No summary available.
የሰ/መ/ ታህሳስ 03 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል አዳነ ንጉሴ መኰንን ገ/ህይወት ሙስጠፋ አህመድ አመልካች፡- አቶ አስፋው ጉደታ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ - አልቀረበም መዝገቡ የተቀጠረው ለምርምራ ሲሆን፤ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ የቀረበው በግራ ቀኙ መካከል ከተደረገው ጊዜያዊ/ኮንትራት/ የሰራተኛ ቅጥር ግንኙነት የመነጨን ክርክር እንደጊዜው ቅደም ተከተል በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የአሰሪና ሰራተኛ ችሎት ጉዳዩን ለማየት ሥልጣን የለኝም በማለት የአሁን አመልካችን ካሰናበተው፤ እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 515/99 የተቋቋመው የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች አስተዳደር ፍ/ቤትም ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን ሥልጣን የለኝም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ ካደረገው፤ የአመልካች ጉዳይ በየትኛው የዳኝነት አካል ላታይ ይገባል? የሚለውን ነጥብ ለይቶ ለመወሰን ሲባል ነው።
ለዚህ የሰበር ጉዳይ መነሻ በሆኑት በየደረጃው በተሰጡት ዳኝነቶች እና በግራ ቀኙ ክርክር እንደተረጋገጠው አመልካች የአሁን ተጠሪ ቋሚ ሰራተኛ አይደለም። ግንኙነቱ በጊዜያዊ የቅጥር ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው። ተጠሪም በአዋጅ ቁጥር 515/99 የሚገዛ መንግስታዊ መ/ቤት ስለመሆኑም አላከራከረም።
አመልካች ለዚህ የሰበር ጉዳይ ምክንያት የሆነውን ክስ በሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍ/ቤት ከማቅረቡ በፊት በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የአሰሪና ሰራተኛን ጉዳይ በመጀመሪያ ደረጃ ለማየት ስልጣን ባለው የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ማቅረቡና ችሎቱም ሥልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ዳኝነት ከዚህ የሰበር ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው ባይሆንም ከላይ በፍሬ ነገር ረገድ እንደተረጋገጠው አሰሪው የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በፍድራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/99 መሰረት የሚተዳደር በመሆኑ የግራ ቀኙ ክርክር በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ላዳኝ የሚችል አይደለም። በዚህ ረገድ የአሰሪና ሰራተኛ ችሎቱ ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን ስልጣን የለኝም በማለት የሰጠው ዳኝነት በአግባቡ ነው ከሚባል በቀር የአሁን አመልካችን ፍትህ ለማግኘት መብት በሚያጣብብ አኳኋን በስልጣን ረገድ የተሳሳተ ዳኝነት ሰጥቷል በመሆኑም አመልካች ፍትህ የማግኘት መብቱን የት ያረጋግጥ? ፍትህ የመግኘት መብቱ ተነፍጓል፤ ለሚለው መደምደሚያ መነሻ ላሆን የሚችል ዳኝነት አይደለም።
በልላ በኩል የአሁን ተጠሪ የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በፍድራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ መሰረት የሚገዛ፤ የሚተዳደር መ/ቤት ይሁን እንጂ በእርሱ እና በሰራተኞች መካከል ከስራ ግንኙነት የመነጨ ክርክር በተነሳ ጊዜ በማን እና በምን አኳኋን መሰረት ላስተናገድ እንደሚችል በሚደነግገው በአዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 2(1) ስር የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደር ፍ/ቤቱ ሥልጣን በፍድራል የመንግስት መ/ቤቶች ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ በሚሰራ ሰራተኛ ላይ ብቻ የተወሰነ በመሆኑ ለዚህ የሰበር ጉዳይ መነሻ በሆነው በይ/መ//2004 ግንቦት 30 ቀን 2004 ዓ/ም በዋለው ችሎት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አስተዳደር ፍ/ቤት የአመልካችን ጊዜያዊ ወይም የኮንትራት ሰራተኛ መሆን መነሻ አድርጎ ጉዳዩን ለማየት በህግ ተለይቶ የተሰጠን ሥልጣን የለም በሚል የሰጠው ብይንም መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
ይልቁንም የአዋጅ ቁጥር 515/99 የተፈፀሚነት ወሰን በቋሚ ሰራተኞች ላይ የተወሰነ በመሆኑ የተነሳ በፍድራል መንግስት መ/ቤቶች ጊዜያዊ የኮንትራት ሰራተኞች ጉዳይን ጭምር ላሸፈን ያልቻለ መሆኑ ታይቶ ይህንኑ ክፍተት ለመሙላት በፍድራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 22(3) መሰረት የፍድራል መንግስት ጊዜያዊ የኮንትራት ሰራተኞች ቅጥር አፈፃፀም መመሪያ በመስከረም ወር 2000 ወጥቷል። ይህ መመሪያ ቀጣሪ በሆነውና በጊዜያዊ የኮንትራት ሰራተኛ መካከል ላነሱ ሚችሉትን ክርክሮች ሁሉ አይቶ መብትና ግድታን በመወሰን ረገድ በተሟላ አኳኋን የወጣ መመሪያ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጉዳይ እንዳለ ሆኖ የዚህኑ መመሪያ አፈፃፀም በሚመለከት ቀጣሪው በሚሰጠው ውሳኔ ተቀጣሪው ካልተስማማ አቤቱታውን ወይም ይግባኙን ለመደበኛው ፍ/ቤት ማቅረብ ይችላል በሚል የተደነገገው ለዚህ ለተያዘው ጉዳይ አግባብነት እንዳለው ተረድተናል።
በመሆኑም የአሁን አመልካች የአዋጅ ቁጥር 515/99 የአፈፃፀም ወሰን፤ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 22(3) መሰረት የፍድራል መንግስት ጊዜያዊ የኮንትራት ሰራተኞች ቅጥር አፈፃፀም መመሪያ ለማውጣት ከተፈለገበት ዓላማ እና የተፈፃሚነት ወሰን አንፃር አገናዝቦ ሲታይ መ/ቤቱ በሰጠው ውሳኔ ላይ ጉዳዩን ለፍድራል ከፍ/ፍ/ቤት መቅረብ የሚገባው እንጂ በአዋጅ ቁጥር 377/96 ሆነ በአዋጅ ቁጥር 515/99 አንፃር እንደቅደም ተከተሉ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ሆነ በፍድራል ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር አስተዳደር ፍ/ቤት ላታይ የሚችል አይደለም በሚል የተሰጠው ዳኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
በዚህ ጉዳይ የፍድራል ሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር የአስተዳደር ፍ/ቤት በይ/መ//2004 ግንቦት 30 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ብይን፤ ይግባኝ ሰሚው የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዳዩ በይግባኝ ተመልክቶ ይኸው ብይን በህግም ሆነ በፍሬ ነገር ረገድ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም በማለት በፍ/ብ/ይ/መ/ ሐምል 19 ቀን 2004 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ሁሉ ፀንቷል።
አመልካች ጉዳዩን ሥልጣን ላለው አካል አቅርቦ የማሰማት መብቱን ይህ ፍርድ አያግደውም ብለናል።
በዚህ የሰበር ጉዳይ ክርክር የተነሳ ግራ ቀኙ ላወጡት ወጭና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
No topics extracted.