No summary available.
ጥቅምት 06 ቀን 2005 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወል ዓላ መሐመድ አዳነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢት/ያ ኦርቶዶክስ ቅድስት ሥላሴ መንፈሣዊ ኮልጅ ነገረ ፈጅ ፀዳለ ዳና ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አሰገድ ሣህሉ ቀረቡ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፣ መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ግራ ቀኙን ያከራከረው ጉዳይ በፍርድ ላያልቅ የሚገባው ጉዳይ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለውን ለይቶ ለመወሰን ሲባል በዚህ ሰበር ሰሚ ችሎት የቀረበ ነው።
የጉዳዩ መነሻ የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ ያቀረበው ክስ ሲሆን ፍሬ ቃሉም፡ለ2003 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የዲግሪ ፕሮግራም መሥፈርት አሟልቼ ትምህርቱን እየተከታተልኩ እያለ፣ ማስታወቂያ በወጣበት ጊዜ ያልነበረነ መሥፈርት መሰረት በማድረግ ወደ ማታው የትምህርት ፕሮግራም ያዛወረኝ ከመሆኑም በላይ የአባልነት ማስረጃ በአጥቢያ ቤተክርሲቲያን ማቅረቤ እየታወቀ ትክክለኛ ማስረጃ አላቀረብክም በማለት እንዲሁም ለብዙ ቀናት በትምህርት ገበታ ላይ አልተገኘህም በሚሉ ምክንያቶች ትምህርቴን እንዳቋርጥ ስለወሰነ ትምህርቴን እንድቀጥል ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የአሁን አመልካች ለዚሁ ክስ በሰጠው መልስ ኮልጁ የኢት/ያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክስቲያን እምነቷን ለማስፋፋት እና አማኞቿን ለማስተማር ሲባል የተቋቋመ ኃይማኖታዊ ኮልጁ ስለሆነ በዚህ ጉዳይ ፍ/ቤት ውሣኔ ለመስጠት አይችልም። ውሣኔ ለመስጠት ስልጣን አለው ከተባለ በሃይማኖታዊ ጉዳዩ ጣልቃ እንደመግባት ይቆጠራል ስለዚህ ፍ/ቤቱ ጉዳዩን ለማየት ስልጣን ስለልለው መዝገቡ ይዘጋልኝ በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ክርክር ካስቀደመ በኃላ በአማራጭም ከሣሽ ላቀረበው የፍሬ ጉዳይ ክርክር የበኩሉን ክርክር አቅርቧል። ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ስልጣንን በሚመለከት የቀረበው ክርክር ተመልክቶ የኮልጁ ዋና ዓላማ መንፈሣዊ ትምህርት መስጠት የመሆኑ እውነታ ብቻውን ይህ ፍ/ቤት ጉዳዩን አይቶ ከመወሰን ላያግደው የሚችል አይደለም። ከሣሽ ከትምህርት ገበታው የተሰናበተው በአግባቡ ነው ወይስ አይደደለም?
የሚለውን ጉዳይ የግለሰብ መብትን ከህገ መንግስቱና ከልሎች ህጐች አንፃር ማስከበር መሆኑን ስለሚያመለክት ጉዳዩን ለማየት ስልጣን አለኝ የሚል ብይን ከሰጠ በኃላ በመቀጠልም ከሣሽ ቤተክርስትያኗ አስተምሮት ወጥና አራማጅ ነው ወይስ አይለም?
ለምልመላ የሚያበቃውን ማስረጃ ከትክክለኛው የሰበካ ጉባኤ አቅርቧል ወይስ አልቀረበም?
ከትምህርት ገበታው ስለመቆየቱ ተረጋግጧል ወይስ አልተረጋጠም? በሚሉት አከራካሪ ነጥቦች ላይ ማስረጃ ከሰማ በኃላ ሐምል 07 ቀን 2005 ዓ.ም በዋለው ችሎት የኢት/ያ ኦርቶዶክስ ቤተክስርስቲያን የማትቀበለውን ትምህርት ከሣሹ ስለሚያራምዱ በተከሣሽ ምስክሮች በሚገባ አልተረጋገጠም። ለምለመላ አስፈላጊ የሆነው የደብር ማስረጃ ከሣሹ ካቀረበ በኃላ በማታለል መሆኑ ተገልፆ የተሰረዘው ከሣሹ ከትምህርት ከታገደ በኃላ ስለሆነ ለማገዱ ተግባር መሰረት ነው ለማለት የማይችል በመሆኑ በላይ በሥራ ኃላፊ በሚፃፍ የዘፈቀደ ደብዳቤ የተማሪ የመማር መብት ላገደብ አይገባም እንዲሁም ከትምህርት ቀርቷል ተባለ እንጂ ለመቅረቱ ማስረጃ አልቀረበም። ስለሆነም ከሣሹ የማታ ትምህርቱን እዲቀጥል ይደረግ በማለት ዳኝነት ሰጥቷል።
ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት የቀረበለትን የይግባኝ ጉዳይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 እንደተደነገገው ከላይ የተመለከተው ፍርድ ጉድለት ያለበት ባለመሆኑ ተጠሪን መጠራት አያስፈለግም በማለት መዝገቡን ዘግቶ አመልካችን አሰናብቶታል። ለዚህ የሰበር ጉዳይ መነሻ የሆነውም አመልካች በዚህ የመጨረሻ ፍርድ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚላቸውን ነጥቦች በመዘርዘር የሰበር አቤቱታውን በማቅረቡ ፍ/ቤቶች ጉዳዩን አይተው ለመወሰን ስልጣን አላቸው ወይስ የላቸውም? የሚለውን ነጥብ በመመለከት ተጠሪው ቀርቦ ክርክሩን እንዲያሰማ ተደርጓል።
በዚህም መሰረት የአሁን ተጠሪ ተከሣሹ ኮልጅ በእራሱ ህጋዊ ሰውነት ያለው ስለሆነ ላከስም ላከሰስም ስለሚችል በስልጣን ረገድ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ፍርድ አይደለም በማለት ተከራክሯል። አመልካች የመልስ መልሱን በፅሑፍ ያቀረበ ቢሆንም ይዘቱ በሰበር ቅሬታው ከገለፀው የተለየ አይደለም።
የጉዳዩ አመጣጥ ከላይ በቀደም ተከተል የተጠቀሰው ሲሆን፤ እኛም ጉዳዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል። መደበኛ ፍ/ቤቶች በክሱ ደረጃ የቀረበላቸውን ጉዳይ ተቀብለው ወደ ዋናው የክርክር ይዘት ዘልቀውበት ከመግባታቸው በፊት ክስ የቀረበበት ጉዳይ በፍርድ ቤት ቀርቦ በፍርድ ላያልቅ የሚገባው ጉዳይ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን በቅድሚያ የመመርመርና የማየት ግድታ ያለባቸው ስለመሆኑ ኢት/ያ ፍድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብላክ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 ሥር ተደንግጓል። ዝርዝር ህግ በሆነው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 4 ላይም ቢሆን መደበኛ ፍ/ቤቶች የቀረበላቸውን ማናቸውም ጉዳይ ያለገደብ ተቀብለው ለማስተናገድ የሚያስችል ስልጣን እንደልላቸው ተመልክቷል።
ከዚህ በቀር አንድ ሰው በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ለማስወሰን የሚችለው ከህግ የመነጨ መብት ያለው መሆኑን በክሱ ዝርዝር በፍሬ ነገር ደረጃ ማመልከት የቻለ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33(2) ተደንግጓል።
ከዚህ አንፃር አሁን የቀረበውን ጉዳይ ስንመለከት ከሣሹ የአሁን ተጠሪ ለትምህርት ከገባበት ኮልጅ ያለአግባብ የተሰናበት ስለመሆኑ ገልፆ ከቀረበው የፍሬ ጉዳይ ክርክር አንፃር ማጣቀሻ ላሆን የሚችል የአገሪቱ የህግ ማእቀፍ አካል የሆነን ህግ መሰረት አድርጎ ክርክርሩን አላቀረበም።
በፍ/ቤት ላከበር የሚችል መብት በልላ የዳኝነት አካል እንዲታይ ካልተደረገ በቀር ከህግ የመነጨ መብት ላሆን እንደሚገባ ከላይ እንደተመለከተው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33(2) በግልጽ ተመልክቷል።
ይልቁንም ክስ የቀረበበት ኮልጅ ከተቋቋመበት ዓላማ፣ በኮልጁ ከሚሰጠው የትምህርት ይዘት ይህንንም መነሻ በማድረግ ለተማሪነት ማንን እንደሚመለምል፣ለምልመላው ማሟያ የሆኑ መስፈርቶች፤ እነዚህ መስፈርቶች መሟላትና አለመሟላታቸውን በኮልጁ ትምህርት ተካፋይ የሆኑ ተማሪዎች በትምህርት አቀባበል ሂደት ላገልጿቸው ስለሚገቡ የዲሲፒላን ጉዳዩች ምን ምን እንደሆኑ ኮልጆችን ለአቋቋመችው ቤተ ክርስቲያን የተተው ከመሆኑ በቀር ይህንን ጉዳይ ሁሉ ላሸፍን የሚችል ዝርዝር ህግ በህግ አውጭው በኩል የተቀረፀ አይደለም።
የተለያዩ ሙያዎችንና ክህሎቶችን ለማስረጽ እንዲቻል በሚል የተቋቋሙት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንኳ ለትምህርት ነፃነት ሲባል በተመሣሣይ ከላይ የተመለከቱትን ጉዳዩች አስመልክቶ ክርክር ቢነሣ እንኳ እንደማናቸውም ጉዳይ ያለገደብ በፍርድ ቤት ቀርበው ላታዩ የማይችሉ ጉዳዩች እንደሆኑ በአዋጅ ቁጥር 650/2001 ለአብነት ማሣያ ነው።
ስለሆነም የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ከትምህርት ገበታው የተሰናበተው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን አከራካሪ ነጥብ የግለሰብ መብቱን ስለሚመለከት ከህገ መንግስቱ አንፃር ማስከበር ስለሆነ የሚለውን ትርጉም በህገ መንግስቱ አንቀጽ 37 የግለስብ ፍትህ የማግኘት መብት በፍርድ ላያልቁ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ የተወሰነ መሆኑ ተገልፆ የተደነገገ መሆኑን ያላገናዘበና ከልሎች ህጐች አንፃር በሚል በደፈናው ከመግለጽ ውጭ በየትኛው የህግ ዘርፍ ሥር እንደተመለከተም ያልተገለፀና ከላይ በዝርዝር እንደተመለከተውም የግራ ቀኙን ጉዳይ የሚገዛ በህጋችን ማእቀፍ የተካተተ ዝርዝር ህግ የልለ ከመሆኑ እንፃር ሁሉ ሲታይ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስላገኘነው የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 36114 በ24/7/2003 እና በሐምል 07/2003 ዓ.ም የተሰጡት ብይን እና ፍርድ ተሽረዋል።
የከፍተኛ ፍ/ቤት በጉዳዩ ላይ በኮ/መ/ቁ. 115269 በ28/03/2004 የሰጠው የመጨረሻ ዳኝነት የሆነውም ትእዛዝ ተሽሯል።
ከሣሽ ክስ ያቀረቡበት ጉዳይ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 37 እንደተደነገገው በፍድራል ፍ/ቤቶች አማካኝነት በፍርድ ላያልቅ የሚገባው ጉዳይ አይደለም ብለናል። በዚህ ሰበር ችሎት ለተደረገው ክርክር ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ። መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.