No summary available.
ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ ተኽላት ይመስል አመልካች፡- የሟች የአቶ ዋሲሁን መኮንን ሚስትና ወራሾች
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዳዩ የንግድ ቤት ይመለስልኝ ጥያቄን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በኢትዩጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጂንሲ ሲሆን በዚህ አካል አቤቱታ ያቀረቡት የአሁኑ አመልካቾች አባት ሲሆኑ ጊዜውም ጥቅምት 13 ቀን 1988 ዓ/ም ነው። የአመልካቾች አባት አቤቱታ ይዘት ሲታይም በአዲስ አበባ ከተማ በቀድሞው ወረዳ 7፣ ቀበል 34፣ የቤት ቁጥር 703 የሆነውን ንግድ ቤት በደርግ መንግስት ከአዋጅ ውጪ የተወሰደባቸው መሆኑን ገልጸው ንግድ ቤቱ እንዲመለስላቸው ይወሰን ዘንድ መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። ከአቤቱታቸው ጋርም የቤቱን ባለሃብትነትና ቤቱ ከአዋጁ ውጪ ስለመወረሱ ያሳያሉ ያሐቸውን በርካታ የሰነድ ማስረጃዎች አያይዘው አቅርበዋል። አቤቱታ የቀረበለት ኤጀንሲም የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት አቤቱታ ስለቀረበበት ንግድ ቤት በዝርዝር መግለጫ በማዘጋጀትና ከመስሪያ ቤቱ ሕጋዊ ውክልና በተሰጠው ሰው አማካኝነት ምላሽ እንዲሰጥበት ያደረገ ሲሆን ተጠሪ በወቅቱ በሰጠው ምላሽ ንግድ ቤቱ በመንግስት እጅ ያለ መሆኑን በመግለፅ ነገር ግን በምን ሁኔታ ላወረስ እንደቻለ ማረጋገጫ ማስረጃ የልለ መሆኑን ጠቅሶ መልስ ሰጥቷል። ከዚህም በኋላ አቤቱታ የቀረበለት ኤጀንሲ ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክርና ምላሽ በመመልከትና ተገቢ ነው ባለው መንገድ ሁሉ ጉዳዩን ከአጣራ በኋላ ጉዳዩን መርምሮ አቤቱታ የቀረበበት ንግድ ቤት ለአመልካቾች አባት እንዲመለስላቸው ሲል በመ/ቁጥር 20/ነ2/497/9987/93 በቀን 15/05/1993 ዓ/ም ውሳኔ ሰጥቷል። ከዚህም በኋላ በወቅቱ ስያሜ ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ ተብሎ የሚታወቀው አካል በመሰል ጉዳዮች የይግባኝ ስልጣን ለአለው የፕራይቬራይዜሽን ቦርድ ይግባኙን አቅርቦ ቦርዱም ጉዳዩን አመልካቾች በልሉበት አይቶ ንግድ ቤቱ ለአመልካቾች አውራሽ እንዲመለስ በማለት የተሰጠውን የኤጀንሲውን ውሳኔ ሽሮታል። በዚህ ውሳኔ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቢያቀርቡም የሰበር ችሎቱ አጣሪ ችሎት ጉዳዩን መርምሮ የኤጀንሲው ቦርድ ውሳኔ አስተዳደራዊ ከመሆኑ ባሻገር ይህንን አስተዳደራዊ ውሳኔ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል ወይም አልተፈጸመበትም ለማለት ችሎቱ ስልጣን የለውም በሚል ምክንያት ወደ ፍሬ ጉዳዩ ሳይገባ መዝገቡን ሚያዚያ 21 ቀን 2001 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ዘግቶታል።
ከዚህም በኋላ የአሁኑ አመልካቾች ጉዳዩ የሕገ መንግስት ትርጉም የሚያስነሳ ነው በማለት ለሕገ መንግስት አጣሪ ጉባኤ ጥያቄ ቢያቀርቡም ተቀባይነት ያጡ ሲሆን ጉዳዩን በመጨረሻ ለኢትዮጵያ ፍድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብላክ መንግስት የፍድሬሽን ምክር ቤት አቅርበው ምክር ቤቱም ጉዳዩን ተመልክቶ የኤጂንሲው ቦርድ ዳኝነት መሰል አካል (Quasi judicial body) በመሆኑና ይህ አካል የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ በመሆኑ ጉዳዩን የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በዳኝነት ስልጣኑ ማየት እንደሚችል በመግለጽ የኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37፣ 803(ሀ))፣ አዋጅ ቁጥር 110/87 አንቀፅ 2(3)፣ 5(3) እና አዋጅ ቁጥር 87/86 አንቀፅ 8(5) ድንጋጌዎች በዋቢነት በመጥቀስ ጉዳዩን ሰበር ችሎት እንዲመለከተው በሙሉ ድምጽ በመወሰን ጉዳዩ ለዚህ ችሎት እንዲመለስ ተደርጓል። ከዚህም በኋላ የሰበር ችሎቱ አጣሪ ችሎት ጉዳዩን መርምሮ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 87/1986 አንቀጽ 8(5) መሰረት የቀረበለትን ይግባኝ መርምሮ ውሳኔው ላይ ለመድረስ የተከተለው አካሄድ የሕግን አግባብ የተከተለ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዳዩን ለዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት እንዲቀርብ ያደረገ ሲሆን ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለትም ተጠሪ ቀርቦ በሰጠው መልስ ሰበር ችሎቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን እንደልለውና የኤጀንሲው ቦርድ ጉዳዩን በይግባኝ ሲመለከት የተከተለው አካሄድም አግባብነት ያለው መሆኑን ጠቅሶ እንዲሁም አከራካሪው የንግድ ቤት ለአመልካቾች የሚመለስበት ሕጋዊ አግባብም እንደልለ ዘርዝሮ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል።
አመልካቾች በበኩላቸው ጉዳዩን የሰበር ችሎት ለመዳኘት ከኢ.ፍ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት የመነጨ ስልጣን ያለው መሆኑን ጠቅሰውና የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዳዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችሎትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዳዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችሎቱን ምላሽ የሚያስፈልጋቸው አበይት ጭብጦች፡-
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች የፕራይቬታይዜሽን ኤጂንሲ ቦርድ ጥቅምት 28 ቀን 2001 ዓ.ም. በሰጠው ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘትና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሞበታል በሚል ምክንያት የካቲት 09 ቀን 2001 ዓ.ም. በተጻፈ የሰበር አቤቱታ ቅሬታቸውን ለሰበር ችሎቱ አቅርበው አጣሪው የሰበር ችሎት የኤጀንሲው ቦርድ የሚሰጠው ውሳኔ አስተዳደራዊ በመሆኑ ጉዳዩ ላይ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ወይም አልተፈፀመም ለማለት ችሎቱ ስልጣን የለውም በሚል ምክንያት መዝገቡን ዘግቶት ጉዳዩ እስከ ፍድሬሽን ምክር ቤት ደርሶ የፍድሬሽን ምክር ቤት ጉዳዩን መርምሮ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ጉዳዩን የማየት ስልጣን ያለው መሆኑን በመዘርዘር የወሰነና ጉዳዩ በችሎቱ እንዲታይ የመለሰ መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የፍድሬሽን ምክር ቤት በኢ.ፍ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 62(1) መሰረት ሕገ መንግስትን የመተርጎም ስልጣን ያለው አካል ሲሆን የዚህን አካል ስልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀፅ 3(1) ስርም ህገ መንግስትን የመተርጎም ስልጣን የምክር ቤቱ መሆኑ በግልጽ ሰፍሯል። በዚህ አዋጅ አንቀፅ 56(1) ስር ደግሞ ምክር ቤቱ በቀረበለት ጉዳይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ስለመሆኑ የተደነገገ ሲሆን በዚሁ ድንጋጌ ንኡስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ስርም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ውሳኔውን የማክበርና የመፈፀም ግድታ ያለባቸው መሆኑ አስገዳጅነት ባለው መልኩ ተቀምጧል። የፍድሬሽን ምክር ቤት ከላይ በተገለፁት የሕግ ማዕቀፎች በተሰጠው ስልጣን መሰረት አመልካቾች ያቀረቡትን ጥያቄ መርምሮ ጉዳዩ ላይ ውሣኔ ለመስጠት የፍድራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የዳኝነት ስልጣን ያለው መሆኑን ዘርዝሮ ወስኗል። ይህ ውሳኔ ለጉዳዩ የመጨረሻ ሲሆን በዚህ ችሎትም ሆነ በልሎች በሚመለከታቸው አካላት መከበርና መፈፀም ያለበት ስለመሆኑ የአዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀጽ 56 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የሚያስነዝበን ጉዳይ ነው። ስለሆነም የተጠሪ ነገረ ፈጅ ይህ ችሎት ጉዳዩን ለማየት የዳኝነት ስልጣን የለውም በማለት የሚያቀርቡት ተቃውሞ የፍድሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ ይዘትና የአዋጅ ቁጥር 251/1993 አንቀፅ 56 ድንጋጌን ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የልለው ሆኖ አግኝተናል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የፕራይቬታይዜሽን ኤጂንሲ ቦርድ የኤጂንሲውን ውሳኔ የሻረው የአሁኑን አመልካቾችን ጠርቶና ተገቢውን ክርክርና ማስረጃ እንዲያስሙ በማድረግ ያለመሆኑን ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ ይህ የኤጀንሲው ቦርድ አካሄድ በአዋጅ ቁጥር 87/1986 እና ይህንኑ አዋጅ ተከትሎ በወጡትና ስራ ላይ በነበሩት የቦርዱ መመሪያዎች ተገቢ ነው በማለት የሚከራከር መሆኑን ነው።
በመሰረቱ የኢትዮጵያ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲን ለማቋቋም የወጣው አዋጅ ቁጥር 87/1986 በአንቀጽ 8 ስር የኤጀንሲውን ቦርድ ስልጣንና ተግባር የዘረዘረ ሲሆን በተጠቃሹ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ አምስት ስር የኤጀንሲውን ውሳኔ በሚመለከት ከማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት የሚቀርብለትን ይግባኝ ሕጋዊነቱን መርምሮ መወሰን ከስልጣንና ተግባራቱ አንዱ ስለመሆኑ ያሳያል። ይህ ድንጋጌ የኤጀንሲው ቦርድ ይግባኙን ሲመረምር ላከተለው ስለሚገባው ስነ ስርዓት በግልጽ አያስቀምጥም። ይሁን እንጂ የአዋጁ አንቀጽ 9 የቦርዱ ስብሰባ የሚመራበትን ስርዓት የሚደነግግ ሲሆን ስብሰባው የሚመራበትን ደንብ ቦርዱ ላያወጣ እንደሚችል ደግሞ በአንቀፁ ንዑስ ቁጥር አራት ድንጋጌ ስር ያስቀምጣል። ይህ አካል ከፊል የዳኝነት ስልጣን ያለው አካል እንደመሆኑ መጠን የሚሰጠው ውሳኔ የተፈጻሚነት ኃይል ያለው ስለመሆኑ ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት በአዋጅ ቁጥር 454/1997 አንቀጽ 2(1) መሰረት የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም በመ/ በቀረበው ጉዳይ ላይ ሰጥቶታል። ቦርዱ ከፊል ውሳኔ ሰጪ አካል እንደመሆኑ መጠን የሚሰጠው ውሳኔ የሕጉን ስርዓት ተከትሎ ላሰጥ ይገባል። ከፊል የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው አካል በሕጉ ተለይቶ የተቀመጠለት የክርክር አመራርና አሰጣጥ ስርዓት እስከልለ ድረስ በኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት የተጠበቁትን ፍትህ የማግኘት፣ የመሰማትና በእኩል ሚዛን የመታየት መብት ላያከብር ይገባል። በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላጠበቁ ከሚገባቸው ሕገ መንግስታዊ መብቶች አንዱ ደግሞ ክርክር የማቅረብና ማሰረጃ የማሰማት መብት ነው። ይህ የዳኝነት አሰጣጥ ስርዓት የግድ ከሚላቸው የስነ ስርዓት አካሄዶች አንዱ ነው። ክርክሩን በአግባቡ እንዲያቀርብ እድል ያላገኘ ሰው በኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 37 የተከበረለት ፍትህ የማግኘት መብቱ ውጤታማ ላሆን አይችልም። ስለሆነም የመሰማት መብት በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ላከበር የሚገባው መብት ነው። የመሰማት መብት ከመጀመሪያው ክርክር ጀምሮ እስከመጨረሻው የዳኝነት ሰጪ አካል መከበር ያለበት ስለመሆኑ በሕገ መንግስቱና ስለ ክርክር አመራር በተደነገጉት እንደፍትሐብሕር ስነ ስርአት አይነት ሕጎች ከተደነገጉት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው። ይግባኝ ሰሚ የሆነ መደበኛ ፍርድ ቤትም ሆነ ከፊል የዳኝነት ስልጣን ያላቸው አካላት በይግባኙ የክርክር ሂደት የተከራከሪ ወገኖችን የመሰማት መብት ሳያከብሩ ውሳኔ የሚሰጡበት ሂደት መኖር እንደልለበት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337፣ 338፣ 339 እና ከልሎች ስለ ማስረጃ አቀራረብ ከተመለከቱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ቦርድ ጉዳዩን በይግባኝ ሲመለከት አመልካቾች በአካል አስቀርቦ የመሰማት መብታቸውን በመጠበቅ ጉዳዩን የመረመረ ስላለመሆኑ ተጠሪም የሚክደው ፍሬ ጉዳይ አይደለም። ተጠሪ አጥብቆ የሚከራከረው የኤጀንሲው ቦርድ የአፈጻጸም መመሪያ 001/88 አንቀፅ 8.1 እስከ 8.6 እና ከአንቀጽ 9.1 -9.4.3 እንዲሁም 11.4 ስር ባሉት ድንጋጌዎች የአቤቱታ አመዘጋገብ፣ ማጣራትና ውሳኔ አሰጣጥ እንድት መሆን እንዳለበት በዝርዝር የተቀመጠ በመሆኑ የኤጀንሲው ቦርድ የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን የፍርድ አሰጣጥ ስነ ስርዓት ባለመከተሉ ብቻ የሕግ ስህተት ፈጽሟል ለማለት አይቻልም በማለት ነው። ይሁን እንጂ ተጠቃሹ መመሪያ ምንጭ ማድረግ ያለበት አዋጅ ቁጥር 87/87 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ሲሆን በዚህ ረገድ የክርክር አመራርን በተመለከተ ስነ ስርዓት ሕጉን ቦርዱ እንደሚያወጣ የሚያሳይ ድንጋጌ የልለ ሲሆን የአዋጁ አንቀጽ 9 የአማርኛ ቅጂው ርእሱ “የቦርዱ ስብሰባ" በሚል የተቀረፀ ሲሆን የእንግላዝኛው ቅጂ ደግሞ “Meetings of the board” በሚል የተቀመጠ እና በአንቀፁ ንዑስ ቁጥር አራት ድንጋጌ ስር ደግሞ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ስነ ሥርዓት ደንብ ላያወጣ ይችላል ተብሎ መደንገጉን የድንጋጌው የአማርኛ ትርጉም ሲያሳይ፣ የእንግላዝኛው ትርጉምም “The Board may determine its own rules of procedure.” በሚል ሰፍሯል። ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው አዋጁ የይግባኝ ክርክር አመራር ስርዓትን በተመለከተ ግልፅ የሆነ ድንጋጌ ያላስቀመጠና ለቦርዱ ደንቡን እንዲያወጣ ስልጣኑን የሰጠውም የራሱን ስብሰባ በተመለከተ እንጂ የክርክር አመራሩን፣ የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማት ሂደትንና አተገባበሩን በተመለከተ ያለመሆኑን ነው። በመሆኑም ተጠሪ አለ የሚለው መመሪያ በይግባኝ ክርክር ሂደት ላሰሙ የሚገባቸውን ሰዎችን መብታቸው ሳይጠበቅ እንዲያልፍ ለማድረግ ሥልጣን ባለው አካል የወጣ ነው ለማለት የማያስችልና መመሪያው ስልጣን ባለው አካል የወጣ ነው ቢባል እንኳ ይዘቱና መንፈሱ ሲታይ የክርክር አመራሩ ሂደት የተከራካሪ ወገኖችን የመሰማት መብትን የሚገድብ ሳይሆን ቦርዱ ጉዳዩን ሕጋዊ ስርዓቱን በመጠበቅ ለራሱ አሰራር አመቺ ነው ባለው መንገድ እንዲመራ ለማስቻል ነው ተብሎ የሚታመን ነው። ከዚህ ውጪ የሚከናወን የክርክር አመራር በኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት በአንቀጽ 37 እና ኢትዮጵያ ተቀብላ ባጸደቀቻቸው አለም አቀፍ ስምምነቶች የተከበረውን ፍትህ የማግኘት እና የመሰማት መብቶችን የመሸርሸር ውጤት የሚያስከትል በመሆኑ ተቀባይነት ላሰጠው የሚገባ አካሄድ አይደለም። የኤጀንሲው ቦርድ ይግባኙን የተመለከተውና ውሳኔ የሰጠው የአመልካቾችን የመሰማት መብት ሳያከብር መሆኑ ግልፅ ነው። ይህ ደግሞ ስለ ክርክር አመራር በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕጉ የተደነገገውን ስርዓት የጣሰ ሲሆን በክርክር አመራር ሂደት የስነ ስርዓት ሕግ ድንጋጌዎችን ያለመጠበቅ ደግሞ የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዘኛን የሚያሟላ ነው። በመሆኑም የኤጀንሲው ቦርድ ይግባኙን የተመለከተው ሕጋዊ ስርዓትን ተከትሎ ባለመሆኑ ይህ ችሎት በኢ.ፍ.ዲ.ሪፐብላክ ህገ መንግሰት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀፅ 10 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በጉዳዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝቷል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.