲም/ አውጥቻለሁ። ስለዚህ ይህንን ገንዘብ ይተኩልኝ በማለት በሁለተኛ ተጠሪ ላይ ክስ አቅርቧል። ሁለተኛ ተጠሪ አመልካች ጉዳት ያደረሰው መኪና በሶስተኛ ወገኖች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት የመድን ሽፋን ሰጥቷል። በክርክሩም የሶስተኛ ወገን ተከራካሪ ሆኖ ይጠራልኝ በማለት ተከራክሯል።
አመልካች በክርክሩ ሶስተኛ ወገን ተከራካሪ እንዲሆን ተጠርቶ ገብቶ ለጉዳቱ ኃላፊነት የልለበት መሆኑንና ኃላፊነት አለብህ ከተባልኩም የምከፍለው ካሳ መጠን ክስ ከቀረበበት ገንዘብ ያነሰ ነው የሚል መከራከሪያ አቅርቧል ።
የስር ፍርድ ቤት ጉዳት ያደረሰውን የሰልዳ ቁጥር 3-16776 (ኢት) የሆነው ተሽከርካሪ ይሽከረክር በነበረው በሁለተኛው ተጠሪ ሹፍር ጥፋት ነው በማለት አመልካች ክስ ያቀረበቡትን ገንዘብ ለአንደኛ ተጠሪ እንዲከፍል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች ይግባኝ ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል። የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ.ም በተጻፈው የሰበር አቤቱታ አመልካች የመድን ሽፋን የሰጠው የሰልዳ ቁጥር ኢት 3-16776 ለሆነው መኪናና የሰልዳ ቁጥሩ 3-07520 ኢት ለሆነው ተሳቢ ነው። የአንደኛ ተጠሪ መኪና የተገኘው ተሸካርካሪውን የሚያንቀሳቅሰው ሞተር በተገጠመለት የሰልዳ ቁጥር 3-16776/ኢት/ ሳይሆን ከዚህ መኪና ጋር ተገጥሞ ሲጎተት በነበረውና አመልካች የመድን ሽፋን ባልሰጠው የሰልዳ ቁጥሩ 3-06469 (ኢት) በሆነው ተሳቢ ተገጭቶ ነው። ስለዚህ የቀረበውን ክርክርና የፅሑፍ ማስረጃ በአግባቡ ሳይመረምር አመልካችን በኃላፊነት ይጠይቃል በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩሉ ሰኔ 10 ቀን 2004 ዓ.ም አመልካች የሰልዳ ቁጥሩ 3-16776 ኢት ለሆነው መኪና ከነተሳቢው የመድን ሽፋን እንደሰጠ አምኗል። የሰልዳ ቁጥሩ 3-06469 የሆነው ተሳቢ መኪና ነው። ይህ ተሳቢ አመልካች የመድን ሽፋን የሰጠው መኪና እየተጎተተ ሲሄድ ጉዳት ማድረሱ ካልተለየ የመኪና ላይ የተጫነ እቃ ወይም የሚጎተት አካል የደረሰው ጉዳት ባለመኪናውና ለመኪናው የመድን ሽፋን የሰጠው ሰው በኃላፊነት መጠየቃቸው ተገቢ ነው በማለት ተከራክሯል። አመልካች የመድን ሽፋን በሰጠሁት የሰልዳ ቁጥር 3-16776 (ኢት) እና ጉዳት በደረሰበት የሰልዳ ቁጥሩ 3-35774 (ኢት) መካከል ምንም አይነት አካላዊ ንኪኪ የለም።
ስለዚህ የመድን ሽፋን ባልሰጠሁት አካል ጋር ተገምቶ ለደረሰው ጉዳት በኃላፊነት የምንጠየቅበት ምክንያት የለም በማለት ሐምል 5 ቀን 2004 ዓ.ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዳዩን መርምረናል። ጉዳዩን እንደመረመርነው አመልካች የተሳቢ የሰልዳ ቁጥር 3-06469(ኢት) በአንደኛ ተጠሪ ደንበኛ ላይ ያደረሰውን ጉዳት የመሸፈን ኃላፊነት አለበት በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን ግራ ቀኙ ባደረጉት ክርክርና ባቀረቡት ማስረጃ የተረጋገጡትን ፍሬ ጉዳዮች መመልከት ተገቢ ነው። አመልካች የተጠሪ ንብረት ለሆነው የሰልዳ ቁጥሩ 3-16776 (ኢት) ለሆነ የጭነት መኪናና በዚሁ መኪና ለሚጎተተው የተሳቢ ቁጥሩ 3-07520 (ኢት) ለሆነው ተጎታች ሀምል 2 ቀን 2000 ዓ.ም በተፈረመ የመድን ውል በሶስተኛ ወገን ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት የመድን ሽፋን የሰጠ መሆኑ በግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ የተረጋገጠ መሆኑን ተረድተናል። ከዚህ በተጨማሪ የአንደኛ ተጠሪ ደንበኛ መኪና በሆነው የሰልዳ ቁጥሩ 3-35774 (ኢት) የሆነው መኪና የተጎዳው የሰልዳ ቁጥር 3-16776 (ኢት) ከሆነው መኪና ጋር ተገጥሞ ሲጎተት በነበረው የተሳቢ ቁጥሩ 3-06469 /ኢት/ በሆነው ተጎታች የኋላ ክፍል ተገጭቶ መሆኑን በትራፊክ ፕላን መግለጫና በትራፊክ ፖላስ በተሰጠው የምስክርነት ቃል የተረጋገጠ መሆኑን የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን መዝገብ በማስቀረብ ተረድተናል። ይህም አመልካች የመድን ሽፋን የተሰጠውን የተሳቢ ቁጥር 3-07520 /ኢት/ የሆነው ተጎታች ሣይሆን የመድን ሽፋን ያልተሰጠውን የተሳቢ የሰልዳ ቁጥሩ 3-06469 /ኢት/ የሆነው ተጎታች በማንቀሣቀስ ላይ እያለ፣ የተሳቢው የኋላ ክፍል የአንደኛ ተጠሪ መኪናን በመግጨት ጉዳት ያደረሰበት መሆኑን የሚያሣይ ነው።
ከላይ የገለፅናቸው ፍሬ ጉዳዮች የሰልዳ ቁጥር 3-16776 /ኢት/ በሆነው ባለሞተር ተሽከርካሪ ሲጎተት በነበረው የተሳቢ ቁጥሩ 3-66469 ኢት የሆነው ተጎታች ለደረሰው ጉዳት፣ የባለሞተሩ መኪና ባለሀብት የሆነው ሁለተኛ ተጠሪ በኃላፊነት የሚጠየቅ መሆኑን ከፍታሐብሕር ሕግ ቁጥር 2081/1/ ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ አደጋው የደረሰው በሁለተኛው ሰራተኛ /ሹፍር/ ጥፋት መሆኑ ስለተረጋገጠ ሁለተኛ ተጠሪ በፍታሐብሕር ሕግ ቁጥር 2130 ድንጋጌ መሰረት ጉዳቱን የመሸፈን ኃላፊነት ይኖርበታል።
በልላ በኩል አመልካች የሰልዳ ቁጥር 3-16776/ኢት/ የሆነው ባለሞተር ተሽከርካሪ፣ ሲንቀሣቀስ ለሚያደርሰው ጉዳትና፣ ይህ መኪና ተጎታች በሚጎትትበት ጊዜ የተሳቢ ቁጥሩ 3- 07520 /ኢት/ የሆነውን ተጎታች ብቻ ሲያንቀሣቅስ በተጎታቹ ለሚደርሰው ጉዳት ኃላፊ ለመሆን የመድን ውል ተዋውሐል። አመልካች የሰልዳ ቁጥር 3-16776 /ኢት/ የሆነው ባለሞተር ተሽከርካሪ፣ ማናቸውንም አይነት ተጎታች ሲያንቀሣቅስ፣ በተጎታቹ ለሚደርሰው ጉዳት ኃላፊነት ለመውሰድ አልተስማማም። ኢንሹራንስ ሰጭው በውሉ ለተመለከተው አደጋ ብቻ መድን ለገባው ሰው መድን እንደሚሆን በንግድ ሕግ ቁጥር 663 ንዑስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። እንደዚሁም ኢንሹራንስ ሰጭው በውሉ ውስጥ የተመለከተው አደጋ በደረሰ ጊዜ ወይም በውሉ የተስማሙበት ቀን በደረሰ ጊዜ የተስማሙበትን ገንዘብ የመክፈል ግድታ እንዳለበትና ይህ ግድታው በውለታው ከተጠቀሰው ላበልጥ እንደማይችል “የኢንሹራንስ ሰጭው ግድታ” በሚል ርዕስ ባለው በንግድ ሕግ ቁጥር 665 ተደንግጓል። አመልካች የሰልዳ ቁጥሩ 3-16776 /ኢ.ት/ የሆነው ባለሞተር ተሽከርካሪ መኪና የተሳቢ ቁጥሩ 3-07520/ኢት/ የሆነውን ተጎታች ሲጎትት፣ በተጎታቹ ለሚደርሰው ጉዳት የመድን ሽፋን የሰጠ ሲሆን፣ ከዚህ የመድን ሸፋን ከሰጠው ተጎታች ውጭ ልላ ተሳቢ ሲጎትት፣ በተጎታች የሚደርስ ማናቸውንም ጉዳት ለመሸፈን የመድን ውል አልተዋዋለም። ይህ ከሆነ የአንደኛ ተጠሪ ደንበኛ መኪና ጉዳት የደረሰበት የሰልዳ ቁጥሩ 3-16776/ኢት/ በሆነው ባለሞተር ተሽከርካሪ ተገጭቶ ሣይሆን፣ በዚህ ባለሞተር መኪና ሲጎተት የነበረውና አመልካች የመድን ሽፋን ያልሰጠው የሰልዳ ቁጥር 3-06469 /ኢት/ በሆነው ተሳቢ የኋላ ክፍል ተገጭቶ መሆኑ ፍሬ ጉዳይ የማጣራትና የመመዘን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።
ስለሆነም አመልካች ከሁለተኛው ተጠሪ ጋር ሐምል 2 ቀን 2000 ዓ.ም ከገባው የመድን ውል ውጭ፣ የሁለተኛው ተጠሪ መኪና የመድን ሽፋን የልለውን ቁጥሩ 3-06469/ኢት/ የሆነውን ተሳቢ እየጎተተ ሲያንቀሳቅስ በተሳቢው ግጭት ላደረሰው ጉዳት አመልካች በኃላፊነት ይጠይቃል በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የንግድ ህጉን አንቀጽ 663 ንዑስ አንቀጽ 1 እና አንቀጽ 665 ድንጋጌዎች ይዘት መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሐል።
በአንደኛው ተጠሪ ደንበኛ መኪና ላይ ለደረሰው ጉዳት አመልካች በኃላፊነት አይጠየቅም በማለት በንግድ ሕግ አንቀጽ 633/1/ እና አንቀጽ 665/1/ መሰረት ወስነናል።
በአንደኛው ተጠሪ መኪና ላይ የደረሰውን ጉዳት የመካስ ኃላፊነት ያለበት ሁለተኛው ተጠሪ ነው በማለት ወስነናል።
ሁለተኛው ተጠሪ አንደኛ ተጠሪ የደንበኛውን መኪና ለማስጠገን ያወጣውን ብር 30,556.62 /ሰላሣ ሺህ አምስት መቶ ሀምሳ ስድስት ብር ከስልሳ ሁለት ሣንቲም/ ከኀዳር 3 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር እና የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለዳኝነት፣ ለጠበቃ አበልና ኪሣራ የወሰነውን ብር 3,102 /ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሁለት ብር/ ከ
No topics extracted.